ግብፅ ወደ ናይል ተፋሰስ ትብብር እንደማትመለስ አስታወቀች
ግብፅ ወደ ናይል ተፋሰስ ትብብር እንደማትመለስ አስታወቀች፡፡
ግብፅ ይህንን አቋሟን በድጋሚ የገለፀችው ሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱም ላይ ትናንት በተካሄደው የትብብር ተቋሙ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የውኃና የመስኖ ሚኒስትሯ በተወካያቸው ባስተላለፉት መልዕክት መሆኑን የኢትዮጵያ የውኃ፣ የመስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ ለቪኦኤ በሰጡት ማብራሪያ ገልፀዋል፡፡
ግብፅን ጨምሮ አሥር አባላት ያሉትና ኤርትራ በራሷ ፍላጎት በታዛቢነት የሚገኙበት የናይል ወይም የአባይ ተፋሰስ ትብብር ጅማሮ ትናንት ባካሄደው 22ኛው መደበኛ የሚኒስትሮች ስብሰባው ላይ ከግብፅ ጋር ከትብብሩ እራሷን አግልላ የቆየችውንና ባለፈው ዓመት መመለሷን ያሳወቀችውን የሱዳንን የውኃና መስኖ ሚኒስትር ሙታዝ ሙሳ አብደላ ሳሊምን የመጭው ዓመት የትብብሩ ፕሬዚዳንት…