የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበረሰብ የቤተሰብ የሽርሽር ዝግጅት በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ

የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር ኦክቶበር 8 ቀን 2011 አርሊንግተን፣ ቨርጂኒያ ውስጥ በሚገኘው የመናፈሻና የስፖርት መስክ ላይ ያዘጋጀው የቤተሰብ የሽርሽር ዝግጅት በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ። በዚሁ ዝግጅት ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ከነልጆቻቸው የተገኙ ሲሆን የመናፈሻ ቦታው በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አሸብርቆ ታዳሚዎችም በተለያዩ የኢትዮጵያ የአገር ባህል አልባሳትን ተጎናጽፈው አምረውና አጊጠው ተገኝተዋል። በዝግጅቱ ላይ የተሟላ የኢትዮጵያ ምግቦችና የፍም ጥብስ የተስተናገደ ሲሆን በተለይም ለልጆች ልዩ ምሳ ቀርቦላቸው የነበረ ከመሆኑም ባላይ ልጆች እርስ በርሳቸው ሲጫወቱና ሲቦርቁ ውለዋል።ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ የቡና ሥርዓት ተካዷል። በዝግጁ ላይ በርካታ የኢትዮጵያ የንግድ ድርጅቶችና ምግብ ቤቶች አስተዋጽኦ አበርክተዋል።