ዶ/ር ቴዎድሮስና ሌሎቹ
ግርማ ጌታቸው ካሳ
ኢሕአዴግን እንደ አንድ የሚመለከቱ፣ ሁሉን አባላቶቹን በጅምላ የሚፈርጁ ጥቂቶች አይደሉም። ነገር ግን ኢሕአዴግ ውስጥ የተለያዩ ቡድኖች አሉ። አንዱ የገነባውን አንዱ ያፈርሳል። አንዱ ሲያነሳ አንዱ ይጥላል። አንዱ ሰላማዊ ሰልፍ ሲፈቅድ፣ አንዱ በጎን የዜጎችን ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት ይጋፋል። አንዱ የታሰሩ የሕሊና እስረኖች እንዲፈቱ ሲፈልግ፣ ሌላው “እዚያው ቃሊቲ ይበስብሱ” ይላል። አንዱ በጎና ቀና ሕሊና ሲኖረው፣ ሌላው ደግሞ የጠመመና የጫካ አስተሳሰብ ያለው ሆኖ ይገኛል።