የኢትዮጵያ አይሁዳውያን መታሰቢያ በእሥራኤል

እአአ በሰማንያኛዎቹ ዓመታት በሱዳን በኩል አድረገው ወደ እሥራኤል ለመሄድ ሲሞክሩ በጉዞ ላይ ለሞቱት የኢትዮጵያ አይሁዳውያን በሄርዝል ተራራ በቆመው የመታሰቢያ ሐውልት በያመቱ በሚደረገው ሥነ ሥርዓት ላይ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የ1,500ዎቹ ስም በሐውልቱ ላይ ተቀረጸ።