ሚሊዮኖች ድምጽ – የአስተዳደሩ ህገ ወጥነትና የአንድነት መንገድ – ሰለሞን ስዩም

የአንድነትፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን በአዲስ አበባ ለመጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቷል፡፡ ማፊያው አስተዳደር የተለመደውን መልስ ሠጥቷል፡፡ ህግ እና ስርዓት ያፈነገጠ፡፡

በአስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ያወጣው “ስለ ሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ስርዓት” አዋጅ ቁ. 3/1983 የሚመለከተው አካል “ሰላማዊ ሰልፉ ወይም ህዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባው በሌላ ጊዜ ወይም በሌላ ስፍራ ቢደረግ ይሻላል የሚል አስተያየት ካለውም ክንያቱን በመግለፅ ይህንኑ ጥያቄው በደረሰው በ12 ሰዓት ውሳጥ በፅሁፍ ለአዘጋጁ የማሳወቅ ኃላፊነት አለበት፡፡” ይላል፡፡

ዋናው ነገር ግን የሚከተለው ነው፡- “ሆኖም የከተማው ወይም የአውራጃው አስተዳደር ፅ/ቤት ሰላማዊ ሰልፉ ወይም ህዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባው ምንጊዜም በየትኛውም ቦታ ሊካሄድ አይችልም ማለት አይችልም፡፡” ይላል፡፡

አስተዳደሩ ግን አዋጁን ሳይሆን ማንም የማያውቀውና ይፋ ያልሆነ (ህገወጥ “ህግ”) “የከተማ አስተዳደሩ የስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ አሰራርና ስነሥርዓት” ነገር ይጠቅሳል፡፡ ሰላማዊ ትግል ማለት ለህገወጥ ህጎች ጭምር ያለ መታዘዝ መሆኑን አንድነት ያውቃል፡፡ ስለዚህ ራሱ ህገ ወጡ አስተዳደር ይጨነቅበት እንጂ እኛስ እንወጣለን፡፡

ሌላው አስገራሚ ጉዳይ አስተዳደሩ በ12 ሰዓት ውስጥ ከነአማራጩ መልስ ይስጥ የሚለውን አዋጅ ሽሮ አማራጭም ሳያቀርብ ከ54 ሰዓታት በኋላ ነበር መልስ የሰጠው፡፡ Shame up on them!

ለላክነው ሁለተኛ ደብዳቤም ከ48 ሰዓታት በኋላ እኛነን ፖስታ ቤት ሄደን የወሰድነው፡፡ ከአስራ ሁለት የሚልቁ ሰዎችም ታስረዋል፡- አንዳርጌ መስፍን (“በሙት መንፈስ ሀገር ሲታመስ” ፣ ደም በደም፣ ጥቁር ደም፣ ቅሌትና እና የሌሎችም መፃሕፍት ደራሲ ነው)፣ አክሊሉ ሰይፉ፣ አሸናፊ ጨመዳ፣ ሀብታሙ ታምሩ፣ ኤፍሬም ሰይፉ እና ሌሎችም፡፡

በቅርቡ ድርባ ኩማ ጅዳ (ሰሜን ሸዋ፣ ኦሮሚያ) ሄዶ የትውልድ መንደሩን ውሃ አስመርቆ ነበር፡፡ ከዚያ ይልቅ ግን ለሚያስተዳድረው የአዲስ አበባ ህዝብ ውሃ፣ መብራት፣ ኔትዎርክ (ትይይዝ)፣ ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከህገ ወጥ ክልከላው በዳነ ነበር፡፡ እኔ ደግሞ እለዋለሁ፡- Obboo Diribaa kumaa “Hima didduun du’a hin diddu”