አገር ቤት ያሉ መሪዎች ቁርጠኝነት ያስደንቀኛል። ግርማ ሰይፉ «ለመታሰር እንዘጋጅ» አለ። ዳንኤል ተፈራ «ገዥዎች፣ እመኑኝ ባሮጌው መንገዳችሁ በርካቶችን ነፃነት ናፋቂዎች በሰፋፊ እስር ቤታችሁ ታጉሩ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የዚህን ትውልድ የነፃነት መንፈስ ግን ልታስሩት አትችሉም» አለ። የፍኖት ዋና አዘጋጅ ነብዩ «ጨቋኞችን መታገል ፅድቅ እንጂ ኩነኔ እንደሌለው አምናለሁ፤ ጭቆናን እምቢ በማለቴ የምጠጣት እያንዳንዷ ፅዋ በፈጣሪ ዘንድ ወሮታ […]

ግፍና ሰቆቃ ወልዶናል – የአዲስ አበባ አንድነት ሕዝብ ግንኙነት ያሬድ አማረ ************************************************************ እንታሰራለን ስንል አንፈታም ማለት አይደለም ፤ በትግል ውስጥ አልፈን እናሸንፋለን ስንልም ላንሞት እንችላለንም ለማለት አይደለም ፡፡ ሊሰመርበት የሚገባው ግን በሰላማዊ ትግሉ ማሳ ላይ ዘር ሆነን ተዘርተን ብዙ ፍሬ እንዳፈራን በተራዳን ወቅትና ወደ ጎተራ በአንድነት ተሰባስበን በገባን ወቅት የተነሳንለት ዓላማ ጥልቅና ምጡቅ እንደሆነ ልባችን […]

ይህንን ደብዳቤ ስጽፍ ፊት ለፊቴ የቤተሰባችንን ፎቶ ግድግዳው ላይ እያየሁ ነው፡፡ ‹‹ይናገራል ፎቶ›› አሉ፡፡ አቤት በፎቶማ እንዴት ያምርብናል፡፡ ፎቶ ላይ ያለው ፈገግታ እንዲሁ ትዳር ውስጥም ቢቀጥል እንዴት ጥሩ ነበር፡፡ ግርም ይላልኮ፡፡ፎቶ አንሺዎች ሁሉ ከአንድ እናት የተወለዱ ይመስል ለምንድን ነው በግድ ‹‹ፈገግ በሉ›› የሚሉት፡፡ በቃ ፎቶ ማለት ደስታን ማሳያ ብቻ ነው እንዴ፡፡ የከፋው ሰው ፎቶ አይነሳም ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ፎቶ አንሺዎችና ቪዲዮ ቀራጮችኮ በገዛ ሠርጋችን ተዋንያን ያደርጉናል፡፡ እንደ ራሳችን ሳይሆን እንደ እነርሱ ፈቃድ ያስኬዱናል፣ ያሳስሙናል፣ ያስተቃቅፉናል፣ ያሰልፉናል፣ ያጣምሙናል፣ ያቃኑናል፡፡ እነርሱ ግን የፊልም ዳይሬክተር ናቸው ወይስ የሠርግ ቪዲዮ ቀራጮች? እኛስ ሙሽሮች ነን ወይስ ተዋንያን?

ከተለያየን ጀምሮ ይህንን ፎቶ ደጋግሜ እያየሁ ደጋግሜ አስባለሁ፡፡ ለብቻ መሆን አንድ የሚጠቅመው ነገር ቢኖር የማሰቢያ ጊዜ መስጠቱ ነው፡፡ ሰው ለመኖር ለካ ከምግብና መጠለያ እኩል የማሰቢያ ጊዜም ያስፈልገዋል፡፡ እንዲሁ ስንዞር፣ እንዲሁ ስንወጣና ስንወርድ፣ እንዲሁ ቀዳዳ ለመሙላት ወዲህ ወዲያ ስንል፣ እንዲሁ ጠዋት ወጥተን ማታ ስንገባ አይደል እንዴ የኖርነው? አሁን ሳስበውኮ የኑሮ ወንዝ ወደወሰደን ፈሰስን እንጂ አስበን አልኖርንም፡፡

እስኪ ልጠይቅሽ ለመሆኑ ለኛ ትዳር ምንድን ነበር? አንድ ቤት መኖር፣ አንድ አልጋ ላይ መተኛት፣ ልጆች መውለድ፣ ወላጆቻችን ቤት አንድ ላይ መሄድ፣ መጎራረስ፣ <ከባለቤትዎ ጋር> ተብሎ መጠራት፣ ምንድን ነው ግን ትዳር? ለመሆኑ ሠርገን ነበር ወይስ ተጋብተን ነበር? ጋብቻ ነበረን ወይስ ትዳር? አቤት ለሠርጋችን እንዴት ነበር የለፋነው፡፡ ‹‹ጋብቻ የትዳር መጀመሪያው ሥነ ሥርዓቱ ነው፤ ሠርግ ማጀቢያው ድግስ ሲሆን፣ ትዳር ደግሞ በዚህ በኩል ተገብቶ የሚኖረው ኑሮ ነው›› የሚል ካነበብኩ በኋላ ይህንን ጥያቄ መጠየቅ ጀምሬያለሁ፡፡ አዳራሽ ለማግኘት፣ መኪና ለማግኘት፣ የሠርግ ልብስ ለመምረጥና ለማሰፋት፣ ድግሱን ለማሣመር፣ የሚጠሩ ሰዎችን ለመምረጥ፣ ሚዜዎቻችንን ለመምረጥ ስንቴ ነበር ያሰብነው፤ ሰሐንና ብርጭቆ እንኳን ሳይቀር አስበንበት፣ ሰው አማክረን፣ ዙረን መርጠን፣ ከሌሎች ልምድ ወስደን ነበር የተከራየነው፡፡

በእኔና ባንቺ ሠርግ ስንት ሰዎች ተሳተፉ፣ ስንቶች ለፉ፣ የስንት ሰዎች ሐሳብ ተዋጣ፣ የስንቶች ልምድ ተቀሰመ፣ የስንቶች ጉልበትስ ፈሰሰ፡፡ በያንዳንዱ ጉዳይ እንወያይ፣ እንከራከር፣ እንጨቃጨቅ፣ እንለያይ ነበር፡፡ በያንዳንዱ ጉዳይ እንደገና እንገናኝ፣ እንግባባ፣ እንስማማና እንታረቅ ነበር፡፡ በብዙ ሰዎች ታግዘን አግብተን ትዳርን ብቻችንን ገጠምነውና አልቻልነውም፡፡ ሠርግ ላይ ያለው እገዛ ትዳር ላይ ቢሆን እንዴት ጥሩ ነበር፡፡

አሁን ሳስበው የለፋነው ለሠርጋችን እንጂ ለትዳራችን አልነበረም፡፡ እስኪ ትዝ ይበልሽ፡፡ ከኛ በፊት የተጋቡ ሙሽሮችን ልምድ የወሰድው ስለ ሙሽራ ልብስ፣ ስለ ቬሎ፣ ስለ ሚዜ፣ ስለ መኪና፣ ስለ ድግስ፣ ስለ አዳራሽ፣ ስለ መጥሪያ ካርድ፣ ስለ ባንድ፣ ስለ ቪዲዮ እንጂ ስለ ኑሯቸው አልነበረም፡፡ እነርሱምኮ ‹ዲል› ባለ ድግስ፣ የሁላችንንም ቀልብ በማረከ ሥነ ሥርዓት ተጋብተው ይሆናል፡፡ ከዚያስ? ነው ጥያቄው፡፡ የኛስ ሠርግ ጉ-ድ የተባለ አልነበረም፡፡ እስካሁን ድረስ የእኔና የአንቺን ሠርግ እንደ ትንግርት የሚያወሩት አሉኮ፡፡ ከሠርጉ በኋላ የሆንነውን ስለማያውቁ፡፡

አንድ ወዳጄ ትዳርና ችግኝ አንድ ነው ብሎኛል፡፡ ሁለቱም ክብካቤ ይፈልጋሉ፡፤ ሁለቱም በየጊዜው መኮትኮትና ማሳደግን ይጠይቃሉ፡፡ ሁለቱም መከርከምና ድንጋይና አረሙን እንዲያስወግዱላቸው ይፈልጋሉ፡፡ ሁለቱም የዕለት ተዕለት ትኩረት ይሻሉ፡፡ እኛ ግን እንደዚያ ያደረግን አይመስለኝም፡፡ ጉልበታችን ሁሉ ለሠርጉ ፈሰሰና ትዳሩ ላይ አቅም ጠፋ፡፡ ‹‹ዳገት ላይ ሰው ጠፋ›› አሉ ፕሮፌሰር መስፍን፡፡ ድሮ ልጆች ሆነን

ገንዘባችን ሁሉ አለቀ በሻይ

ሚስት ሳናገባ ዓለምን ሳናይ – እንል ነበር፡፡ ከየት የመጣ ግጥም እንደሆነ እንጃ፡፡ የኛም ጉልበታችንና ዐቅማችን ሁሉ ሠርጋችን ላይ ፈሰሰና ‹ዓለምን ሳናይ› ቀረን፡፡ ይገርምሻል፡፡ በቴሌቭዥን ሰሞኑን የችግኝ ተከላ ዜና ሲነገር ትዝ የሚለኝ የእኔና የአንቺ ትዳር ነው፡፡ ድሮ በሠፈራችን በሚገኝ ጋራ ላይ ሰኔ በመጣ ቁጥር በቀበሌ ትእዛዝ እየወጣን የምንተክለው ችግኝ ነበር፡፡ ከተከልነው በኋላ ግን ዞር ብሎ የሚያየው የለም፡፡ ሰኔና ሰኞ የገጠመለት  ችግኝ ይጸድቃል፡፡ ሌላው ግን ደርቆ ይቀራል፡፡ ቀበሌውም ማስተከል እንጂ ማሳደግ አያውቅበትም፡፡ የብዙዎቻችን ትዳር እንደዚያ ይመስለኛል፡፡ ልክ አንድ አገር ሰው ተሰብስቦ ችግኝ እንደሚተክለው ሁሉ አንድ አገር ሰው ተሰብስቦ ትዳር የሚባለውን ችግኝ የሠርግ ቀን ይተክለዋል፡፡ ችግኙን ማንም ዞር ብሎ እንደማያየው ሁሉ ትዳርን የሚከባከበው፣ ውኃ የሚያጠጣው፣ አረም የሚነቅልለት፣ አፈር የሚያደርግለት፣ ፋንድያ የሚደፋለት፣ አውሬ እንዳያበላሸው አጥር የሚቀጥርለት የለም፡፡ ልክ ያደለው ችግኝ በዕድል አድጎ እንደሚገኘው ሁሉ፣ ያደለው ትዳርም አድጎ ተመንድጎ እናየው ይሆናል፡፡ ‹‹አፍራ ያለው ተኝቶም ያፈራል›› ይባል የለ፡፡ ብዙ ትዳሮች ግን እንደ ብዙዎቹ ችግኞች ከስመው ቀርተዋል፡፡

እኔማ አንዳንዴ ‹ለሠርጋችን ከተጨነቅነው ግማሹን እንኳን ለትዳራችን አድርገነው ቢሆን ኖሮ እንደዚህ ባልሆንን ነበር› እላለሁ፡፡ እንዴው ብቻዬን ስለሆንኩ ሰው አያየኝም እንጂ፣ ያበድኩኮ ነው የምመስለው፡፡ ብቻዬን እስቃለሁ፤ ብቻዬንም አወራለሁ፡፡ ባለፉት ዓመታት ያወራናቸውን ሳስባቸው ስለ ቤት ወጭ፣ ስለ ልጆች ትምህርት ቤት፣ ስለ ወላጆቻችን፣ ስለ ጎረቤቶቻችን፣ ስለ ልቅሶና ሠርግ፣ ስለ ርዳታና መዋጮ፣ ስለ መኪናና የቤት ዕቃ፣ ስለ ሥራ ቦታ ችግሮች ሆነው አገኛቸዋለሁ፡፡ እነዚህ ነገሮች ግን ብቻ እንዴት ትዳርን ያሳድጉታል? እንዴትስ ፍሬያማ ያደርጉታል? ስለ እኔና ስለ አንቺ፣ ስለምትወጅውና ስለምትጠይው፣ ስለምንጨምረውና ስለምናርመው፣ አንቺን ይበልጥ ስለማስደሰትና እኔን ይበልጥ ስለማርካት፣ እኔ ላንቺ ማድረግ ስላለብኝና አንቺ ለእኔ ማድረግ ስላለብሽ ነገር ማውራታችንን፣ መወሰናችንንም አላስታውስም፡፡

ደግሞ የሚገርምሽ ነገር፤ ዛሬ ዛሬ ሳስበው ግርም የሚለኝ፣ የምንነጋገረውኮ በሚያጋጥሙን ነገሮች ላይ ብቻ ነው፡፡ አንዳች ነገር ካልገጠመን አንነጋገርም፡፡ ለነገሩማ በዝምታ አድገን እንዴት መነጋገር እንልመድ ብለሽ ነው፡፡ ‹‹ጥፋቱስ አይደለም ካንቺ ወይም  ከእኔ፣

ፍቅር በመሆኑ እንጂ ጽድቅና ኩነኔ፣

አንቺ አንቺን መሆንሽ እኔ እኔን መሆኔ››

አሉ አብዬ መንግሥቱ እውነታቸውን ነው፡፡ እንዴው ጊዜ ወስደን፣ ከሌላው ነገር ወጣ ብለን፣ እየተዝናናንም ቢሉ ወይም ለራሳችን ጊዜ ሰጥተን ስለ ወደፊት ኑሮአችን፣ ስለ እኔና አንቺ ጉዳይ፣ ልናደርገው ስለምንፈልገው ነገር ወይም መሆን ስለምንሻው ጉዳይ አውርተን እናውቃለን ብለሽ ነው? እንዴው ሊመጣልኝ አልቻለም፡፡ አንድ ነገር ይገጥመናል፣ በዚያ ላይ እናወራለን፣ ጉዳዩ ከእኔ ወይንም ካንቺ ጋር ይገናኝና አንዳችን አጥቂ ሌላችን ተከላካይ እንሆናለን፡፡ ከዚያማ ‹‹ጨሰ አቧራው ጨሰ›› ማለት ያኔ ነው፡፡ ግን ለመሆኑ ይህንን ‹‹ጨሰ አቧራው ጨሰ›› የሚል የሠርግ ዘፈን ያመጣው ማነው? መቼም እንደኔ አግብቶ የፈታ ሰው መሆን አለበት፡፡

በተለይማ ልጆች ከመጡ በኋላ ባሰብን፡፡ እኔም ባልሽ መሆኔ ቀርቶ የልጆችሽ አባት ሆንኩ፤ እንቺም ሚስቴ መሆንሽ ቀርቶ የልጆቼ እናት ሆንሽ፡፡ ለመሆኑ ግን ከኛ የሚተርፈንን ጊዜ ነው ለልጆች መስጠት ያለብን ወይስ ከልጆች የሚተርፈውን ጊዜ ነበር እኛ መውሰድ የነበረብን? ለመሆኑ በትዳር ውስጥ ዋናው ጉዳይ ምንድን ነው? ‹ባለቤቴ› የሚለውን ባሕላዊ አጠራር የወደድኩትም ያደነቅኩትም አሁን ነው፡፡ ለምን መሰለሽ? በቀጣዩ ደብዳቤዬ እነግርሻለሁ፡፡

ብንጣላም፣ ብንለያይም፣ ባንግባባም፣ ግን ደኅና ሁኚ፡፡

ያንቺው የቀድሞ ባለቤት

(ሳምንት ይቀጥላል)

 © ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

በ፲፱፻፹፯ ዓ.ም. ዳግመኛ ከተከፈተ ወዲህ የተመረቁት ደቀ መዛሙርት ብዛት 2175 ደርሷል የተቋማዊ ነፃነት ዕጦትና የበጀት እጥረት ‹‹ጥናትና ምርምር ላይ እንዳላተኩር አድርጎኛል፡፡›› መሠረቱ የወጣው ሕንፃ ሥራ እንዲቆም በጀቱም እንዲመለስ የተላለፈው ትእዛዝ አወዛግቧል ወደ ዩኒቪርስቲ ደረጃ የማሸጋገሩ ሒደት በግንባታ ላይ የሚገኘውን ሕንፃ መጠናቀቅ ይጠብቃል ‹‹ከዛሬው ደስታችኹ የሚበልጥ ደስታ ከፊታችኹ ስለተዘጋጀ ደስታችኹ ዕጥፍ ድርብ ነው፡፡›› /ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ/ …

ሐምሌ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገር ውስጥ እና በውጭ ከፍተኛ ጫና የተፈጠረበት የኢህአዴግ መንግስት የአቶ አንዳርጋቸውን ምስል በቴሌቪዥን ካቀረበ በሁዋላ የተለያዩ አስተያየቶች በማህበራዊ የመገናኛ መንገዶችና በስልክ እየተሰጡ ነው።አብዛኛው አስተያየት ሰጪ በቴሌቪዥን የቀረበው ምስልና ድምጽ መቆራረጡን ፣ ኢቲቪን የሚያክል ድርጅት ጥራት ያለው  ቀረጻ ለማካሄድ አለመቻሉ ገዢው ፓርቲ ለፕሮፓጋንዳ የሚሆን ነገር ለማግኘት አለመቻሉን ገልጸዋል። ሚኒሊክ ሳልሳዊ  …

ሐምሌ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከአገር ቤት በተከታታይ የሚደወሉ ስልኮችን ለማስተናገድ ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት እየገለጸ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ደዋዮች አቶ ለአቶ አንዳርጋቸው ያላቸውን ከበሬታ የሚገልጹና ኢህአዴግን በሃይል ለማንበርከክ የሚታገሉትን ቡድኖች ለመቀላቀል እንዴት እንደሚቻል የሚጠይቁ ናቸው። በሌላ ዜና ደግሞ የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተፈጸመውን የአፈና ተግባር አውግዟል። ትህዴን ” የወያኔ አምባገነን …

ሐምሌ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ  የጸጥታ  ሃይሎች  የአንድነት ፓርቲን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ  የሆነውን ወጣት ሃብታሙ  አያሌውን ፣  የፓርቲውን  የድርጅት ጉዳይ  ምክትል  ሃላፊ  አቶ  ዳንኤል ሽበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነውን የሽዋስ አሰፋን እንዲሁም በማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን ከመቀሌ በመጻፍ የሚታወቀውና አረና ፓርቲ አባል የሆነው  መምህር አአብራሃ ደስታን ይዞ አስሯል። እሰረኞቸ ማእከላዊ በሚባለው …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

እ ጎ አ ካለፈው ጥር ወር መግቢያ ወዲህ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ፣ ኒው ዮርክ፤ ቢል ደ ብላሲዮ የተባሉት የዴሞክራቱ ፓርቲ አባል የከተማይቱን የከንቲባነት ሥልጣን ከመረከባቸው በፊት፤ ከዚያ በፊት ፣ 3 ጊዜ ተመርጠው እ ጎ አ ከ ጥር 1፤ 2002

የመን ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፋ የሰጠቻቸው የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ፓርቲ ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በኢትዮጵያ እሥር ቤት ውስጥ ይበደላሉ ብሎ እንደሚፈራ ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩመን ራይትስ ዋች አስታወቀ ።

ደቡብ ሱዳን ሶስተኛ ዓመት የነፃነት በዓሏን ዛሬ አከበረች ።ርዕሠ-ከተማ ጁባ ዉስጥ በከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ በተከበረው በዚሁ የነፃነት በዓል ላይ የደቡብ ሱዳን መሪ ሳልቫ ኪር ፣ተቀናቃናቸው የቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር የሰላም ንግግሩን እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል ።

የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆነው ወጣት ሀብታሙ አያሌው፣ በትላንትናው ዕለት በማዕከላዊ እስር ቤት ከታሰረበት ጊዜ ጀምሮ በቤተሰቦቹ እና በወዳጅ ጓደኞቹ እንዳይጎበኝ በመደረጉ ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ እንዳልተቻለ የፓርቲው አመራሮች ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡ አመራሮቹ አክለውም፣ በዛሬው ዕለት ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት ያመሩት፣ የሀብታሙ ጠበቆች አቶ ተማም አባቡልጉ እና አቶ ገበየሁ እስረኛውን መጠየቅ አትችሉም ተብለው መባረራቸውን አስረድተዋል፡፡

ሐብታሙን ይህ ይገልጸው ይሆን ? ********************************* በምረቃ መጽሔቱ ፎቶ ስር‹‹የፈራ ይመለስ››ብሎ ነበር ******************************************** ሐብታሙ አያሌው ራሱን ለፈጣሪው ያስገዛ ሐይማኖተኛ ሆኖ ያገኙት ኢህአዴጎች በአነጋገሩና ነገሮችን ለመግለጽ ያለውን ውስጣዊ ድፍረት ተገንዝበው ከቤተክርስቲያን ጠለፉት ፡፡አባላቸው አደረጉት፡፡ሐብታሙ አባል የሆነበት ኢህአዴግ ጭንቅ ውስጥ ነበርና በልጁ የመናገርና የማሳመን ችሎታ ለመጠቀም ከወጣቶች አደረጃጀት አንስቶ እስከ ወጣቶች ፌደሬሽን ፕሬዘዳንትነት አድርሶታል፡፡ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር […]

የሰሞኑ የኢትዮጵያችን ሁኔታ ሀዘን፣ ቁጣ፣ ንዴት፣ እልህ፣ ብሎም የደስታ ስሜትን የቀላቀለ ነበር፡፡ የእሰሩ ሁኔታ ቀጥሏል፡፡ ዛሬ እንኳን ከአንድነት ፓርቲ አቶ ሀብታሙ አያሌው እና ከሰማያዊ ፓርቲ አቶ የሺዋስ አሰፋ መታሰራቸውን ሰምተናል፣ አውቀናል፡፡ የዚህ መሰል አካሄድ ግን መዘዘን የሚስከትል ይመስለኛል፡፡ አሁን አሁን ሰዎች እንደጥጃ ከቤታቸው፣ ከየመንገዱ፣ ከሚሰሩባቸው ቦታዎች …እየተወሰዱ መታሰራቸው በሀገራችን እየተለመደ የመጣ አዲስ ክስተት ሆኗል፡፡ ሥልጣን […]

የፓርላማ አባልና የአንድነት ከፍተኛ አመራር አባል አቶ ግርማ ሰይፉ የኢሕአዴግ መንግስት በሰላም የሚታገሉ ወጣት ፖለቲከኞችን የማሰሩን ጉዳይ እብድነት ብለዉታል። «እነዚህ ሰዎች አብደው መሆን ይኖርበታል፡፡ ሀብታሙ አያሌውን ፖሊሶች ይዘውት እንደሄዱ ሰማው፡፡ ስልኩ ይጠራል ግን አይመልስም፡፡ የእነርሱን ሃሳብ የሚቃወም ሁሉ አሸባሪ እየመሰላቸው በሽብር እራሳቸውን እያናወዛቸው ያለ ይመሰለኛል፡፡ ሀብታሙን ሊያስሩት ይችላሉ በህዝብ ውስጥ ያለውን የነፃነት መንፈስ ግን ማስረ […]

ነፃነታችን እስከምንጎናፀፍ አንዲት ኢንች አናፈገፍግም!!! አሳሪዎች አዳምጡኝ፡፡ አይደለም እስራትን ሞትን የማይፈሩ ወጣቶች በቅለዋል፡፡ የኢህአዴግ አሮጌ መንገድ የሰለቻቸው ውድ የኢትዮጵያ ልጆች በርክተዋል፡፡ ተቀምጦ ያለነፃነት ከመኖር ቆሞ በነፃነት መሞት እንደሚሻልም እናውቃለን፡፡ ዘመናችሁን ቀርጥፋችሁ በልታችሁ የኛን ዘመን ለማጨለም፤ የወጣቱን ዕድሜ ለመኖር የምትተጉ ባለጊዜዎች፤ ዘመናችንን ለመንጠቅ የምትቅበዘበዙ ገዥዎች እመኑኝ ባሮጌው መንገዳችሁ በርካቶችን ነፃነት ናፋቂዎች በሰፋፊ እስርቤታችሁ ታጉሩ ይሆናል፡፡ ነገር […]

የፓርቲያችን ከፍተኛ አመራሮች አቶ ሀብታሙ አያሌው እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እናሳስባለን!!! ከአንድነት ፓርቲ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ በቅርቡ ለህዝቡና ጋዜጠኞች ይፋ እንዳደረግነው ሕወሓት/ኢህአዴግ ለአለፉት 23 ዓመታት ወደር የሌለው የዴሞክራሲያዊ መብት ገፈፋና የሰብአዊ መብት ረገጣ በዜጎች ላይ ሲፈጽም መቆየቱ ዓለም የሚያውቀው እውነታ መሆኑን፤ በአሁኑወቅትይህየሰብአዊመብትረገጣና ድፍጠጣ በእጅጉ ተባብሶ ወደ መንግሥታዊ የውንብድናና ጥቃት መቀየሩን፤ ዜጎች […]

ሃብታሙ አያሌው ፣ ዳንኤል ሺበሺ እና የሺዋስ አሰፋ ወደ ማእከላዊ መዉረዳቸዉን የሚገለጽ ዜና ተመለከትኩ። በጣም አዝኛለሁ። ሃብታሙ አያሌው በአንድነት ፓርቲ ዉስጥ ትልቅ ሥራ እየሰራ ያለ፣ በቅርቡ ወዳጅ አባቷን ያጣችው እህታችን ባለቤት እና የአንዲት ቆንጅዬ ልጅ አባት ነው።የአንድነት ፓርቲ እና መኢአድ የቅድመ ዉህደት ስምምነት ፈርመው ፣ ዉህደቱን ለማስፈጸም ያቋቋሙት የጋራ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነው። ያ ብቻ አይደለም […]

የግብፅ መንግሥት በነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጭማሬ አደረገ። የሀገሪቱ የዜና አገልግሎት አል- አህራም እንደዘገበው ግብፃዉያን ከዛሬ ጀምሮ በየነዳጅ ማድያው ከ40 እስከ 80 በመቶ ጭማሪ ገንዘብ በማዉጣት ነዳጅ ይሸምታሉ።

አገር ቤት ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚታገሉ ወጣት ፖለቲከኞች መታሰራቸዉን የደረሰን ዘገባ ገለጸ። ከታሰሩት ወጣቶች ዉስጥ የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው፣ የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ም/ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ የሺዋስ አሰፋና የአረና አመራር አባል እና ታዋቂ ብሎገር አቶ አብርሃ ደስታ ይገኙበታል። በጉዳዩ ላይ የአንድነት ፓርቲ መግለጫ […]

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ መቀመጫውን በኢትዮጵያ ያደረገ አንድ ታዋቂ የአሜሪካ የዜና አውታር በቅርቡ ኮካኮላ በኢትዮጵያ እንዳይጠጣ በሚል ያሰራጨሁትን ጽሁፍ በማስመልከት የተሰማውን ቅሬታ አስመልክቶ አንድ የኢሜይል መልዕክት ላከልኝ፡፡ እንዲህ የሚል ጽሁፍ ጻፈ፣ “በድፍረት ልናገርና ሆኖም ግን ኮካኮላ እንዳይጠጣ ለማሳሰብ …

ኢትዮጵያ ከዓለም ለምን ሁለተኛዋ ደሀ አገር ሆነች? Read more »

በአጓጊነቱ የቀጠለዉ ብራዚል ላይ እየተካሄደ ያለዉ የዓለም የእግር ኳስ ግጥምያ ዛሬ በአስተናጋጅ ሀገር ብራዚል እና በጀርመን መካከል ጀምሮአል። ግጥምያዉ በጀርመን በጉጉት እየተጠበቀ ነዉ

በአጓጊነቱ የቀጠለዉ ብራዚል ላይ እየተካሄደ ያለዉ የዓለም የእግር ኳስ ግጥምያ ዛሬ በአስተናጋጅ ሀገር ብራዚል እና በጀርመን መካከል ጀምሮአል። ግጥምያዉ በጀርመን በጉጉት እየተጠበቀ ነዉ

ከግማሽ የሚበልጠዉ የየመን ሕዝብ ሠብአዊ ርዳታ እንደሚያሥፈልገዉ የተባበሩት መንግሥታት የሠብአዊ ርዳታ ማስተባባሪያ ቢሮ (OCHA በምሕፃሩ) እስታወቀ።OCHA እንደሚለዉ ለችግር ለተጋለጠዉ የመናዊ እስቸኳይ ርዳታ ካልደረሰ ለመገመት የሚከብድ ሠብአዊ ድቀት መከሰቱ አይቀርም።

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ከግማሽ የሚበልጠዉ የየመን ሕዝብ ሠብአዊ ርዳታ እንደሚያሥፈልገዉ የተባበሩት መንግሥታት የሠብአዊ ርዳታ ማስተባባሪያ ቢሮ (OCHA በምሕፃሩ) እስታወቀ።OCHA እንደሚለዉ ለችግር ለተጋለጠዉ የመናዊ እስቸኳይ ርዳታ ካልደረሰ ለመገመት የሚከብድ ሠብአዊ ድቀት መከሰቱ አይቀርም።

የብሪታኒያ መንግሥት ዜጋው አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከየመን ለኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታቸው በእጅጉ እንዳሳሰበው ለኢትዮጵያ መንግሥት ማንሳቱን አስታወቋል። የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የመን ላይ መያዝና ወደ ኢትዮጵያ መወሰድን በመቃወም ዛሬ በተለያዩ ሐገራት ሠልፍ ተደርጓል።

አንድ የጀርመን የስለላ መሥሪያ ቤት ባልደረባ ለአሜሪካጠቃሚ መረጃ በመስጠት ንም በመሰለል መጠርጠሩ የጀርመንን መንግሥትና ህዝብ አስቆጥቷል ። የጀርመን መንግሥት የስለላው እውነትነት ከተረጋገጠ ሃገሪቱ በአሜሪካን ላይ ያላትን እምነት አደጋ ላይ እንደሚጥል አስጠንቅቋል ።

በጎርጎሪዮሳዊዉ 2000 ዓ,ም የታቀደዉ የአምዓቱ የልማት ግብ በዋነኝነት በ15ዓመታት ዉስጥ በመላዉ ዓለም ያለዉን ድህነትና ረሃብ በግማሽ ለመቀነስ ያለመ ነዉ። የተመድ እንደሚለዉ የተጀመረዉ ጥረት ባለበት ሁኔታ ከቀጠለ አብዛኞቹ የታለሙት እቅዶች እስከ መጪዉጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ማብቂያ ድረስ ሊደረስባቸዉ ይችላል።

 

 

 

ካለፈው ቅዳሜ አንስቶ በሳን ሆዜ – ካሊፎርኒያ ሲካሄድ የሰነበተው በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያዊያን የስፖርትና የባሕል ፌስቲቫል ከትናንት በስተያ ቅዳሜ ተጠናቅቋል፡፡

የዓመቱ የክለቦች ደረጃዎችም ታውቀዋል፡፡

የቨርጂነያ ቡድን በኔልሰን ማንዴላ ስም የተሰየመውን ዋንጫ አሸንፏል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የአዲሱ አበበን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ሰኔ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን የጸጥታ ሃይሎች የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አሳልፈው በሰብአዊ መብት ጥሰትና ህዝብን በማሰቃየት በአለም የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ዘወትር ለሚወገዘው ለኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች አሳልፈው መስጠታቸው ያበሳጫቸው በአገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የነጻነት ትግሉን የምንቀላቀልበትን” መንገዱን ምሩን” በማለት ጥያቄ ሲያቀርቡ፣ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደግሞ የተቃውሞ ሰልፎችን እያዘጋጁ ነው። ለኢሳት …

ሰኔ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታዋቂው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሂውማን ራይትስ ወች ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ፣ አቶ አንዳርጋቸው ከማንም ጋር እንዳይገናኙ ተደርጎ ለኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች ተላልፎ መሰጠቱን ከታማኝ ምንጭ ማግኘቱን ገልጿል። የየመን ባለስልጣናት ሰነዓ ከሚገኘው ኤል ራህባ አየር ማረፍያ ላይ እኤአ ጁን 23 ወይም 24 ከእንግሊዝ ኢምባሲ ጋር እንዳይገናኝ አድርገው አቶ አንዳርጋቸውን ወዲያውኑ ወደ ኢትዮጵያ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ጀርመን አንድ ዜጋዋ በሀገሪቱ የስለላ ተቋም ተቀጥሮ ለዩናይትድ ስቴትስ እንደሚሰልል ከደረሰችበት ወዲህ ጉዳዩ የሀገሪቱን ከፍተኛ የፖለቲካ ኃይሎች እያነጋገረ ነዉ። በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለመሰላለልን ስምምነት ለመፈረም ዝግጁ አለመሆኗን ዋሽንግተን ባለፈዉ ሳምንት መገባደጃ ላይ አመልክታለች።