በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ብቻ ስለምትጾመው የነነዌ ጾም የመጽሐፍ ቅዱስ ቀጥተኛ ማስረጃ

በየዓመቱ ከአብይ ጾም አስራ አምስት ቀናት በፊት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮች ለሶስት ቀናት ያህል የምትጾመው የነነዌ ጾም በመላው ዓለም የሚገኙ ክርስቲያኖች ቢተዋትም በኢትዮጵያዊያኖች ዘንድ ስትጾም ከሁለት ሽህ ዓመት በላይ ሆኗታል። አንዳንድ አባቶች ጾመ ነነዌን “ጾመ ኢትዮጵያ” እያሉ ይጠሯታል። ከጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በፊት በወቅቱ በሥልጣኔዋና በታላቅነቷ ቀደምት የነበረችው የነነዌ ከተማ ከእግዚያብሔር ህግና ትዕዛዝ ውጭ ሆና ሀጢዓት የተንሰራፋባት ሆና እግዚያብሔርን አሳዝና ነበር። ሆኖም ልዑል እግዚያብሔር ነቢዩ ዮናስን በመላክ ከጥፋቷ እንድትመለስ የተላከላትን መልዕክት ተቀብላ ለሶስት ቀናት ያህል ጾምና ጸሎት በማድረግ ከታዘዘባት መዓት ለመዳን ችላለች። ከሁሉም የሚያስደንቀው በወቅቱ የነበረው የነነዌ ንጉስ ሕዝቡን አዋጅ በማሳወጅ ለጾምና ለጸሎት ማስተባበሩ ብቻ ሳይሆን እራሱም ከዙፋኑ ወርዶ ማቅ ለብሶ አመድ ላይ ተቅምጦ ከህዝቡ ጋር በጾምና በጸሎት መሳተፉ ነው። ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 3 ከቁጥር 6 እስከ 9 ድረስ ያለው ይህንን ይላል።

“……..ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፥ በአመድም ላይ ተቀመጠ። 7 አዋጅም አስነገረ፥ በነነዌም ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፥ እንዲህም አለ። ሰዎችና እንስሶች ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ፤ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ፤ 8 ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፥ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ  ይመለሱ። እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደ ሆነ፥ ከጽኑ ቍጣውም ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል? “………..

እግዚያብሔርም መመለሳቸውን ተመልክቶ ምህረት አድረገላቸው። ለእኛም ለኢትዮጵያዊያን ከጥፋታችን ተመልሰንና ተጸጽተን ምህረት የምናገኝበትን ልቦና ይስጠን። በጣም አጭር የሆነውን ትንቢተ ዮናስን በተለይ ዛሬ የነነዌ ጾም የመጨረሻ ቀን ስለሆነ የነነዌ ሕዝብ ከዳነበት ለእኛም ለኢትዮጵያውያን በረከቱ እንዲተርፈን  በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ትንቢተ ዮናስ 

 

ትንቢተ ዮናስ

 

ምዕራፍ 1

1የእግዚአብሔርምቃልወደአማቴልጅወደዮናስእንዲህሲልመጣ

2ተነሥተህወደዚያችወደታላቂቱከተማወደነነዌሂድ፥ክፉታቸውምወደፊቴወጥቶአልናበእርስዋላይስበክ።

3ዮናስግንከእግዚአብሔርፊትወደተርሴስይኰበልልዘንድተነሣ፤ወደኢዮጴምወረደ፥ወደተርሴስምየምታልፍመርከብአገኘ፤ከእግዚአብሔርምፊትኰብልሎከእነርሱጋርወደተርሴስይሄድዘንድዋጋሰጥቶወደእርስዋገባ።

4እግዚአብሔርምበባሕሩላይታላቅነፋስንአመጣ፥በባሕርምላይታላቅማዕበልሆነ፥መርከቢቱምልትሰበርቀረበች።

5መርከበኞቹምፈሩ፥እያንዳንዱምወደአምላኩጮኸ፤መርከቢቱምእንድትቀልልላቸውበውስጥዋየነበረውንዕቃወደባሕርጣሉት፤ዮናስግንወደመርከቡውስጠኛውክፍልወርዶነበር፥በከባድእንቅልፍምተኝቶነበር።

6የመርከቡምአለቃወደእርሱቀርቦ።ምነውተኝተሃል? እንዳንጠፋእግዚአብሔርያስበንእንደሆነተነሥተህአምላክህንጥራአለው።

7እርስበእርሳቸውም።ይህክፉነገርበማንምክንያትእንዳገኘንእናውቅዘንድኑ፥ዕጣእንጣጣልተባባሉ።ዕጣምተጣጣሉ፥ዕጣውምበዮናስላይወደቀ።

8የዚያንጊዜም።ይህክፉነገርበማንምክንያትእንዳገኘንእባክህንገረን፤ሥራህምንድርነው? ከወዴትስመጣህ? አገርህስወዴትነው? ወይስከማንወገንነህ? አሉት።

9እርሱም።እኔዕብራዊነኝ፤በሕሩንናየብሱንየፈጠረውንየሰማይንአምላክእግዚአብሔርንእመልካለሁአላቸው።

10እነዚያምሰዎችከእግዚአብሔርፊትእንደኰበለለእርሱስለነገራቸውአውቀዋልናእጅግፈርተው።ይህያደረግኸውምንድርነው? አሉት።

11ባሕሩንምሞገዱአጥብቆያናውጠውነበርና።ባሕሩከእኛዘንድጸጥእንዲልምንእናድርግብህ? አሉት።

12እርሱም።ይህታላቅማዕበልበእኔምክንያትእንዳገኛችሁአውቃለሁናአንሥታችሁወደባሕርጣሉኝ፥ባሕሩምጸጥይልላችኋልአላቸው።

13ሰዎቹግንወደምድሩሊመለሱአጥብቀውቀዘፉ፤ዳሩግንባሕሩእጅግአብዝቶይናወጥባቸውነበርናአልቻሉም።

14ስለዚህወደእግዚአብሔርጮኸው።አቤቱ፥እንደወደድህአድርገሃልናእንለምንሃለን፤አቤቱ፥ስለዚህሰውነፍስእንዳንጠፋንጹሕምደምበእኛላይእንዳታደርግእንለምንሃለንአሉ።

15ዮናስንምወስደውወደባሕሩጣሉት፤ባሕሩምከመናወጡጸጥአለ።

16ሰዎችምእግዚአብሔርንእጅግፈሩ፥ለእግዚአብሔርምመሥዋዕትንአቀረቡ፥ስእለትንምተሳሉ።

 

 ምዕራፍ 2

1 እግዚአብሔርም ዮናስን የሚውጥ ታላቅ ዓሣ አሰናዳ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣው ሆድ ውስጥ ነበረ።

2 ዮናስም በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ እንዲህም አለ።

3 በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ እርሱም ሰማኝ፤ በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ፥ ቃሌንም አዳመጥህ።

4 ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ውስጥ ጣልኸኝ፥ ፈሳሾችም በዙሪያዬ ነበሩ፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፉ።

5 እኔም። ከዓይንህ ፊት ተጣልሁ፤ ነገር ግን ወደ ቅዱስ መቅደስህ ደግሞ እመለከታለሁ አልሁ።

6 ውኆችም እስከ ነፍሴ ድረስ ከበቡኝ፤ ጥልቁ ባሕር በዙሪያዬ ነበረ፤ የባሕሩ ሣር በራሴ ተጠምጥሞ ነበር።

7 ወደ ተራሮች መሠረት ወረድሁ፤ በምድርና በመወርወሪያዎችዋ ለዘላለም ተዘጋሁ፤ አንተ ግን፥ አቤቱ አምላኬ፥ ሕይወቴን ከጕድጓዱ አወጣህ።

8 ነፍሴ በዛለችብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን አሰብሁት፤ ጸሎቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ገባች።

9 ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ ምሕረታቸውን ትተዋል።

10 እኔ ግን በምስጋና ቃል እሠዋልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እከፍላለሁ። ደኅንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።

11 እግዚአብሔርም ዓሣውን አዘዘው፥ እርሱም ዮናስን በየብስ ላይ ተፋው።

 

ምዕራፍ 3

1 የእግዚአብሔርም ቃል ሁለተኛ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ።

2 ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ የምነግርህንም ስብከት ስበክላት አለው።

3 ዮናስም ተነሥቶ እንደ እግዚአብሔር ቃል ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነዌም የሦስት ቀን መንገድ ያህል እጅግ ታላቅ ከተማ ነበረች።

4 ዮናስም የአንድ ቀን መንገድ ያህል ወደ ከተማይቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም። በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች አለ።

5 የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።

6 ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፥ በአመድም ላይ ተቀመጠ።

7 አዋጅም አስነገረ፥ በነነዌም ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፥ እንዲህም አለ። ሰዎችና እንስሶች ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ፤ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ፤

8 ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፥ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ።

9እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደ ሆነ፥ ከጽኑ ቍጣውም ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?

10 እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም።

ምዕራፍ 4

1 ይህም ዮናስን ከቶ ደስ አላሰኘውም፥ እርሱም ተቈጣ።

2 ወደ እግዚአብሔርም ጸለየና። አቤቱ፥ እለምንሃለሁ፤ በአገሬ ሳለሁ የተናገርሁት ይህ አልነበረምን? አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋሽም፥ ምሕረትህም የበዛ፥ ከክፉው ነገርም የተነሣ የምትጸጸት አምላክ እንደ ሆንህ አውቄ ነበርና ስለዚህ ወደ ተርሴስ ለመኰብለል ፈጥኜ ነበር።

3 አሁንም፥ አቤቱ፥ ከሕይወት ሞት ይሻለኛልና እባክህ፥ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ አለው።

4 እግዚአብሔርም። በውኑ ትቈጣ ዘንድ ይገባሃልን? አለ።

5 ዮናስም ከከተማይቱ ወጣ፥ ከከተማይቱም በስተ ምሥራቅ በኩል ተቀመጠ፤ ከተማይቱንም የሚያገኛትን እስኪያይ ድረስ በዚያ ለራሱ ዳስ ሠርቶ ከጥላው በታች ተቀመጠ።

6 እግዚአብሔር አምላክም ቅል አዘጋጀ፥ ከጭንቀቱም ታድነው ዘንድ በራሱ ላይ ጥላ እንድትሆን በዮናስ ላይ ከፍ ከፍ አደረጋት፤ ዮናስም ስለ ቅሊቱ እጅግ ደስ አለው።

7 በነጋው ግን ወገግ ባለ ጊዜ እግዚአብሔር ትልን አዘጋጀ፥ እርስዋም ቅሊቱን እስክትደርቅ ድረስ መታቻት።

8 ፀሐይም በወጣች ጊዜ እግዚአብሔር ትኩስ የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ ዮናስ እስኪዝል ድረስም ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራሱም ሞትን ፈለገና። ከሕይወት ሞት ይሻለኛል አለ።

9 እግዚአብሔርም ዮናስን። በውኑ ስለዚች ቅል ትቈጣ ዘንድ ይገባሃልን? አለው። እርሱም። እስከ ሞት ድረስ እቈጣ ዘንድ ይገባኛል አለ።

10 እግዚአብሔርም። አንተ ትበቅል ዘንድ ላልደከምህባት ላላሳደግሃትም፥ በአንድ ሌሊት ለበቀለች፥ በአንድ ሌሊትም ለደረቀችው ቅል አዝነሃል።

11 እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሀያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን? አለው።