(Video) የኢትዮጵያ ታሪክ በአቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ አንደበት:
የኤርትራ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ አፈወርቅ ባሳለፍነው ሳምንትየኢትዮጵያ አዲስ ዓመት መባቻ ምክንያት በማድረግ እ.አ.አ መስከረም 06/2013 ከአገር ውስጥ (ከኤርትራ) የዜና አውታሮችና መገናኛ ብዙሐን በትግርኛ ቋንቋ ባያደረጉት ረጅም ቃለ መጠይቅ የሀገራችን የኢትዮጵያ ታሪካዊ አመጣጥና አመሰራረት አስመልክተው “ኢትዮጵያ ሁለተኛ የዓለም ጦርነት ተከትሎ የተፈጠረች ሀገር ናት። ያም ሆነ ይህ ሌላ ሰው የፈልገው ሊል ይችላል ይህች ኢትዮጵያ በመባል የምትታወቀው ሀገር ግን ሁለተኛ የዓለም ጦርነት ተከትሎ የመጣ የዓለም ሥርዓት ሥርዓቱ ራሱ በሚመርጣቸው ገዢዎች ይጠቀምባት ዘንድ የፈጠራት ኃይል ናት።” በማለት ሉዓላዊት አገር ሀገረ ኢትዮጵያ የገሸለጡበትና ምድሪትዋ የሸለቱበት ቃል ቀጥሎ የተቀመጠውን ሊንክ (11. 16 ጀመሮ) በመጫን ያደምጡ ዘንድ ተጋብዘዋል። http://www.youtube.com/watch?v=MoU7vG3bCBQ
ኢሳት ጨምሮ የአማርኛ “የዜና” አውታሮችና ድረ ገጾች ይህን መዘገብ ያልፈለጉበት ወይም መልስ ያልሰጡበት ምክንያት ለእርስዎ ትቻለሁ።
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
E-mail: [email protected]
http://salsaywoyane.wordpress.com/
United States of America
Sep. 12, 2013