ወደኢትዮጵያ በቀን ከስምንት መቶ በላይ የደቡብ ሱዳን ስደተኛ እየገባ ነው
ኢትዮጵያ የደቡብ ሰዳን ግጭት ከተጀመረ ካለፈው ታኅሣስ ወዲህ ባለፈው ጊዜ ውስፋ 130 ሺህ ደቡብ ሱዳናዊያን ስደተኞችን መቀበሏንና እስከ ያዝነው የአውሮፓ ዓመት መጨረሻ በሚቀሩት ሰባት ወራት ውስጥ ይህ ቁጥር እስከ 350 ሺህ ሊደርስ ይችላል ብሎ እንደሚጠብቅ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ፡፡
አዲስ አበባ የሚገኙት የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር – የዩኤንኤችሲአር የኢትዮጵያ ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ክሱት ገብረእግዚአብሔር ለቪኦኤ በሰጡት ቃል በአሁኑ ጊዜ በቀን ከ800 እስከ 1000 ስደተኛ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም ድንበሮቿ አቅራቢያ ባሉ የስደተኞች መጠለያዎች ውስጥ ከ550 ሺህ በላይ ከሶማሊያ፣ ከኤርትራ፣ ከሱዳንና ከኬንያ የገቡ ስደተኞች መኖራቸውን አቶ ክሱት አመልክተው ከግማሽ…