ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት በም/ጠ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሚመራው የልኡካን ቡድን ላይ ጥቃት ፈጽሞ በርካታ ወታደሮችን መግደሉን የግንባሩ ቃል አቀባይ ለኢሳት ገለጹ። አቶ ሀሰን አብዱላሂ እንደገለጹት ጥቃቱ የተፈጸመው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ9 የክልል መሪዎችንና ባለሀብቶችን አስከትለው በአካባቢው ጉብኝት ለማድረግ ቀብሪደሀር አየር ማረፊያ ባረፉበት ወቅት ነው። ባለስልጣኖቹ ጉበኝት እንደሚያደርጉ አስቀድሞ …

ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ልሳን የሆነው ፍኖተ-ነፃነት እንደዘገበው፦አብረሃ ጅራ እና አብደራጊ የተባሉ ሁለት ወረዳዎች ከዚህ በፊት በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን ስር የነበሩ ቢሆንም፤  መሬቱ  ግን ባብዛኛው በቅርብ ጊዜ ከትግራይ ክልል በመጡ ገበሬዎች ተይዟል፡፡ ቦታዎቹ በብዛትና በስፋት የሰፈሩት ገበሬዎቹች አስተዳደራዊ የበላይነትን በመጠቀም ወረዳዎቹን ወደ ትግራይ ለማካለል እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተጠቁሟል፡፡ …

ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ራሱ  የ 40 በ 60 መኖሪያ ቤት ሠርቶ  ለመስጠት የሰጠውን መግለጫ አምነው ከ81 ሺህ ሰዎች በላይ ሙሉ ክፍያ ከፈፀሙ በሁዋላ፤  ሀሳቡን በመቀየር ከፋዮቹ በማህበር ተደራጅተው ቤቱን ራሳቸው እንዲሠሩ መወሰኑ ተመዝጋቢዎችን አሳዝኗል። እንደ ሪፖርተር ዘገባ በአሁኑ ጊዜ  መቶ በመቶ  የከፈሉ የ40/60 ተመዝጋቢዎች በመኖርያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበር ወደ ተነደፈው …

ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ(ህወሀት) ውስጥ የተካረረ አለመግባባት እንደተፈጠረ በስፋት በሚነገርበት በዚህ ወቅት አቶ ስብሀት ነጋ ፣ የኢህአዴግ እንጂ የመለስ የሚባል ራእይ የለም ብለዋል። የህወሀት መስራች የሆኑት አቶ ስብሀት ነጋ ይህን ያሉት ከጋዜጠኛ ደረጀ ደስታ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው። አቶ ስብሀት ፦” መለስ የ ኢህአዴግን ራዕይ ለማስፈፀም ከፊት ሆኖ ብዙ …

ጥቅምት ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦጋዴን የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰትና የጦር ወንጀል የሚያሳየው ዘጋቢ ፊልም በቅርቡ በስዊድን ቴሌቪዥን መለቀቁን ተከትሎ ዛሬ አርብ፣ የስዊድን የጦር ኮሚሽን ማስረጃዎችን ተረክቧል። ማስረጃዎችን ለኮሚሽኑ ያስረከቡት ሂደቱ ዋና ተወናይ የሆነው ወጣት አብዱላሂ የሱፍና የአለማቀፍ የህግ ባለሙያዎች ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ስቴላ ጋርደ ናቸው። የጦር ኮሚሽኑ የቀረበለትን ማስረጃ በማየት አፋጣኝ ውሳኔ እንደሚሰጥ …

ጥቅምት ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰብአዊ መብት ድርጅቱ ” በማዕከላዊ የሚገኙት መርማሪ ፖሊሶች ታሳሪዎች ጥፋታቸውን እንዲያምኑ፣ እንዲናገሩ ወይም ሌላ መረጃ እንዲያወጡ የሚያደርጉት በሃይል የማስፈራራት መንገድን በመጠቀም ሲሆን ይህም እስከ ማሰቃየት እና ሌላ ጎጂ አያያዝ እስከ መፈጸም ይደርሳል፡፡ ” ብሎአል። ከ2002 ዓም እስከ 2005 ዓም ባለው ጊዜ ውስጥ በማእከላዊ እስር ቤት የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን …

ጥቅምት ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ከሙስና መንሰራፋት ጋር በተያያዘ የገጠመውን ፈተና በድል ለመወጣት ሕዝቡን ማሳተፍ እንዳለበትና ያለሕዝቡ ተሳትፎ የሚደረጉ ነገሮች ሁሉ የማይመለስ ጥፋትን ያስከትላሉ ሲሉ አቶ ስብሃት ነጋ ለኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮችን ምክር ለግሰዋል። የጸረ ሙስና ኮምሽን በሸራተን ሆቴል ያዘጋጀውና በምክትል ጠ/ሚኒስትር ማዕረግ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ሙክታር ከድር እና የፓርላማው አፈጉባዔ አቶ …

ጥቅምት ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመንገድ ጋር በተያያዘ ከዋግ ህምራ ዞን ርዕሰ ከተማ ሰቆጣ የሚሰማው የተቃውሞ ድምጽ በሁሉም የዞኑ ወርዳዎች መዳረሱን በስፍራው ያሉ ወኪሎች ገልጸዋል፡፡ ” የልማት ጥያቄያችን አልተመለሰም ፤  መንግስት ሰቆጣን እረሰቱዋል ፤ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ትግራይ መሄድ ግድ ብሎናል” ሲሉ ነዋሪዎች ለመንግስት ባለስልጣናት  ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ በቅርቡ ከሰቆጣ ፤ አበርገሌ ፤ ዝቋላ፤ ስሃላ …

ጥቅምት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የፓለቲካ እስረኞች ላይ ምርመራ ሲያካሂዱ ስቃይ እንደሚፈጽሙ ተቀማጭነቱን በአሜሪካ ያደረገው ሂዩማን ራይትስ ዎች ዛሬ ይፋ አደረገ፡፡ መንግስት በበኩሉ የቀረበውን ውንጀላ አስተባብሎ ሪፖርቱ ከእውነት የራቀና ተአማኝነት የሌለው ነው ብሏል፡፡ ድርጅቱ ታስረው የነበሩ እማኞች ዋቢ በማድረግ ባወጣው ሪፖርት ባለስልጣናት ከእስረኞች ቃል ለመቀበል ሲሉና ምርመራ ሲያካሂዱ ድብደባ እንደሚፈጽሙ አመልክቷል፡፡ …

ጥቅምት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያና ኬንያ በግልገል ጊቤ ሶስተኛ የሀይል ማመንጫ ግድብ ላይ ያላቸውን አለመግባባት እልባት ለመስጠት የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ፕሮግራም ሁለቱንም ሀገራት በማግባባት ላይ እንደሆኑ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ በኦሞ ወንዝ ላይ በመገንባት ላይ ያለችው የሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት በቅርብ የሚገኘውን የኬንያን ቱርካና ሀይቅ ይጎዳል በሚል የኬንያ መንግስት የአካባቢ ተቆርቋሪ ድርጅቶች ቅሬታቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡ …

ጥቅምት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢትዮጵያዊውን የእርሻ ሳይንቲስት አዲስ ለተቋቋመ የሳይንቲስቶች አማካሪ ቦርድ አባልነት መረጠው፡፡ ሳይንቲስቱ ፕሮፌሰር ገቢሳ ኢጀታ 26 አባላትን ላካተተው የተባበሩት መንግስታት የሳይንቲስቶች አማካሪ ቦርድ ሲመርጥ ብቸኛ የእርሻ ሳይንቲስት እንደሆነ ኢሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ አዲሱ የተባበሩት መንግስታት የሳይንቲስቶች አማካሪ ቦርድ በአለም አቀፍ በተለያዩ ዘርፍ የታወቁ ሳይንስቶችን በአባልነት ይዞ ይገኛል፡፡ …

ጥቅምት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በጋምቤላ ክልል ንዌር ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ሚኒኛንግ ከተማ የተፈጠረው ግጭት ተባብሶ የሞቱ የመከላከያ ሰራዊት ቁጥር መጨመሩና በርካታ መሳሪያዎች ከመከላከያ ካምፕ መወሰዳቸው ተገለጸ፡፡ ባለፋው እሁድ አንድ መሳሪያ የታጠቀ ሰው እግር ኳሱን ሲመለከቱ በነበሩ ሰዎች መካከል ባስነሳው አለመግባባት የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና ነዋሪዎች ግጭት ውስጥ ገብተው ሰንብተዋል፡፡ ግጭቱ …

ጥቅምት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል ዳውሮ ዞን ከሁለት ዓመት በፊት ተቀስቅሶ የነበረው የመልካም አስተዳደር እጦት ጥያቄ በአዲስ መልክ መቅረብ በመጀመሩ በዞኑ ውጥረት መንገሱን ተገለጸ፡፡ በዞኑ የሚኖሩ ማህበረሰብ ከፍተኛ የሆን የመልካም አስተዳደር ችግር እንዳለባቸው በመግለጽ ላይ መሆናቸውን የዳውሮ ዞን አካባቢ ተወላጅ የሆኑት አቶ ፍሰሀ ተስፋዬ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አመልክተዋል፡፡ አዲስ …

ጥቅምት ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን በጨንጫ ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤት መምህራን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ከደሞዛቸው ላይ ገንዘብ መቆረጡን ተከትሎ ካለፉት 3 ቀናት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ እያደረጉ ነው፡፡ የጨንጫ ፣ ጭነቶ፣ ጦሎላ፣ ጨፌ፣ ጺዳ እና ቱክሻ  ትምህርት ቤቶች መምህራን በአድማ ላይ መሆናቸውን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ተማሪዎች ቤታቸው …

ጥቅምት ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚ ሀይለማርያም ዛሬ በተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከፓርላማ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ መንግስት የጎዳና ላይ ነውጥ ከሚያሰቡት ሀይሎች ጋር ለመነጋገር የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል። አቶ ሀይለማርያም በተቃዋሚዎች በኩል የሚቀርበው ቅጥ ያጣ ፍረጃ እና የጥላቻ ፖለቲካ እንዲቆም  እንዲሁም የጎዳና ላይ ነውጥ እናደርጋለን በማለት የሚያስቡ ሀይሎችም ሀሳባቸውን እንዲያቆሙ ጠይቀዋል። “የጎዳና …

ጥቅምት ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስብሰባው ላይ የተሳተፉ አባቶች ለኢሳት እንደገለጹት በዛሬው ስብሰባ የልማት ኮሚሽኑ ሪፖርት ሰፊ ሽፋን የተሰጠው ሲሆን፣ መንግስት በቤተክርስቲያኑዋ ገቢ ላይ እየተጠቀመ መሆኑ ተነግሯል። የኮሚሽኑ መሪ ” በጭንቅ ውስጥ ነው እየሰራን ያለነው ፣ በመኖርና ባለመኖር ውስጥ እንገኛለን ያሉ” ሲሆን፣ ስሜታቸውን በድፍረት ሲናገሩ ከዋሉት ጳጳሳት መካከል ብጹዕ አቡነ ቄርሊዎስ ” ዛሬ ጀመርነው፣ …

ጥቅምት ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ኃ/ማርያም ዛሬ ጠዋት የአገር አቀፍ የጸረ ሙስና ጥምረት 2ኛ መደበኛ ስብሰባ በሸራተን አዲስ በተካሄደበት ስነስርኣት ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር አንዳንዶቹ ባለሃብቶች ከከፍተኛ መንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ሳይቀር የጠበቀ ቁርኝት ፈጥረው እንደነበር አምነው በዚህም ምክንያት ሰዎቹን መንግስት አይደፍራቸውም ተብሎ በህብረተሰቡ ዘንድ እስከመገመት ደርሶ ነበር ሲሉ ተናግረዋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት የመንግስት …

ጥቅምት ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ በአዲስ አበባ የውሀ ቀለም አይቶ የማያውቅ ህዝብ አለ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ 65 በመቶ የሚሆነው የአዲስ አበባ ህዝብ ውሀ 24 ሰአት እንደሚያገኝ ገልጸው፣ 20 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በሳምንት 5 ቀናት፣ ከ10-15 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በሳምንት አንድ ቀን ውሀ ያገኛል ብለዋል። በአብዛኛው የአፍሪካ ዋና ዋና ከተሞች የውሀ …

ጥቅምት ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው መንበረ ፓትሪያርክ ስብሰባ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ባለው 32ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በቤተክርስቲያኑዋ ታሪክ  ተሰምቶ የማያውቅ ተቃውሞ ተከስቷል። አንድ በስብሰባው ላይ የተሳተፉ አባት እንደገለጹት በስብሰባው ላይ ”  ይህ መንግስት የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ እንደተነሳ በስፋት ተነግሯል። የፌደራል ጉዳዮች የሀይማኖት ክፍል ሃላፊዎች ዛሬ ስለ አክራሪነትና ጽንፈኝነት …

ጥቅምት ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ልዩ ሀይል እየተባለ በሚጠራው ታጣቂ ሚሊሺያ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት፣ አስገድዶ መድፈርና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መፈጸሙን የሚያመለክት ዛጋቢ ፊልም በስዊድን ቴሌቪዥን መለቀቁን ተከትሎ ፣ የክልሉ መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንቱን ቃለመጠይቅ በማድረግ አዲስ ዘጋቢ ፊልም ሰርቶ አቀረበ። የክልሉ መንግስት በለቀቀው አዲስ ፊልም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አድናቆታቸውን የገለጹበት ክፍል የተካተተ ሲሆን፣ …

ጥቅምት ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከተማሪዎች አለባበስ ጋር  በተያያዘ ከቀናት በፊት የተጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ እልባት ሳያገኝ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፡ ትናንትና ከትናንት ወዲያ ምሽት ላይ ጥይት ሲተኮስ ማምሸቱን የገለጹት አንዳንድ የተማሪዎች ቤተሰቦች፣ የተኩሱ ምክንያት ጩሀት የሚያሰሙ ተማሪዎችን ዝም ለማሰኘት ያለመ ነው ብለዋል። ተማሪዎች በየክፍላቸው ሆነው ተቃውሞ እአሰሙ እንደሚገኙ የገለጹት ቤተሰቦች፣ አንዳንዶች …

ጥቅምት ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በወጣት አብዱላሂ ሁሴን አማካኝነት በኢትዮጵያ የኦጋዴን ክፍል የተፈጸመውን የጦር ወንጀልና የሰብአዊ መብት ጥሰት ፊልም የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም በስዊድን ቁጥር አንድ ቴሌቪዥን በትናንትናው እለት መቅረቡን ተከትሎ አለማቀፉ ጠበቆች ጉዳዩን ወደ አለማቀፍ ፍርድ ቤት ለመውሰድ እንቅስቃሴ ጀመረዋል። ወጣት አብዱላሂ ለኢሳት እንደገለጸው ፊልሙ ከተላለፈ በሁዋላ ሚዲያዎች ሸፊ ሽፋን የሰጡት ሲሆን፣ ስቴላም የተባሉ …

ጥቅምት ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእየአመቱ የሚከበረው የኢድ-አል አድሃ ( አረፋ) በአል ኢብራሂም ልጁን ለመስዋት ያቀረቡበትን እለት ለመዘከር ነው። በአዲስ አበባ በተካሄደው የበአል አከባበር ስነስርአት ከዚህ ቀደም ያልታዩ ክስተቶች ታይተዋል። ዘወትር እንደሚደረገው የመጅሊስና አዲስ አበባ መስተዳድር ባለስልጣናት ንግግር አላደረጉም። ድምጻችን ይሰማ ትናንት ባወጣው መግለጫ የመንግስት ባለስልጣናት ወይም የመጅሊስ አመራሮች መልእክቶችን ለማስተላለፍ ንግግር ማድረግ ከጀመሩ …

ጥቅምት ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመስተዳድሩ ውስጥ የሚሰሩ የኢሳት ወኪሎች እንደገለጹት ከዚህ ቀደም በመስተዳድሩ ውስጥ የሚፈጸመውን ሙስና ማጋለቱን ተከትሎ መንግስት ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ከቦታቸው በማንሳት ወደ ሌሎች መስሪያ ቤቶች በማዛወር የህዝቡን ቅሬታ ለመመለስ ጥረት ቢያደርግም፣ አሁንም በአስተዳደሩ ኢንዱስትሪ ልማትና ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት ስር በሚገኙት የከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ፣ የመሬትና መሬት ነክ ቋሚ ንብረት ምዝገባ …

ጥቅምት ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአለማቀፍ የወንጅል ፍርድ ቤት 50 አመታት የተፈረደባቸው ቻልረስ ቴለር  በዛሬው እለት ለእንግሊዝ ፍርድ ቤት ተላልፈው የተሰጡ ሲሆን፣ በሩዋንዳ እንዲታሰሩ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተድርጎባቸዋል። ፕሬዞዳንቱ በሴራሊዮን ለተፈጸመው የጦር ወንጀል እጃቸው አለበት በሚል ዘሄግ የሚገኘው የወንጀል ፍርድ ቤት አምና የ50 አመታት እስር እንደፈረደባቸው ይታወቃል።  

ጥቅምት ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለወራት ተቋርጦ የነበረው የድምጻችን ይሰማ ተቃውሞ ነገ በመንግስት ባለስልጣናትና በመጅሊስ መሪዎች ንግግር ላይ ተግባራዊ እንደሚሆን ከወጣው መርሀግብር ለማወቅ ተችሎአል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚካሄደው ዝግጅት የመንግስት ባለስልጣናትም ሆኑ የመጅሊስ አመራሮች ንግግር የሚያደርጉ ከሆነ ንግግሩ እስኪቆም ድረስ ተቃውሞው ይቀጥላል። ተቃውሞው በመላ አገሪቱ እንደሚከናወን ድምጻችን ይሰማ ያወጣው መረጃ ያመለክታል። ፖሊስ ጸጥታ ለማስከበር …

ጥቅምት ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲሱን የትምህርት አመት ለመጀመር ምዝገባ ያጠናቀቁት ተማሪዎች ፣ ከአለባበስ ጋር በተያያዘ ባነሱት ተቃውሞ የግቢው መስታውቶችና አንዳንድ አገልግሎት መስጪያ እቃዎች መሰባበራቸው ታውቋል፡፤ ይህንንም ተከትሎ ፖሊስ ግቢውን መቆጣጠሩን ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ተማሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። የተቃውሞው መነሻ የዩነቨርስቲው ባለስልጣናት ከቤተከርስቲያን መልስ ነጠላ ለብሰው ወደ መመገቢያ ክፍል የገቡትን ተማሪዎች ፣ ነጠላ ለብሳችሁ መግባት …

ጥቅምት ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሕአዴግ ካድሬዎችን ለማሰልጠን የተገነባውን የፖለቲካ ማሠልጠኛ ተቋም በሚኒስትር ማዕረግ ሲመሩ የነበሩት አቶ አዲሱ ለገሰ ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የተውጣጡ ምክትሎች ተሹመውላቸዋል፡ ፡ ከብአዴን አቶ ለገሰ ቱሉ፣ ከደሕዴን አቶ ወንድሙ ገዛኸኝ፣ ከሕወሓት አቶ ነጋ በርሄ ሲሆኑ፣ ከኦሕዴድ የተወከለው አመራር እስካሁን አለመታወቁን ሪፖርተር ዘግቧል። ማሠልጠኛ ማዕከሉ  በስድስት ዙሮች በርካታ ካድሬዎችን ያሰለጠነ መሆኑን …

ጥቅምት ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክረምቱን መውጣት ተከትሎ ወባ በሚያጠቃቸው ወረዳዎች ወረርሺኙ መከሰቱን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በገዳይነቱ  ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ  የሚይዘው የወባ በሺታ በአሁኑ ስዓት በአርሶ አደሩ ህይዎት ውስጥ ፈታኝ መሆኑን ከሁሉም ክልሎች ለፌድራል ጤና ጥበቃ ሚኒስትር የተላለፈው መረጃ ያመለክታል፡፡ በበሺታው ፈውስ አጥተናል የሚሉት ኗሪዎች ከገበያ እንደ ሸቀጥ እቃ የሚገዙዋቸው መዳህኒቶች የማዳን አቅም …

ጥቅምት ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሱዳናዊው ቱጃር ሞ ኢብራሂም የተቋቋመው የሞ ፋውንዴሽን መልካም አስተዳደርን ያሰፈረ፣ ስልጣኑን በሰላም ለለቀቀ የአፍሪካ መሪ 5 ሚሊዮን ዶላር በሽልማት መልክ ይሰጣል። በዚህ አመትም ለ4ኛ ጊዜ አሸናፊ የሚሆን የአፍሪካ መሪ አልተገኘም። እስካሁን ድረስ ሽልማቱን ያሸነፉት የኬፕ ቨርዴው ፔድሮ ቬሮና ፓይሬስ፣ የቦትስዋናው ፌስተስ ሞጋኤና የሞዛምቢኩ ጆአኪም ቺሳኖ ናቸው።

ጥቅምት ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ ባወጣው ዘገባ እንደገለጸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በናይጀሪያ ቡድን መሸነፉ ያበሳጫቸው  ደጋፊዎች የናይጀሪያን ቡድን አሳፍሮ ሲጓዝ በነበረው አውቶቡስ ላይ ድንጋይ በመወርወር አንድ ተጫዋች አቁስለዋል። ኖሳ ኢግቦር የተባለው ተጫዋች መዳፉ አካባቢ መመታቱን የዘገበው ቢቢሲ፣ የናይጀሪያ ቡድን ባለስልጣናት ክስተቱን ለአለማቀፉ እግር ኳስ ፌደሬሽን ማሳወቃቸውንም ገልጿል። ድርጊቱን ተከትሎ ምናልባትም ፊፋ በኢትዮጵያ ላይ …

ጥቅምት ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ እያካሄደ ባለው የአባላት ግምገማ ወቅት ከ15 ሺ በላይ አባላት በአንድ ጊዜ መልቀቂያ ማስገባታቸው ይፋ ተደርጓል። ስራቸውን ከሚለቁበት ምክንያቶች መካከል  በድርጅቱ አመኔታ ማጣት ፣ ተገቢውን አገልግሎት ክፍያ አለማግኘት፣ ለድርጅቱ የሚከፍሉት ገንዘብ ከፍተኛ መሆን እና የድርጅቱ አባላት ሹመት በወገን መሆኑ የሚሉት ተጠቅሰዋል። ከፍተኛ የአባላት መልቀቂአ ቁጥር ከተመዘገበባቸው ክልሎች መካከል ኦሮሚያ …

ጥቅምት ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አስተዳደሩ ቀደም ሲል በወር 530 ሺ ብር ገደማ ቤት በመከራየት ውል ከፈጸመ በኋላ ከሕዝብ በተከታታይ ተቃውሞ መሰማቱን ተከትሎ እንዲሰረዝ በመወሰን ለሁለተኛ ጊዜ 400 ሺ ብር የሚያወጣ ቤት በአዲስአበባ አክሱም ሆቴል አካባቢ መከራየቱ ሌላ ተቃውሞና ውግዘትን እያስከተለበት ይገኛል፡፡ አስተዳደሩ ፕሬዚደንቱ በመስከረም ወር 2006 ስልጣን እንደሚያስረክቡ አስቀድሞ እያወቀ ምንም ዓይነት ዝግጅት …

ጥቅምት ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዓለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ፍትሀዊ ባልሆነ መልኩ በ አፍሪካ ላይ ስጋት እያሳደረ ነው  ሲሉ  አንድ ከፍተኛ  የህብረቱ ባለስልየጣን መናገራቸውን ቢቢሲ ዘገበ። የኢትዮጵያው  የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሀኖም ይህን ያሉት፤ዛሬ በአዲስ አበባ በተጀመረው የህብረቱ ልዩ ስብሰባ ላይ ነው። ቴዎድሮስ በስብሰባው ላይ ፦”ፍርድ ቤቱ ያነጣጠረው አፍሪካ ላይ ነው።”ማለታቸውን የገለጸው ቢቢሲ፤ በስብሰባው …

ጥቅምት ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመንግስት ጋር ባላቸው ከመጠን ያለፈ ወዳጅነትና ቅርበት የሚታወቁት ሼህ መሀመድ ሁሴን አል-አሙዲ ለእግዶች ማረፊያ የተከራዩዋቸውን  ቤቶች እንደተነጠቁ የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ሼሁ፤ ከውጪ አገራት ለሚመጡባቸው እንግዶች በአያት ሲ.ኤም. ሲ   25 መኖሪያ ቤቶችን ለውጪ አገር ጎብኝዎች በተሰላ ሂሳብ ተከራይተው +በዶላር ምንዛሬ እየከፈሉ ሲገለገሉባቸው መቆየታቸውን የጠቀሱት እነዚሁ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ  ምንጮች፤ መንግስት …

ጥቅምት ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእስር ላይ የምትገኘው የጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ እህት እስከዳር ዓለሙ የቃሊቲ ማረሚያ ቤትን ይቅርታ ካልጠየቀች እህቷን መጎብኘት እንደማትችል ተገለጸላት። እስከዳር”  አስቂኝም፤አስገራሚም ነገር”በሚል ርዕስ  በፌስ ቡክ ገጿ ላይ እንዳሰፈረችው፦ማረሚያ ቤቱ በደብዳቤ ይቅርታ ካልጠየቅሽ ሁለተኛ እህትሽን አታያትም እንዳላት ገልጻለች። “ሰብዐዊ ጥሰት የተፈፀመብን ፣ የተጉላላን ፣ የተሰደብን ፣ የተዛተንብ፣የተደበደብን . . . እኛ፡፡ …

መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በ2005 ዓም የስራ ክንውንና በ2006 ዓም የስራ እቅድ በሚል ርእስ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የኢህአዴግ አባላት ግምገማዎች እየተካሄዱ ነው። በኦሮሚያ ክልል በርካታ የኢህአዴግ አባላት የሆኑ የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች አክራሪነትንና ሽብረተኝነትን በተመለከተ ኢህአዴግ የሚከተለውን ፖሊሲ መተቸታቸውን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል። በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ባለው ግምገማ ደግሞ በርካታ የብአዴን አባላት በፓርቲውና …

መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነት ጋር በተያያዘ ባለፈው አመት የተጀመረውን ተቃውሞ ተከትሎ 40 ሰዎች በቅርቡ ከእስር ቢፈቱም፣ ከተፈቱት መካከል 20ዎቹ ከስራ ተባረዋል። ከተባረሩት መካከል ዳኞችና አቃቢ ህጎች ይገኙበታል። 14 ቱ ቀደም ብለው የተባረሩ ሲሆን፣ 6ቱ ደግሞ በትናንትናው እለት መባረራቸው ታውቋል። እንዲሁም በወረዳው ሌላ ተቃውሞ እንዲቀሰቀስ እየመከሩ ነው የተባሉ 6 ሰዎች ደግሞ ካለፈው ሀሙስ …

መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጣው እንደዘገበው  መላኩ ደምሴ  ሐሙስ መስከረም 30 ቀን 2006 ዓ.ም. እኩለ ቀን ላይ አዲስ አበባ ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ ከሚገኘው የሪፖርተር ቢሮው በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል የፖሊስ ኃይል አባላት ተይዞ ወደ ሐዋሳ ከተማ ተወሰዷል፡፡ ጋዜጠኛው ለጥያቄ የተወሰደው ሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ነሐሴ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. በጋዜጣው የፊት ገጽ ላይ ‹‹የደቡብ …

መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው ሊቢያው አምባገነን መሪ ቻርለስ ቴለር በጦር ወንጀለኝነት ተከሰው ዘ ሄግ በሚገኘው አለማፉ የወንጀል ፍርድ ቤት የ50 አመታት እስር ከተፈረደባቸው በሁዋላ፣ የእስር ጊዜያቸውን በእንግሊዝ እንደሚፈጽሙ ታውቋል። ቻርለስ ቴለር በሴራሊዮን ጦርነት ወቅት በተቃዋሚዎች የተፈጸመውን ኢሰብአዊ ድርጊት ደግፈዋል በሚል ነበር ጥፋተኛ የተባሉት። የ65 አመቱ ቴለር ቀሪ ህይወታቸውን በእንግሊዝ እስር ቤት እንደሚያጠናቅቁ …

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር ፊታውራሪነት የአለማቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤትን አሰራር ለመቃወም አፍሪካ መንግስታት በአዲስ አበባ ለአስቸኳይ ስብሰባ መጠራታቸው ታውቋል። ጠ/ሚ ሀይለማርያም ሰሞኑን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ቀርበው የወንጀል ፍርድ ቤቱን ተችተው ነበር። ይህን ተከትሎ በሚመስል ሁኔታ የወቅቱ የህብረቱ ሊቀመንበር መሪዎችን ከጥቅምት 1 እስከ 2 በሚካሄደው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ …

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የአራት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን የሥራ ዝውውር በዚህ ሳምንት እንደሚያደርግ ሪፖርተር ዘገበ። ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ጽሕፈት ቤቱ ዝውውሩን የሚያደርገው በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የተፋሰስ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር  በሆኑት አቶ ሽፈራው ጃርሶ፣ የአውሮፓ ኅብረትና ቤኔሉክስ አገሮች አምባሳደር …

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ2005 በጀት ዓመት የአገሪቱ ኢኮኖሚ 9 ነጥብ 7 በመቶ ማደጉን የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር አብርሃም ተከስተ በበርካታ ፈተናዎች ባሉበት ወቅት እንዲህ አይነት እድገት መመዝገቡን አወድሰዋል። የግብርና ዘርፍ በ2005 በጀት ዓመት የ7 ነጥብ 1 በመቶ የአገልግሎት ዘርፉ  ደግሞ የ4 ነጥብ 9 በመቶ እድገት መመዝገቡ ተገልጿል። …

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሰኞ አዲስ ፕሬዚደንት በመምረጥ የዚህን ዓመት ሥራውን የጀመረው የኢትዮጵያ ፓርላማ በፕሬዚደንት ሙላቱ ተሾመ በንባብ የቀረበውን የመንግስት የዚህ ዓመት የትኩረት አቅጣጫና ዕቅድ ጋር በተያያዘ በቀጣይ ሳምንት ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በተገኙበት በሚቀርቡ የድጋፍና የተቃውሞ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ይወያያል፡፡ ፓርላማው በትላንት ውሎው መስከረም 27 ቀን 2006 ዓም አዲሱ ፕሬዚደንት ያደረጉትን …

  መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ውይይታቸውን ያደረጉ የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ ጋዜጠኞች ሚዲያዎቹ በመንግስት የአፈና እና የእጅ አዙር ቁጥጥር ስር የወደቁ ናቸው ብለዋል።   በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተካሄደው የባለሙያዎች የጥናት እና ምርምር ግኝት ስራዎች ላይ ተመርኩዞ ከባለሙያዎች ጋር በተደረገው ውይይት ላይ በቀረቡት ጽሁፎች እንደተገለፀው የኢትዩጵያ ሚዲያዎች አዲስ የሚቋቋሙትም ሆነ ነባር …

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሱፐር ኤግልስን ካሸነፉ መንግስት  እንደሚሰጣቸው ቃል የገባላቸው ቦነስ በቂ እንዳልሆነና ስሜታቸውን የሚያነሣሳ እንዳልሆነ ነው  ተጫዋቾቹ የተናገሩት። አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ከቀናት በፊት የ22ቱን ተጫዋቾች ስም ይፋ ያደረጉ ሲሆን፤ በቡድኑ ውስጥ ወሳኝ ተጫዋቾች የሆነው ጌታነህ ከበደ በጉዳት ምክንያት በቡድኑ ውስጥ አልተካተተም። በቀራቸው የደርሶ መልስ ጨዋታ ናይጀሪያን አሸንፈው ለዓለም ዋንጫ ካለፉ …

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከአማራ ክልል ባለስልጣናት ባገኘው መረጃ  የጃን አሞራ፣ የማይጸብሪ አዋሳኝ፣ ራስዳሸንን ጨምሮ የአዲአርቃይን አካባቢዎች ወደ ትግራይ፣ በመተማ በኩል ደግሞ የተወሰነውን ክፍል ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለመስጠት ድርድር በመካሄድ ላይ ነው። ባለስልጣናቱ ቀደም ብለው የህዝቡን የልብ ትርታ ለማዳመጥ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር የደረሰን መረጃ የሚያመለክት ሲሆን፣ አንዳንድ የወረዳ ባላስልጣናት ጉዳዩን ወደ …

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰማያዊ ፓርቲ ትናንት ባወጣው መግለጫ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በምስራቅ ጎጃም በአዋበልና አነደድ ወረዳ የሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስትያናት ከሚያዚያ እስከ ነሐሴ 2005 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ብቻ በእሳት ተቃጥለው በቤተክርስቲያናቱ ውስጥ የሚገኙ ነዋየ ቅድሳት፣ ልዩ ልዩ አልባሳት፣ ብዙ መጽሐፍትና ንብረት መውደሙን ጠቅሷል። ፓርቲው እንዳለው  የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት በኩል ምክንያቱ …

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከፍተኛ የአመራር ደረጃ የሚገኙ የኦህዴድ ባለስልጣናት ለ10 ቀናት በአዳማ ከተማ በአክራሪነት እና ሽብርተኝነት ዙሪያ ስልጠና ሲሰጣቸው ከቆየ በሁዋላ፣ አሁን ደግሞ ስልጠናው ወደ ታች አመራር አባላት በመውረዱ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ሰራተኞች ለ10 ቀናት ያክል ጽህፈት ቤቶቻቸውን ዘግተው ስልጠናውን እየወሰዱ ነው። ህዝቡ  ጉዳይ ለማስፈጽም ወደ ተለያዩ መስሪያ ቤቶች ሲሄድ …

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደቡብ ሱዳን ውጪ ጉዳይ ምኒስትር የሆነው ባርናባ ማርያል  እንደተናገረው ህዝበ ውሳኔ ባፋጣኝ መደረጉ በአበየ ግዛት ለሚኖሩ ነዋረዎች አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚሰጥና በውሳኔው መሰረት ነዋሪው ወደ ደቡብ ሱዳን ካልሆነ ወደ ሰሜን ሱዳን መቀላቀል እንደሚችል ገልፅዋል:: የደቡብ አፍረካ ሽምጋይ የሆኑት ታቦ እምቤኪይ የሚመራወ የአፍረካ ከፍተኛው አስፈጻሚው አካል የአብየ ሪፈረደም በዚህ ወር …