ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ2003-2005 ዓ.ም መንግስት መንደር ማሰባሰብ በሚል በሚጠራው የሠፈራ ፕሮግራም በጋምቤላ በ12 ወረዳዎች 38 ሺ፣በቤንሻንጉል ጉሙዝ በ18 ወረዳዎች 77 ሺ ፣በአፋር በ8 ወረዳዎች 10ሺ፣ በሶማሌ በ21 ወረዳዎች 150 ሺ አባወራና እማወራዎች በድምሩ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሕዝብ እንዲሰፍር ተደርጓል፡፡ እስከ2007 የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ማጠናቀቂያ ድረስ 85ሺ ቤተሰብ ለማሰባሰብ …

ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአገሪቱ ጦር ሀይሎች ቃል አቀባይ እንደገለጹት አማጽያኑ የነዳጅ ማውጫ ጉድጓዶች የሚገኙባትን ቤንቲዩን ለቀው የወጡት እኩለ ቀን ላይ ነው። የደቡብ ሱዳን መንግስት አካባቢውን መቆጣጠሩን ቢገልጽም፣ በአማጽያኑ በኩል የተሰጠ ምንም አይነት ምላሽ የለም። መንግስት የነዳጅ ከተማዋን መቆጣጠሩ አማጽያን በመንግስት የቀረበውን ቅድመ ሁኔታ ለመቀበል ይገደዱ ይሆናል የሚል አስተያየቶች ቀርበዋል። በኢትዮጵያ …

በሕዋ ሣይንስ ዘርፍ የሚሠራው የሥነ ፈለክ ኅብረት አሥራ አራት አገሮችን የሚያስተባብር ፅሕፈት ቤት አዲስ አበባ ላይ ለመክፈት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ስምምነት ተፈራርሟል።

የፅሕፈት ቤቱ አዲስ አበባ ላይ መከፈት ኢትዮጵያን ይበልጥ ተጠቃሚ ሊያደርግ እንደሚችል የኢትዮጵያ የጠፈር ሣይንስ ማኅበረሰብ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተፈራ ዋልዋ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

በደቡብ ምዕራብ ወሎ፥ ቦረና ውስጥ ካሁን ቀደም የማይታወቁ ጥንታዊ የድንጋይ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናትን ማግኘታቸውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች አስታወቁ።

አብያተ ክርስቲያናቱ ለአደጋ የተጋለጡ መሆናቸውንም ባለሞያዎቹ አክለው አስረድተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የመለስካቸው አምሃ ዘገባ ያዳምጡ፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በከፋ ዞን፣ ኣርሶ ኣደሮች ያለፍላጎታችን ማዳበሪያ እንድንገዛ እየተገደድን ነው ኣሉ።

ማዳበሪያ ኣንቀበልም ያሉ በርካታ ኣርሶ ኣደሮች ደግሞ ከሚደርስባቸው እስራትና ወከባ በመሸሽ በየጥሻው እየተንከራተቱ ነው ተብሏል።

።ጄቶዲያ ንጃሚና ቻድ በተደረገዉ የማዕከላዊ አፍሪቃ የምጣኔ ሐብት ማሕበረሰብ (ECCAS) ጉባኤ ላይ ሥልጣን መልቀቃቸዉን ሲያዉጁ፥ የአዉሮጳ ሕብረት ደግሞ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት ለማዝመት ማሰቡ ከብራስልስ ተሰምቷል

የሰሜን ጎንደር የማረሚያ ቤት ሀላፊ ኮማንደር መተከል አያልሰዉ እርምጃተወሰደበት::
አርምጃዉ የተወሰደዉ ትናት ማታ ሰባት ሰአት ሲሆን በተደጋጋሚ ከግፍ ስራዉ እንዲቆጠብ መልክት ቢደረሰዉ አሻፈረኝ በማለቱ ተገሎአል :: አወጋን

ኢትዮጵያን ለረጅም ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩትና ሰፊ ስልጣን የነበራቸው መለስ ዜናዊ በነሃሴ ወር በድንገት መሞት በሃገር ውስጥም ሆነ በኢትዮጵያ ዓለማቀፍ አጋሮች ዘንድ የሀገሪቱን ፖለቲካዊ ሽግግር የሚመለከቱ ጥያቄዎችንና አጠራጣሪ ሁኔታዎችን አስነስቶ ነበር።በኢትዮጵያ ያለው የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በተለይ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ እየከፋ ሄዷል።አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በመስከረም ወር ስልጣኑን የተረከቡ ቢሆንም መንግስት በርሳቸው አመራር ሰብአዊ መብቶችን የሚመለከቱ ለውጦች ያደርግ ወይስ አያደርግ እንደሆነ ገና የሚታይ ነው።

እ.ኤ.አ በ2013ም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት መሰረታዊ የሆኑትን ሃሳብን በነጻ የመግለጽ፣ የመደራጀት እና የመሰብሰብ መብቶች በጥብቅ መገደባቸውን ቀጥለዋል።ለኣሻሚ ትርጉሞች በተጋለጠውና በ2002 ዓ.ም በወጣው የሀገሪቱ የጸረ ሽብርተኝነት ሕግ 30 ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት ተከሰው ተፈርዶባቸዋል።በዋና ከተማዪቱ አዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል የእስልምና እምነት ተከታዮች ላካሄዷቸው የተቃውሞ ሰልፎች የጸጥታ ሃይሎች የሰጡት ምላሽ የዘፈቀደ አፈሳ፣ እስር እና ድብደባ ነበር።

የኢትዮጵያ መንግስት በአምስት ክልሎች የሚኖሩ የገጠር ነዋሪዎችን የተሻለ የመሰረታዊ ግልጋሎቶች አቅርቦት ሊያገኙ ወደሚችሉባቸው አካባቢዎች ለመውሰድ በሚል ምክንያት 1.5 ሚሊዮን የገጠር ነዋሪዎችን መልሶ ለማስፈር የሚያካሂደውን የሰፈራ ፕሮግራም ቀጥሎበታል።በጋምቤላ ክልል የሚገኙ በርካታ ነዋሪዎች ከፍላጎታቸው ውጭ በሃይል እንዲፈናቀሉ በመደረጋቸው ለከፍተኛ ችግሮች ተጋልጠዋል። ከዚህ በተጨማሪም መንግስት ለሚያካሂደው ሰፊ የስኳር ልማት መሬት ለማስለቀቅ ሲባል በኢትዮጵያ የታችኛው ኦሞ ሸለቆ ነዋሪ የሆኑትን አርብቶ አደር ማህበረሰቦች ከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ እያደረገ ነው።

ሃሳብን በነጻ የመግለጽ፣የመደራጀት እና የመሰብሰብ መብቶች

መንግስታዊ ያልሆኑ ደርጅቶችን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር የበጎ አድራጎት ደርጅቶች እና ማህበራት አዋጅ እንዲሁም የጸረ ሽብርተኝነት ሕግ በ2002 ዓ.ም ከታወጁ ወዲህ በኢትዮጵያ ሃሳብን በነጻ የመግለጽ፣የመሰብሰብ እና የመደራጀት መብቶች ከፍተኛ ገደብ ተጥሎባቸዋል። እነዚህ ሁለት ሕጎች መንግስት በሲቪል ማህበረሰብ መሪዎች፣በጋዜጠኞች እና በሌሎችም የመንግስትን ፖሊሲ በሚተቹና መንግስት እንዲነሱ በማይፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ሃሳባቸውን በሚገልጹ ሰዎች ላይ ካካሄደው ሰፊ እና የማያቋርጥ ማዋከብ፣ዛቻ እና ማስፈራራት ጋር ተዳምሮ ያስከተሉት ውጤት የከፋ ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ የጎላ እንቅስቃሴ ያደርጉ የነበሩ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች እንቅስቃሴዎቻቸውን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንሱ ወይም ሰብአዊ መብቶችን የሚመለከቱ ጉዳዮችን ከስራ ዝርዝራቸው ውስጥ እንዲያወጡ የተገደዱ ሲሆን ቁጥራቸው ያልታወቀ ድርጅቶችም ጭራሹኑ ተዘግተዋል። በደረሰባቸው ማስፈራሪያ ምክንያት ሰፊ ልምድና መልካም ስም የነበራቸው ብዙ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ሃገሪቱን ለቀው ሄደዋል። አሁን ሰፍኖ የሚገኘው ሁኔታ ለነጻ ፕሬስ እንቅስቃሴም እንዲሁ የተመቸ አይደለም።ባለፉት አስር ዓመታት በደረሰባቸው ዛቻ እና ማስፈራራት ሳቢያ ሃገራቸውን ለመልቀቅ በተገደዱ ጋዜጠኞች ቁጥር በዓለም ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ ናት። የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች የሆነው ድርጅት ሲፒጄ እንደሚገልጸው ቢያንስ 79 ጋዜጠኞች ሃገራቸውን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል።

የጸረ ሽብርተኝነት አዋጁ፣ ተቃዋሚ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ ሰዎችን ዒላማ ለማድረግ፣ተቃውሞን ለማፈን እና ጋዜጠኞችን ዝም ለማሰኘት ስራ ላይ እየዋለ ነው። እ.ኤ.አ በ2012 ዓ.ም 30 የፖለቲካ መሪዎች፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት እንዲሁም ጋዜጠኞች በግልጽ ባልተብራሩ የሽብርተኝነት ወንጀሎች ተከሰው ተፈርዶባቸዋል።ከ2011 ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ 11 ጋዜጠኞች በዚሁ ሕግ ተከሰው ተፈርዶባቸዋል።

ጥር 17 ቀን 2004 ዓ.ም አሁን የተዘጋው አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ምክትል አዘጋጅ በነበረው ውብሸት ታዬ እና የጋዜጣው ዓምደኛ በነበረችው ርዕዮት ዓለሙ ላይ በአዲስ አበባ የሚገኝ ፍርድ ቤት የ 14 ዓመታት እስር ፈርዶባቸዋል።የርዕዮት ዓለሙ ፍርድ በኋላ በይግባኝ ወደ አምስት ዓመታት የተቀነሰ ሲሆን ከቀረቡባት ክሶች ውስጥም አብዛኞቹ ተሰርዘዋል።

ከፍተኛ ክብር ያለውን የፔን አሜሪካ ፍሪደም ቱ ራይት ሽልማት በሚያዝያ ወር 2004 ዓ.ም ያሸነፈው አንጋፋው ጋዜጠኛ እና ብሎገር እስክንድር ነጋ ሐምሌ 6 ቀን 2004 ዓ.ም ከሌሎች ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ጋር በቀረበበት ክስ የ 18 ዓመታት እስራት ተፈርዶበታል። በስደት ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች አብይ ተክለማርያም እና መስፍን ነጋሽም እስካሁን ድረስ ጋዜጠኞች ላይ ብቻ ተግባራዊ በተደረገው የጸረ ሽብርተኝነት ሕጉ አንቀጽ መሰረት ጥፋተኛ ተብለው እያንዳንዳቸው የ 8 ዓመታት እስራት ተፈርዶባቸዋል። በይፋ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀሰው ተቃዋሚ ፓርቲ አንድነት ለፍትሕ እና ለዲሞክራሲ አባል የሆነው አንዷለም አራጌ በስለላ፣ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን በመናድ እንዲሁም የሽብር ተግባር ለመፈጸም ምልመላ እና ስልጠና በማካሄድ ወንጀሎች ጥፋተኛ ተብሎ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል።

በመስከረም ወር 2004 ዓ.ም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የእስክንድር ነጋ እና በስደት ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ አበበ በለው እንዲሁም የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባሉ አንዷለም አራጌ ንብረቶች እንዲወረሱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ፍትሕ ጋዜጣ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚያካሂዱትን ተቃውሞ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩን የጤንነት ሁኔታ አስመልክቶ ያዘጋጃቸው ዘገባዎች የሃገሪቱን ብሔራዊ ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ናቸው በማለት መንግስት ሀምሌ 20 ቀን ጋዜጣው እንዳይሰራጭ አግዷል። ነሃሴ 18 ቀን 2004 ዓ.ም የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ በቁጥጥር ስር ውሎ ዋስትና ተከልክሏል። ተመስገን ነሃሴ 24 ቀን ከእስር የተለቀቀ ሲሆን ተጨማሪ ምርመራ እስኪካሄድ ድረስ ሁሉም ክሶች ተነስተውለት ነበር።

ሀምሌ 13 ቀን 2004 ዓ.ም ‘የሙስሊሞች ጉዳይ’ የተሰኘው ተወዳጅ የሙስሊሞች መጽሄት ዋና አዘጋጅ የሆነው የሱፍ ጌታቸው ቤት በፖሊሶች የተፈተሸ ሲሆን በዚያው ዕለት ምሽትም የሱፍ በቁጥጥር ስር ውሏል። መፅሄቱ ከዚያ በኋላ መታተም ያቆመ ሲሆን ይህ ዘገባ እስከሚዘጋጅበት ጊዜም የሱፍ በቁጥጥር ስር ይገኛል።

በሕገ ወጥነት ከተፈረጀው አማጺው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ጋር በምስራቃዊ ኢትዮጵያ ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር የዋሉት ማርቲን ሺብዬ እና ዮሃን ፒርሰን የተባሉ ሁለት ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ለሽብርተኛ ድርጅት ድጋፍ በመስጠት ወንጀል ታህሳስ 17 ቀን 2004 ዓ.ም የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶባቸዋል። በተጨማሪም በሕገ ወጥ መንገድ ወደሃገሪቱ በመግባት ጥፋተኞች ተብለዋል።ፍርድ ቤቱም በ 11 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ወስኗል። ሁለቱ ጋዜጠኞች አዲሱን ዓመት በማስመልክት በየዓመቱ ለእስረኞች በሚሰጠው ምህረት ከሌሎች 1950 በላይ ከሚሆኑ እስረኞች ጋር ምህረት ተደርጎላቸው ጳጉሜ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ከእስር ተለቀዋል።

መንግስት በሃገሪቱ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ጉዳዮች ምክር ቤት ውስጥ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ለታቃውሞ የወጡ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ለመበተን በሐምሌ ወር 2004 በተለያዩ ቀናት የፌደራል ፖሊስ ድብደባን ጨምሮ ከልክ ያለፈ ሃይል ተጠቅሟል።ሀምሌ 6 ቀን አዲስ አበባ ወደሚገኘው የአወሊያ መስጊድ በሃይል በመግባት ፖሊሶች መስኮቶችን የሰባበሩ ሲሆን በመስጊዱ ውስጥ አስለቃሽ ጭስ ተኩሰዋል። ሐምሌ 14ም በመስጊዱ ለተቃውሞ ተቀምጠው የነበሩ ሰዎችን ሃይል በመጠቀም እንዲበተኑ አድርገዋል። ከሐምሌ 12 እስከ 14 በነበሩት ቀናትም በርካታ ሰዎች የታፈሱ ሲሆን 17 ከፍተኛ የእምነቱ መሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ክስ ሳይመሰረትባቸው ከአንድ ሳምንት በላይ በእስር ቆይተዋል።ብዙዎቹ ታሳሪዎች በእስር ላይ እያሉ ማንገላታት እንደተፈጸመባቸው ገልጸዋል።

ተገዶ መፈናቀል

ሰፈራ በሚባለው ፕሮግራሙ የኢትዮጵያ መንግስት በአምስት ቆላማ ክልሎች ማለትም በጋምቤላ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣በአፋር፣ በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች እንዲሁም በሶማሌ ክልሎች የሚኖሩ 1.5 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎችን የተሻለ የመሰረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት ወደሚያገኙባቸው አካባቢዎች ለማዛወር በሚል ወደሌሎች ቦታዎች ወስዶ ለማስፈር እቅድ አለው።

በጋምቤላ እና በደቡብ ኦሞ ሸለቆ ከነዋሪዎች ጋር በቂ የቅድሚያ ምክክር ሳይደረግ እና የካሳ ክፍያ ሳይፈጸም አስገድዶ የማፈናቀል ተግባር እየተፈጸመ ነው።ሂዩማን ራይትስ ዎች እንዳረጋገጠው በተለይ በጋምቤላ ወደሌሎች አካባቢዎች አዛውሮ የማስፈሩ ሂደት የሚከናወነው ብዙ ጊዜ ነዋሪዎቹን ለም የሆኑ መሬቶቻቸውን በማስለቀቅ አነስ ያለ ለምነት ወዳላቸው መሬቶች በማስፈር ነው።ወደ አዳዲሶቹ መንደሮች እንዲሰፍሩ የሚላኩት ሰፋሪዎች አብዛኛውን ጊዜ መሬታቸውን መመንጠር እና ጎጆዎቻቸውን መስራት ያለባቸው ሲሆን ይህንንም በወታደሮች ተቆጣጣሪነት ያከናውናሉ።ቃል የተገቡላቸው አገልግሎቶች ማለትም ትምህርት ቤቶች፣ክሊኒኮች እና የውሃ ፓምፖች የተሟሉ አይደሉም።

በደቡብ ኦሞ ቁጥራቸው ወደ ሁለት መቶ ሺህ የሚደርስ ተወላጅ ሕዝቦች መንግስት ለሚያካሂደው የስኳር ልማት ቦታ ለማስለቀቅ ሲባል መሬታቸው ተወርሶ ወደሌሎች አካባቢዎች እንዲሰፍሩ እየተደረገ ነው። ነዋሪዎቹ ከመሬቶቻቸው ላይ በሃይል እነደሚነሱ፣የግጦሽ መሬቶቻቸው በጎርፍ እንዲጥለቀለቁ እንደሚደረግ፣ ማሳዎቻቸው እንደሚገለበጡ እንዲሁም ለህልውናቸው እና ለአኗኗር ዘይቤአቸው እጅግ አስፈላጊ የሆነውን የኦሞ ወንዝ ውሃ እንዳያገኙ እንደሚከለከሉ ተናግረዋል።

ሕገ ወጥ ግድያ፣ማሰቃየት እና በቁጥጥር ስር ባሉ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ ጥሰቶች

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በጋሸሞ ወረዳ ራቅዳ በተባለች መንደር ከነዋሪዎች ጋር የተፈጠረን ግጭት ተከትሎ ‘ልዩ ሃይል’ በሚል ስያሜ የሚታወቅ፣ በኢትዮጵያ መንግስት የሚደገፍ ታጣቂ ቡድን በቁጥጥሩ ስር የነበሩ 10 ሰዎችን እና ሌሎች 9 የመንደሩ ነዋሪዎችን የገደለው መጋቢት 7 እና 8 ቀን 2004 ዓ.ም ነበር።

በሚያዝያ ወር 2004 ዓ.ም ማንነታቸው ያልታወቀ መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች በጋምቤላ ክልል በሚገኝ እና ባለቤትነቱ የሳውዲ ስታር ኩባንያ በሆነ ሰፊ እርሻ ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል። ይህ የእርሻ ልማት በክልሉ የሰፈራ ሂደት በተካሄደበት ወቅት የከፋ የመብቶች ጥሰቶችና ማንገላታት ከተፈጸመባቸው አካባቢዎች በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ነው። ለዚህ ጥቃት ምላሽ ለመስጠት የኢትዮጵያ ወታደሮች ቤት ለቤት በመዞር ድርጊቱን ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎችን የፈለጉ ሲሆን የአካባቢውን ነዋሪዎችም ‘አማጺያኑ’ የሚገኙበትን ቦታ አጋልጡ በማለት ሲያስፈራሯቸው ነበር። ወታደሮቹ በርካታ ወጣት ወንዶችን በዘፈቀደ ከማሰራቸውም በላይ ስለ ጥቃቱ መረጃ ለማግኘት ባደረጉት ሙከራ ማሰቃየት፣አስገድዶ መድፈር እንዲሁም ሌሎች ጥሰቶችን በብዙ ነዋሪዎች ላይ ፈጽመዋል።

ሂዩማን ራይትስ ዎች በአዲስ አበባ ማዕከላዊ በመባል በሚታወቀው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጣቢያ እና በክልሎች በሚገኙ የእስር ቦታዎች እንደዚሁም በሶማሌ፣ በኦሮሚያ እና በጋምቤላ ክልሎች በሚገኙ ወታደራዊ ካምፖች ውስጥ የሚፈጸሙ የማሰቃየት ድርጊቶችን የሚመለከቱ መረጃዎችን ማሰባሰቡን ቀጥሏል። በእነዚህ የእስር ጣቢያዎች ከፖለቲካ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች የተያዙ ታሳሪዎች ከጠበቆቻቸው ጋር የሚገናኙበት እድል በጣም የመነመነ ሲሆን በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ከፍርድ ሂደት በፊት እና በፍርድ ሂደት ወቅት ሊከበሩላቸው የሚገቡ መብቶችን ለማክበር ያለው ፍላጎትም በጣም አናሳ ነው። ይህም ታሳሪዎቹን ለከፉ ጥሰቶች ያጋልጣቸዋል።

የስደተኛ ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞች አያያዝ

በሊባኖስ የቤት ሰራተኛ የነበረቸው ኢትዮጵያዊት ዓለም ደቻሳ ደሲሳ ድብደባ ሲፈጸምባት የሚያሳየው ቪዲዮ ከተሰራጨና ይህነኑ ተከትሎም ዓለም መጋቢት 5 ቀን 2004 ዓ.ም ሕይቷን ካጠፋች በኋላ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩት በመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት በቤት ሰራተኝነት የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ሴቶች የሚደርስባቸው መከራ የተጠናከረ ትኩረት አግኝቶ ነበር። ብዙ በስደት የሚሰሩ የቤት ሰራተኞች ወደ ውጭ ሃገራት ሄደው ከመቀጠራቸው በፊት ከባድ የገንዘብ ዕዳ ውስጥ ይገባሉ፤ እንዲሁም ከቅጥር ሂደቱ ጋር የተያያዙ ሌሎች ማንገላታቶች ይፈጸሙባቸዋል።ውጭ ሀገር ሄደው ስራ ከጀመሩም በኋላ ለረጅም ሰዓታት ከመስራት በተጨማሪ ባርነት በሚመስሉ የስራ ሁኔታዎች ውስጥ እንዲሰሩ ይደረጋሉ፣ እንዲሁም ሌሎች መጠነ ሰፊ ጥቃቶች ይደርሱባቸዋል።(የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ሳኡዲ አረቢያ እና ሊባኖስን የሚመለከቱትን ምዕራፎች ይመልከቱ)።

ዋና ዋና ዓለማቀፍ አጋሮች

በመለስ ዜናዊ አመራር ኢትዮጵያ በአካባቢ ጉዳዮች ላይ የጎላ ሚና ትጫወት ነበር።ወደ አወዛጋቢው የሱዳን አቢዬ ክልል በተባበሩት መንግስታት ስር የሰላም አስከባሪ ሃይሎችን አሰማርታለች፣በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን መካከል የነበረውን አለመግባባት ሸምግላለች እንዲሁም አል ሸባብን ለመውጋት የተደረገውን ዓለማቀፍ ጥረት ለማገዝ ሰራዊቷን ወደሶማሊያ ልካለች። እ.ኤ.አ ከ 1998-2000 ድረስ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተካሄደውን ከፍተኛ ዋጋ ያስከፈለ ጦርነት ተከትሎ ኢትዮጵያ ከጎረቤቷ ኤርትራ ጋር ያላት ግንኙነት መልካም አይደለም። ኤርትራ ለግጭቱ መነሻ የነበሩ ቦታዎች ለኤርትራ እንደሚገቡ የወሰነውን የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ የተቀበለች ሲሆን ኢትዮጵያ ግን ውሳኔውን አልተቀበለችም።

ኢትዮጵያ ለምዕራብ መንግስታት ጠቃሚ ስትራተጂያዊና የደህንነት አጋር ስትሆን ከእነዚህ መንግስታት በአፍሪካ ከፍተኛውን የልማት እርዳታ የምታገኝ ሀገርም ናት።በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በዓመት ወደ 3.5 ሚሊዮን የሚደርስ የአሜሪካን ዶላር በረጅም ጊዜ የልማት እርዳታ መልክ ታገኛለች።የለጋሽ ሃገራት ፖሊሲዎች በሀገሪቱ እየከፋ ከሄደው የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ጋር በተያያዘ ብዙም የተለወጡ አይመስሉም።

እ.ኤ.አ በመስከረም ወር 2012 የዓለም ባንክ ራሱ እና ሌሎችም የልማት ተቋማት ዘለቄታ ላለው ልማት እጅግ አስፈላጊ ናቸው የሚሏቸውን የሰብአዊ መብቶች እና የመልካም አስተዳደር መርሆች ብዙም ከግምት ውስጥ ያላስገባ አዲስ ብሔራዊ የጋራ ሰትራተጂ ባንኩ አጽድቋል።ባንኩ በተጨማሪም ሦስተኛውን ዙር የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጥበቃ ፕሮግራም (ፒቢኤስ 3)ያለፈቃድ የሚደረግ ሰፈራን የሚከለክሉ እና ለተወላጅ ሕዝቦች ጥበቃዎችን የሚያደርጉ ድንጋጌዎችን ሳያካትት አጽድቋል።

HRW
Image

በሦስት ምዕራፎች በተከፋፈለው የድጋፍ መግለጫ ስብሰባ መርሐ ግብር÷ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ካህናት፣ የአብነት መምህራንና ሰባክያነ ወንጌል በመጀመሪያው ምዕራፍ፤ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤያት ሊቃነ መናብርትና ምእመናን በሁለተኛው ምዕራፍ፣ ሰንበት ት/ቤቶች በሦስተኛው ምዕራፍ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋራ ተገናኝተው እንዲወያዩ ዕቅድ ተይዟል፡፡ ለዛሬው መርሐ ግብር መስተጓጎል ተጠያቂ የተደረጉት የፓትርያርኩ አቡነ ቀሲስ እና የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ሓላፊ እርስ በርሳቸው እየተወነጃጀሉ …

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

በኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣን ሳይኖረው ባለሙሉ ሥልጣን፣ እውቀት ሳይኖረው ባለሙሉ እውቀት የሆነ ሰው ስብሐት ነጋ ብቻ ነው፤ እንዲያውም ከዚያም አልፎ ራሱን የቻለ ሉዓላዊ ነጻነት ያለው ግለሰብ ነው ለማለት የሚቻል ይመስለኛል፤ በዚህ ግለሰብ ላይ የማደንቃቸው ሁለት ነገሮች ናቸው፤ በሉዓላዊነቱ የተጎናጸፈውን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ ይጠቀምበታል፤ ይቆጣኛል ወይም ይቀጣኛል ብሎ የሚፈራው የለም፤ ስብሐት ነጋ የሚፈራው ምንም ነገር የለም፤ ሁለተኛ በሉዓላዊነቱ ያለውን ሙሉ ነጻነት በሙሉ ልብ ይጠቀምበታል፤ ናስ በላይ ከበደ እንዳለው ‹‹የቅብጠት መዘላበድ›› ሊሆን ይችላል፤ ስብሐት ነጋ የተናገረው ነገር ትክክል ይሁን አይሁን ጉዳዩ አይደለም፤ ዋናው ነገር መናገሩ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የሕወሓት አትኩሮት ስልጣን በማስረዘም ላይ ነው እንጂ በዜጎች ደህንነት ላይ አይደለም ::
Minilik Salsawi
ዜጎች በየትኛውን የውጭም ይሁን የአገር ውስጥ በባለስልጣናት የሚደርስባቸው መከራና ግፍ መንግስት የለም ወይ ያሰኛል:: እኛ እየተናገርን ያለነው ስለ ፖለቲከ ተቃዋሚዎች ሳይሆን ስለዜጎች ነው:: ስለፖለቲካ ተቃዋሚዎች ራሳቸው እየደሰኮሩት ነው ዜጎች ግን የመኖር የመስራት የማምለክ መብታቸው ሊከበር ይገባል:: ህግ ሲከበር ስልጣን ይረዝማል:: ህግ ሲከበር ዜጎች ሰላም ያገኛሉ:: ኢኮኖሚው ቢዋዥቅ እንኳን ሰላም ካለ ብልሃቱ አይጠፋም::

ሕወሃት መራሹ ኢህኣዴግ ስልጣኑን ለማስረዘም የሚጠቀምበት ስልት የተበላበት እና ያረጀ መሆኑ እሙን ነው::ዜጎች በሃገራቸው መኖር ካልቻሉ ለመኖር ሲሉ የሚፈጥሩት ፍትጊያ ባለስልጣናቱን ከጨዋታ ውጪ አድርጎ በህዝብ እንዲበሉ ያደርጋቸዋል::ዜጎች በገዛ አገራቸው ዛሬም እየተፈናቀሉ ነው::በአለም ላይ ታይቶ የማይታወቅ የፌዴራሊዝም ከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲ በዚህ በሰለጠነ ዘመን ተቀባይነት የሌለው እና ለራስ ጦስ የሚሆን እንደሆነ ወያኔዎች ሊረዱት ይገባል:: እንደጫካ የተለመደው ማፊያዊ መሹለኩለክ የትም የማያደርስ አደጋ የሚያስከትል መሆኑን ሊታወቅ ይገባል::
ሕወሓት ስሟንም ሙዷንም ትቀይርልን::በቃ ነቅተናል!!! ከሕወሓት ውጭ ማንም ወንጀለኛ የለም::
ትላንት ዛሬም ነገም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በህገወጥ መንገድ ቢሞት ቢገደል ቢታነቅ ቢታፈን ቢታሰር እና ከነዚህ ነገሮች ጋር በተያያዘ ከሕወሃት ውጭ ማንም ይህን የሚፈጽም የለም :: ይህንን ደሞ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ አውቆታል:: በቃ ነቅተናል!! ከህወሃት ውጭ ማንም ወንጀለኛ የለም::

በአለማቀፍ ደረጃ ከአሸባሪ ድርጅቶች እኩል ስሟ ሰፍሮ የሚገኘው ሕወሓት በኢትዮጵያ እና በዜጎቿ ላይ በግልጽ እና በድብቅ የተለያዩ ማፊያዊ እርምጃዎችን እየወሰደች ነው::ሕወሓት በተለያዩ የደህንነት መዋቅሯ አማካኝነት ራሷ ከፈጠረቻቸው ከፍተኛ ባለስልጣኖች ጀምሮ እስከ ተራ ዜጎች ድረስ በስውር እጆቿ በልታቸዋለች:: በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ከተሞች በተለያየ ጊዜ ቦምቦችን በማፈንዳት በተቃዋሚዎች ላይ ሰበብ ለመፍጠር ሞክራለች:: በእነዚህ ፍንዳታዎች ያለቁትን ዜጎች አስቧቸው:: ……..ኦነግ ሻእቢያ አልሸባብ ቅንጅት አክራሪ …ምናምን ቢባል ማንም የሚያምን የለም ::አሁንም ያልተነቃ የሚመስላቸው እነዚህ ሰው በላዎች የጫካ ማፊያዊ ድርጊታቸውን እየፈጸሙ ይገኛሉ..በቃ ነቅተናል!!! ከሕወሓት ውጭ ማንም ወንጀለኛ የለም::

ስለዚህ በቃ ነቅተናል ልንል ይገባል:: ሁላችንም በያለንበት የሕወሓትን ስውር እጆች ልናጋልጥ ይገባል:: ሕወሓትን የምንመክረው ግን አመድ ከመሆንሽ በፊት ስምሽን እና ሙድሽን ቀይሪልን ነው::
በቃ ነቅተናል!!! ከሕወሓት ውጭ ማንም ወንጀለኛ የለም::


“አንጥረኛ” ቤተሰብና ታላላቅ ሥራዎቻቸው

Image

አያታችን የአፄ ምኒልክን፣ አባታችን የአፄ ኃይለስላሴን ዘውድ ሰርተዋል
ወንድሜን ሙያውን ጀርመን አገር ያስተማሩት ንጉሱ ናቸው
የአክሱምና ላሊበላ መስቀሎችን ዲዛይን አሻሽሎ የሰራው አባቴ ነው
ወላጆቻቸው የአንኮበር ተወላጆች ናቸው። አባታቸው ከአንኮበር ጀምሮ በአዲስ አበባ ቤተመንግሥትም የወርቅና ብር

ጌጣጌጦች ባለሙያ ነበሩ፡፡ ከታላቅ ወንድማቸው ጋር በመሆን የአባታቸውን ሙያ ከልጅነት ዕድሜያቸው ጀምሮ

የቀሰሙት አቶ ይሔይስ ደጀኔ፤ በጀርመን አገርም ተጨማሪ ዕውቀት ገብይተዋል፡፡ ደምበል ሕንፃ ላይ “ይሔይስ ደጀኔ

የወርቅና ብር ሠሪ” የሚል መደብር ያላቸው አቶ ይሔይስ፤ “አባታችን በሙያው የነበረውን ዕውቀት ዛሬ በ76ተኛ

ዓመቴም አልደረስኩበትም” ይላሉ፡፡ በወርቅና በብር ከሚሰሩ ጌጣ ጌጦች ጋር በተያያዘ የቤተሰባቸውን ታሪክና ተያያዥ

ጉዳዮችን አውግተውናል።
ከትውልድዎና አስተዳደግዎ ይጀምሩልኝ…
በአዲስ አበባ ከተማ ጐላ ሠፈር በ1930 ዓ.ም ነው የተወለድኩት፡፡ በልጅነቴ ያመኝ ስለነበር፤ ከጐንደር የመጡ መምሬ

ቅሩብ የሚባሉ ቄስ ተቀጥረውልኝ ቤት ውስጥ ነበር ትምህርቴን የተከታተልኩት፡፡ ሌሎችም የጐላ ሠፈር ልጆች እየመጡ

እንማርበት የነበረው ቤት የእናቴ ወንድም ነበር፡፡ የቤተመንግሥት ካባ ሰፊና ሙካሽ ጠላፊ ባለሙያ የነበሩት አጐቴ፤

አቶ አድማሱ ኃይለማርያም ይባላሉ፡፡ የቄስ ትምህርቴን ፊደል ከመቁጠር ጀምሬ፣ ዳዊት በመድገም፣ በወንጌል ንባብ

ካዳበርኩ በኋላ፤ በመርካቶው ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን እንድቀድስ ተጠይቄ ነበረ፡፡ እኔ ግን ዘመናዊ ትምህርት

የመማር ፍላጐት ስለነበረኝ፣ በ1944 ዓ.ም ኮከበ ጽባሕ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ትምህርት ቤት ገባሁ፡፡
የትምህርት ቤታችን ርዕሰ መምህር ካርል ማይክል የሚባሉ አሜሪካዊ ነበሩ፡፡ 12ተኛ ክፍልን ካጠናቀቅኩ በኋላ

ለተጨማሪ ትምህርት ወደ ጀርመን አገር እንድሄድ ነገሮችን ያመቻቸልኝ ታላቅ ወንድሜ አቶ ክበርዬ ደጀኔ ነበር፡፡
ይህንን ያደረገበት ምክንያት ደግሞ፤ ቤተሰባችን ለተሰማራበት የአንጥረኝነት ሙያ እኔ ከፍተኛ ፍላጐት እንዳለኝ

በማስተዋሉ ነው፡፡ ታላቅ ወንድሜም ጀርመን አገር ድረስ ሄዶ ሙያውን ተምሮ ስለነበር፣ እኔም ወደዚያ እንድሄድ

ያመቻቸልኝ፤ በጀርመን አገር የሚያውቃቸውን ሰዎች በማነጋገር ነበር፡፡
እስቲ ወደኋላ መለስ ብለው የእናንተ ቤተሰብ ከአንጥረኝነት ሙያ ጋር በተያያዘ ያለው ታሪክ ምን እንደሚመስል

ይንገሩኝ…
የአባቴ አባት አቶ በላይነህ ዓለምነህ እና የእናቴ አባት አቶ ደገፉ ጋሼ፤ በአንኮበር ቤተመንግሥት በአንጥረኝነት ሙያ

ይሰሩ ነበር፡፡ በዚያ ወቅት መስቀልና የቤተክህነት ዕቃዎችን ሠርተዋል፡፡ አፄ ምኒልክ ሲነግሱ የተጠቀሙበትን ዘውድ

አርመናዊው ዲክራን አቢያን ሲሰራ፣ አያቴና ወንድሙ በሥራው ላይ ተሳትፈዋል፡፡ አፄ ኃይለሥላሴ ሲነግሱ

የተገለገሉበትን ዘውድ በመስራትም አባቴ ሙያዊ ዕውቀቱን አዋጥቷል፡፡ ከዚያም በኋላ ብዙ ነገር ሠርቷል፡፡
ጥንታዊውን የአክሱምና የላሊበላ መስቀሎችን ዲዛይን አሻሽሎ የሰራው አባቴ ነው፡፡ አሁን በአራት ኪሎ ቤተመንግሥት

አጥር ላይ የሚታየውና የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ሥም ምህፃረ ቃል በድርብ ዲዛይን የቀረፀውም እሱ ነው፡፡ የጃንሆይ

የክብር አልባሳት ቁልፎችንም ሠርቷል፡፡ የአፄ ኃይለሥላሴ የልብስ ቁልፍ በመጀመሪያ ተሰርቶ የመጣው ከእንግሊዝ

ነበር፡፡ ንጉሡ ከለንደን የመጣውን ዲዛይን ስላልወደዱት አባቴ አሻሽሎ እንዲሰራላቸው ጠይቀውት፣ የልብስ

ቁልፎቻቸውን በ21 ካራት ወርቅ ሠርቶላቸዋል፡፡
የንጉሡ የልብስ ቁልፎች ላይ ምን ዲዛይን ነበረ?
የአፄ ኃይለሥላሴ ልብስ የወርቅ ቁልፎች በተለያየ ዲዛይን ነበር የተሰራው፡፡ መሐሉ ላይ የቅዱስ ጊዮርጊስ አርማ ያለበት

አለ፡፡ ግራና ቀኝ የተጠላለፉ ሻምላዎችን አርማ የያዙም ቁልፎች ነበሩ፡፡ በክብ ቅርጽ የተሰሩት የልብስ ቁልፎች

በዙሪያቸው የዘንባባ ዲዛይን የተሰራላቸው ሲሆን ጫፋቸው ላይ ደግሞ የዘውድ አርማ አላቸው፡፡
አባትዎ በየትኛው ቤተመንግሥት ውስጥ ነበር እነዚህን ሥራዎች የሚሠሩት?
ከቤተመንግሥት ቅጥር ሠራተኞች አንዱ ሆኖ በአንጥረኝነት ሙያ ያገለገለው፤ በጃንሆይ ልዩ ግምጃ ቤት ውስጥ ነበር፡፡

ግምጃ ቤቱ በገንዘብ ሚኒስቴር ስር የሚተዳደር ሲሆን፤ ቦታውም አሁን 6 ኪሎ ዩኒቨርስቲ በሆነው ገነተ ልዑል

ቤተመንግሥት ውስጥ፤ ከማርቆስ ቤተክርስቲያን በስተጀርባ ነበር። ከአባቴ ጋር የሚሰሩ በጅሮንድ ማንደፍሮ የሚባሉ

ሌላ ኢትዮጵያዊም ነበሩ፡፡
በሙያው ላይ የተሰማሩ የውጭ አገር ሰዎችስ አልነበሩም?
የአንጥረኝነት ሙያ በአገራችን በሁለት መንገድ ተስፋፍቶ ነው ለዛሬ የደረሰው፡፡ አንደኛው፤ ከጥንት አክሱማዊያን አንስቶ

ትውልዶች እየተቀባበሉ እዚህ ያደረሱት ሲሆን፤ ሁለተኛው ከአፄ ምኒልክ ጊዜ አንስቶ ልዩ ልዩ ዕውቀት ያላቸው የተለያዩ

አገራት ባለሙያዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ሲደረግ ከገቡት መሐል አርመኖችም ስለነበሩበት፣ እነሱ በአገራችን

የአንጥረኝነት ሙያ እንዲያድግና እንዲስፋፋ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡
አባታችን በንጉሠ ነገሥቱ ግምጃ ቤት በሚሰሩበት ዘመን፣ ፒያሳ ላይ የወርቅና ብር መስሪያና መሸጫ ያለው ሳቫጂያን

የሚባል አርመናዊ ነበር፡፡ በነገራችን ላይ የንጉሡ ግምጃ ቤት “ብር መኪና ቤት”ም ተብሎ ይጠራ ነበር። አባታችን

እንደነገረን፣ በ”ብር መኪና ቤት” ገንዘብ የማተም ሥራ፣ የወርቅና ብር ሥራ ብቻ ሳይሆን ከረሜላ ሁሉ ይመረትበት

ነበር፡፡
አባትዎ የሰሯቸው ሌሎች ሥራዎች ካሉ ቢነግሩኝ…
ለአፄ ኃይለሥላሴና ለቤተመንግሥት ብዙ ነገር ሠርቷል፡፡ የጃንሆይን የልብስ ቁልፎች ከአባቴ ውጭ ማንም

አልሰማራም፡፡ የሲጃራ መያዣ ሣጥን፣ የሴት ቦርሳ ጌጦች፣ የተለያዩ አገራት እንግዶች ሲመጡ፤ ጃንሆይ በሽልማትነት

የሚሰጧቸው ኒሻንና ሜዳሊያዎች፣ የወታደራዊ የማዕረግ ምልክቶች፣ የሸሚዝ እጅጌ ማስያዣ ቁልፎች (ከፊሊንግ)፣ የአበባ

ማስቀመጫዎችና የተለያዩ የሳሎን ጌጣጌጦች፤ በወርቅ፣ በብር፣ በዝሆን ጥርስና በአልማዝ ጭምር ሠርቷል፡፡
አርመናዊው ሳቫጂያንም ለቤተ መንግሥት ብዙ ነገሮችን ሠርቷል፡፡ ማህተም ይቀርጽ ነበር። ለወታደራዊ አገልግሎት

የሚውሉ ጌጣ ጌጦች፣ የማዕረግ ምልክቶችና የልብስ ቁልፎችን ይሰራ ነበር፡፡ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጥይት ፋብሪካም

በተመሳሳይ መልኩ በብዙ ሥራዎች ላይ ተሳትፏል፡፡
ከአፄ ኃይለሥላሴ ውጭ የልብስ ቁልፎችን በወርቅ ያሰራ ሌላ ማን አለ?
አንደኛ ሥራው በሚስጢር ነው የሚሰራው፡፡ ሁለተኛ የዲዛይን ሥራው የዳበረ ዕውቀትና ልምድ ስለሚጠይቅ፤ አሰራሩም

ጊዜ ስለሚወስድ ብዙ ሰው የልብስ ቁልፎችን ከወርቅ ሊያሰራ አይችልም። የማሰሪያ ዋጋውም ቢሆን ውድ ነው፡፡ ልዑል

ራስ አስራተ ካሳ ግን ከወርቅ የተሰራ የልብስ ቁልፎች ነበሯቸው፡፡
ታላቅ ወንድምዎ የወርቅና ብር ሥራን ለመማር ወደ ጀርመን መሄዳቸውን ገልፀውልኛል፡፡ እስቲ ስለ ወንድምዎ

ይንገሩኝ…
አቶ ክብርዬ ደጀኔ ታላቅ ወንድሜ ነው፡፡ አያታችን በአፄ ምኒልክ ዘውድ፣ አባታችን በአፄ ኃይለሥላሴ ዘውድ ሥራ ላይ

እንደመሳተፋቸው ሁሉ፤ አቶ ክብርዬም የሥላሴ ካቴድራልና የአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያናትን መንበር በብርና በወርቅ

በመሥራት ባለታሪክ ነው፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ አባታችን ወደሚሰራበት ቤተመንግሥት እየሄደ በመለማመድ ነበር ሙያውን

ያዳበረው፡፡ በየዓመቱ ለገና በዓል የአበባ ማስቀመጫ ከብር እየሰራ ለንጉሠ ነገሥቱ ያበረክትላቸው ነበር፡፡ ይህንን

ፍላጎቱን ያዩት አፄ ኃይለሥላሴ፤ ሙሉ ወጪውን ችለው ጀርመን አገር ሄዶ ሙያውን እንዲማር ረዱት፡፡ ከጀርመን

ሲመለስ ፒያሳ ከማህሙድ ሙዚቃ ቤት በታች፣ ሱቅ ከፍቶ በወርቅና ብር ሥራ ላይ ተሰማራ፡፡
እርስዎስ ለትምህርት ጀርመን የሄዱት እንዴት ነበር?
ታላቅ ወንድሜ ጀርመን በሄደበት ወቅት፣ ትምህርት በማይኖረኝ ጊዜ፤ ቤተመንግሥት እየሄድኩ አባታችንን በሥራ እረዳ

ነበር፡፡ ወንድሜ የፒያሳውን ሱቅ በ1954 ዓ.ም. ከከፈተም በኋላ በተመሳሳይ መልኩ በሥራው ላይ እሳተፍ ስለነበር፣

ለሙያው ያለኝን ፍቅርና ችሎታ ያየው ወንድሜ፤ ጀርመን ሄጄ እንድማር ሁኔታዎችን አመቻችቶ ሲልከኝ፣ የትራንስፖርት

ወጪዬን የሸፈኑልኝ ንጉሥ ኃይለሥላሴ ነበሩ፡፡
አባታችሁ በሙያቸው እያገለገሉ በቤተመንግሥት ሠራተኛነት የቆዩት ለምን ያህል ጊዜ ነው?
ጃንሆይ የጡረታ ዕድሜውን እያራዘሙለት ብዙ ቆይቷል፡፡ ንጉሡ ወርደው ደርግ የመንግሥት ስልጣን ሲይዝ፤ ኮሎኔል

መንግሥቱ ኃይለማርያም “እናውቃለን፤ ብዙ አገልግለዋል፤ ምንም የተሻለ ነገር ስላላገኙ ባለዎት ደሞዝ ጡረታ

እንዲወጡ ፈቅጃለሁ” ብሎት የቤተ መንግሥት ሠራተኛነት ሲያበቃ፤ ፒያሳ ወንድሜ በከፈተው ሱቅ ለብዙ ጊዜ

ሠርቷል፡፡ አሁን አባቴም ወንድሜም በሕይወት የሉም፡፡ እኔ ሙያውን ያስተማርኩት ታናሽ ወንድሜ ተመስገን ደጀኔ፤

በፒያሳ ወርቅ ቤት እየሰራ ነው፡፡ በውጭ አገር የሚኖሩ ወንድምና እህትም አሉን፡፡
እስቲ ስለ ጀርመን ትምህርትዎ ያጫውቱኝ…
የገባሁበት ትምህርት ቤት 26 ሠራተኞችና 150 ተማሪዎች ነበሩበት፡፡ 149ኙ ተማሪዎች ጀርመናዊያን ነበሩ፡፡ መጀመሪያ

ላይ ቋንቋቸው ቢያስቸግረኝም 6 ዓመት የሚፈጀውን ስልጠና በ3 ዓመት አጠናቅቄ ነው ዲፕሎማዬን ይዤ የመጣሁት፡፡

በብርና ወርቅ ሥራ ዲዛይን በማውጣትም ሆነ ያንን በትክክል ወደ ተግባር በመለወጥ ከልጅነቴ ጀምሮ የዳበረ ዕውቀት

ስለነበረኝ፤ ትምህርቱን በቶሎ ለማጠናቀቅ አስችሎኛል፡፡ ትምህርቱ የሙያ ብቻ ሳይሆን የዓለም ታሪክና ጠቅላላ

ዕውቀትንም ያካተተ ነበር፡፡ በዚህም በኩል ቢሆን አጥጋቢ ውጤት ነበር ያመጣሁት፡፡ በአገር ውስጥ ተማሪ እያለሁ

በሒሳብ ትምህርት ጎበዝ ነበርኩ፡፡ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ብዙ ነገር ባናውቅም የዓለምን ታሪክ በስፋት ነበር የምንማረው፡፡

ይሄ የጀርመኑን ትምህርት ቀላል አድርጐልኛል፡፡
ከጀርመን ከመጡ በኋላ ሥራ የት ጀመሩ?
ወንድሜ አቶ ክብርዬ፤ ከፒያሳውም በተጨማሪ በጊዮንና በሒልተን ሆቴሎች ተጨማሪ ሱቆችን ከፍቶ ስለነበር፣

ከጀርመን እንደመጣሁ ሥራ የጀመርኩት እሱ ጋር ነበር፡፡ በወቅቱ አባታችንም በቤተመንግሥት ይሰራ ስለነበር፣ ሦስታችን

በመተባበር ብዙ ሥራዎችን ሠርተናል፡፡ የአፄ ኃይለሥላሴ 80ኛ ዓመት የልደት በዓል ሲከበር ምድር ጦር፣ ፖሊስ

ሠራዊት፣ ፓርላማ፣ የሐረር ሕዝብ፣ የባሌ ሕዝብ … ትዕዛዝ እየሰጡን ልዩ ልዩ የስጦታ ዕቃዎችን፤ ከወርቅ ከብር፣

ከአልማዝ፣ ከከርከሮ ጥርስ … ሠርተናል። በዲዛይን ሥራዎቹ ላይ ሎሬት አፈወርቅ ተክሌም የተሳተፉባቸው ነበሩ።
እራስዎን ችለው መሥራት የጀመሩት መቼ ነው?
በ1968 ዓ.ም ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት “ይሔይስ ደጀኔ ወርቅና ብር ሠሪ” የሚል መደብር ከፈትኩ፡፡
ከዚያ በኋላ ለአገር ውስጥና ለውጭ ብዙ ታላላቅ ሰዎች በርካታ ጌጣጌጦችን ሠርቻለሁ፡፡ አልችልም ብዬ የምመልሰው

ሥራ የለም፡፡ እንዲህም ሆኖ በሙያው ላይ አባታችን የነበረውን ዕውቀት አሁን በ76ኛ ዓመቴም አልደረስኩበትም

እላለሁ፡፡
ለእኛ ዕውቀት መሠረት አባታችን እንደሆነው ሁሉ፣ እኔም ሙያውን ለሌሎች ኢትዮጵያዊያን በማስተማሬ ደስተኛ ነኝ፡፡

የወንድሜና የእኔም ልጆች የቤተሰባችንን ሙያ ማስቀጠል የሚያስችል ዕውቀት አላቸው፤ ሥራውንም በደንብ እየሰሩት

ነው፡፡
በመጨረሻ በአገራችን የወርቅና ብር ሥራ ያለበትን ደረጃ ቢነግሩኝ…
በወርቅና ብር ሥራ የላቀ ችሎታ ያላቸው ኢትዮጵያዊያን በየቦታው አሉ፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሉ የሚባሉት የከበሩ

ማዕድናትም ብዙዎቹ በአገራችን ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ለመፈለግና ለመስራት ግን አንተጋም። የመስራት ስንፍና አለብን፡፡

ድሆች ተብለን የምንጠራው ለዚህ ነው፡፡ መንግሥትና ሕዝብ ከተባበሩ ይህ ችግር ይቀረፋል ብዬ አምናለሁ። ተባብረንና

ተከባብረን እንስራ የሚል መልዕክት ባስተላልፍ ደስ ይለኛል፡፡

በአንድነት ፓርቲ ምተዳደሪያ ደንብ መሰረት የድርጅቱን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ(ወይንም ካቢኔ) የሚመርጡት የድርጅቱ ሊቀመንበር ናቸው። ሊቀመነንበሩ በጠቅላላ ጉባኤ የሚመረጡ ሲሆን፣ የካቢኔ አባላትን ደግሞ ብሄራዊ ምክር ቤቱ ያጸድቃል። የብሄራዊ ምክር ቤቱ እሽታ ያላገኘ የካቢኔ አባል ተቀባይነት አይኖረዉም። ለማንበብ እዚህ ይጫኑ !

ጊዜው ቆየ እንጂ የአንደኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ “አብሮ መኖር በዓለም ዙሪያ” የሚል መጽሃፍ እንድንማርበት መመደቡ ትዝ ይለኛል። ዛሬ አብረን የምኖረው ዓለም በፈጠረችው የጊዜው ቁሳቁስ ሆነና ሃሎ ስንባል አንዴ ያዝልኝ በማለት ሰውን መስመር ላይ እያስጠበቅን ፌስቡክ፤ ስካይፕ ሌላም ሌላም ነገር ላይ …

በአፍ የመጣ በሽታ – ከአደፍርስ ተሰማ Read more »

‹‹ምእመናን የቤተ ክርስቲያን አባላት እንጂ አካላት አይደሉም›› ባዮቹና በተቃውሟቸው ‹‹መንግሥት እየደገፈን ነው›› ያሉት እነኃይሌ ኣብርሃ÷ ፓትርያርኩ ረዳታቸውን ‹‹እስከ ገና ድረስ ዘወር የማያደርጉ›› ከኾነ እንቅስቃሴያቸው ትጥቃዊ መልክ እንደሚኖረው በማስጠንቀቅ ዝተዋል – ‹‹ያኹኑ ሊቀ ጳጳስ የማን ረዳት ናቸው፤ የማኅበረ ቅዱሳን ናቸው ወይስ የቅዱስነትዎ? በሊቀ ጳጳሱ ፈረጅያ ሥር ተከተው ጀግና ሊቀ ጳጳስ በሠራው ሀ/ስብከት ቢሮ ተሰጥቷቸው እያረቀቁበት ስለኾነ …

ደራሲ – ሣህለ ሥላሴ ብርሃነ ማርያም፤ ቅኝት – መስፍን ማሞ ተሰማ
መንደርደሪያ
ሥነ ፅሁፍ የሀገር ታሪክ ባህልና የህብረተሰብ ህይወት … በቃላት ደርዝ ተደርዘው ላለውና ለሚመጣው ትውልድ የሥነ ፅሁፍ ጠቢባን የሚያበረክቱት ቅርስ ነው። ጥበብ ነው ሥነ ፅሁፍ፤ የሀቅ መልህቅ። ጥበብን ያላሸተ፤ እውነትንና ፍትህን ያላማጠ፤ ያልወለደ ሥነ ፅሁፍ – ምን ቢኳኳል ቃል በቃል፤ ምን ቢቀማጠል፤ ቢያማልል – እንኳንና ዘመን ከዘመን ተሻግሮ፤ ትውልድን በትውልድ አጥፎ ‘ዘለዓለማዊ ህልው’ ሊያገኝ ቀርቶ – እንደ ጠዋት ጤዛ አረጋገፉ፤ ፋታም አይሰጥ አሟሟቱ። እንዲህ ያሉ – በየዘመኑ የመከኑ ብዕራት፤ በየዘመኑ ነበሩ፤ ዛሬም አሉ፤ ነገም ይኖራሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ደራሲ – ሣህለ ሥላሴ ብርሃነ ማርያም
ቅኝት – መስፍን ማሞ ተሰማ

መንደርደሪያ
ሥነ ፅሁፍ የሀገር ታሪክ ባህልና የህብረተሰብ ህይወት…በቃላት ደርዝ ተደርዘው ላለውና ለሚመጣው ትውልድ የሥነ ፅሁፍ ጠቢባን የሚያበረክቱት ቅርስ ነው። ጥበብ ነው ሥነ ፅሁፍ፤ የሀቅ መልህቅ። ጥበብን ያላሸተ፤ እውነትንና ፍትህን ያላማጠ፤ ያልወለደ ሥነ ፅሁፍ – ምን ቢኳኳል ቃል በቃል፤ ምን ቢቀማጠል፤ ቢያማልል –  እንኳንና ዘመን ከዘመን ተሻግሮ፤ ትውልድን በትውልድ አጥፎ ‘ዘለዓለማዊ ህልው’ ሊያገኝ ቀርቶ – እንደ ጠዋት ጤዛ አረጋገፉ፤ ፋታም አይሰጥ አሟሟቱ። እንዲህ ያሉ – በየዘመኑ የመከኑ ብዕራት፤ በየዘመኑ ነበሩ፤ ዛሬም አሉ፤ ነገም ይኖራሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተመስገን ደሳለኝ – አዲስ አበባ
ከሩሲያውያኑ ቦልሼቪክና ሜንሼቪክ አንስቶ፣ የእኛዎቹ ኢህአፓና መኢሶን በፊት-አውራሪነት እስከ ተሳተፉበት ድረስ ያሉ በደም የጨቀዩ አብዮቶች በሙሉ በከተሞች የተካሄዱ ሲሆን፣ አብዛኛው አጋፋሪዎቻቸው ደግሞ ልሂቃኖች እንደነበሩ በጉዳዩ ዙሪያ የተፃፉ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ረቡእ ታጣቂዎቹ  ከቀኑ 10 ሰአት ገደማ ወደ ከተማዋ በመግባት 3 ጠባቂዎችን በመግደልና አንደኛውን ታጣቂ መሳሪያውን በመቀማትና ልብሱን በማስወለቅ ” ሂድና ለአለቆችህ ንገር” በማለት ጉዳት ሳያደርሱበት መልቀቃቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ታጣቂዎቹ አንድ ድግን መትረጊስ፣ አንድ ላውንቸርና አንድ ባዙቃ ማርከው ወስደዋል። ይህንን ተከትሎ በአካባቢው የደረሱት የመከላከያ ሰራዊት …

ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ከ2007 አገር አቀፍ ምርጫ ጋር በተያያዘ በተለይ በአዲስአበባ ከተማ ሕዝብ ቅሬታ የሚያቀርብባቸውን የመልካም አስተዳደር፣ የሙስናና የልማት ችግሮችን ለመፍታት ከፍተኛ በጀት መድቦ እየተንቀሳቀሰ ነው። የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የ2006-2007 ዕቅድ አካል እንዲሆን በተደረገው ይህ ከመጪው ዓመት ምርጫ ጋር በቀጥታ የተያያዘው ዘመቻን በብቃት እንዲያስፈጽሙ ለክፍለከተማና ወረዳ አመራሮች ግልጽ …

ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለስልጣናቱ ማንኛውንም ቃለምልልስ ለኢሳት ቢሰጡ በአሸባሪነት ይከሰሳሉ። የባለስልጣኖች አንደኛው መገምገሚያም ለኢሳት መረጃ በመስጠት እንደሚወሰን ከኢህአዴግ የመረጃ ክፍል የደረሰን መረጃ ያመለክቷል። መመሪያው ለህዝብ ግንኙነት ሰራተኞች፣ ለደህንነት ሰራተኞች፣ ለመንግስት ባለስልጣናት እና ለ ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች መተላለፉ ታውቋል። የመንግስት ባለስልጣናት ለኢሳት መረጃ በመስጠት ድርጅቱን ህጋዊነት እያላበሱትና ሌሎችም ዜጎች አንዲናገሩበት እያደፋፈሩ …

ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሬዚዳንት ሳልቫኪርና የተቃዋሚያቸው ሪክ ማቻር ወኪሎች ለድርድር  አዲስ አበባ በሚገኙበት በዚህ ሰአት ፣ የአሜሪካ መንግስት የኢምባሲ ሰራተኞች በሙሉ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘ። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው ፣ የአሜሪካ የኢምባሲ ሰራተኞች በተዘጋጀላቸው አውሮፕላን ለቀው ይወጣሉ። ከጃንዋሪ 4 ጀምሮም ምንም አይነት አገልግሎት በኢምባሲው በኩል እንደማይሰጥ ግልጽ አድርጓል። …

ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአብዛኛው የኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ዛምቢያ፣ ማሊና ፓኪስታን ዜጎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች መርከብ ጉዳት ከመድረሱ በፊት የጣሊያን ጠባቂዎች ደርሰው እንዳዳኑዋት ቢቢሲ ዘግቧል። ከሶስት ወራት በፊት ላምፓዱሳ እየተባለች በምትጠራዋ የጣሊያን ግዛት አቅራቢያ ከ400 በላይ ሰዎች መስጠማቸውን ተከትሎ የጣሊያን መንግስት ከፍተኛ ትችት ሲቀርብበት ቆይቷል። የአሁኑ እርምጃም ይህን ትችት ለማምለጥ የተወሰደ …

ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች የሚገኙ የሙስሊም ብራዘርስ ሁድ ደጋፊዎች ከፖሊስ ጋር ባደረጉት ግጭት 6 ሰዎች ተገድለዋል። ፓርቲው በበኩሉ የሞቱት ሰዎች 17 ናቸው ይላል። ግጭቱ የተነሳው ግብጽ መንግስት ፓርቲውን አሻበሪ ብሎ መፈረጁን ተከትሎ ነው። የፓርቲው መሪዎችና በቅርቡ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ አሸንፈው ስልጣን ላይ የነበሩት ሙሀመድ ሙርሲ ወደ እስር ቤት …

ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መብቶች መከበር የሚሟገተው ዓለምአቀፍ ጥምረት የ30 ሺህ ዶላር ድጋፍ ለዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት – አይኦኤም ዛሬ አበረከተ፡፡

በከፍተኛ የህክምና ክትትል ሥር ያለው የፎርሙላ አንድ ፈጣን የመኪና እሽቅድድም ሰባት ጊዜ ሻምፕዮን ሹማኽር ዛሬ 45ተኛ ዓመቱን ደፍኗል ። አድናቂዎቹ ዛሬ በተኛበት ሆስፒታል አቅራቢያ ተሰባስበው ልደቱ አስበዋል ።

የማቻርና የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ተደራዳሪ ልዑካኖች አዲስ አበባ ውስጥ በተናጠል ከሸምጋዩ ከምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት በእንግሊዘኛው ምህፃር IGAD ጋር እየተነጋገሩ ነው ። ቀጥተኛው ወይም የፊት ለፊቱ ንግግር ደግሞ ነገ ወይም ከነገ ወዲያ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል ።

የትብብሩ ሊቀመንበር አርቲስት ታማኝ በየነ ማህበሩ የጀመረው የገንዘብ ድጋፍ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ በተቀናጀ መልኩ እንደሚቀጥል አስታውቋል ። በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርቧል ።

ወጣት ተዋናይ ነው፤ በተለይ «ቤቶች» በተሰኘው አስቂኝ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ላይ «ይበቃል» የተሰኘውን ገፀባሕሪ ወክሎ በመጫወት ዝናን አትርፏል። ወደ ፊት ዓየር ላይ በሚበቃው የዶቸቬለ ተከታታይ ድራማ ላይም ተሳታፊ ሆኗል።

በበደኖ አርባጉጉ አሰቦት አበምሳ እና በቀሪው የኦሮሚያ ክልል የተጨፈጨፉ ዜጎች የማን ትእዛዝ ነበር?
“ለረጅም ግዜ ኣብረን የኖርን እና የተዋለድን ስለሆን አንፈርምም :የአማራ ህዝብ አይመታም መመታት ያለበት ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ነው::” ሀጅ ቃሲም (ኣርባጉጉ)
ምንሊክ ሳልሳዊ
የፕ/ር ዓስራት ወልደየስ የመአሕድ ፕሬዝደንት ሰኔ 1ቀን 1984ዓ.ም ቁጥር መአሕድ /48/84 ለኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት ተወካዮች ም/ቤት በአማራ ህዝብ ላይ የደረሰዉን ጭፍጨፋ እንዲያቆሙ የጻፉት ደብዳቤ ኦሕዴድ እን ኦነግ በጋራ የፈጸሙትን ወንጀል የሚያጋልጥ ታሪካዊ ማስረጃ ነው::
አንድ መቶ አመት ወደኋላ ተመልሰን ዛሬም አእምሮኣችንን እርቃኑን ከማስቀረት ከ100 አመት በፊት ከነበሩ ያልተማሩ መሪዎች ያነሰ የሚያስቡ ባዶዎች በዚህ በሰለጠነ ዘመን የፈጸሙት ወንጀል በትውልዳችን መጠየቅ ሊኖርበት ነው ብንል ባያስኬድም ለሁሉ የሚበጀው ግን መልካሙን ይዞ ማደግ ተመራጭ ነው::

በኣርባጉጉ የአውራጃ የኦህዴድ ተወካይ አቶ ዲማ ጉርሜሳ ግንቦት 26/1984 በአበምሳ ከተማና በኣካባቢው የሚኖሩትን የኦሮሞ ተወላጆችን ስብሰባ ከጠሩ በሆላ “ኣሼ :ኦዴ:ዒመና :ኣቡሌ በሚባሉ መንደሮች የሚኖሩ አማሮች ይገደሉ ብላችሁ ፈርሙ ” በማለት ትዕዛዝ ይሰጣሉ ከተሰበሰቡት የኦሮሞ ተወላጅ መካከል ሀጅ ቃሲም የተባሉ እጃቼውን ኣውጥተው
“ለረጅም ግዜ ኣብረን የኖርን እና የተዋለድን ስለሆን አንፈርምም :የአማራ ህዝብ አይመታም መመታት ያለበት ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ነው ” የሚል አስተያየት በማቅረባቼው
የኦህዴዱ ተወካይ በመናደዱ ሽጉጡን ኣውጥቶ “የነፍጠኛ እረዳት ነህ በማለት ማስፈራራት ሲጀምሩ ስብሰባው የሀጅ ቃሲምን ሀሳብ በመከተል ተበተነ ::
ይህንን ባለ 6 ገጽ የፕሮፌሰር አስራትን ፊርማ የያዘ ደብዳቤ ይመልከቱ::
Image

Image

Image

Image

Image

Image

#MinilikSalsawi