የወገን ዋይታ በሳዑዲ ዐረቢያ
የማለዳ ወግ፦ የጅዳ ሸረፍያ እስከ ሽሜሲ የተሰማው የወገን ዋይታና እዚህ ያደረሰን መንገድ!
ነቢዩ ሲራክ
ፈታኙን ወቅት ለማለፍ …
የሳውዲ የምህረት አዋጅ አልቆ በሪያድ መንፉሃ ላይ አለምን ያሳዘነ ሰቆቃ ተፈጸመ … ስጋት ነግሶ፣ ኑሮ ከብዶን ጨንቆን ጠቦን ከርመናል! በዚህ ክፉ ቀን ወገን ወገኑን ለመርዳት ደፋ ቀና በማለቱ ረገድ የሃገሬ ልጅ ከጫፍ እስከ ጫፍ በቁጭት ስሜት ሲንቀሳቀስ የፖለቲካው ትኩሳት ወላፈን እያጓተተን አልሰነበትንም አይባልም።