ዉይይት፤ የገዥዉ ብልፅግና ፓርቲ የ 5 ዓመት ጉዞ – ስኬት እና ድክመት ሲገመገም

ኢትዮጵያን የሚመራዉ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ምህዳርን ከማስፋት ኤኮኖሚን ከማሳደግ ዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶችን ከማስጠበቅ አንጻር ድጋፍም ተቃዉሞም እየተሰማበት ዛሬ ደርሷል። ከ 15 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች እንዳሉት የሚገልፀዉ ብልፅግና መነሻና መዳረሻ ርዕዮተ ዓለሙ እንዴት ይገለፃል? ስኬት እና ድክመቱስ እንዴት ይለካል? አስተያየቶን ይፃፉልን።