የመኢአድና የአንድነት ውህደት በምርጫ ቦርድ ለማጨናገፍ የሚደረገውን ሴራ አስመልክቶ ዛሬ በመኢአድ ጽ/ቤት መግለጫ ሰጡ

መኢአድና አንድነት ወደ ሰላማዊ የትግል ፍልሚያ ውስጥ መግባታቸውን ለሕዝባቸው ማሳወቅ ይወዳሉ!!
መኢአድና አንድነት በዛሬው ዕለት ውህደቱን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በህወሓት/ኢህአዴግ አባላት የሚመራው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በበሰላማዊ ትግሉ ላይ መሰናክሎችን በመፍጠር ካሁን ቀደም የተደረጉ ምርጫዎች እንዲዘረፉና ኮሮጆ እየተገለበጠ ለገዢው ፓርቲ እንዲሰጥ ከፍተኛ ሚና ሲጫወት መቆየቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ እንደሆነ ገልጸው በየክልሉ፣ በየዞኑና ወረዳዎች የተሰማሩ የምርጫ ቦርድ ኃላፊዎች የገዢው ፓርቲ የካቢኔ አባላት፣ የደህንነት አባላት መሆናቸው የማይካድ ሃቅ መሆኑ ግልጽ ቢሆንም ዛሬ በግልጽ እንዳይዋሃዱ የሚደረገው ስውር ደባና ፓርቲዎችን ለመዝጋት የሚደረገው ሙከራ ማድረጉና የነፃው ፕሬስ በመዝጋት የኢትዮጵያ ሕዝብ አማራጭ እንዲያጣ የሚፈጸመው ድርጊት ከድፍረቶች ሁሉ ድፍረት ነው ሲሉ በመግለጫቸው ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከሕዝብ የተጣለበትን ከባድ ኃላፊነት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ከያዘው የጥፋት መስመር በመመለስ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችንና ሕዝባችንን በትክክለኛው መንገድ እንዲያገለግል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን በማለት መግለጫቸውን አጠቃለዋል ፡፡10292467_765562580169160_8034843180235228294_n

10570376_765563496835735_2722916858558515108_n

10577075_765563360169082_3038616007904072020_n

10599505_765562700169148_8550786573985435458_n