የኡጋንዳ ፖሊስ የነገው ስብሠባ መታገዱን ገለፀ!!!
የኡጋንዳ ፖሊስ የነገው ስብሠባ መታገዱን ገለፀ!!!
ትናንት አመሻሽ ላይ የካባላጋላና የሴንተራል ፖሊስ ኮማንደሮች የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ በኡጋንዳ አመራር የሆኑትን አቶ ዘለቀ ጀበሮንና የማህበራዊ ጉዳዮች ተጠሪ የሆኑትን ጋዜጠኛ ደረጀ በጋሻውን በጽ/ቤታቸው ያነጋገሩት አዛዦች ኮሚኒቲው የጠራው ስብሠባ በበላይ አካላት ትዕዛዝ መታገዱን እንደተገለፀላቸው ለኮሚኒቲው ቅርበት ያላቸው ወገኖች ጠቆሙ።
ከኮሚኒቲው ቦርድ አባላት መካከል አቶ ዘለቀ ጀበሮንና ጋዜጠኛ ደረጀ በጋሻውን ብቻ ፖሊስ ጠርቶ ማነጋገሩ ብዙዎችን ያስገረመ ሲሆን ኮሚኒቲው አዳራሽ ተከራይቶና ለማህበረሠቡ በበራሪ ወረቀትና በፌስ ቡክ ጥሪ አስተላልፎ ሕዝባዊው ስብሠባ ሊካሄድ ዐርባ አምስት ሠዓታት ሲቀረው በማስታወቅያው መልዕክት የተደናገጠው የወያኔ የኡጋንዳ ቆንስላ ለኡጋንዳ መንግስት ደብዳቤ ፅፎ የዕሁዱን ስብሠባ እንዳሳገደ ደብዳቤውን በፖሊስ ኮማንደር ዕጅ እንደተመለከተ ጋዜጠኛ ደረጀ በጋሻው ጠቁሞ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሕዝባዊ ስብሰባውን የጠራው በሠላማዊ መንገድ ለመወያየትና በሳውዲ ያሉ ወገኖችን መከራና እንግልት ለመጋራትና ወገናዊነትን ለማሣየት እንጂ ሌላ ምንም አይነት ድብቅ አጀንዳ እንደሌለው ጠቁመው የወያኔ የኡጋንዳ ቆንስላ የሕዝብን ድምፅ ለማፈን መንቀቀሱ ትzብት ላይ እንደሚጥለው ጠቁመዋል።
በመጨረሻም የፖሊስ ኮማንደሮቹ ያስተላለፉትን መመርያ በመቀበል ኡጋንዳ በዓለም አቀፉ የስደተኞች ስምምነት መሠረት የፖለቲካ ጥገኝነት አግኝተን የምንኖርባት ሐገር በመሆኗ የጠራነውን ስብሰባ በመመርያው መሠረት ማቆማችንን በማሣወቅ ከፖሊስ ጋር ያደረጉት ውይይት ተጠናቋል ሲሉ ጋዜጠኛ ደረጀ ጠቁመዋል።