የአ/አበባ ሀ/ስብከት የመዋቅር የአደረጃጀትና የአሠራር መመሪያ ጥናት ሰነድ ርክክብ ተካሔደ፤ የባለሞያ ቡድኑ÷ ጥናቱን ዳግመኛ ለማየት በተቋቋመው የምሁራንና ሊቃውንት ኮሚቴ ላይ አከራካሪ ሐሳቦችን የማብራራት ዕድል እንዲሰጠው ጠይቋል

Expertsየባለሞያ ቡድኑ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ አሰፋ፡-

  • ለባለሞያ ቡድኑ ይህ ታሪካዊ ዕድል ተሰጥቶን ችግር ፈቺ ጥናት እንድናጠና በመደረጋችን ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው፡፡ የጥናት ሰነዱ የካህናት፣ የምእመናንና የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች ሐሳብ የተካተተበት በመኾኑ ከአኹን በኋላ የመላው የቤተ ክርስቲያኒቱ አማኞች ሰነድ ነው ብለን እናምናለን፡፡

???????????????????????????????

  • ለዝግጅቱ መሳካት አስተዋፅኦ ያደረጉ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የሀ/ስብከቱ ሓላፊዎችና አገልጋዮች፣ የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሓላፊዎች፣ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ ከምንምና ከማንም በላይ ከጅምሩ እስከ ፍጻሜው ድረስ በኹሉ ነገር ያልተለዩት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ታላቅ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡
  • መታሰቢያነቱ የለውጥ እንቅስቃሴውን ላስጀመሩት ለብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ ለካህናት፣ ለሰንበት ት/ቤቶችና ለምእመናን እንዲኾን እንመኛለን፡፡
  • ጥናቱን ዳግመኛ ለማየት የተቋቋመው ኮሚቴ በሥራው ሒደት የማይቀበለውን ሐሳብ ከመጣል በቀጥታ ይልቅ ለምን በሰነዱ እንደተካተተ ለማብራራት ዕድሉን እንዲሰጠን እንጠይቃለን፡፡
  • ጥናቱ በቅ/ሲኖዶስ ታምኖበት ሲጸድቅ ዝርዝር የትግበራ ስልቱን ከእያንዳንዱ መመሪያና ፖሊሲ በርካታ ቅጻቅጾችና አባሪዎች ጋራ ሠርተን ለማቅረብ ዝግጁዎች ነን፡፡
  • ይህ ሰነድ የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደር በኹሉም ዘርፍ በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመኾኑ፣ በቅዱስ ፓትርያርኩ በአንድ ወቅት እንደተነገረው፣ ከሌሎች አህጉረ ስብከት ነባራዊ ኹኔታ ጋራ እየተጣጣመ ለእነርሱ በሚኾን አግባብ እንዲዘጋጅላቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ተመክሮበት አቅጣጫ እንዲሰጥበት እንጠይቃለን፡፡

የሀ/ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ በላይ መኰንን፡-

  • ቅዱስ አባታችን፣ ሀ/ስብከቱና ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ናቸው ይህን ጥናት ያስጀመሩት፤ ብፁዕነታቸው ከሀ/ስብከቱ ጋራ ተረካክበው ያምጡልኝ ብለዋል፤ በብፁዕነታቸው ሲቀርብላቸው ቅዱስነታቸው ለሚመለከተው አካል ያስረክባሉ፡፡Handing over ceremony of the A.A Dioceses Change mgt doc00
  • ሊቃውንት ይዩት መባሉ በኹሉም አቅጣጫ ታይቶ ዕንከን የለሽ ሕግ ለማውጣት ያስችላል፤ ለአንድ ዓላማ እየተነጋገርን የአስተሳሰባችን ደረጃና አካሔዳችን ሊለያይ ይችላል፤ ኹሉም ቤተ ክርስቲያን እንድታድግ ነው የሚፈልገው፤ ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅመውን ነገር ደግሞ እግዚአብሔር አያስቀረውም፡፡

በሀ/ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፡-

  • በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደ መነሻ የሚኾን፣ እንድናስብ የሚያስችል ጥናት በእናንተ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ተረቆ ለቤተ ክርስቲያን እንዲሰጥ አድርጋችኋል፤ ከቅዱስ አባታችን ጋራ የቋሚ ሲኖዶስ አባላት ባሉበት እንደምትነጋገሩ እንደሚባርኳችኹ ተነጋግረናል፤ የምስጋና ደብዳቤ በቅዱስ አባታችን እንዲደርሳችኹ እናደርጋለን፡፡ የሰዎችን ድካም የማያስቀር አምላክ ድካማችኹንን ይቀበልላችኹ፡፡ በጎ አገልግሎታችኹን እግዚአብሔር አያጉድልባችኹ፡፡

His Grace Abun Estifanos recieving the doc

  • ቅዱስ አባታችን ሰነዱ ለመጪው ርክበ ካህናት እንዲቀርብ አኹን ለምን አታመጡም ይሉን ነበር፤ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩና ቅዱስ ሲኖዶሱ ሰነዱ ሥራ ላይ የሚውልበትን ሒደት እየቀየሱ ነው፤ አስረከባችኹ እንጂ ሥራችኹ አላበቃም፤ ተጠርታችኹ ጥያቄ ሊቀርብላችኹ ስለሚችል ማስተካከያ በሚያስፈልግበት ጊዜ ኹሉ ተሳትፎ ይኖራችኋል ብዬ አስባለኹ፡፡
  • ኹላችንም ወደ አንድ መጥተን ቤተ ክርስቲያናችንን እንድንታደጋት ነው የሚያስፈልገው፤ ብጣሽ ወረቀት ከኛ ሳትጠየቁ ለቤተ ክርስቲያን ቋሚ አገልግሎት ሊሰጥ በሚችል መንገድ ሌት ተቀን ደክማችኹ አዘጋጅታችኹ ያስረከባችኹንን ሞያዊ ዐሥራታችኹን በነገው ዕለት ለቋሚ ሲኖዶሱ እናስረክባለን፡፡

the team with his grace abune estifanos

  • ነገ ካስረከብን በኋላ የራሳችንን ሓላፊነት ተወጥተናል ማለት ነው፤ ከዚያ በኋላ ባለቤቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፤ በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ለቤተ ክርስቲያናችን የሚሠራ በቂ ሕግ ነው ሲል ጸድቆ ይተገበራል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ይከታተሉ