የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማሕበረሰብ ያዘጋጀው የአድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ-በዓል

የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማሕበረሰብ ያዘጋጀው የአድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ-በዓል ማርች 2 ቀን በ 2 ፒ.ኤም. ሲልቨር ስፕሪንግ፣ ሜሪላንድ ውስጥ ይካሄዳል። ይህንን ክብረ-በዓል የሞንትጎመሪ አውራጃ አስተዳዳሪ የሆኑት ክቡር አቶ አይዛ ሊጌት በንግግር ይከፍታሉ። በዚሁ ዝግጅት ላይ ታዋቂ የታሪክ ምሁራን የምርምር ጽሁፎቻቸውን ያቀርባሉ። እነሱም ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ፣ ዶ/ር ቤንጃሚን ታልቶን እንዲሁም ፕሮፌሰር ሬመንድ ጆናስ ናቸው። ስለ ክብረ በዓሉ የተዘጋጀውን ማስታወቂያ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። የአድዋ ክብረ በዓል ማስታወቂያ 1    የአድዋ ክብረ በዓል ማስታወቂያ 2