መለስ እሽሩሩ

መለስ እሽሩሩ ምን ሁን ትለኛለህ
ለምን እንደጥላ ትከተለኛለህ?
ኢትዮጵያን ለቅቄ ስመጣ አሜሪካ
ካድሬዎችህ ቀድመው ገብተው ኖሯል ለካ!
እንደ ኤዲስ ቫይረስ እንደ ክፉ ገላ
ካንት የሚያላቅቀኝ ምነው አጣሁ መላ?
ኧረ በዝቶብኛል ተንከዋረርኩልህ
ባህር ተሻገርኩኝ አገር ለቀኩልህ፤
እንዲያ እንደ ቁልቋሉ እንደሚደማው
አጋም ተጠግቶ እንደበቀለው፤
ለቅሶው ቢበዛብኝ በምሥራቅ አፍሪካ
ከለላ ብጠይቅ እዚህ አሜሪካ፤
ካድሬዎችህ ቀድመው ገብተው ኖሯል ለካ!
ከደርጎች ኢሠፓ የጭቆና ቀንበር
ወያኔ መባሱን አልገመትኩም ነበር።
ትሻልን ሰድጀ ትብስን አመጣሁ
ሆነና ነገሩ ያው ትቸልህ ወጣሁ።
መለስ እሽሩሩ ቀንደኛው ወያኔ
ውረድ ከጀርባዬ ሰልችቶኛል እኔ።

በሊሊና ኒና ወርቁ (ዳላስ 8/28/2010)