አቡጊዳ – አንድነቶች ቅስቀሳዉ ቀጥለዋል ! ዜጎች እየታሰሩ ነው ! ከታሰሩ ወገኖችን የጥቂቶቹን ፎቶ ይመልከቱ!

የሚሊዮኖች ንቅናቄ እንደዘገበው በአዲስ አበባ ቅስቀሳው ቀጥሏል። ፖሊሶች በርካታ ዜጎችን ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ እያሰሩ ሲሆን፣ አገዛዙ የዜጎችን መሰረታዊ የዉህ.፣ የኔትወርቅን የመብራትና የትራንስፖርት ችግሮችን ከመፍታት ፣ ጊዜና ጉኦልበቱን ሕግን በመናድና ዜጎንች በማሸበር ላይ ያተኮረ ይመስላል።

የሚከተሉት ከሚሊዮኖች ንቅናቄ ፌስ ቡክ ገጽ የተወሰዱ ናቸው ፡

የአንድነት ወጣቶችን ቅስቀሳቸውን ቀጥለዋል::
————————————————
አሁንም ፖሊስ እንቅስቃሴያቸውን እያወከ ይገኛል::
————————————————
ካዛንቺስ አካባቢ ከሚገኘው የቅስቀሳ ቡድን ወጣት ወርቁ አንድሮ የቀድሞ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ካዛንቺስ በእስር ላይ ይገኛል፡፡
—————————————
የአዲስ አበባ ፓሊስና ሲቪል ለባሾች ህግ መጣሱን ቀጥለውበታል
—————————————————–
በአዲስ አበባ ከተማ የፊታችን እሁድ ለሚካሄደው ሰለማዊ ሰልፍ የተሟሟቀ ቅስቀሳና እስር ቀጥሏል:: አሁን በደረሰን መረጃ በስታዲየም አካባቢ ቅስቀሳ ላይ የነበሩት አክሊሉ ሰይፉ እና ሰለሞን ፀሀይ ለገሀር ፖሊስ ጣቢያ ከባድ ድብደባ እየተፈፀመባቸው ይገኛል:: በተያያዘ ሁኔታ ሲኤምሲ አካባቢ በቅስቀሳ ላይ የነበሩት ኤፍሬም ሰለሞንና ታሪኬ ኬፋ ላይ ሲቪል ለባሾች ድብደባ ፈፅመውባቸዋል:: በእስርና በድብደባ ያልበገራቸው የአንድነት ልጆች ቅስቀሳቸውን ቀጥለዋል ፡፡
——————
የአዲስ አበባ ፓሊስ ህግ መጣሱን ጀመረ
——————————————–
በአዲስ አበባ ከተማ የፊታችን እሁድ ለሚካሄደው ሰለማዊ ሰልፍ የተሟሟቀ ቅስቀሳ እየተደረገ ቢሆንም በመገናኛ አካባቢ በቅስቀሳ ላይ የነበሩት
1ኛ.ሀብታሙ ታምሩ
2ኛ.አሸናፊ ጨመዳ
3ኛ.መቶ አለቃ አንዳርጌ መስፍንን ፖሊስ በመያዝ ወደ የካ ክፍለ ከተማ ፓሊስ መምሪያ ወስደዋቸዋል ፡

werku

udj-youth1

udj_youth7

udj_youth6

udj_youth5

andarge

udj_youth2

udj_youth3