በጀርመን አይሁዶች ላይ የተፈፀመው ግፍ 75 ተኛ ዓመት መታሰቢያ
ከዛሬ 75 ዓመት በፊት ጀርመን ውስጥ በአይሁዶች ላይ የተፈፀመው ግፍ ሰሞኑን እዚህ ጀርመን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየታሰበ ነው ።
በጎርጎሮሳውያኑ ህዳር 9 ለህዳር 10 አጥቢያ 1938 ዓም በመላ ጀርመን የሚገኙ የይሁዲዎች ሙክራቦች ፣ ሱቆችና መኖሪያ ቤቶች በናዚዎች ትዕዛዝ እንዲወድሙ ተደርጓል ። ይሁዲዎችም ግፍ ተፈጽሞባቸዋል ።