የአዲስ አበባው የእሪታ ቀን ተቆረጠ – የአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቅ ክፍል የፓርቲውን ደብዳቤ ተቀብሏል፤ – ፍኖተ ነጻነት

የአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቅ ክፍል የፓርቲውን ደብዳቤ ተቀብሏል

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የከተማይቱ መሰረታዊ ችግሮች እየተባባሱ ከመምጣት ውጪ ለውጥ ማሳየት ባለመቻላቸው ለዚህ ተጠያቂ መሆን ያለበትን የከተማይቱን አስተዳደርና ገዢውን ፓርቲ የሚቃወም ‹‹የእሪታ ቀን››በሚል መሪ ቃል መጋቢት 28/2006 ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደርግ አስታውቋል፡፡

በዛሬው እለት የፓርቲው ተወካዩች ለአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቅ ክፍል ስለ ሰልፉ የሚገልጽ ደብዳቤ በማስገባት ተመልሰዋል፡፡ሰላማዊ ሰልፉ በተያዘለት ቀነ ገደብ የፓርቲው ጽ/ቤት ከሚገኝበት ቀበና በመነሳት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ፊት ለፊት እንደሚጠናቀቅ የአዲስ አበባ አንድነት ህዝብ ግኑኝነት አቶ ያሬድ አማረ አስታውቀዋል፡፡AA-001

1 Comment on “የአዲስ አበባው የእሪታ ቀን ተቆረጠ – የአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቅ ክፍል የፓርቲውን ደብዳቤ ተቀብሏል፤ – ፍኖተ ነጻነት”

  1. yeinanten tsinat ena tinkare ye ethiopian andinet egziabiher yamtalin/yawridilin/.yehulum ethiopiawi firat weyane sayhon yeinante yeandinet tinkare newna eske mecheresha yatsinachihu.amen!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*