እሁድ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም አንድነት ፓርቲ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በደቡብ ክልል በደራሼ ወረዳ ጊዶሌ ከተማ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደ፡፡ – ፍኖተ-ነፃነት

ይህን ሰልፍ ለማስተባበር ከአዲስ አበባ የተጓዙት የአንድነት ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ስዩም እንዲሁም የምዕራብ ቀጠና አደራጅ አቶ ብርሃኑ ፈከና ነበሩ፡፡ ምንም እንኳ የወረዳው ምክር ቤት ለሰልፉ እውቅና ለመስጠት ያንገራገረ ቢሆንም በነበረችው አጥር ጊዜ ቅስቀሳ ተደርጎ እጅግ የደመቀ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ እንደቻሉ ለፍኖተ-ነፃነት ገልፀዋል፡፡

ጊዶሌ ከተማ በ19ኛው መቶ ክ/ዘመን የተቆረቆረች ሲሆን በ1938 ዓ.ም የመጀመሪያውን ትምህርት ቤት ያገኘች ጥንታዊ ከተማ ነች፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ሶስት መኝታ ቤት ካላቸው ትንንሽ ሆቴሎች በቀር እንግዶቿን ለማስተናገድ አትችልም፡፡ የስልክ መብራትና የውሃ አገልጎሎት የለም ቢባል ይቀላል፡፡ አካባቢው ለገበያ የሚቀርቡ (cash crop) በማምረት ቢታወቅም ከአስተዳደሩ ሙሰኝነት የተነሳ ነዋሪው ተጎሳቁሏል፡፡ መንገዶቿ መንገድ ሊባሉ የሚችሉ አይደሉም ዝናብ ከዘነበ በአቅራቢያ ካሉ ከተሞች ጋር መገናኘት አይቻልም፡፡ በተረፈ ሕዝቡ ፍቅር ነው ሲሉ የአንድነት ስራ አስፈፃሚና የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰለሞን ስዩም ለፍኖተ ነፃነት ገልጸዋል፡፡10343534_630711490347122_7706564031341293509_n

1363368086574