ማንዴላ ለኢትዮጵያዊነት – ቤዛ ነበሩ!
መራራ ስንብት – ከመብራታችን ጋር …
ሥርጉተ ሥላሴ
በዘመነ ወያኔ የተከበሩ ማንዴላ የተስፋዬ ሀገር የሚሏትን ሀገርና ህዝብ፤ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵውያንን ሳያዩ አረፉ። ስለ ምን? ለጥቁሮች የተፈሪነት ፍጹም ልዩ ዓርማ የሆነችውን የሀገራችንን ቀደምትነት፤ ያን የአፍሪካዊ የጥቁር ገድል፤ የቅኝ ግዛትን ቀንበር በምኞት ያስቀረ የፈካ ታሪክ በዕብሪትና በበቀል የጣሰው የወያኔ ሓርነት ትግራይ ማንፌስቶ አልተመቻቸውም ነበርና።