ከአቶ ኃይለማርያም መጠበቃችን ስህተት ነበር
ግርማ ካሳ
በሕገ መንግሥቱ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ናቸው። የጦር ኃይሎች ኤታ ማጆር ሹምን፣ ተቀዳሚ ጠቅላይ ሚኒስትርን፣ የሚኒስቴር ካቢኔዎችን፣ የፌደራል ፖሊስ አዛዦችን … የመሾምና የመሻር ሙሉ ሥልጣን አላቸው። ፓርላማውን በትነው አዲስ ምርጫ መጥራትም ይችላሉ። ፓርላማው በፈለገ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትሩን አውርዶ፣ ሌላ መሾም ይችላል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ተጠሪነታቸው ለፓርላማው ብቻ ነው።