ሞት፣ ወያኔና “እኛ”
ፊልጶስ
የግፍ ጽዋው ሞልቶ፣ ...
ሞልቶ፣ ... ሞልቶ ፈሶ
ሰው መባል በሰው፣ ስዕብናችን አሶ
ከ'ጥናፍ - እስከ - አጥናፍ፣ ደማችን "'ረክሶ"፤
ውቅያኖስ፣ ባህሩን፣ ወንዙን አደፍርሶ
እዩት ይ'ጣለላል፣ አስፋልቱን አልብሶ።
ግን እኮ፣ ... እንኳ' ደም
ውኃ ፈሶ፣ አይቀርም
ይዘገያል እንጂ፣ በሰፈሩት ቁና፣ መሰፈር አይቀርም።
"ዓለም የም'ጠፋው፣ ሰይጣናዊ ምግባር በሚፈጽሙ ሳይሆን፤ ምንም ሳያደርጉ ቀጭ ብለው በሚመለከቷቸው ሰዎች ነው።" /አልበርት አነስታይን/