ወያነ እና ሻእቢያ ሃዘን ተቀምጠዋል።

ምንሊክ ሳልሳዊ፦በተመሳሳይ ቀን የወያነ ባለስልጣኖች አለማየሁ አቶምሳን በሞት ሲነጠቁ የሻእቢያ ባለስልጣኖች ደግሞ ከፍተኛ የጦር አዛዣቸውን እና ታጋይ መጀር ጀነራል ገብረዝገር "ዉጩ" አንደማሪያምን በሞት ተነጥቋል።
አቶ አለማየሁ በባንኮክ በከፍተኛ ውጪ ሲታከሙ የሞቱ ሲሆን የሻ እቢያው ጀነራል ግን በአስመራ ከተማ በህክምና ሲረዱ ቆይተው አርፈዋል። አቶ አለማየሁ አቶምሳ ከሕወሓት ሰራሹ ኦሕደድ ጋር ተቀላቅለው ታጋይ የነበሩ(ማረጋገጫ አልተገኘም) ሲሆን ጀነራል ገረዝገር ሻ እቢያ ከደርግ ጋር ባደረገው ጦርነት ከ1971 ጀምሮ የተሳተፉ ታጋይ እንደነበሩ ከአስመራ የወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ምንሊክ ሳልሳዊ