ለምን ተለያይተንም ቢሆን አንሞክረውም?
እንደ የአንዲት ሉዓላዊት ሀገር ልጆች ሰላም ለመፍጥርና እርስበርስ በመዋደድ፣ በምህረትና በይቅርባይነት ላይ የተመሰረተ ህይወት ለመኖር ብዙ ምክንያት እንዳለን ሁሉ እንደ ሕዝብ እርስ በርስ ተጨፋጭፈን ለመተላለቅ፣ ጦር ተማዘን ደም ለመፋሰስ እንዲሁም ተለያይተንና ተበጣጥሰን ዘንተዓለማችን እንደ ጋለሞታ ልጆች በጎሪጥ እየተያየን ለመኖርም ብዙ ምክንያት አለን። በነገራችን ላይ ጸብ ከፈፈለገ አሁንኑ ከ 70- 80 የሚደርሰው ቋንቋችን ባህላዊ ልማዶቻችንና ወጎቻችንን፣ ሃይማኖታችን፣ የመልከዓ ምድር አቀማመጣችን፣ ታሪካዊ አመጣጣችን ወዘተ ምክንያቶችን በመደረደር እርስበርስ ተበቋቅሰንና ተላልቀን ምድሪቱ ኦናና በደም የታጠበች የወደመች ሀገር ለማድረግ ይህን ያክል ከባድም አይደለም። የአለመቀባበል ፍጻሜው ግልጽ እንደሆነ ሁሉ መንገዱም ቀላል ነውና። ሙሉ የጽሑፉ ይዘት ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ http://wp.me/p3MQOW-7l
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል