የአራቱ ኃያላን ቅኝት
ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ
(አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ፊሎሎጂ ትምህርት ክፍል)
• ርእስ – አራቱ ኃያላን፦አቡነ በጸሎተ ሚካኤል፣ አቡነ ፊልጶስ፣አቡነ አኖሬዎስ፣ አቡነ አሮን
• አዘጋጅ – ዲ/ዳንኤል ክብረት
• የገጽ ብዛት – 460 (መግቢያውን፣ዋቤ መጻሕፍትን እና መዘርዝሩንጨምሮ)
• አሳታሚ – አግዮስኅትመትና ጠቅላላ ንግድ ሥራኃላ. የተ. የግልማኅበር
• ማተሚያ ቤት – አማኑኤልማ/ቤት
• ምረቃው የተካሄደበት ቦታ – መንበረፀባዖት ቅ/ሥላሴካቴድራል ሁለገብ አዳራሽ
• ቀን– ኅዳር 15/2006 ዓ.ም.
• አስተያየት ሰጪ – አምሳሉተፈራ
የመጽሐፉ ሥነ ድርሳናዊ (ፊሎሎጂካል(1)) ጠቀሜታ
፩. መግቢያ
መጽሐፉበጣም ብዙ እናአዳዲስ ነገሮችን ይዟል። ታሪክ፣ ሃይማኖት፣ ባህል፣ የዓላማ ጽናት፣ በዘመኑ የነበረው ቅጣትና ፍርድ አሰጣጥወዘተ2 … ከያዛቸው ውስጥ ዋናዋናዎቹ ናቸው። የታሪክ አሰናሰሉ፣ የቋንቋ አጠቃቀሙ፣ የማስረጃዎቹ ተአማኒነት (ባብዛኛው ጥሬ መረጃዎችንናየመጀመሪያ ምንጮችን ማቅረቡ) ወዘተ… ለየትያደርገዋል።
ይህደግሞ እስካሁን ድረስ ያልተሟላውንየሀገራችንን መካከለኛ ዘመን ታሪክእንዲሟላ ብዙ ድርሻንይወስዳል። በዋናነት ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ታሪካችንን የዚያን ዘመን ገጽታናየአበው ቅዱሳንን ታሪክ በስፋትስለሚያሳይ ፋይዳው የጎላ ነው(2)።
ገድላቸውተተርጉሞ የቀረበው አራቱም አባቶች – አቡነ በጸሎተሚካኤል፣ አቡነ ፊልጶስ፣አቡነ አኖሬዎስ፣ አቡነ አሮን – በተመሳሳይ ዘመን የኖሩስለነበር በአንዱ ገድል ውስጥየሌላውንም ታሪክ እናገኛለን።ይህም ታሪኩን ይበልጥ ተአማኒና ተያያዥ ያደርገዋል። ገድላቱ የቅዱሳኑን የተጋድሎ ዜና፣ ሐዋርያዊአገልግሎትና ያደረጓቸውን ተአምራት አካተዋል። እነዚህን ገድላት ለመጀመሪያ ጊዜ ያጠኗቸውከ100 ዓመት በፊትየውጭ አገር ሊቃውንትሲሆኑ፤ አራቱንም ገድላት በግእዝ አትመው ወደ አውሮፓቋንቋዎች ተርጉመዋቸዋል(3)3። እኔእስከማውቀው አራቱም ገድላት እስካሁን በአማርኛ ያልተተረጎሙ ሲሆን የአባበጸሎተ ሚካኤል ገድል4 ግንበቅርቡ (በ2004 ዓ.ም.) ተተርጉሞ(4)ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገድል ጋር በአንድ ላይ በማኅበረቅዱሳን ታትሟል(5)5። ስለዚህ ይህ የዲ/ን ዳንኤል ዝግጅት በተፈላጊው ሰዓት የቀረበናተፈላጊነቱም እጅግ የጎላነው የሚል እምነትአለኝ።
የኢትዮጵያኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንየምትቀበላቸውንና የምትገለገልባቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት፣ ድርሳናት፣ ገድላት እንዲሁም ልዩ ልዩመጻሕፍትን ስናጠና ምንጫቸውን በተመለከተ በ2 እንከፍላቸዋለን።
የመጀመሪያዎቹ መሠረታቸውየውጭ ቋንቋ ሆኖበኋላ ወደ ኢትዮጵያቋንቋ (ግዕዝ) የተመለሱእና ሁለተኛዎቹ ደግሞ ሀገር በቀልሆነው ከመጀመሪያው በግዕዝ የተጻፉ ናቸው። በውጭ ቋንቋማለትም በግሪክ፣ በሱርስት፣ በዐረብኛ ተጽፈው ወደግዕዝ የተተረጎሙ በርካታ ናቸው። አንዳንድ አጥኚዎች ይህን ዘመንከአክሱም (በተለይም ከ5ኛው መ.ክ.ዘ.) እስከ15ኛው መ.ክ.ዘ. ያደርሱታል። በሌላ በኩልደግሞ ሀገርኛ ሥራዎች ይበልጥ የተስፋፉት ከ15ኛው መ.ክ.ዘ. በኋላሲሆን ከዚያ በፊትምግን እንደነበሩ ለአብነት ያህልም የቅዱስ ያሬድን ድርሰቶች መጥቀስ እንደሚቻል ባማስረዳት የሚሞግቱ ብዙዎች ናቸው።
ተጋድሏቸውናትምህርታቸው እንዲሁም ታሪካቸው ተተርጉሞ የቀረበው እና አዘጋጁአራቱ ኃያላን ብሎ የሠየማቸው
አበውገድላቸው ሀገር በቀል፣ምንጩም ግዕዝ ነው።ወደ አማርኛ ቋንቋ መመለሱምየአንባቢውን ቁጥር በእጅጉ እንዲጨምርና ቅዱሳኑምየተጋደሉለትን ዓላማ ሁሉምበውል እንዲረዳው በእጅጉ ያግዛል። ከዚህም ጋር እያንዳንዱ ለብቻ ቢዘጋጅ4 ታላላቅ መጻሕፍት ሊወጣው የሚችለውን እና እንደመቅድም የቀረበው ታሪካዊ ትንታኔ ደግሞ ራሱን የቻለ 5ኛ መጽሐፍ ሆኖ ሊወሰድየሚገባው ሲሆን ሁሉንምበአንድ ላይ በማቅረቡዲ/ዳንኤል ለአንባቢ አሳቢነቱን ያሳያል የሚል እምነትአለኝ።
፪. መጽሐፉ ከሥነ ድርሣናዊ ሙያ አንጻር ሲታይ
ረጅምዘመን ባስቆጠረው የጥንታዊ ጽሑፎች ጥናት መስክየጥናቱ ማዕከል ሆነው የሚወሰዱትጥንታዊ፣ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸውየብራና ጽሑፎች፣ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች፣ልዩ ልዩ መዛግብት፣ደብዳቤዎችና በመጽሐፍ መልክምይሁን በጥቅልል መልክ የተዘጋጁሠነዶች ናቸው። ከዘመን አንጻርም ስናያቸው ከዘመነ አክሱም (አንዳንዴም ከዚያ የሚቀድሙ ተገኝተዋል) እስከ መካከለኛውዘመን ገፋ ካለምእስከ ቅድመ ዘመናዊየኢትዮጵያ ታሪክ (19ኛው መ.ክ.ዘ.) ያሉትናቸው። የጥንታዊ ሰነዶቹ ቋንቋ ባብዛኛውግዕዝ ሲሆን የድንጋይላይ ጽሑፎቹን ቋንቋ ስንመለከት የሳባ ቋንቋ፣አናባቢ የሌለው ግዕዝ እናግሪክኛም ይገኝበታል። ከዚህም በተጨማሪ በጥንታዊ አማርኛና ሐረሪ(6) ቋንቋ፣ እንዲሁም በክርስቲያናዊ ዐረብኛ የተጻፉ ሰነዶች በኢትዮጵያ ተገኝተዋል። እነዚህ ሁሉ በወጉሊጠኑ፣ ሊተረጎሙ እና የያዙት መልእክትም ለሕዝብ ሊዳረስ ይገባዋል። ከዚህም ባሻገር የተለያየ ቅጅ ካላቸውአፈላልጎ ማስተያየትና የጎደለውን ማቃናት ተገቢ ነው።
ከነዚህእውነታዎች አንጻር በዛሬው ዕለት እየመረቅነውየሚገኘውን የዲ/ዳንኤልመጽሐፍ ስንቃኘው:-
1. ከቋንቋው አንጻር ከግዕዝ ወደአማርኛ መተርጎሙ፣ ከዘመን አንጻር የሀገራችንን መካከለኛ ዘመን ታሪክ በተለይም በዓምደጽዮን እና ንጉሥሰይፈ አርዕድ የነበረውን ታሪክ በስፋትበመያዙ ፍይዳው ብዙ ነው።
2. የተለያዩ ቅጂዎች ይኖሩ እንደሁብሎ ማሰቡና ይህንንም ለማሳካት የተለያዩ ገዳማትና አድባራትን፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገርየሚገኙ አብያተ መጻሕፍትንና መዘክሮችን ማሰሱ፣ እንዲሁም በአንዳንድ ግለሰቦች ይዞታ ሊገኙ የሚችሉመረጃዎችን ማፈላለጉ፣ ይህንንም ባብዛኛው ማሳካቱ ዲ/ዳንኤልንያስመሰግነዋል።
3. ተጨማሪየገድል ቅጂዎችን ማግኘቱ እና መጠቆሙበጣም ጠቃሚ ነው።ለምሳሌ ያህልም፥
• እስካሁን ከሚታወቀው የዳጋ እስጥፋኖስገድለ አባ በጸሎተሚካኤል (ኮንቲሮሲኒ በ1905 ያሳተመው) በተጨማሪ በተንቤን እንዳ እጨጌኪዳነ ምሕረት ሌላ ገድልመኖሩን መጠቆሙ ለሌላ አጥኚ ጥሩመረጃ ነው።
• ገድለ ፊልጶስን በተመለከተ ቱራኤቭ በ1905 ካሳተመውውጭ ሌሎች 6 መኖራቸውንከነዚህም መካከል የአምሐራ ሳይንቱ አዲስና እርሱ ያገኘውእንደሆነ መጠቆሙ በጣም ጠቃሚነው።
• ገድለ አኖሬዎስን አስመልክቶ ኮንቲሮሲኒ በ1905 ካሳተመውበተጨማሪ 10 ቅጂዎችን ማግኘቱ የሚደነቅ ነው።
• ገድለ አቡነ አሮንንቱራኤቭ በ1905 አሳትሞትነበር። ዲ/ዳንኤልይህን እትም ከመቄቱገድለ አሮን ጋር አስተያይቶ ነው ወደአማርኛ የመለሰው። ከዚህ ሌላግን በብሪቲሽ ሙዚየም የሚገኝ አንድ ገድልና በትግራይ ተንቤን ሌላ ቅጅሊኖር እንደሚችል እርሱ ግንሊያገኘው እንዳልቻለ መጠቆሙ መልካም ጥረት ነው።
4. የትርጉም ሥራው የግርጌማስታዎሻ ጠቀሜታ – ዲ/ዳንኤልአራቱንም ገድላት ከመገኛቸው ቋንቋ ከግዕዝ ወደአማርኛ መልሷል። አይግለጸው እንጅ ትርጉሙየቃል በቃል ቀጥታትርጉም ይመስላል። ከዚህ በላይ ግንማብራሪያ የሚያስፈልጋቸውንና እርሱ ያገኛቸውንአዳዲስ መረጃዎች ቁጥር በመስጠትአብራርቷል፣ ተንትኗል። በጥቅሉ በገድለ በጸሎተ ሚካኤል ላይ 251፣ በገድለ ፊልጶስ ላይ 378፣ በገድለ አኖሬዎስ ላይ 156፣ በገድለ አሮን ላይ181 ማብራሪያዎችን በግርጌ ማስታዎሻ አስቀምጧል። ይህም ለሥራውምን ያህል እንደተጨነቀ የሚያሳይ ሲሆን እስካሁንከተለመደው የገድላት የአማርኛ ትርጉም የእርሱን የተለየ ያደርገዋል። ከዚህም በላይ የሚተነትናቸው ጉዳዮችአዳዲስና ተዛማጅ ጉዳዮች ስለሆኑ መጽሐፉን የበለጠ ተመራጭ ያደርገዋል።
5. በአንዳንድ ነጥቦች ላይ እስካሁንየተሰሩ ሥራዎችን ከዳሰሰ በኋላ መረጃዎችተስተካክለው እንዲቀመጡ ማድረጉ ሌላው ጠቀሜታውነው። ለምሳሌ ቱራኤቭ ያሳተመው ገድለ ፊልጶስዘመኑ በ14ኛውመ.ክ.ዘ. ሳይሆን በ18ኛውመ.ክ.ዘ. የተገለበጠ መሆኑን ማሳየቱ፤ ገድለ አቡነአሮን የ15ኛውመ.ክ.ዘ. ሥራ ሊሆን እንደሚችል ለማሳያነትም ገድሉ የደብረሊባኖስን እጨጌዎች ሲዘረዝር የሚያቆመው አቡነ መርሐክርስቶስ7 (1455-1489) ላይ መሆኑንመጥቀሱ(7) ወዘተ… ጥንታዊሰነዶች/መዛግብት ሲጠኑ እንዲህእየተገናዘቡ መሆን እንደሚገባው የሚያስረዳ ነው።
፫. አስተያየት
ከላይባጭሩ እንዳየነው ይህ ሥራበጣም ማለፊያ ነው። ሆኖምእጅግ የተወጣለት ለማድረግ እና ምናልባትጊዜ ቢፈቅድለት ዲ/ዳንኤልይህን ሥራ በድጋሚቢያሳትመው ወይም ተመሳሳይሥራዎችን ለወደፊቱ ሲሰራ ቢጠቀምባቸው ብየ የምጠቁመውሁለት አስተያየቶች፣
• የሚያገኛቸውን የገድል ቅጂዎች ሁሉንም እያመሳከረ ልዩነታቸውን እየነቀሰ አንድ ወጥና የተመሳከረ ከሁሉምቅጂዎች የተውጣጣ እትም (8) ቢሰራ፣ቢተረጉም።
• የውጭ ሊቃውንት ያጠኗቸውን ከሚተረጉም ይልቅ እርሱያገኛቸውን አዳዲስ ገድላት ቢተረጉም ወይም በፊት ከተሰሩትጋር እያነጻጸረ ቢሠራ የርሱሥራ ሚናው የጎላሊሆን እንደሚችል ይታየኛል፤ በማለት ሃሣቤን እዚህ ላይእደመድማለሁ።
በመጨረሻምውድ ወንድሜ ዲ/ዳንኤልእግዚአብሔር ኃይልና ብርታቱን ሰጥቶ እንኳንይህን ጠቃሚ ሥራ አስፈጸመህ፤ እንኳንምደስ አለህ፤ ለወደፊቱም የበለጠ ያትጋህ በማለት መልካም ምኞቴን በመግለጽ አስተያየቴን እደመድማለሁ።
ስላደመጣችሁኝ ሁላችሁንም እግዚአብሔር ያክብርልኝ !!!!
1 ፊሎሎጂ የተሰኘውን ጥናት ስያሜወደ አማርኛ በቀጥታአቻ ትርጉም ለመስጠትለጊዜው አልተቻለም። በዚህ አቀራረብግን “ሥነ ድርሳን” ወይም “ጥንታዊ የጽሑፎች ጥናት” ብለንልንወስደው እንችላለን።
2 ከዚህ መካከል እኔ የማቀርበው ፊሎሎጂያዊ ጠቀሜታውን ነው።
3 የአቡነ አሮንና አቡነፊልጶስ ገድላት በራሺያዊውሊቅ በቱራኤቭ (Boris Turaev, 1905, Acta S. Aaron et S. Philippi,
Corpus Scriptorum Christianorum Orientalium, Scri. Aeth., ser xx)፣ የበጸሎተሚካኤል እና የአኖሬዎስገድላት
በጣሊያናዊው ምሁር በካርሎኮንቲሮሲኒ (K. Conti Rossini, 1905, Acta S. Basalota Mikael et S. Anorewos , in
Corpus Scriptorum Christianorum Orientalium, vol. 28-29, Scri. Aeth., 11-12) ታትመዋል።
4 የጋስጫው ቅጅ
5 ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እና ገድለ አቡነ በጸሎተሚካኤል – ግእዝ እና አማርኛ – አሳታሚ ማኅበረቅዱሳን፤ ታኅሣሥ ፳፻፬ዓ.ም.
6 በሐረሪ ቋንቋቀድመው ከተጻፉት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች መካከል በቀዳሚነቱየሚጠቀሰው በ16ኛው መ/ክ/ዘ እንደተጻፈ የሚገመተው ስለ ሐረር 4ቱ ከሊፋዎች ታሪክ የሚናገረውነው።
7 በእርግጥ የእርሱ ትርጉም“ኁልቈ ተዝካሮሙ ለአቡነ አሮንወዘደቂቁ” ብሎ በገጽ435 ላይ የደብረ ዳሬቶቹንአበው ብቻ ይዟልእንጅ የደብረ ሊባኖስ እጨጌዎችንአይዘረዝርም።
8 በሙያው አጠራርCritical Edition የሚባለውሲሆን የበለጡቱ የቅጂ ቤተሰቦችየተስማሙበት ዘር በንባቡ(text) ውስጥ ሲካተት ልዩነቶቹ (Variants) ደግሞ ለንጽጽርበግርጌ ይቀመጣሉ። ይህም Critical Apparatus የሚባለው ነው።

