ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከእስር ተፈተው በሄሊኮፕተር ወደ ጦሩ ሆስፒታል ለምርመራ ተወስደዋል፣ ጊዚያዊው መንግስት ከቤታቸው እንደማይወጡ አስታውቋል። ፕሬዚዳንቱ ከቀረረበባቸው የሙስና ክስ ነጻ በመሆናቸው መፈታታቸው ተገልጿል። ይሁን እንጅ ከሁለት አመት በፊት በግብጽ ከተካሄደው አብዮት ጋር በተያያዘ አሁንም ሌሎች ክሶች ቀርበውባቸዋል። ደጋፊዎቸቻቸው ደስታቸውን ቢገልጹም፣ የሙስሊም ብራዘርሁድ ደጋፊዎች ደግሞ …

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢሳት የወረዳው ምንጮች እንደገለጹት ከተባረሩት ሰራተኞች መካከል 2 አቃቢ ህጎች፣ 2 ዳኞች ፣ 1 ፍርድ ቤት ሬስጅስትራርና አንድ ፖሊስ ይገኙበታል። 8 ሰዎች ደግሞ ከስራ ገበታቸው ላይ ለቅቀው ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተሰደዋል። የሚታሰሩ ሰዎች እየተበራከቱ መምጣቱን የሚናገሩት ምንጮች፣ 16 ሰዎች ሰሞኑን ተይዘው ታስረዋል። ካለፈው ወር ጀምሮ በቁጥጥር ስር …

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቡሬ ግንባር የሰፈረው የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተለያዩ ጊዜያት የአፋር ሴቶችን አስገድደው እንደሚደፍሩ ከስፍራው ደረሰን መረጃ አመለከተ። የሰራዊቱ አባላት ለቅኝት ወይም ለተለያዩ ስራዎች በሚወጡበት ጊዜ ግመል እና ፍየል የሚጠብቁ ሴቶች ሲያገኙ በሀይል ይድፍራሉ። ነሀሴ 3 ቀን 2005 ዓም አንዳባ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ሀሊማ አህመድ የሱፍ የተባለች እድሜዋ ከ45 …

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለሳምንታት መብራት የተቋረጠባቸውን አካባቢዎች በማስመልከት ዘገባውን ያጠናከረው ዘጋቢያችን እንደሚለው በየጊዜው እየሄደ ሳይታሰብ የሚመጣው የኤሌክትሪክ ሀይል፣ መንግስት ላለፉት 21 ዓመታት ገነባሁት የሚላቸው የሀይል ማመንጫዎች የት እንደደረሱ ጥያቄ የሚፈጥር ነው። ያለምንም መብራት መቋረጥ አንድ ሳምንት መድፈን ብርቅ ነው የሚለው ዘጋቢያችን፣ በተለይ የህክምና መስጫ ተቋማት ከመብራት …

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰንደቅ እንደዘገበው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አንዳንድ ሰራተኞች የኢህአዴግ የ2006 እቅድ መስሪያ ቤቱ ካለበት መደበኛ ስራ ውጪ የገዢውን ፓርቲ ድርጅታዊ ስራ በልዩ ሁኔታ እንዲያስፈፅም ማስገደዱን እየተቃወሙ ነው።አብዛኛዎቹ ሰራተኞች ሚኒስቴሩ በ2006 ዓ.ም ድርጅታዊ ስራን ትኩረት ሰጥቶ እንዲተገብር መድረጉ ሰራተኛው ያለፍላጎቱ የመንግስትንና የድርጅትን ስራ ቀይጦ እንዲሰራ የሚያስገድድ ነው ብለዋል። ለጋዜጣው …

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሲኤን ኤን፣ ቢቢሲ እና ሌሎችም ታዋቂ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን የተለያዩ የፖለቲካ ተንታኞችን በማነጋገር እንደዘገቡት የቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከእስር መፈታት ግብጽን በድጋሜ ከሁለት ሊከፍላት ይችላል። አንዳንድ ተንታኞች እንደሚሉት ሙባረክን ለማውረድ የታገሉ ወጣቶች ምናልባትም ራሳቸውን ከሙስሊም ብራዘርሁድ ጋር በማቀናጀት በስልጣን ላይ ባለው መንግስት ላይ ሊዘምቱ ይችላል። ይሁን …

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወጣቱ ዙከርበርግ እንደገለጸው ድርጅቱ ከኤሪክሰን፣ ኖክያ፣ ኦፔራ፣ ኳልኮም እና ሳምሰንግ ጋር በመተባበር በሞባይል መረጃ ላይ የሚጠየቀው ክፍያ እንዲቀነስ ያደርጋል። በማደግ ላይ ያሉ አገሮች የኢንተርኔት አግልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ ለማመቻቸት እንደሚሰራ ዙከርበርግ ተናግሯል። አንዳንድ ባለሙያዎች በበኩላቸው የአፍሪካውያን ችግር የኔትወርክ እና የሀይል አቅርቦት ችግር መሆኑን በመጥቀስ በዚህ በኩል ቅድሚያ …

  ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  በዓሉን አስመልክቶም ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ 21 ጊዜ መድፍ ተተኩሶአል፡፡ የአቶ መለስ ሙት ዓመት ጉለሌ በሚገኘው የዕጽዋት ማዕከል የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣የጎረቤት አገር መሪዎች፣ዲፕሎማቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብርዋል፡፡ በተለይ የመንግስት ሠራተኞች በግዳጅ   በመስቀል አደባባይ የሻማ ማብራት ስነስርዓት እንዲያካሂዱ መታዘዛቸው ታውቋል፡፡ ይህን ተከትሎም …

ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራር የሆነቸው ወ/ት አዲያ አህመድ ከሀምሌ 22 ቀን 2005 ዓም ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ  ስቃይ እስር ቤት ውስጥ ከደረሰባት በሁዋላ በዛሬው እለት በዋስ ተፈታለች። ወ/ት ሐዲያ እንዳለችው መርማሪ ፖሊሶቹ በቁጥጥር ስር ያዋሉዋት አንድነት ፓርቲ ሀምሌ 28 በሶዶ ከተማ ሊያደርገው የነበረውን ህዝባዊ ስብሰባ በተመለከተ …

ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው የቁጫ ሕዝብ ጥያቄ ሕጋዊ ምላሽ እንዲያገኝ እንጠይቃለን” በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ ፓርቲያችን አንድነት ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆኑ ከሚታገልላቸውና ገዥው ፓርቲ ከወረቀት አልፎ ያልተገበራቸው ሀገራዊ ቁምነገሮች ውስጥ ዜጎች ሳይሸማቀቁ በነፃነት ሃሳባቸውንና አመለካከታቸውን የመግለፅ፣ በነጻነት የመደራጀት፣ በገዛ ሀገራቸው በነጻነት የመንቀሳቀስ፣ በፈለጉበት አከባቢ የመኖር፣  የመደገፍ፣ የመቃወም እና  ስለመብታቸው …

ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  የኢሳት ወኪል ከስፍራው ባደረሰን መረጃ  አስከሬኑ ዛሬ ንጋት ላይ ተኝቶ ሲታከምበት ከነበረው ከናይሮቢ -ወደ አዲስ አበባ ገብቷል። እዮብ ከሳምንት በፊት ልጁን በብሽክሊሊት ትምህርት ቤት አድርሶ ከተመለሰ በሁዋላ ቤቱ መግቢያ በር ላይ ሲደርስ ድንገት ሰውነቱ አልታዘዝ ብሎት መዝለፍለፉን የገለጸችው ባለቤቱ ቲና፤ከዚያ እንደምንም የበሩን ደወል ተጭኖ መጥሪያ ካሰማ በሁዋላ …

  ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሙት ዓመት በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ጉለሌ ዕጽዋት ማዕከል በልዩ ልዩ ፕሮግራም ታስቦ እንደሚውል ለማወቅ የታቸለ ሲሆን፣ በዛሬው እለት ደግሞ  የተለያዩ የመንግስት ሰራተኞች ምሽትና ነገ  ሻማ በማብራት እንዲዘክሩት ታዘዋል። አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞች  ኢቲቪ አቶ መለስ ዜናዊ ከተናገራቸው ንግግሮች መካከል እያለ ሲያቀርብ መሰንበቱ …

ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  በወረዳው የተነሳውን ከማንነት ጋር የተያያዘ ጥያቄ ለማፈን መንግስት የጀመረውን ዘመቻ በማጧጧፍ ለውጭ አገር ሚዲያ መረጃ ይሰጣሉ የተባሉትን የቁጫን ህዝብ በመወከል ሲከራከሩ የነበሩት መቶ አለቃ ማሴቢ ማዳልቾ፣ ባለፈው ቀድሜ ተይዘው ዛሬ ወደ አርባምንጭ ተልከዋል። በአጠቃላይ እየታደኑ ካሉት መካከል 12 አንጋፋና ታዋቂ ሰዎች ሲታሰሩ፣ 9ኙ የገቡበት  አልታወቀም። በወረዳው የተነሳውን …

ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  ስምምነቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሞባይል ስርጭት ተጠቃሚ ወደ 50 ሚሊዮን ለማሳደግ የተደረገ ነው ተብሎአል። መንግስት ለዘርፉ ከመደበው 1 ቢሊዮን 600 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ ከፊሉን ለሌላው የቻይና ኩባንያ ሀዋይ መስጠቱ ታውቋል። ሁለቱም የቻይና ኩባንያዎች የመንግስትን የስልክና የሌሎች የመገናኛ መንገዶች ጠለፋ አቅም እንደሚያዳብሩለት ኢሳት ምንጮችን በመግለጽ መዘገቡ ይታወሳል። የኢህአዴግ …

ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  “በሳምንት አንድ ቀን ውሃ ማግኘት ብርቅ የሆነባቸው ሰፈሮች፣ በውሃ እጦት አካባቢያቸውን በመጥፎ ጠረን የሚበክሉ የኮንዶሚኒየም መኖሪያዎች፣ ለተደጋጋሚ አቤቱታ ምላሽ ሳያገኙ በርካታ ወራት እየተቆጠሩ የሚማረሩ ነዋሪዎች የአዲስ አበባ የዘመኑ ገጽታ ሆነዋል” ሲል አዲስ አድማስ ዘገበ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ” በቂ ውሃ ስለሌለ በራሽን ለማከፋፈል እየሞከረ” መሆኑን ገልጿል። ባለስልጣኑ …

ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  ታዋቂው ድምጻዊ እዮብ መኮንን በብስክሌት ላይ ሆኖ ሲጓዝ በመውደቁ ሆስፒታል ከገባ በሁዋላ በህክምና ሲረዳ ቆይቷል። አርቲስት እዮብ በባልደረቦቹ እርዳታ  ወደ ኬንያ በመሄድ ለአጭር ቀናት በህክምና ሲረዳ ቆይቷል። ኢሳት በአርቲስት እዮብ ሞት የተሰማውን ሀዘን ለመግለጽ ይወዳል።

  ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

ነሃሴ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  መንግስት ትናንት ሼህ ኑሩን ማን ገደላቸው በሚል ርእስ በኢቲቪ በለቀቀው ዘጋቢ ፊልም ላይ አንድነት ፓርቲ የሼህ ኑሩን ግድያ ደግፎ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲጠራ ማድረጉን የግንቦት7 ልሳን የሆነው ኢሳት ቴሌቪዥንም አሸባሪዎችን ” አይዞአችሁ በርቱ” እያለ ድጋፍ እንደሰጣቸው አንድ ግለሰብን በማናገር አቅርቧል በዘጋቢ ፊልሙ ላይ ሶስት ተጠርጣሪ ገዳዮች ቀርበው የሚናገሩ ሲሆን፣ …

ነሃሴ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከደጋፊዎቹ የመረጃ ለውውጥ ለመረዳት እንደተቻለው ኮንግረስ ማን ክሪስ ስሚዝ በቅርቡ በኢትዮጵያ ዙሪያ የግንቦት 7 መሪ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋን፣ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሀላፊ ሚ/ር ያማማቶ እና ሌሎችንም ታዋቂ ሰዎች በመጋበዝ በኢትዮጵያ ዙሪያ የተለያዩ ሀሳቦችን ማሰባሰባቸው ይታወቃል። ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችን እንድታከብርና …

ነሃሴ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ፈቃዱን የቀማው ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ሲንቀሳቀስ ተገኝቷል በሚል ነው። ከታላቁ ሩጫ በተጨማሪ  እስላማዊ የምርምርና የባህል ማዕከል ፣ ጎህ ቻይልድ ዩዝ ውመንስ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ፣ዋን ዩሮ ኢትዮጵያ ፣ ብራይት አፍሪካ ኢንተግሬትድ ዴቨሎፕመንት አሶሲየሽን እና ፓድ ኢትዮጵያ ሊትሬሲ ኢዱኬሽን ኤንድ ቮኬሽናል ሴንተር ናቸው። የድርጅቶቹን ሃብትና ንብረት በስማቸው በማዞር ሲጠቀሙ ፥ …

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ በአዲስ አበባ ወረዳ ሶስት አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ድላችን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመንግስት ተወካዮች ‹በሀይማኖት መቻቻል› ዙሪያ የተጠራ የውይይት መድረክ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠመው ተሰማ፡፡ በስብሰባው ላይ የታደሙት የእስልምናና የክርስትና እምነት ተከታዮች የመንግስት ተወካዮች እየተካሄደ ያለውን የሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ከአክራሪነትና አሸባሪነት ጋር ለማያያዝ ያደረጉትን ማብራሪያ አንድ አይነት አቋም …

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ የገቡ ታጣቂ ሀይሎች አራት የኬንያ ተጠባባቂ ፓሊሶችንና ስድስት አሳ አጥማጆችን በመግደላቸው በሁለቱ ድንበር አካባቢ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል፡፡ የኬንያና የኢትዮጵያ የፀጥታ እና ደህንነት ባለስልጣናት ጉዳዩን አስመልክቶ በመወያየት ላይ ሲሆኑ ጉዳዩ ያሳሰበው የኬንያ ተጠባባቂ ልዩ ሀይል ዛሬ ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ በገቡት ታጣቂ ሀይሎ ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን …

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አራቱ የደቡብ ክልል ውሃ ሀብት ልማት ቢሮ ከፍተኛ ሀላፊዎች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኙ የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል፡፡ የክልሉ ውሃ ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊው አቶ ውብሸት ፀጋዬ፣ የግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ሀላፊው አቶ ይገረሙ ፋሲቆ፣ የክፍያዎች ሀላፊው አቶ አቦሰጥ መብራቱ፣ መሐንዲሱ አቶ ሞገስ ዩሀንስ እና ኮንትራክተር የነበሩት …

  ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቀድሞ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ፣ አሁን ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ እየተባለ የሚጠራው ታዋቂው ድርጅት ባወጣው 127ኛ ልዩ መግለጫ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት አርሲ ዞን በመንገድ ሥራ ላይ በተሰማራው የጃይናው CGCOC (ሲጂሲኦሲ) ዲራ ማኛ መቻራ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ማህበር የሆነው የዳንዲ ደራርቱ አርሲ ሰራተኛ ማህበር አመራርና አባላት በአሰሪዎቻቸው …

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከኢትዩጵያ በህገ ወጥ የተሻገረውን 11 ቢሊዩን ዶላር ለማስመለስ እና የባለስልጣናትን የሀብት መጠን ይፋ ለማድረግ የተያዘው ቀጠሮ በመለስ ሞት ምክንያት ዳር ሳይደርስ መቅረቱን የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኪሚሺን ኪሚሺነር አቶ ዓሊ ሱሊማን ተናገሩ፡፡ አቶ አሊ በጠቅላይ ሚኒስተር መልስ ዜናዊ የስራ ትጋት እና አርቆ  አሳቢነት ምስክርነት ለመስጠት በ ኢቲቪ የፖሊስ …

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስትን ከአካባቢው ማግኘት የነበረበትን ከ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የገቢ ግብር መሰብሰብ እንዳልቻለ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተገኘ መረጃ ጠቆመ፡፡ የመንግስትን የገቢ ግብር መሰበሰብ ያልተቻለው የአዲስ አበባና የአገሪቱ የንግድ ማዕከል በሆነው በመርካቶ አካባቢ እስከ ቅርብ ጊዜ ሲከናወን የቆየው የግብይት ስርዓት በአብዛኛው ሕገወጥ በመሆኑ ነው ብሏል። ይህንን ችግርም ለመቅረፍ ባለሰልጣኑ …

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ ከነሃሴ 1/2005 እስከ መስከረም 25/2005 ዓ.ም ድረስ በዳኞች እረፍት ቀን ምክንያት ዝግ የሚሆን ሲሆን በነዚህ የእረፍት ጊዜያት በአዲስ አበባ ካሉት አስር ምድብ ችሎቶች አምስት ያህሉ በተረኝነት የሚሰሩ ሲሆን በድሬዳዋ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠቀሰው ጊዜም መደበኛ ስራውን የሚቀጥል መሆኑን አስታውቆአል፡፡ …

  ነሃሴ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የ33 ፓርቲዎች ትብብር ለኢሳት በላከው መግለጫ እንዳመለከተው መንግስት እየተከተለ ያለው የሀይል እርምጃ በዜጎች ህገመንግስታዊ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ላይ የተፈጸመ ህገወጥ አምባገነናዊ ድርጊት በመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ድርጊቱን ሊቃወምና ሊያወግዝ ይገባዋል። በአገር ቤትና በውጪ ያሉ የመገናኛ ብዙኃን፣ የነጻው ፕሬስ አባላት እና ማኅበራዊ ድረ-ገጾች በህዝበ ሙስሊሙና ክርስቲያኑ መካከል ያለመተማመን ለመፍጠር ከሚሰራጨው …

ነሃሴ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሜሪካ በሰጠችው የአጎዋ የገበያ ዕድል ቀነ ቀጠሮ ማራዘም ላይ በሰፊው ሲመክር የነበረው 12ኛው የአጎዋ ጉባዔ አፍሪካ ዕድሉ እንዲራዘም መፈለጓን የአሜሪካ የህግ አውጭ ምክርቤት ተወካዮች ለምክር ቤቱ እንዲያሳውቁላቸው በመጠየቅ ተጠናቋል፡፡ በ12ኛው የአጎዋ ፎረም የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ  ኢትዮጵያ ባለፉት 12 ዓመታት ወደ አሜሪካ የላከችው ምርት በየዓመቱ በአማካይ 80 በመቶ …

ነሃሴ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል ፖሊስ የጋራ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል እንዳስታወቀው፣ ሁለቱ ሲሊንደሮች የተገኙት በጽዳት ሰራተኞች ጥቆማ ነው። መንግስት ባእድ ነገሩን ማን እንዳስቀመጠው፣ በባእድ ነገሩ ውስጥ ምን እንዳለ ያስታወቀው ነገር የለም።

ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢድ አልፈጥርን በዓል ለማክበር ባለፈው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ ከተጓዙ በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል አስራ ሁለት የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት አስታወቁ፡፡ አራት የአሜሪካ፣ ሁለት የሲዊዲን፣ አንድ የአውስትራሊያና አምስት የተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያኑ ከትላንትናው እለት ጀምሮ በማዕከላዊ ማረሚያ ቤት …

ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአሜሪካ ፖሊሶች ከኢትዮጵያ ለምስክርነት መጥቶ የጠፋን ኢትዮጵያዊ ዱካ ለማግኘት ፍለጋ ላይ መሆናቸውን ሲአትል ኒውስ ዛሬ ዘገበ፡፡ ካሳይ ወልደ ፃድቅ የተባለው ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊያኖቹ ጥንዶች ከኢትዮጵያ በማደጎ ያመጧትን ልጅ ገድላችኋል ተብለው ለተከሰሱበት ወንጀል አቃቢ ህግ ለምስክርነት ማስረጃ ይሆን ዘንድ ብለው ነበር ከኢትዮጵያ ያመጡት፡፡ ካሳይ በፍርድ ሂደት ላይ ላለው ጉዳይ ባለፈው አርብ …

ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት አለም አቀፍ የምግብ ድርጅት በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በተለያዩ ግጭቶችና አደጋዎች ጉዳት ለደረሰባቸው 250 ሺህ ዜጎች አስቸኳይ እርዳታ መስጠት መጀመሩን ለኢሳት በላከው መግለጫ አስታወቀ፡፡ ድርጅቱ በኦሮሚያና አማራ ደርሶ ስለነበረው ግጭት ዝርዝር መረጃን ከመስጠት ቢቆጠብም 250ሺህ ለሆኑት ዜጎች ግን ጊዜያዊ የሆነ የምግብና የገንዘብ እርዳታ መስጠት ላይ እንደሆነ ገልጿል፡፡       …

  ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንዲት አራስን ጨምሮ ከ19 ያላነሱ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ለአንድ ወር ያክል በእስር ካሳለፉ በሁዋላ ዛሬ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ምንም መፍትሄ ሳይሰጥ ወደ እስር ቤት እንደሚለሱ ተደርጓል። የአካባቢው ሰዎች ፍትህ ለማግኘት በፍርድ ቤቱ አካባቢ ቢሰባሰቡም በፖሊስ ሀይል እንዲበተኑ ተድርጓል። አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ፍርድ ቤቱ በተከሳሾች ላይ በቂ ማስረጃ ያልቀረበለት …

ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ መለስ ዜናዊን አንደኛ የሙት አመት መታሰቢያ በማድረግ በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች የዝክረ መለስ ዝግጅቶች እየተካሄዱ ነው። በአዲስ አበባ 100 ሄክታር መሬት ስፋት ያለው ቦታ ከሀያት ሆስፒታል ፊት ለፊት ለመለስ ማእከል ግንባታ ተከልሏል። መስተዳድሩ ማእከሉን እንደሚያሰራ የአዲስ አበባ መስተዳድር አዲሱ ከንቲባ ድሪባ ኩማ የመሰረት ድንጋይ ባስቀመጡበት ወቅት ገልጸዋል። ግንባታው …

ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የኦሮሚኛ ፕሮግራም ባልደረባ የነበረው ባለቤቷ ጋዜጠኛ ዳበሳ ዋቅጅራ ከሦስት ዓመት እስር በሁዋላ ከአገር መውጣቱን ተከትሎ   በኦነግ አባልነት ክስ ተመስርቶባት  ታስራ የቆየችው  ጋዜጠኛ ሌሊሴ ወዳጆ ከ እስር ተፈታች። በ 1995 ዓመተ ምህረት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እየሠራ ሳለ  ድንገት ለእስር የተዳረገው ጋዜጠኛ ዻበሳ ዋቅጅራ አንዳችም ክስ ሳይመሰረትበት ለሦስት ዓመታት በእስር …

  ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የሕዝበ ሙስሊሙን ከ18 ወራት በላይ የዘለቀ እንቅስቃሴ በኃይል ለማፈን ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ እየወሰደ ያለው እርምጃ በሙስሊም አባላቱ ዘንድ ቅሬታ ማሳደሩ የግንባሩን ከፍተኛ አመራር ስጋት ውስጥ እንደጣለ የውስጥ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ አብዛኛዎቹ የግንባሩ ሙስሊም ከፍተኛ የአመራር አባላትን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ መካከለኛ፣ ዝቅተኛ አመራር አባላት መንግስት በሙስሊሙ ጥያቄ አፈታት …

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቁጫ ወረዳ ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በአካባቢው የተሰማራው የፌደራል ፖሊስ ከ50 በላይ ሰዎችን ማሰሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከታሰሩት መካከል 6ቱ ሴቶች ናቸው። ባለፈው ሐሙስ የኢህአዴግ ካድሬዎችና ፖሊሶች መደብደባቸውን የሚያመለክት ሪፖርት መቅረቡን ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ አካባቢው በብዛት በማቅናት ሰዎችን በማሰር ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ መረጃዎችን በማቀባባል የአካባቢውን ህዝብ ለአመጽ …

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመልካም አስተዳደር ኮማንድ ፖስት እየተባለ የሚጠራው መስሪያ ቤት በክልሉ ባሉ የአስተዳደር ቢሮዎች ባካሄደው ቅኝት የመልካም  አስተደዳር ችግር በክልሉ ተባብሶ መቀጠሉን ገልጿል፡፡ በተለይም በፍትህ ፤ በፖሊስ ፤ በማረሚያ ቤቶች ፤ በመሬት ፤ኢንቨስትመንት፤ መብራት እና ውሃ ደግሞ የችግሩ መለያ ቦታዎች መሆናቸውን ለክልሉ ካቢኔ የቀረበው ሪፖርት የቅሬታ ምንጭ መሆናቸውን ያወሳል፡፡ በክልሉም ከጊዜ …