ኢትዮጵያና የምግብ ዋስትናዋ

ኢትዮጵያ ቀደም ሲል የተደመጠውን ዓይነት አዎንታዊ ውጤት ብታስመዘግብም፣ አሁንም የምግቡ ዋስትና ዝቅተኛ ከሆነባቸው ሃገራት መደዳ ነው የምትቆጠረው። በግምት፣ ከየሦስቱ ኢትዮጵያዊ አንዱ ከድህነት አፋፍ ስር እንደሚኖር ነው የዓለም ምግብ ድርጅት ዘገባ ያሳየው።