አርባምንጭ በፌደራል ፖሊስ አባላት ስትታመስ ዋለች
ጥቅምት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአርባምንጭ ምንጮች እንደተናገሩት በቅርቡ የአርበኞች ግንቦት 7 ደጋፊዎች ኢህአዴግን የሚያወግዙና ወጣቱ ለመብቱ እንዲነሳ የሚቀሰቅሱ በራሪ ወረቀቶችን ከበተኑ በሁዋላ፣ ድርጊቱን ፈጽመዋል ብለው የጠረጠሩዋቸውን ወጣቶች በጅምላ ለማሰር ከትናንት ጀምሮ አሰሳ አካሂደዋል። አሰሳውን ተከትሎ የ70 አመት አዛውንት እናትን ጨምሮ ሴቶችና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶች ተይዘዋል። ከተያዙት መካከል የሰማያዊ …
