የዋሽንግተን ዲሲው ሠልፍ የተሳካ እንደነበር ተገለፀ

March for freedom, Washington DC June14, 2010Ethiopia Zare (ሐሙስ ሰኔ 10 ቀን 2002 ዓ.ም. June 17, 2010) ”ማርች ፎር ፍሪደም” በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ መዲና ዋሽንግተን ዲሲ በኋይት ሐውስ እና በአሜሪካን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት በጠራው ሠልፍ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተው፤ የ2002ቱን ምርጫ ኢህአዲግ ማጭበርበሩን በመቃወም የአሜሪካ መንግሥት ኢትዮጵያን አስመልክቶ የሚከተለውን ፖሊሲ እንዲቀይር ጠየቁ። ሠለፉ የተሳካ እንደነበር አዘጋጆቹ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለፁ።