ከጊቤ ባሻገር ያለችው ጂማ
![]() |
| The palace of Abba Jifar, Jimma, |
![]() |
| The palace of Abba Jifar, Jimma, |
ኢትዮጵያ 26ኛውን የዓለም የኤድስ ቀን ጋምቤላ ከተማ ላይ ትናንት በተካሄደ ይፋ ሥነ-ሥርዓት አስባለች፡፡
26th World AIDS Day in Ethiopia
ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃገሪቱ ህገ መንግስት አንቀጽ 31 መሰረት በህጋዊ መልኩ ተመዝግበው ሰላማዊ የፖለቲካ እንቃስቃሴ የሚያደርጉ ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን በሽብርተኝነት እና ጽንፈኝነት በመፈረጅ የጥቃት ኢላማ ለማድረግ መታሰቡን ኢሳት የፌደራል መንግስት የጸጥታ ጉዳዮች ሰሞኑን ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ካካሄደው ውይይት ለመረዳት ተችሎአል፡፡ የትግራይ፣ቤንሻንጉል ጉሙዝና አማራ ክልል ሃላፊዎች ሰማያዊ ፣አንድነትና መኢአድ ፓርቲዎች ጽንፈኞች በመሆናቸው …
ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሺን፣ ፓርቲዎቹ ይህን አስታወቁት ባወጡት መግለጫ ነው። ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ደብዳቤ ለመቀበል አሻፈረን ሲል የነበረው መስተዳድሩ በፖስታ የተላከለትን ደብዳቤ ከተቀበለ በሁዋላ ከህገመንግስቱና ከአዋጁ ቁጥር 3/1983 ተቃራኒ የሆኑ ምክንያቶችን በመደርደር ለሠላማዊ ሠልፉ ዕውቅና አልሰጠሁም ሲል ህዳር 22 ቀን ድብዳቤ መጻፉን አስታውቀዋል፡፡ “በመሠረቱ መስተዳድሩ ጊዜና ቦታ እንዲቀየር አስተያየት …
ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት 111 በመቶ የደሞዝ ጭማሪ ያደረገው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሺን፣ በአማራ እና በኦሮምያ ክልል በተከታታይ ተገቢ የሆነ የደሞዝ ማስተካካያ አላደረገም በሚል ጥያቄ ሲቀርብብት ቆይቷል። ሰሞኑን የካቢኔ አባላት ተሰብስበው የአማራ ክልል ጋዜጠኞች ከግንቦት ሰባት እና አርበኞች ግንባር እንዲሁም የኦሮምያ ክልል ጋዜጠኞች ከኦነግ ጋር የሚሰሩትና ለኢሳት መረጃ በማቅረብ በክልሎች …
ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን እንዳለው በዋና ከተማዋ ጁባ አንድ ወንድና አንድ ሴት ሲገደሉ ሁለት ሴቶች ግን በጠና ቆስለው ወደ ኢትዮጵያ ተወስደዋል። የሁለቱም ሟቾች አስከሬንም በኢትዮጵያውያን እርዳታ ወደ ኢትዮጵያ መሄዱ ታውቆል:: ሰዎቹ በምን ሁኔታ እንደተገደሉና እንደቆሰሉ እንዲሁም ጥቃቱን ያደረሱትን ወገኖች ዝርዝር ለማወቅ አልተቻለም። በደቡብ ሱዳን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በኢትዮጵያውያን የሚደረገውን ግፍና …
ኑ- ለነጻነታችንና ክብራችን ድምጻችንን በጋራ እናሰማ!
ከባርነትና ውርደት ለመላቀቅ ነውና በፍጹም አይቀርም፣ አይቀርም!
የ9ኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ ››በሚል መርህ የመጀመሪያ ዙር ዕቅዱን ለህዳር ወር አዘጋጅቶ ወደ እንቅስቃሴ ከገባ ሦስት ሣምንታትን አሳልፏል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያከናወናቸውን ተግባራትና የተጓዝንበትን መንገድ ለጉዳዩ ቀዳሚ ባለቤትና ለባለ ድርሻ አካላት ስናሳውቅ የነበረ በመሆኑ ያጋጠሙንን ችግሮች በመደጋገም ማሰልቸት አንሻም፡፡
ስለሆነም የዛሬው መግለጫችን በቀጣይ ለቀሩን ተግባራት የደረስንበትን ድምዳሜና ያወጣነው ዕቅድ በሚመለከት ይሆናል፡፡ በአጠቃላይ በእስከዛሬው እንቅስቃሴያችን ይዘን የተነሳነው ‹‹ ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› የሚለው መርህ ትክክልና ወቅታዊ፣ ያነሳናቸው ጥያቄዎችም አግባብ መሆናቸውን ያረጋገጥንበትና ገዢው ፓርቲ መድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ማለት ፍጻሜዬ ነው በሚል ከገባበት ከፍተኛ የፍርኃት ስሜትና ሥጋት ለተቃውሞ ጎራው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚያስችል ሁኔታ በሩን ለመዝጋት የተዘጋጀ መሆኑን አገር ለ23 ዓመታት በላይ ካስተዳደረ መንግስታዊ ሥርዓት የማይጠበቅ መረን የለቀቀ የውንብድና ተግባራት ያረጋገጥንበት ነው፡፡ በመሆኑም ጥያቄዎቻችንን በህገ መንግስቱና በአገሪቱ ህጎች መሠረት ለመመለስ ቀርቶ ለመስማትና ለማንበብ ፍቃደኝነቱና የኃላፊነት ስሜቱ እየተሟጠጠ በመሆኑ የአፈናና ማስፈራራት መንገድን ብቸኛ አማራጭ አድርጎታል፡፡ ይህ በመሆኑም የራሱን መንግሥታዊ መዋቅር አሰራር ሥርዓት እንኳ በአደባባይ ለመቀበል እምቢተኛ መሆኑን በአደባባይ አረጋግጧል፡፡ ባለሥልጣናቱ በግንባር ያቀረብነውን ደብዳቤ ካለመቀበል አልፈው በመንግሥታዊው ፖስታ ቤት የተላከ ደብዳቤ ያለመቀበላቸው የሚያመለክተው ይህንና የደረስንበትን የመልካም አስተዳደር አዘቅት ነው፡፡
በተቃራኒው አበረታችና መልካም ዜናም አለ፡፡ ይህም ይህን የአፈናና ማስፈራትት አካሄድ አንቀበልም ያሉ ለነጻነታቸውና ክብራቸው፣የራሳቸው ብቻ ሣይሆን የመንግሥት መዋቅሮችና ባለሥልጣናትም ነጻነት መረጋገጥ አለበት ብለው የቱንም መስዋዕትነት ለመክፈል በቁርጠኝነት የተዘጋጁ በትብብሩ የታቀፉ ፓርቲዎች፣ አመራርና አባላት መኖራቸውና በትግሉ ለመቀጠል መወሰናቸው ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ትብብሩ ለመጀመሪያ ዙር ዕቅዱ ማጠቃለያ የህዳር 27/28 የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ደብዳቤ አመራሩ በግንባር ቢያቀርቡም አሻፈረኝ አንቀበልም ያሉት አሰራርና ባለሥልጣናት ከፖስታ ቤት እንዲቀበሉ ተደርጓል፡፡ለዚሁ ደብዳቤ መስተዳድሩ ከህገመንግስቱና ከአዋጁ (ቁጥር 3/1983) ተቃራኒ የሆኑ ምክንያቶችን በመደርደር ለሠላማዊ ሠልፉ ዕውቅና አልሰጠሁም ሲል በዛሬው ቀን (22/03/07) መልስ አድርሶናል፡፡ በመሠረቱ መስተዳድሩ ጊዜና ቦታ እንዲቀየር አስተያየት ከማቅረብ ያለፈ ዕውቅና የመንፈግ መብት የሌለው በመሆኑ ትብብሩ የደብዳቤውን መልዕክት ያልተቀበለ መሆኑንና ሠልፉም በታቀደው ጊዜና ቦታ እንደሚደረግ ወስኖ የመልስ ደብዳቤ አስገብቷል፡፡ በመሆኑም ለተግባራዊነቱ ዝግጅቱን በሙሉ አቅም ጀምሯል፤ ለዚህም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከአገር ውስጥና ከውጪ አጋርነታቸውን ገልጸዋል፤ አበረታተውናል፡፡ ይህም የያዝነው የትብብር የጋራ ዓላማችን ተቀባይነት፤ የኅብረትና አንድነትን ዋጋ አመላካች፣ ለማይቀረው ሠላማዊ ትግላችን ሥንቅ ነውና በታላቅ አክብሮት ተቀብለነዋል፡፡
ስለሆነም ይህ መግለጫ ትግላችን ነጻነታችንና ክብራችን የማስመለስ መንገዱም ፍጹም ሠላማዊ፣ ህጋዊና ህገ- መንግሥታዊ ስለሆነ የህዳር 27/28 ሠላማዊ ሰልፍ የማይቀርና የማይቀርበት መሆኑን ለመግለጽና ነጻነትና ክብርን ወዳድ ኢትዮጵዊያንና የፖለቲካ ኃይሎች በሙሉ ለዚህ ታሪካዊ ዕለትና ሠላማዊ ትግል ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ነጻነታችንና ክብራችን ለማስመለስ ዋጋ ለመክፈል እንዘጋጅ፣ ያለመስዋዕትነት ድል የለምና!!
የፕሮግራም መግለጫ
ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡
የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡
ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና
ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና
ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ
ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት
ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)
ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና
ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡
ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡
የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡
ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስና የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን አንድነት ፓትሪያርክ በርጦሎሜዎስ ቀዳማዊ ፣ ክርስቲያኖች ከመካከለኛው ምሥራቅ እንዲጠፉ የመላው ዓለም ፍላጎት አይደለም አሉ።
በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ቸልሲ ፈጣን ግስጋሴው ገታ ብሏል፥ የአምናው ባለዋንጫ ማንቸስተር ሲቲ እግር በእግር መከተሉን አላቋረጠም። በጀርመን ቡንደስ ሊጋ ኃያሉ ባየር ሙንሽን እንደልማዱ ሊጋው ከመጠናቀቁ ቀደም ብሎ ዋንጫውን ለመጨበጥ ተቃርቧል፤ የቀድሞው ብርቱ ተፎካካሪ ቦሩስያ ዶርትሙንድ አቅም አንሶት በወራጅ ቃጣናው ጠርዝ ላይ እያጣጣረ ነው።
ኢትዮጵያም -በአብዮትና ፀረ-አብዮት ግብግብ ትናወጥ ነበር።የሶማሊያ ጦርም ገሚስ ኢትዮጵያን ለመያዝ ምሥራቅና ደቡባዊ ኢትዮጵያን ተቆጣጠረ።የአብዮቱ ትርምስ፤ የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት፤ የዩናይትድ ስቴት መንግሥት ፀረ-ኢትዮጵያ አቋም መያዝ፤ ለቤገን ዕቅድና ቃላቸዉን ገቢር ለማድረግ ጥሩ አጋጣሚ ነበር።
የገዳዩን የኤቦላ ተሐዋሲ የመዛመት ዜናን ተከትሎ ሰናይ ዜናን መሰማቱ ያልተለመደ ነበር። በቅርቡ ግን ተሐዋሲዉን ለመከላከል ያስችል ይሆናል ተብሎ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበት የክትባት መድሃኒት፤ ሰዎች ላይ ተሞክሮ ተስፋ ሰጭ ዉጤትን አስገኝቶአል። ። በሌላ በኩል ክትባቱ አሉታዊ ገፆች እንዳሉትም ነዉ የተነገረዉ።
የጀርመን ዓለም አቀፉ የትብብር ድርጅት በምህፃሩ GiZ በአዲስ አበባ 11 000 የቁጠባ ቤቶች ያሉት 700 የቁጠባ ህንፃዎች ሰርቶ ጨርሶ ማስረከቡን ይፋ አድርጓል።
ምንም እንኳን በግብፅ በኩል አድርገው በህገ ወጥ መንገድ ወደ እስራኤል የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር፣ ባለው ጥብቅ ቁጥጥር የተነሳ ቢቀንስም፣ አሁን ድረስ በእስራኤል 48 000 የአፍሪቃ ስደተኞች እንደሚገኙ ይታመናል።
በአለፈው ዓመት በ22.11. 2013 የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ፣ በእስራኤል ለሚገኘው የወያኔ ሚዲያ ለ“IETV” ያመጣው የክስ መዘዝ፣ቀጥሎ ለውሳኔ መቀጠሩ የክሊክ ሃበሻ ዘገባ አመልክቷል::የዛሬ ዓመት ኖቨምበር 22 ቀን 2013 ነበር፤ ቴል አቪቭ ከሚገኘው ኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽ/ቤት ፊት ለፊት ኢትዮይሁዳያንና ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ ዓረቢያ በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን ግፍና መከራ፣ ሞተና የሴቶች መደፈር፣ ሰቃይና ሰቆቃ የወያኔ/ኅውሃት ገዥውና እምባገነኑ መንግሥት ችላ ብሎታል ብሎ በመቆርቆርና በመበሳጨት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደው እንደነበር የሚታወስ ነው። http://www.clickhabesh.com/?p=105083

ከሰላማዊ ሰልፈኞቹ መካከል አብዛኛዎቹ በልጅነት እድሜ የመጡና ከዚህ የተወለዱ ወጣት የኢተዮጵያ ይሁዳውያን የተሳትፉበት ከመሆኑም ባሻገር፤በዚህ መልኩ በኢምባሲው ጽ/ቤት ፊት ለፊት ወጣት ኢትዮ ይሁዳውያንን አልገብግቦ እንደዚህ ዓይነት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በእሥራኤል ሲካሄድ በዓይነቱ የመጀምሪያ ነበር ቢባል ማገነን አይሆንም። ምክንያቱም ቴል አቪቭ የሚገኘው አምባሳደር ኽላዊ ዮሴፍ የወጣት ኢትዮ ይሁዳውያን በሰልፉ መሳተፋቸው አስደንግጦት፣ እዚሁ እሥራኤል በሚገኘው የአማረኛ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ቀርቦ ከተናገረው፣ በእሥራኤል መንግሥት ሙሉ በሙሉ በሚተዳደረ የአማረኛው ሬዲዮ ጣቢያ የተናገርውን አዳምጡ የሬዲዮውን ቃለ ምልልስ አዳምጡና ንባቡን ቀጥሉ፦
ልብ በሉ፦ በዲሞክራሲና በነጻው ሚዲያ ሃገረ እሥራኤል ውስጥ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ “የአንድን ወገን ብቻ አቅርቦ” በተደጋጋሚ ማለትም አምባሳደሩንና ደጋፊዎቹን ቃለመጠይቅ ሲያደርግ፣ ቴሌቪዥኑም ሆን ሬዲዮው ከሙያው ህግ ውጭ በመሆን አንድም ቀን የተቃዋሚውን ወገን በጋራም ሆነ በተናጠል ቃለ መጠይቅ አካሂዶ አያውቅም። ህዝቡ በነጻውሚዲያ ሃገር የሁለቱንም ሃሳብ ሳያዳምጥ አንድ ወገን ብቻ ይዞ እንዲጓዝ መደረጉ ያበሳጫቸው ከዚህ ህዝብ አብራክ የወጡ በተናጠል ትግል የጋራ ትግል በማለት ተደራጅተው፣ “መሬት
ኢትዮ እሥራኤል የሰብዓዊና ነጻነት ድምጽ ምክር ቤት” ብለው ያቋቋሙት የመጅመሪያ ትግላቸው ማተኰር ያለበት በዲሞክራሲና በነጻ ሚዲያ ሃገር የህዝብ ድምጽ የታፈነውን መብተማስጠበቅ መሆኑን እጠቁማለሁ። ይህ የአምባሳደሩ መግለጫ አንዳንድ የዋህ አዛውንቶችን የኢትዮጵያን ህዝብ እያስራበ በሚያስመጣው “ጤፍ” በማታለል ለማሳመን መሞከሩ ነበር። ምክንያቱም የሚያስበው እሥራኤል የሚገኘው ኢትዮ ቤተ እሥራኤላውያን እኛ እንዳዘዝነው ነው ብሎ ያስብ ስለነበር ሳያስበው የደረሰበት የውርደት ካባ የተከናነበበት በመሆኑ ለማስተባበል መሞከሩ ነበር።ስለጤፍ ከአንድ ስብሰባ ላይ የተናገረውን ተመልከቱ፦ይህን ያህል ለመንደርደሪያ ካልኩ ዘንዳ፣ ወደ ዋናው ሃሳብ ልንደርደር።
ምንም እንኳ ዓርብ ቀን ድምጻውያን እንድሚሉት “….ዓርብ ዓርብ ይሸበራል እየሩሳሌም!” ያለ ምክንያት አይደለም። ዓርብ ህዝበ እሥራኤላውያን ለ 26 ስዓታት ሰንበትን የሚቀበሉበት ቀን ስለሆነ፤ ሁሉም ነገር ከመዘጋጋቱ በፊት ማልደው በመገዛዛት ሲያበስሉና ቤታቸውን ሁሉ ሲያጸዱ ከዋሉ በኋላ ሁሉም ቤተሰብ ሰውነቱን ታጥቦ ጽዓዳ በመልበስ ወደ ጸሎት ቤት ሄደው ሲመለሱ፣ ሰንበት ከመግባቱ በፊት ያበሳስሥሰሉትን፣ መላው ቤተሰብ በአንድ የጠረጴ ዙሪያ በመቀመጥ እየበሉና ወይናቸውን እየተጡ አምላካቸውን የሚያመሰግኑብት ቀን ሲሆን፤ የህዝብ ማመላለሻዎች፤ ሱቆች፤ መ/ቤቶች፤ ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ማንኛውም በሙሉ ዓርብ ከስዓት በኋላ ከቀኑ 14፡00 ማለት 02፡00ስዓት (በኢትዮጵያ ስዓት አቆጣጠር ከቀኑ 08፡00 መሆኑ ነው) ይዘጋል።
ሆኖም ግን በዚህ ቀን የቤተሰብ ኃላፊነት ያላቸው ሌሎች በእድሜ ትንሽ ከፍ ያሉ ቢኖሩም፤ አንዲት ወጣት ቤተ እሥራኤል ከገጠሪቱ ኢትዮጵያወደ እሥራኤል በ8 ዓመት ዕድሜዋ፤ ኅውሃት አዲስ አበባን ከመቆጣጠሩ ከሁለት ቀን በፊት “ዘመቻ ሰሎሞን” (Operation Solomon) በተባለውየመጣች፤ አሁን የ 31 ዓመት ወጣት፤ በፌስ ቡክ ያተላለፈውን በሳዑዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን መከራና ሥቃይ ችግርና ስቆቃ ተመልክታ “ለወገን ደራሽ ወገን ነው!” ብላ፤ ልጆቿን ዛሬ የ7 እና የየ5 ዓመት ዕድሜ፡(ባለፈው ዓመት የ6 እና የ4 ዓመት) ከወላጆቿ አስጠግታ፤ ከምትኖርበት ከተማከተወሰኑ ጓደኞቿ ጋር በባቡር ተሳፍራ በስዓቱ ከተባለው ቦታ ቴል አቪቭ በመድረስ ከሌሎች ከሰላማዊ ሰልፈኛው ጋር በመሆን፤ በሳዑዲ ዓረብያ ጭካኔ የተጐዱትንና የሞቱትን ኢትዮጵያኖች ፎቶ በማንገብ፤ የኢትዮጵያው መንግሥት ለዜጐቹ ግድ ሳይሰጠው ዝም ማለቱ በጣም ስለአንገበገባት፣ የዲሞክራሲ መብቷን በመጠቀም በጉዳት ላይ ላሉት ወገኖቿ ስትጮህላቸውና ድምጿን ስታሰማ ዋለች፡፡
ታዲያ ከሰላማዊ ሰልፉ አንድ ሳምንት በኋላ (በሳምንቱ ዓርብ) “IETV” በተባለው ቴሌቪዥን ይህችን ወጣት ያልተናገረችወን በኤዲቲንግ የተቀነባበረ ፕሮግራም ቀረበ። (የኢዲቲንግ ዕውቀቱ ወይም ሙያው ያለው አቆራረጡንና አቀጣጠሉን ይረዳል)ይህን ፓርት/ክፍል ተመልከቱ፤ፊልሙ ተጀምሮ እስኪያልቅ “ሰባት” (7 ጊዜ)ይህ ቃል በፕሮግራሙ ተደጋግሟል። ለምን? ተደጋገመ የሚለውን የፍርዱ ሁኔታ ሲያበቃ ከህግ ጠበቃዋና ከወጣቷ ጋር ፈቃደኛ ከሆኑ በቃለ መጠየቅ ከአንደበታቸው እንሰማለን የሚል እምነት አለኝ። እንደ ባለመያ እስኪ የራሴን አስተያየት ጠቆም አድርጌ ልለፍ፤
1ኛ) እንደዚህ ዓይነት ነገር ልጅቱ ከተናገረች፣ መሆን ያለበት ሙሉ ንግግሯን ከነመልኳ ማቅረብግዴታ ነው፤ ከዚያ በኋላ ቋንቋ ልማይረዱ ትክክለኛ ትርጉሙን ማቅረብ የሙያ ግዴታ ነው፣
2ኛ) በጋዜጠኛ ህግናደንብ መሰረት “Sling” ወይም “የመንገድ ቋንቋ” ብሎ ነገር የለም። ለህዝብ መቅረብ ያለበት “እውነተኛና ሃቅ ብቻ እና ሃቁ ብቻ ነው”፤ ምክንያቱምሚዲያ የአንድ ሃገር ህዝብ ጠበቃ ማለት ነው፣ወደ ታሪኩ ልመልሳቸሁ፣ ይህን የተላለፈ ፕሮግራም ያዩ ዘመድ አዝማድና ቤተሰቦቿ ”እንዴት ፋሲል ይገደል ትያለሽ?” “ለምን ልጆችሽን ዝም ብለሽ አታሳድጊም?” እያሉ
ሲያዋክቧት በመደናገጥ በጣም ተረብሻ ወዲያውኑ የሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊ የነበሩትን ስታማክር፤ በመጀመሪያ እንድትረጋጋ ከመከሯት በኋላ፡
ፕሮግራሙን በኢንተርኔት በማየት በፍጹም ቃላት የተለቃቀመበት የተቀጣጠለ ስለሆነ፤ ቴሌቪዥኑንና አቅራቢውን “በስም ማጥፋት” የሚያስወነጅል እንደሆነ ገለጹላት። ይህች የ31 ዓመት ወጣት የኢኮኖሚ ችግር እንዳለባትና ልጆችዋን ብቻዋን እንደምታሳድግ ስታማክር፤ የተወሰኑ ከተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉ የተሳተፉ በመመካከር ወደ5 የሚሆኑ ገንዘብ በማዋጣት ከፍለውላት“ፒኒ ጌልዓድ” የተባለ የሀግ ጠበቃ እንድትይዝ ሆነ።
በተላለፈው ፕሮግራም ላይ እንዳያችሁት፦የሀግ ጠበቃዋ በህጉ መሰረት ክሱን ጀመረ፣ “IETV” ወዲያውኑ ከኢንተርኔትና ከፌስ ቡክ ላይ ሙሉ ፕሮግራሙን አወረደው፤ ነገር ግን እንደዚህ ዓይነት ፕሮግራሞችን እያወረደ የሚያስቀምጥ የተጠናከረ የወጣቶች ቡድን ቀድሞ ቀድቶ አስቀምጦታል።ክሱ ተጀመረ ብያለሁ፤ እናስ ማለታችሁ አይቀርም፤ እናማ የቴል አቪቭ ወረዳ ፍ/ቤት ዳኛ የከሳሽና ተከሳሽን የህግ ጠበቆችን ቃል ከሰማ በኋላ፤ እንደ እሥራኤል ህግና ደንብ መሰረት የሚቻል ከሆነ ሁለቱ የከሳሽ የህግ ጠበቃና የተከሳሽ የሀግ ጠበቃ በጋራ ተስማምተው እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ገለልተኛ ለሆነ የሀግ ጠበቃ ሁኔታውን በመካከላቸው ሁና ከህግ አንጻር እንድታሸማግል “Court Mediators” ዘንድ ተላኩ። እዚያ መስማማት ባለመቻላቸውም በአለፈው ኦጐስት/ነሃሴ 2014 ወረዳው ፍ/ቤት ቀርብው ነበር።
ታዲያማ የተከሳሽ ጠበቃ ለዳኛው በ”ይፋ” ከሳሾችና ተከሳሾች በተገኙበት(በ”ይፋ” የሚለው ይሰመርበት) በመከራከሪያነት የተጠቀመው (የ“IETV” የህግ ጠበቃ በሂብሪው የተናገረውን ቃል በሂብሪውና በእንግሊዝኛ ላስቀምጠው) በሂብሩ የተጠቀመው ቃል “להבהיר” (Apologize) ከማለቱም በተጨማሪ፤ ከሳሿ ፈቃደኛ ከሆነች በዚያው ቃለ መጠይቅ ልናደርግላት እንችላለን ሲል የመከላከያ መልሱን አቅርቧል። የወጣቷ የህግ ጠበቃ ግን በወጣቷ ማህበራዊ ህይዎትም ሆነ የሥነ ልቦና ላይ ከፍተኛ መረበሽና አለመረጋጋትን ስላስከተለባት፤ ሆን ተብሎ በወጣቷ ላይ የተክናወነ የስም ማጥፋት ዘመቻ ስለተካሄደ፤ ለድርጊቱ “IETV” ይቅርታ ከመጠየቅም ባሻገር የሥነ ልቦና ጉዳት ካሳና የህግ ጠበቃዋን ወጭ ሊከፍል ይገባዋል ሲል መልስ ሰጥቷል።
ዳኛውም ወጣቷን ተከሳሾቹ በሚሉት ትስማማ አትስማማ እንደሆን ተጠይቃ፤ በ“IETV” ምን ዓይነት ቃለ ምልልስ እንደማትሰጥና፣ ይህ ቴሌዥን በህይወቴ ላይ ከፍተኛ የሆነ መጥፎ አሻራ ያጣለባት መሆኑንና፤ የተለያዩ ዛቻና ማስፈራሪያዎች ከተለያዩ ክፍሎች የደረሳት መሆኑንም ለፍ/ቤቱ አስረድታለች። ፍ/ቤቱም ለ19.01.2015 ቀጥሯል። ችሎቱ ክፍት ስለሆነ ማንም ሰው የዲሞክራሲ መብቱን ተጠቅሞ መገኘት ይችላል። ቦታው ቴል አቪቭ ወረዳ ፍ/ቤት ነው፤ “ቫይጽማን ጎዳና 1 ቴል አቪቭ“ ትክክለኛውን ስዓትና ቀን ቀኑ ሲቃረብ እናሳውቃለን። ለወገን ደራሽ ወገን ነው ብላ ድምጿን ለማሰማት ወጥታ ሥነ ልቦናዊ ድቀት ለደረሰባት ወጣት እህታችን፤ ፍትህና ዲሞክራሲ ያለበት ሃገር ያለሽ በመሆንሽ ሁላችንም መልካሙን ሁሉ እንመኝልሻለን!!
ሐና መከተ – ጋዜጠኛ እሥራኤል
የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ህዳር 27 እና 28/2007 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ሊያደርገው ላቀደው የአዳር ሰላማዊ ሰልፍ አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግለት፣ ህዳር 17 ቀን 2007 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ መጠየቁ የሚታወስ ቢሆንም አስተዳደሩ በቁጥር አ.አ/ከፅ/10/30.4/55 ህዳር 19 ቀን 2007 ዓ.ም በፃፈው የመልስ ደብዳቤ ለሰላማዊ ሰልፉ እውቅና አለመስጠቱን አስታውቋል፡፡
ትብብሩ ለሰልፉ የመረጠው ቦታ መስቀል አደባባይ ሲሆን፣ አስተዳደሩ በበኩሉ የ24 ሰዓቱን ሰልፍ ላለማወቁ ምክንያት ነው ያለውን ሲያስቀምጥ፣ ‹‹የተጠየቀው ቦታ በልማት ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅና ትላልቅ የመንግስት ተቋማት እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ያሉበት ስለሆን ጥያቄውን ተቀብለን ለማስተናገድ የምንቸገር መሆኑን እየገለጽን፣ የአደባባይ ስብሰባውም ሆነ ሰላማዊ ሰልፉ እውቅና ያልተሰጠው መሆኑን እናስታውቃለን›› በማለት አስፍሯል፡፡
የትብብሩን ሰልፍ እያስተባበሩ ያሉት ፓርቲዎች አመራሮች ዛሬ ለአስተዳደሩ በጻፉት ደብዳቤ እንደጠቀሱት ደግሞ፣ የሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 3/1983 አንቀፅ 6 ንዑስ አንቀፅ 2 “የከተማው ወይም የአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት በዚህ አዋጅ አንቀፅ 6 ንዑስ አንቀፅ 1 የተመለከቱትን ሁኔታዎች በማገናዘብ ሰላማዊ ሰልፍ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባው በሌላ ጊዜ ወይም በሌላ ሥፍራ ቢደረግ ይሻላል የሚል አስተያየት ካለው ምክንያቱን በመግለፅ ይህንኑ ጥያቄው በደረሰው በ12 ሰዓት ውስጥ በጽሁፍ ለአዘጋጁ የማሳወቅ ኃላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም የከተማው ወይም የአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት ሰላማዊ ሰልፍ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባው ምን ጊዜም ወይም በየትኛውም ቦታ ሊካሄድ አይችልም ማለት አይችልም” በማለት አስተዳደሩ እውቅና የመንፈግ ስልጣን እንደሌለው ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም፡-
‹‹1ኛ. እውቅና እንዲሰጥ የተጠየቀ ማንኛውም አካል ከላይ የተደነገገውን በማገናዘብ ለሌላ ጊዜና በሌላ ቦታ እንዲደረግ ሃሳብ ከማቅረብ ውጭ ሰላማዊ ሰልፉ ምን ጊዜም ወይም በየትኛውም ቦታ ሊካሄድ አይችልም ለማለት ለመስሪያ ቤታችሁ ስልጣን ያልተሰጠ በመሆኑ፤
2ኛ. ሰላማዊ ሰልፉና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ የሚከናወኑት በመሰረታዊነት ለትላልቅ የመንግስትና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ለማሳወቅ በመሆኑ በእነዚህ አካባቢ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ማድረግ በአዋጁ ያልተከለከለ በመሆኑ፤
ለጥያቄያችን የተሰጠን መልስ ከምክንያታዊነትና ህጋዊነት ውጭ ሰልፉ እንዳይካሄድ ለመከልከል ስለሆነ እንዲህ ዓይነቱን ኢ-ህጋዊ የሆነ ውሳኔና አሰራር ፈፅሞ የማንቀበል በመሆኑ አስቀድመን ባሳወቅነው መሰረት ሰላማዊ ሰልፉን በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ የምናካሂድ መሆኑን እያሳወቅን በጽ/ቤታችሁ በኩል አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግልን በድጋሚ እናስታውቃለን›› ብሏል ትብብሩ ዛሬ ለአስተዳደሩ በጻፈው ደብዳቤ፡፡
ሰዎች በማንኛውም መንገድ ሸብረክ ሸብረክ የሚሉ ከሆነ መርህ አልባ መሆናቸውን ከማሳየት ውጭ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡ ባለፈው ሳምነት ፍኖተ ነፃነት ላይ ወጣቱ ፀሃፊ ኢዮኤል ፍስሃ ዳምጤ ለምን እንደምንፈራ ቁልጭ አድርጎ አሳይቶን ነበር፡፡ የገዢዎቻችን በትር የበረታብን በእነርሱ ጥንካሬ ሳይሆን ከፍርሃት በመጣ ዝምታችን እንደሆነ አስምሮበታል፡፡ መፍትሔውም ከፍርሃት መላቀቅና ዝምታውን ማፍረስ ነው፡፡ በዛሬው ፅሁፌ ማንሳት የፈለኩት ደግሞ ለምን […]
በእርግጥም “ እንዲህ እንደዋዛ ሲጠሩት ቀላል ይመስላል ቃሉ፤ እረ ሁላችሁም፤ አገር አገር በሉ፤ አገር አገር በሉ”። የምትለዋ ስንኝ በጋራ ስንላት ንዝረቷ ለጉድ ነበር። ተመኩሮዬን ያኔ ቆርጦ ሰልፉ ላይ የነበረ በቅርብ ፅፎ አስታወሰኝ። “ተርቲብ” የምትለዋን ቃል ትርጉም እስካሁን ስለማላውቅ ሙሉ መልክቱን በእርግጥ በትክክል አልረዳውም። ያም ሆኖ “ተርቲብ፤ አላህ ዋአክበር”። በጋራ ስትሉት ሲያምር። ምጥን ያለና ጉልበታም ነበር። […]
የፕሮግራም መግለጫ
ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡
የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡
ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና
ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና
ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ
ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት
ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)
ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና
ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡
ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡
የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡
ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡
1- ሁለቱም በፈጣሪ አያምኑም ( የራሴ የሚሉት እምነት የላቸውም)
2- የጦር አዛዦቻቸው::ሂትለር በራሱ ግዜ ሮሚዮን ማርሻል አድርጎታል –መለስ ሳሞራን < ጀነራል> አድርጎታል
3-ሂትለር ሁለት ልጅ ነበረው::መለስም ሁለት ልጆች አሉት
4-ሁለቱም በጅምላ ህዝቦችን ጨርሰዋል (የዘር ማጥፋት ፈጽመዋል)
5-ሁለቱም insomnia ይሰቃዩ ነበር :; ( የመተኛት ችግር ከተኙም ቶሎ አለመንቃት)
6-ሁለቱም የሶሻሊዝም issue ነበራቸው:;ለዚህም ማሌሊትን ልብ ይልዋል
7- በዘር እና በጎሳ ላይ የተመሰረተ ፓርቲ በመፍጠርም ይታወቃሉ ::
8-ሂትለር ታላቅዋን ጀርመን ለመመስረት እቅድ የነበረው ሲሆን መለስ ደግሞ ታላቅዋን ትግራይን ..
9-E -ዲሞክራሲ ናቸው
10-ራሳቸውን በራሳቸው የፓርቲ እና የአገር መሪ አድርገው ሾመዋል Dagem Ahunem
Eyasped Tesfaye…….(የግል ዕይታ)
‹‹……ሪቮሉሽን የአዳራሽ ዙሪያ አመፅ አይደለም፤ የሰፊው ህዝብ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ሰፊው ህዝብ ካልተሳተፈበት፣ ካልደገፈው፣ አይሆንም፤ አይፀናምም፡፡ የጥቂቶች አመፅ በሌሎች ጥቂቶች አመፅ ይገለበጣል፡፡ መሰረታዊ ለውጥ፣ በሰፊው ህዝብና በጨቋኝ መደቦች መካከል የሚካሄደው የትግል ፍሬ ነው፡፡….››ዴሞክራሲያ ቅፅ1 ቁ15
የኢትዮጲያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል በ1993 ያሳተመው አማርኛ መዝገበ ቃላት አብዮት የሚለውን ቃል ‹‹በአንድ ነገር ክስተት ወይም ሂደት ውስጥ ያሉ ቅራኔዎች ተካረው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርሱ የሚፈጠር መሰረታዊ ለውጥ፤ አዲስ ከፍተኛና የተሻለ ነገር፤ ክስተትና ሂደት ወይም አስተሳሰብና እውቀት የሚከሰትበት፡፡›› የሚል ትርጓሜ ይሰጠዋል፡፡
አብዮት በተለያየ የታሪክ ወቅት እንዲሁም በተለያየ ቦታ ተከስቷል፣ እየተከሰተ ነው፤ ወደፊትም ይከሰታል፡፡ ከፈረንሳይ አብዮት እስከ ሩሲያው አቢዮት፤ ከላቲን አሜሪካ ሀገሮች እስከ ሩቅ ምስራቅ እስያ ብሎም እስከ አረቡ አብዮት፤ የአብዮት ንፋስ ያልነፈሰበት የአለማችን ክፍል የለም፡፡ በተለያዩ ቦታዎች የተካሄዱ አብዮቶች እንደወቅቱ እና እንደቦታው የራሳቸው የሆኑ መለያዎች ያሏቸው ይሁን እንጂ ሁሉም የሚጋሯቸው የወል የሆኑ ባህርያትም አሏቸው፡፡ ይኸውም ሁሉም አብዮቶች በጭቆና ማህፀን ውስጥ ተፀንሰው መወለዳቸው ነው፡፡
አብዮቶች ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ አሊያም ኢኮኖሚያዊ መነሾ ምክንያቶች ሊኖሯቸው ይችላል፡፡ ለምሳሌ ታሪካዊውን የፈረንሳይ አብዮት ያየን እንደሆነ ሶስቱም መነሾ ምክንያቶች እንደነበሩት እንረዳለን፡፡ የፈረንሳይ ህዝብ በፈላጭ ቆራጭ ንጉሳዊ አስተዳደር ስር ሆኖ መብቶቹን መገፈፉ የአብዮቱ ፖለቲካዊ መነሾ ሲሆን፤ በፈረንሳይ ህዝብ መካከል የነበረው የመደብ ልዩነት በተለይም አብዛኛው የፈረንሳይ የህብረተሰብ ክፍል በድህነት የሚማቅቅበት እና መብቱን የተነፈገበት ሶተኛው መደብ ውስጥ መካተቱ የአብዮቱ ማህበራዊ መነሾ ሆኗል፡፡ እንዲሁም ደግሞ በወቅቱ ፈረንሳይ በከፍተኛ የኢኮኖሚ ድቀት ውስጥ መገኘቷ እና በዜጎች ላይም ያለው የግብር ጫና ከፍተኛ መሆኑ የአብዮቱ ኢኮኖሚያዊ መነሾ ሆኗል፡፡
አብዮቶች አብዛኛውን ጊዜ በገዢው መደብ በኩል ሳይጠበቅ የሚከሰት ክስተት ነው፡፡ ለዚህም ነው የሩቁ የፈረንሳይ አብዮትም ሆነ የቅርብ ግዜው የአረቡ አለም አብዮት አለምን ያስደነቀው፡፡ አንዳንድ አብዮቶችን ትልልቅ የስለላ ተቋማት(ሲ.አይ.ኤ፤ ኬጂቢ) ሳይቀር ያልጠበቁት ክስተት እንደነበር ታሪክ ያስገነዝበናል(መሀመድ ሬዛን ያስወገደውን የኢራኑን አብዮት ልብ ይሏል)፡፡ ይህ የሚሆንበትን ምክንያት ቲሙር ኩራን የተሰኘው ፀሀፊ ‹‹sparks and praire fires: a theory of unanticipated political revolution›› በተሰኘው ፅሁፉ ላይ በአለማችን ላይ የተከሰቱትን ሶስት ዋና ዋና አብዮቶችን እንደምሳሌ በማንሳት ህዝብ የተቃውሞው ወገን እስኪጠናከር ድረስ በገዢው ወገን ላይ ያለውን ጥላቻ በውስጡ ደብቆ መያዙ አብዛኛውን ግዜ ገዚዎችን እንዲዘናጉ እንደሚያደርጋቸው ገልፆ አብዮቱ አንድ ግዜ ከፈነዳ በኋላ ለማስቆም አስቸጋሪ የሚያደርገውም በህዝብ ዘንድ ስር የሰደደ እና የቆየ ጥላች እና ቅራኔ መኖሩ እንደሆነ ያስረዳል፡፡
ለአብዮት መነሳት ምክንያቱ ከላይ የዘረዘርናቸው ቅራኔዎች(ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ) ቢሆኑም ከእነዚህ ሁሉ ቀድሞ የሚመጣው ግን የህብረተሰቡ የንቃተ ህሊና(enlightenment) ጉዳይ ነው፡፡ በላቲን አሜሪካ የተካሄዱት አብዮቶች ላይ ጥናት ያካሄዱት እንደ ዴቪድ ክሎስ ያሉ ምሁራኖች ለአብዮቱ መነሳት ዋና ምክንያት አድርገው የሚያቀርቡት የህብረተሰቡ ንቃተ ህሊና መዳበሩን እና በሌሎች ሀገራት የተካሄዱትን አብዮቶች ከራሱ ሀገር ነባራዊ ሁኔታ ጋር ማስተያየት እና ማገናዘብ መቻሉ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡
በሀገራችን በኢትዮጲያም ተከስቶ የነበረውን የ66ቱን አብዮት ያየን እንደሆነ በአለም ዙሪያ የነበረው ሁኔታ በወቅቱ የነበሩትን ወጣቶች ላይ ተፅእኖ ማሳደር መቻሉ እና የወጣቱ ንቃተ ህሊና የዳበረ መሆኑ ከነበረው ጭቆና ባሻገር ለአብዮቱ መነሳት አበይት ምክንያት ነበር፡፡
እነዚህን ከላይ የዘረዘርናቸውን የአብዮት መነሾዎች ይዘን የሀገራችን ነባራዊ ሁናቴ ካጤንን በኢኮኖሚው በፖለቲካውም ሆነ በማህበራዊው ዘርፍ ያለው ከፍተኛ የሆነ ምስቅልቅል እና ብሶት ለአብዮቱ መነሳት በቂ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ነገር ግን መረጃ የማግኘት መብቱን የተነፈገው ሰፊው የህብረተሰብ ክፍል መብቱን በማስከበር ዙሪያ ላይ ያለው የንቃተ ህሊና መዳበር በጥያቄ ውስጥ ያለ ጉዳይ ይመስለኛል፡፡
የቡርኪና ፋሶው የአብዮት ንፋስ በፍጥነት ወደ ቶጎ እና ጋቦን ተዛምቶ አምባገነን መንግስታትን ሲያንቀጠቅጥ ይህንን ጀብዱ የሰማው የኢትዮጲያ ህዝብ ምን ያህል ነው; ሰምቶስ ወስጡን የኮረኮረው እና መንፈሳዊ ቅናት ያደረበት ስንቱ ነው; የሚለው ጉዳይ ያሳስበኛል፡፡
በእኛ ሀገር አብዮት እንዲነሳ ካስፈለገ አብዮቱ መሪ ያሻዋል፡፡ በቡርኪና ፋሶም ሆነ አሁን በቶጎ እና በጋቦን የተነሳው ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ናቸው እየመሩት ያሉት፡፡ በእኛም ሀገር ባለው ተጨባጭ ሁናቴ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተባባሪነት ውጪ በአሁኑ ሰዓት በራሱ የሚፈነዳ አብዮት ይኖራል ብሎ መገመት አስቸጋሪ ነው፡፡ ነገር ግን ተቃዋሚዎች
1ኛ፡- ለህዝብ ወቅታዊ መረጃዎችን በማቀበል እና በመተንተን የህዝብን ንቃተ ህሊና የሚያሳድጉበትን መንገድ መቀየስ ይኖርባቸዋል፡፡
2ኛ፡- በህዝብ ዘንድ ያላቸውን ቅቡልነት በማሳደግ የሚሞትላቸው ድርጅቶች መሆናቸውን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
በኢትዮጵያ የሚፈጸመውን ወሲባዊ ጥቃት አሳሳቢ ነው ተባለ። በ17 ዓመቷ ታዳጊ ሐና ላላንጎ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሞባት ህይወቷ ካለፈ በኋላ ድርጊቱ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል።

ሠማያዊ ፓርቲ እና ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች የአንድነት መድረክ በመፍጠር ሰላማዊ ሰልፍ ከህዳር 27/2007 ዓ.ም እስከ ህዳር 28/2007 ዓ/ም ለማድረግ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልፀው የሐገሪቱ ህዝብ በቦታው በመገኘት ድምፁን እንዲያሠማ ባሳወቁት መሠረት የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሠማ ጊዜያዊ ኮሚቴ እና የማህበሩ አባላት በሠላማዊ ሠልፉ ላይ ከሌላው የሐገራችን ህዝብ ጋር በመሆን ድምፃችንን እንደምናሠማ እየገለፅን ለሠላማዊ ሠልፉ መሣካት የበኩላችንን ደርሻም ለመወጣት ዝግጁ መሆናችንን ስንገልጽ በዚህ በጨለማ ዘመን ኃላፊነት ወስደው ይህንን ታላቅ ሠለማዊ ሠልፍ ላዘጋጁት የሠለማዊ ሠልፉ አዘጋጆች ምስጋናችንን በማቅረብ ነው፡፡
እንዳለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያን እያስተዳደሩ ሳይሆን እየገዙ ያሉት ብዙሀኑ ባለስልጣናት ከትምህርት አለም እርቀው ወደ ትግል የገቡ እና አሁንም ቢሆን በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እና የተሻለ ንቃተ ህሊና ያለው ሰው እንዳይፈጠር ትግል ላይ ናቸው በተለይ ለመምህራንና ባጠቃላይ ለትምህርት ስርአቱ ያላቸው ጥላቻ ላቅ ያለ ነው ይህንን እንኳን ስላልተማሩ ነው ብለን እንዳናልፈው የስርአቱ አመራሮች እና አጃቢዎች አለማወቃቸውንም ሊደብቁ ፍቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ሟቹ መለስ ዜናዊ በህይወት ያለው ተፈራ ዋልዋ መምህራኑን ለማሰደብ አፋቸውን ከፍተው ባዶነታቸውን በነጻ ሲያስኮሞኩሙን ኖረዋል፡
እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ መምህር እንደሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ ጥርስ ውስጥ ከገቡት መካከል ዋነኛው መሆኑ ይታወቃል፡፡ ገዢው የወያኔ ቡድን ጠንካራውን የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር በማፍረስ ተለጣፊ ማህበር ከማቋቋም አልፎ ታላላቅ የማህበራችንን አመራሮች ከአሰፋ ማሩ ጀምሮ በመግደል በተለያዩ ጊዜያት ከኢትዮጵያዊው መምህር ሊነሱ የሚችሉ ተቃውሞችን ለማፈን ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል በ2004 እንኳን የደመወዝ ጭማሪን ተከትሎ በተነሳው የመምህራን ጥያቄ መብታችን ይከበር ያሉ የማህበራችንን አባላት ከስራ ማባረር ጀምሮ ለእስር መዳረጉ የሚታወስ ሲሆን ይህም ሳያንስ በወቅቱ ከአንድ የሐገር መሪ ነኝ ከሚል ግለሠብ የማይጠበቅ ንግግር ከቀድሞው የሐገራችን አምባገነን ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ በሐገራችን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መስማታችን ይታወሳል ይህ በወያኔ አመራች ዘንድ ያለውን ከፍተኛ ንቀት እና ፍርሐት የሚያሳይ ነው፡፡ በዚህ ውስጣዊ ፍርሀት የተነሳ በርካታ መስራት የሚችሉ እና ሀገሪቱን ሊቀይሩ ምሁራንን እንዲሰደዱ በማድረግ ያልተሰደዱትን ደግሞ በማሰር እና በማንገላታት የመምህርነትን ሙያን እንደማሰሪያ ብሎም አነስተኛ ደመወዝ በመክፈል የመምህራኑ አእምሮ በማጀት ወሬ እንዲጨናነቅ ማድረጉ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡
ከሰሞኑም ይህንን ውስጣዊ ፍራቻውን ለካድሬዎቹ በመመሪያ መልክ በመስጠት በየት/ቤቱ የሚገኙ የገዢው ፓርቲ አባላት ያልሆኑ መምህራንን ስማቸውን ከተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር በማያያዝ ማስፈራሪያ እና ዛቻ ሲያቀርብባቸው ሰንብቷል በተለይ የግንቦት ሰባት እና የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቹህ በማለት በየእለቱ ዛቻ የሚደርስባቸው መምህራን ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ነው በተለይ ከሰሞኑ የአባይ መዋጮ እንደአዲስ ለማስከፈል የሚደረገውን ጥረት ተከትሎ በተነሳው የመምህራን ጥያቄ በመምህራን ላይ የሚደርሰው መከራ እና ግፍ መጠኑ ጨምሯል፡፡
ስለሆነም የዚህ የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ለትምህርት ሚኒስቴር ጉዳዩን ቢያሳውቅም እልባት ሊያገኝ አልቻለም፡፡ የትምህርት ሚኒስቴሩም ለጉዳዩ እልባት ከመስጠት ይልቅ የአባዬን ወደእምዬ እንዲሉ በኮሚቴው አባላት ላይ ወቀሳ እና ማስፈራሪያ አቅርቧል ይኸውም ወትሮውም በትምህርት ሚኒስቴር ላይ አመኔታ ያልነበረውን ኮሚቴ ኢትዮጵያን ነፃ ለማውጣት ከሚታገሉ ሌሎች የሙያ ማህበራት እና ፓርቲዎች ጎን እንዲሠለፍ አድርጎታል በዚህም የተነሳ የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ኮሚቴ አባላት በሰልፉ ላይ እንደምንገኝ ቃል እየገባን ሌላው የሀገራችን መምህርም ከጎናችን በመሆን በሠላማዊ ሠልፉ ላይ ይገኝ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
የኢትዮጵያ መምህራን ድምጽ ይሠማ ጊዜያዊ ኮሚቴ
ህዳር 21/2007
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ማስታወሻ፡ ይህች ጽሁፍ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከተከሰሰባቸው ሁለት መጣጥፎች አንደኛዋ ናት። በመጭው ወር በአሶሳ የሚደረገውን የብሄር ቀን ድራማ እሳቤ በማድረግ – በርካታ አንባብያን በጠየቁት መሰረት እነሆ በድጋሚ ለንባብ አቅርበናል። – ክንፉ አሰፋ – “እኛ ጭቁን ብሄረሰቦች ከዚህ ቀደም በየሰው ቤት ተቀጥረን የምንሰራ፣ አሽከሮች እየተባልን ነበር የኖርነው። አሁን ግን ይኸውና ህገ-መንግስታችን መብታችንን ሰጥቶናል… ኑሯችንም ተሻሽሎ ዛሬ […]
በላይ ማናዬ
‹‹መብቴን አሳልፌ አልሰጥም፤ የትም ብሆን ስለመብቴና ሀገሬ ያገባኛል፡፡ እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል!››
ከፕሮ/ር አለማየሁ ገብረማርያም – ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ለአራት አስርት ዓመታት እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው እና በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ከህዝብ ፍላጎት ውጭ በኃይል በስልጣን ወንበር ላይ ተፈናጥጦ የሚገኘው የወሮበላ የማፊያ ቡድን ኢትዮጵያን ለማጥፋት ቀጣይነት ያለው እና የማያቋርጥ የፖለቲካ፣ የማህበራዊ እና የባህል ጦርነት በመክፈት ዕቅድ አውጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡
ኢሕአዴግ አምባገነን መንግስት ነው::የአምባገነን መሰረቱ ደግሞ ፍርሃት ነው:: የህሊና እስረኛ የሆነው አንዷለም አራጌን ንግግር ያድምጡት::
የፕሮግራም መግለጫ
ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡
የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡
ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና
ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና
ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ
ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት
ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)
ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና
ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡
ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡
የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡
ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡
የግብፅ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከተመሰረተባቸው ክስ በነፃ መሰናበታቸውን በመቃወም በመዲናይቱ ካይሮ ደም አፋሳሽ ግጭት መቀስቀሱ ተነገረ።ሙባረክን በነፃ ያሰናበተውን የግብፅ ፍርድ ቤት ለመቃወም ታህሪር አደባባይ በወጡ በሺህዎች የሚቆጠሩ ጸረ-ሙባረክ ሠልፈኞች እና ፖሊሶች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ቢያንስ ሁለት ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል።
የግብፅ ከፍተኛው ፍርድ ቤት፥ የቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክን ከተከሰሱበት የግድያ እና የሙስና ወንጀሎች በነፃ ማሰናበቱ ተገለጠ።
ይህ ፅሑፍ አብርሐ ደስታ በህወሀት ማፍያዎች ተይዞ እስር ቤት ከመግባቱ በፊት የፃፈው ነው፡፡ ስለትግራይ ህዝብ የተለያዩ ሠዎች የተለያዩ ፅሁፎችን ይፅፋሉ እንደዚህ እንደአብርሐ ደስታ ግን እስካሁን ሳነበው የሚመስጠኝ የለም
መልካም ንባብ
የትግራይ ህዝብ ከኢሕአዴግ መንግስት ምን ተጠቅሟል? የትግራይ ህዝብና መንግስት ምን አይነት ግንኙነት አላቸው? እነዚህንና ተያያዥ ጥያቄዎችን በተመለከተ አብርሃ በላይ ከመቀሌ አጥጋቢ መልስ ሰጥቷል:: አብርሃ እንደመነሻ ያደረገው ከአንድ የትግራይ ተወላጅ የቀረበለትን ጥያቄ ነው:: ጥያቄውም ይህ ነው:: “ኢህኣዴግን ትቃወማለህ፣ ግን ህዝብን ለለውጥ ኣነሳስተህ ከህወሓት የባሱ ፅንፈኛ የፖለቲካ ድርጅቶች ስልጣን ቢይዙስ ??? ስትቃወም ስለዉጤቱም ማሰብ ኣለብህ። በምትፅፋቸውን ነገሮች ለአዳንድ የትግራይ ጠላቶች መጋበርያ እየሆንክ ነው።”
መልስ
ሁሉም ዜጋ (የገዢው ፓርቲ ደጋፊም ተቃዋሚም) መጠየቅ ያለበት (የፖለቲካ ስርዓት ለውጥ ባህሪያዊ ሂደት መሆኑ ተገንዝቦ) በኢህኣዴግ እጅ ያለው ስልጣን (በለውጡ ሂደት) ‘ለማን ይሰጥ’ የሚለውን ነው። ሁለት ስልጣን ለመቀበል ያሰፈሰፉ ሃይሎች ኣሉ፤ (1) የኢትዮዽያ ህዝብና (2) ስልጣን በሃይል ለመያዝ የጓጉ የፖለቲካ ቡድኖች።
ኣንድ
እኔ ታድያ ‘ስልጣን ለኢትዮዽያ ህዝብ መሰጠት ኣለበት’ ከሚሉ ሰዎች ጎራ ነኝ (የምቃወምም ለዚህ ነው)። ምክንያቱም ስልጣን ለህዝብ ማስረከብ ዲሞክራሲን ማስፈን ነው። በዲሞክራሲያዊ መንግስት ህጋዊ ተቃዋሚዎች ይበረታታሉ፣ ኣማራጭ ፖሊሲያቸው ለህዝብ እንዲያቀርቡ ነፃ ሚድያ ይኖራል። ህዝቦች በነፃነት የፈለጉትን ፓርቲ ይመርጣሉ፤ ድምፃቸውም በገለልተኛ የምርጫ ቦርድና የፍትሕ ኣካላት መኖር ይከበራል። የህዝብ ድምፅ ከተከበረ ሲቪላዊ መንግስት የማቋቋም ዕድል ይኖራል። በዚ መንገድ በሃይል ስልጣን ለመያዝ የሚቋምጡ ሃይሎች ቦታ ኣያገኙም። ዓፈናው ከቀጠለ ግን ….
ዲሞክራሲ ማስፈን የብዙ ችግሮች መፍትሔ ይሆናል። የ’ኣፍርሶ መገንባት’ ስትራተጂ ዕዳ ይቀንሳል። ደም ማፋሰስ ያስወግዳል። ኧረ ሲንቱን …… ህወሓት/ኢህኣዴግ ኣሁን ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ማድረግ የሚችለው ትልቁ ኣስተዋፅኦ ዲሞክራሲን በማስፈን ስልጣን ለህዝብ ማስረከብ ነው። የትግራይ ህዝብ ትግልም ለውጥ ኣመጣ እንላለን።
በኢትዮዽያ ታሪክ (እስከ ኣሁን ድረስ) ስልጣን የተያዘው በህዝብ ፍላጎትና ምርጫ ሳይሆን በጠመንጃ ኣፈሙዝ ነው። ፓርቲዎች ተጠናክረው ስልጣን መያዝ ከቻሉ ለመጀመርያ ግዜ ሰለማዊ የስልጣን ሽግግር ተግባራዊ ያደርጋሉ (የኢትዮዽያ የፖለቲካ ታሪክ ይቀይራሉ) ። ሰለማዊ ሽግግር ተደረገ ማለት ደግሞ ስልጣን ወደ ህዝብ ወረደ ማለት ነው። ህዝብ የስልጣን ባለቤት ከሆነ የመንግስት ኣካላት የሰው ጌቶች ሳይሆኑ የሰው ኣገልጋዮች ሆኑ ማለት ነው። በዚህ መልኩ የህዝቦች ነፃነት ተከበረ ማለት ነው፤ ቀጥሎም እኩልነት፣ ኣንድነት፣ መከባበር ይኖራሉ። እኛም ተዋደድን። ስለዚ ፓርቲዎች ሊከበሩ ይገባል።
ህወሓቶች የስልጣን ዕድሜ ማራዘም መፍትሔ እንዳልሆነ መገንዘብ ኣለባቸው። የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ ድጋፍ ማሰባሰብ ዘለቄታ ያለው የህዝብ ደህንነት ዋስትና ሊሆን ኣይችልም። የህዝብ ዋስትና ዲሞክራሲያዊ (ጠንካራ፣ ነፃና ገለልተኛ) ተቋማት ናቸው። መሪዎች ይመጣሉ፣ ይሄዳሉ፤ ሲሄዱና ሲመጡ እንደ ድልድይ ሁኖው በማገልገል ለህዝብ ደህንነት ዋስትና (ወይ ጋሻ) የሚሆኑ እነዚህ የፍትሕ ተቋማት ናቸው።
ሁለት
ህወሓት /ኢህኣዴግ የያዘውን ስልጣን በፍቃደኝነት (በምርጫ) ለህዝብ ካላስረከበ በሃይል እስኪወርድ ድረስ በስልጣን ይቆያል ማለት ነው። ይህንን የሚያሳየን ህወሓት ስልጣኑን ለሌላ ታጣቂ (ተዋጊ) ሃይል እንጂ ለህዝብ ለመስጠት ፍላጎት የለዉም ማለት ነው።
ሌላ የታጠቀ ሃይል ስልጣን ከያዘ ሌላ ህወሓት /ኢህኣዴግ መጣ ማለት ይሆናል። ምክንያቱም ስልጣን በሃይል ለመያዝ ሰው መግደልን ጨምሮ ሌሎች የተወሰኑ ወንጀሎች ይሰራሉ፣ ግድያ ይኖራል። (ሃይል ስንጠቀም ወንጀሎችም ይኖራሉ ኣለበለዚያ ግን ለውጡ የመጣው በሃይል ሳይሆን በሰለማዊ መንገድ ነው ማለት ነው)። እነዚህ የተወሰኑ ወንጀሎች ለመሸፈን ሲባል ሌሎች ተጨማሪ ወንጀሎች ይፈፀማሉ። እነዚህ ወንጀሎች እንዳይጋለጡ ለማድረግ (ጉዳቸውን እንዳይወጣ) ስልጣን የያዘውን የፖለቲካ ቡድን የራሱ ዳኞች፣ ወታደራዊ መኮነኖች፣ የደህንነት ሃላፊዎች ወዘተ ይኖሩታል።
ከተሸናፊው የፖለቲካ ድርጅት ‘ደህንነታዊ ስጋት’ በመስጋትም የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በጠላትነት ይፈርጃል። እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎችም ለራሳቸው ደህንነት ሲሉ ሌላ የኣደረጃጀት ኣማራጭና የፖለቲካ ስልት ያፈላልጋሉ። የሃገር ኣንድነትም ኣደጋ ላይ ይወድቃል።
ስልጣን ላይ የወጣ ሃይል ድክመቱን ለመሸፈን ሲል የሚጠራጠራቸውን ህዝቦች ለመቆጣጠር (የመገንጠል ጥያቄን በሃይል ለመመለስ) እንዲችል ኣሻንጉሊት ድርጅቶችን ያቋቁማል። ይህንን ሁኔታ ሌላ ኢህኣዴግ ያደርገዋል። እኛ ደግሞ “ኣዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ …” እንዘፍናለን።
ሦስት
በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ መንግስት ህዝቦችን የመጨቆን ዕድሉ ይቀንሳል። ምክንያቱም ፖለቲከኞቹ ከወንጀል ነፃ የመሆን ዕድል ኣላቸው። (ከወንጀል ነፃ ካልሆኑ ኣይመረጡማ) ወይም ከስልጣናቸው ለማውረድ ቀላል ይሆናል። እነሱም ከስልጣን መውረድን የሞትን ያህል ኣይፈሩም (በህዝብ የተመረጡ ናቸዋ)። ስልጣን ላለመልቀቅ ኣያንገራግሩም (ህዝቡ ሰልፍ ይወጣላ)። መሪዎቹ ሰልፍ ለወጣ ህዝብ እንዲገድሉ ወታደሮቻቸውን ኣያዙም። ምክንያቱም በፖለቲከኞችና ወታደሮች መሃከል (ህገ መንግስታዊ ከሆነ በቀር) ልዩ ግንኙት ወይ ትስስር ኣይኖራቸውም።
በህዝብ የተመረጡ መሪዎች ተጠያቂነታቸው ለመረጣቸው ህዝብ ይሆናል (የስልጣን ምንጫቸው ህዝብ ነውና)። ስልጣን የያዙት በሃይል ከሆነ ግን ተጠያቂነታቸው ለጠመንጃቸው ነው። የህዝብ ጉዳይ ኣያሳስባቸውም። ስለ ካድሬዎቻቸው እንጂ ስለ ህዝቡ ችግር ላይጨነቁ ይችላሉ።
ኣራት
ኢህኣዴግን መቃወም ለምን???
(1) ገዢው ፓርቲ ስልጣን ወደ ህዝብ እንዲመልስ ለማገዝ ያስችላል። ኢህኣዴግ የህዝብን ድምፅ ኣላከበረም፣ ህዝብ እየገዛ እንጂ እያስተዳደረ ኣይደለም ያለው። ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት እንፈልጋለን። የሁሉም ህዝቦች ደህንነትና ልማት የሚረጋገጠው ዲሞክራሲያዊ ነፃነት ሲፈቀድ ነውና።
(2) ኢህኣዴግ ችግሮቹን እንዲያርም ለማድረግ ነው። የመናገር መብት ያፍናል፤ ህወሓት በትግራይ ህዝብ ስም ሌሎች ህዝቦች ይጨቁናል፤ ለራሱ ጥቅም ሲባል ኣሻንጉሊት ድርጅቶች በማቋቋም የሚገዙትን ህዝብ የማይወክሉ መሪዎች በኣስገዳጅነት እንዲገዙ ያደርጋል። እነዚህ ህዝቦች ራሳቸው ይወክሉናል ብለው በመረጡዋቸው ድርጅቶች መተዳደር ኣለባቸው። ህዝቦች በሚወክሉዋቸው መሪዎች ሲተዳደሩ የትግራይ ህዝብ ቢጠቀም ‘ጂ ኣይጎዳም።
(3) ለውጥ ፈልገን ነው። ለውጥ የመፈለግ ኣባዜ የተፈጥሮ ጥሪ ነው። እያንዳንዱን ትውልድ የራሱ /ለራሱ የሆነ ለውጥ የማምጣት ወይም የማድረግ የግል የቤት ስራ ኣለው። የኣባቶቻችን ታሪክ ለኛ (የኛ) ሊሆን ኣይችልም። ስለዚ ለውጥ መፈለግ በራሱ ስሕተት ኣይደለም። ለለውጥ መነሳት የህይወት ግዴታችን ነው።
ኣምስት
የትግራይ ስጋት የሚመነጨው ከነዚህ ዲያስፖራ ፖለቲከኞች ከሚያራምዱት ኣስተሳሰብ እንደሆነ ተነግሮኛል። እነዚህ የ ‘ትግራይ ጠላቶች’ እንደሆኑ ተደርገው የሚታሰቡ ሃይሎች መነሻቸው ምንድነው ? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው።
እነዚህ ሰዎች በኢህኣዴግ መንግስት በጠላትነት ተፈርጀው ‘ኣሸባሪ’ ተሰይመው ከሃገራቸው የተባረሩ ናቸው። ከሃገራቸው ከተባረሩ ታድያ እንዴት ለህወሓት ጥሩ ኣመለካከት ሊኖራቸው ይችላል? በህወሓት ዘመነ መንግስት ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ ካልተፈቀደላቸው ሃገራቸውን ለመግባት ህወሓትን በሃይል ማስወገድ ግድ ሊላቸው ነው። ስለዚ ጥረታችው ኣይደንቀኝም።
ጥያቄው እነዚህ ሰዎች ለምን የትግራይን ህዝብ target ያረጋሉ የሚል ነው። መልሱ ግን ቀላል ነው። (1) ህወሓት ራሱ … ህወሓትና የትግራይ ህዝብ ኣንድ እንደሆኑ ኣድርጎ ይሰብካል (ድጋፍ ለመሰብሰብ)።
(2) የዲያስፖራው የፖለቲካ ስትራተጂ ተደርጎ ይወሰዳል። የትግራይን ህዝብ target ሲያደርጉ የትግራይን ህዝብ ፈርቶ ህወሓትን ከመደገፍ ይቆጠባል ከሚል ኣስተሳሰብና ከትግራይ ህዝብ ውጭ ያለው ኢትዮዼያዊ ‘በኣንድነት በመቆም’ ህወሓትን ከስልጣን ለማውረድ እንዲነሳ ታስቦ ነው።
(3) ተሳዳቢዎቹ ዲያስፖራ ኣራት ዓይነት ናቸው።
(ሀ) የፖለቲካ ብቃት የሚያንሳቸው (ህዝብና ገዢው ፓርቲ መለያየት ያቃታቸው ወይም መለያየት ያልፈለጉ)። እነዚህ በቀጥታም በተዘዋዋሪም ህወሓትን ያግዛሉ። የትግራይን ህዝብ ሲሳደቡ , የትግራይ ተወላጆችም ሳይፈልጉ ከህወሓት ጎን እንዲሰለፉ ይገደዳሉ። ግን ስጋት ሊሆኑ ኣይችሉም ስልጣን ኣይዙምና (በሃይል ካልሆነ በቀር)፤ የፖለቲካ ዕውቀት ፤ስለሚያንሳቸው ።
(ለ) ወደ ሃገራቸው እንዳይገቡ የተከለከሉ (በሰለማዊ መንገድ እንዲታገሉ በህወሓት ያልተፈቀደላቸው)። እዚ ላይ ስጋት ፈጣሪው ህወሓት ራሱ ነው።
(ሐ) በሻቢያ ተልከው ኢትዮዽያን ለመበጥበጥ ተከፍሎቸው የሚሰሩ (ኣብዛኞቹ ኤርትራውያን ናቸው)። ኢትዮዽያውያን ካልተባበርናቸው የትም ኣይደርሱም።
(መ) ከህወሓቶች ጋ ግንኙነት ያላቸው …. ይህንን ስትራተጂ ‘ዲያስፖራ ፖለቲከኞች ጥላቻ የሚሰብኩ ናቸው’ ተብለው እንዲፈረጁና የትግራይ ህዝብ እነሱን ፈርቶ ና ሰግቶ ከህወሓት ጎን እንዲሰለፍ ለማድረግ የታለመ ነው።
ስለዚህ ጥላቻን የሚሰብኩ ኣንዳንድ ፖለቲከኞች ሃገራቸውን እንዲገቡ ተፈቅዶላቸው በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ህዝባቸውን ለለውጥ እንዲያነሳሱ ቢደረግ የትግራይ ህዝብ የሚያዋሩዱበት ምክንያት ባልኖራቸው ነበር። ስለዚ የትግራይ ስጋት ሆን ተብሎ በህወሓት የተቀናበረ ነው።
ስድስት
ስጋቱ ቢኖርስ??? መፍትሔው በህወሓት እጅ ነው። ሥጋቱን ለመቀነስ ራሳችን የሌሎች ህዝቦች ስጋት ፈጣሪ መሆን የለብንም። እንደ ኣሰራርም :
(1) ህወሓት በትግራይ ህዝብ ስም ሌሎች ህዝቦች መጨቆን እንዲሁም ስጋት መፍጠር የለበትም። (ካልጨቆነ ስጋቱ ኣይኖርም)። ከዚህ ኣልፎም የትግራይ ህዝብ ከሌሎች የኢትዮዽያ ህዝቦች በሰላም መኖር የሚፈልግ እንጂ የህወሓት የጥላቻ ፖለቲካ እንደማይደግፍ በግልፅ መናገር ኣለበት። ይህ ካልሆነ ደግሞ መፍትሔው መደራጀት እንጂ ስልጣን የሙጥኝ ይዞ ህዝቦችን መጨቆን ኣይደለም።
(2) ህወሓት ዲሞክራሲን ማስፈን ሲገባው የታጠቁ ሃይሎችን ወደ ስልጣን መጋበዝ የለበትም። ህወሓት ህጋዊና ሰላማዊ የተቃውሞ ድርጅቶችን ሲያዳክምና ሲያፈርስ ስልታቸውን ቀይሮው የሃይል መንገድ ተከትለው ከስልጣን እንዲያወርዱት እየጋበዛቸው ነው። ይህ ኣካሄድ ደግሞ ህወሓት በሌሎች ህዝቦች እንዳደረገው ሁሉ ኣሻንጉሊት ድርጅት መስርተው የትግራይን ህዝብ ለመጨቆን ያስችላቸዋል።
ሰባት
“ለአዳንድ የትግራይ ጠላቶች መጋበርያ እየሆንክ ነው” የሚል ነገር ኣለ። የትግራይ ጠላት ማነው? እንደኔ እምነት: የትግራይ ህዝብ ጠላት ጭቆና ነው። ጠላቶቹ ጨቋኞቹ ናቸው። ድሮ ደርግ ነበር ጨቋኝ፣ ኣሁን ደግሞ ህወሓት። ስለዚህ የትግራይ ጠላቶች ጨቋኝ ገዢዎቹ እንጂ ሌሎች ብሄሮች ወይ ሌላ ሃይማኖት ተከታዮች ኣይደሉም።
ተጋሩ (የትግራይ ተወላጆች) የራሳቸው የፖለቲካ ኣቋም ይዘው ገዢውን መደብ ሲቃወሙ ‘ከጠላቶቻችን ኣብረዋል’ ወይ ‘ለጠላቶቻችን ያጋሉጥናል’ በሚል ሴራ በመንግስት ደጋፊዎች ይወቀሳሉ፣ ይገለላሉ። ግን እንዲህ ከተነቀፉኮ የትግራይ ተወላጆች የመቃወም መብት የላቸውም ማለት ነው። (ወይም እንዲቃወሙ ኣይፈቀድላቸውም ማለት ነው?)
በዚህ መልኩ (ተጋሩ የመቃወም መብታቸውን ከተገደበ) ‘ከትግራይ ወጥቼ ለትግራይ እቆማለሁ’ የሚል የህወሓት ድርጅት ፀረ ተጋሩ እየሆነ ነው ማለት ነው። ህወሓት ለትግራይ ቢቆም ኑሮ እኛ ተጋሩ የፈለግነውን የፖለቲካ ኣመለካከት እንድነራመድ ለምን ኣይፈቅድልንም? ደርግ ኣፈነን። ህወሓትም እንዲህ ካፈነን፣ ህወሓት ከደርግ (ለትግራይ ህዝብ) በምን ይሻላል? በምንስ ይለያል???
ህወሓት የመናገር መብታችን ካላከበረ፣ ሁሉም የትግራይ ሰው በእኩል ዓይን ካልታየ፣ በተግባሩና በስራ ኣፈፃፀሙ መመዘን ሲገባው በጎጠኝነት በስራው ግልፅ የሆነ ኣድልዎ ከተፈፀመበት፡ ከዚህ በላይ የህዝብ ጠላትነት ከየት ሊመጣ ነው? የትግራይ ህዝብ እንደማንኛውም ሌላ ህዝብ በነፃነት ሓሳቡ የመግለፅ መብት ኣለው፤ ሊከበርለትም ይገባል።
ህይወቱ ሙሉ ከጭቆና ነፃ ለመውጣት ሲታገል የኖረ ህዝብ የእኩልነት መብቱ ሲነፈግ እኛ ዝም ብለን ሳንቃወም ማየት ነበረብን? ብዙ መስዋእት የተከፈለበት የ17 ዓመት የትጥቅ ትግል በተወሰኑ ሰዎች ተጠልፎ ለግል ስልጣንና ጥቅም ሲውል እኛ ዝም ብለን ተመልካች እንድንሆን ነው የሚጠበቀው? ወይስ የራሳችን ሚና መጫወት ይኖርብናል!?
ስምንት
የኢህኣዴግ መንግስትን የተቃወመ ሰው ወይ የፖለቲካ ድርጅት የትግራይ ህዝብ ጠላት እንደሆነ ኣድርገው በማቅረብ የትግራይን ህዝብ ለማጭበርበር የሚሞክሩ የመንግስት ኣካላት እንዳሉም ይታወቃል። ግን ህወሓትን መጥላት የትግራይ ህዝብን መጥላት ኣያሰኝም። ህወሓትን መቃወም የትግራይ ህዝብን መቃወም ማለት ኣይደለም። ምክንያቶች
(1) ህወሓት (ገዢው መደብ)ና የትግራይ ህዝብ (ተገዢው ህዝብ) አንድ አይደሉም፤ ሊሆኑም ኣይችሉም። ፓርቲና ህዝብ አንድ ተደርጎ የሚወሰደው ለፕሮፓጋንዳ (የህዝብ ግንኙነት) ሥራ ነው። የትግራይ ህዝብ ከህወሓት በፊት ነበር፤ ከህወሓት በኋላም ይኖራል።
(2) ተቃዋሚን በጠላትነት ማየት የፖለቲካዊ ኣስተሳሰብ ችግር ውጤት ነው። መቃወም ተፎካካሪ (ኣማራጭ ሃይል) መሆን እንጂ ጠላትነት ኣይደለም። ዴሞክራሲ ኣሰፍናለሁ የሚል መንግስት ተቃዋሚዎችን በጠላትነት መፈረጅ ተገቢ ኣይደለም።
(3) ሰዎች ወይ ድርጅቶች ህወሓትን (እንደገዢ ፓርቲ) የመቃወም ተፈጥሮኣዊ መብት ኣላቸው። የትግራይ ህዝብ ህወሓትን ከፈለገ (በፍላጎቱ ) ይምረጠውና ትግራይን ያስተዳድር (መብቱ ነው)። ህወሓት ላልመረጠው ህዝብ ኣሻንጉሊቶችን በመፈብረክ ሌሎች ህዝቦችን በእጃዙር የመግዛት መብት ግን የለውም።
ህወሓት ለኢትዮዽያ ህዝቦች መሪዎች የመምረጥ መብት ማን ሰጠው? ራሳቸው እንዲመርጡ ለምን ኣይፈቀድላቸውም? ስለዚ ህወሓትን ለመቃወም በቂ ምክንያት ኣላቸው። ይህን ሁኔታ በመቃወማቸው ‘የትግራይ ህዝብ ጠላቶች’ ሊያሰኛቸው ኣይችልም። የኢትዮዽያ ህዝቦች የራሳቸውን ተወካዮች በነፃነት የመምረጥ ሙሉ መብት ኣላቸውና።
(4) ህወሓት ለትግራይ ህዝብ የቆመ ድርጅት ከሆነ ለምን እንድንደራጅ ኣይፈቅድልንም? መደራጀትኮ ሃይል ይፈጥራል። ለምንድነው ተደራጅተን ሃይል እንዳንፈጥር የሚያደርገን? ከዚህ በላይ ጠላትነት ኣለ እንዴ? ስለዚ ‘የትግራይ ህዝብ ጠላት ህወሓት ነው’ ማለት እችላለሁ።
(5) የትግራይ ህዝብ (ባይሳካም) አንድ ኣስተሳሰብ እንዲኖረው ጥረት ማድረግ ትውልድን መግደል ነው። ብዙ ሰዎች አንድ ዓይነት ኣስተሳሰብ እንዲይዙ ለማድረግ የብዙዎቹ ኣስተሳሰብ መግደል ግድ ይላል። ኣስተሳሰብ ታፈነ፣ ተገደለ ማለት ደግሞ ትውልድን ተገደለ ማለት ነው። ምክንያቱም የለውጥ ምንጭ ኣስተሳሰብ ነው።
(6) ደሞ የትግራይ ህዝብ ከህወሓት አገዛዝ ነፃ መውጣት ኣይፈልግም ያለ ማነው? በትግራይ ሁሉም ቢሮዎች (ከላይ እስከ ታች) በተወሰኑ ሰዎችና ቤተሰቦቻቸው ቁጥጥር ስር ነው። ማነው ትግራይ የነሱ ብቻ ናት ያለው? ትግራይኮ የሁላችን ናት? ወይስ የነሱ ባሮች (Slaves) ሁነን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል?
ማንም ሰው የመደገፍም የመቃወምም ተፈጥሮኣዊ መብት ኣለው። የመቃወም መብት የህወሓት የግል ስጦታ ኣይደለም። ህወሓት ሲፈልግ የሚሰጠን ሲፈልግ ደግሞ የሚከለክለን የግል ሃብቱ መሆን የለበትም።
ዘጠኝ
የስርዓቱ ተጠቃሚዎች (በቤተሰባዊ ሙስና) ገዢውን ፓርቲ በሚቃወሙ ግለሰዎች ላይ ስም የማጥፋት ዘመቻ ከማካሄድ ኣይቦዝኑም። “የስርዓቱ ተጠቃሚዎች” ያልኩበት ምክንያት፡ ሕገ ወጥና ተቀባይነት የሌለው መንገድ በፈጠረው ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥገኝነታቸው በራስ የመተማመን ስሜታቸው ካላሽመደመደው በቀር ሃሳባቸውን በነፃነት በሚፅፉ ሰዎች ስም የማጥፋት ዘመቻ ማድረግ ኣስፈላጊነቱ ኣይታየኝም ከሚል እሳቤ በመነሳት ነው።
ህወሓቶች ለሚቃወማቸው ሰው ኣንድም ያስራሉ (ያዋክባሉ) ኣልያም ስም በማጥፋት ተግባር ይሰማራሉ። ለምን ስም ያጠፋሉ???
(1) በሙስና የበሰበሰ ስርዓት ተቃውሞ የሞትን ያህል ይፈራል። ምክንያቱም የግለ ሰዎች የተቃውሞ ፅሑፎች ድጋፍ ሊያሳጡት ይችላሉ። ድጋፍ ካጣ ስልጣን ሊለቅ ይችላል፤ ስልጣን ከለቀቀ የሰራውን ጥፋት ይጋለጣል።
(2) ጥቅሙ እንዲጎድልበት ኣይፈልግም (የእህል-ውሃ ጉዳይ ነው)። (“ኣብ ፃሕልና ኢድኩም ኣይትሕወሱ፤ ንሕና ክንበልዕ ንስኹም ጠጠው ኢልኩም ረኣዩ” ዝዓይነቱ።) ኣጥንት የያዘ ውሻ …… ይሆናል።
ህወሓት ተቃውሞ ሲያይልበት (ሁሉም ነገር ለብቻው ጠቅልሎ በመያዙ) ” እኔ ብቻ ኣይደለሁም የበላሁት፡ የትግራይ ህዝብም ኣብሮኝ በልቷል፤ ስለዚ እኔ ብቻ ተጠያቂ ኣልሁን፣ ከትግራይ ህዝብ ኣትነጥሉኝ” የሚል መልእክት ያለው ተግባር እያከናወነ ይገኛል።
የትግራይ ህዝብ ባልዋለበት (‘የማዩ የሰማዩ’) ሊያስወነጅለው እየሞከረ ነው (‘ጅብ ይበለሃል’ ከሚል ማስፈራርያ በተጨማሪ መሆኑ ነው)።
እኔ ግን እላለሁ፡ የህወሓት ሰዎች ባጠፉት ጥፋት የትግራይ ህዝብ ተጠያቂ ሊሆን ኣይገባም። እውነታውን መካድ የችግሩ መፍትሔ ኣይሆንም።
አስር
ሓሳብ በመግለፅ ብቻ ኣንድን ብሄር ወይ ፓርቲ ከስልጣን ለማውረድ ወይ ለማውጣት ኣይቻልም ። ሓሳባችን በነፃነት በመግለፃችን ከህወሓት ‘የባሱ’ ሃይሎች ስልጣን እንድይዙ ኣያስችልም ። እነዚህ ‘የትግራይ ጠላቶች ’ እየተባሉ የሚፈረጁ ግለሰዎች ተሳክቶላቸው ስልጣን ብይዙ እንኳ የራሳችውን ህዝብ ነው የሚያስተዳድሩ። ትግራይን የሚያስተዳዱርበት መንገድ የለም (እነሱም ትግራይን የማስተዳደር ስራ ‘ለኛ ይሰጠን’ ኣላሉም)። በህወሓት የሚሰጠን “እኔ ከሌለሁ ጅብ ይበላችኋል” ዓይነቱ ማስፈራርያ ግን ለትግራይ ህዝብ ያለው ንቀት የሚያሳይ ነው። ትግራይ የህወሓት ባለስልጣናት ብቻ ወልዳ የቀረች መኻን ኣይደለችም።
It is so!!!
ኣብርሃ ደስታ
– ክፍተኛ አነስተኛ እና ጥቃቅን በሚል ተከፍለው እየተሰለሉ ስልካቸው እየተጠለፈ መሆኑ ታውቋል::
– የሕወሓት ስጋት ውስጥ ውስጡን ክሻእቢያ ጋር ግንኙነቱን እንዲያጠናክር አድርጎታል::
– የኢትዮጵያ ሕዝብ ውስኝ የለውጥ ወቅት ላይ መሆኑን አውቆ አደባባይ በመውጣትወያኔን ሊያስወግድ ይገባል::
Minilik Salsawi
ከፊታችን አደጋ አለ በሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ የገቡት እና በመፍትሄፍለጋ ስብሰባዎች የተወጠሩት የሕወሃት ሰዎች ክከፍተኛ ባለስልጣናት ጀምሮ እንከ በታች ሹሞች ድረስ በብአዴንና በኦህዴድ ባለስልጣናት ላይ ክፍተኛ የማስፈራራት እና የማዋከብ ሽብር እየፈጸሙ መሆኑን አንድ ከፍተኛ የኢሚግሬሽን እና ደህንነት ባለስልጣን ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል::
በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ የሚገኙ የብአዴን እና የኦሕዴድ አባላት በግል እንዳይገናኙ እንዲሁም ከመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ጋር እንዳይገናኙ ከፍተኛ የሆነ ክትትል እየተደረገባቸው ሲሆን በባለስልጣናት ደረጃ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚያጠና የደህንነት ቡድን የተመደበባቸው ሲሆን ስልኮቻቸውም እየተጠለፉ መሆኑን እኚሁ ባለስልጣን ተናግረዋል::
የብአዴንና የኦሕዴድ ሰዎችን ከፍተኛ አነስተኛ እና ጥቃቅን በሚል ተከፍለው በሕወሓት እየተሰለሉ ስልካቸው እየተጠለፈ ሲሆን እንደ በግ የሚታዘዝላቸው የደቡብ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ውስጥ ዘልቀው እንዳይገቡ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑ ታውቋል::ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የሆኑ የብኣዴን እና የኦሕዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት መቀራረብ እና አብሮ መዋል የሕወሓት ሰዎችን ማሳሰቡን እና የደህንነት ክትትል እያደረጉባቸው እንደነበረና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከደመቀ መኮንን እና ከሙክታር ከድር ጀምሮ እስከ በታች የፌዴራል ባለስልጣኖች ላይ ከፍተኛ ስለላ እየተካሄደ ምንጮች መረጃ ሰተው እንደነበር ሲታወቅ ይህ በአሁኑ ወቅት በእጥፍ ተጠናክሮ መቀጠሉ ታውቋል::
ሁኔታዎች መልካም አይደሉም ከፊታችን አደጋ ተደቅኗል::ለውጥ ያስፈልጋል::የሚሉ የተቆጡ ድምጾች በስፋት በኢሕኣዴግ አባላት እየተሰሙ ያለበት አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው ሕወሓት በግል እና በጋራ ባለስልጣናቱ ላይ ከፍተኛ ማስፈራራት እና ዛቻ እያደረገባቸው መሆኑን የተናገሩት ምንጮቹ ኢሕአዴግን ለመናድ ብትሞክሩ ሃገሪቷ ትበታተናለች::እንደ ሱማሊያ መንግስት አልባ ሆና እንደ ሩዋንዳ ትበጠበጣለች እያሉ ከማስፈራራትም አልፎ በግል የተነከራችሁበት ሙስና አደባባይ እናወጣዋለን:: እኛን ማንም ሊጠይቀን አይችልም ቁልፉ እኛ ጋር ነው የሚሉ በኣደገኛ መርዞች የተሞሉ ማስፈራሪያዎች መሰንዘር ክጀመሩ እንደቆዩ ተገልጿል::
የኢትዮጵያን ህዝብ እንደ ሶማሌ እና ሩዋንዳ ማስብ ጅልነት ነው::የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ እንጂ ፍጅት ስለማይፈልግ ኢሕ አዴግ ሲፈርስ ሕወሓት እንደሚያስበው ሳይሆን ትልቅ ሰላም በሃገሪቱ ላይ ይሰፍናል ያሉት ምንጩ የብኣዴን እና የኦሕዴድ ባለስልጣናት የየቀን ሪፖርት እና ግንኙነት በተመለከተ ማን ከማን ጋር እንደዋለ ማን እነማን ቤት እንደሄደ በመከታተል እየቀረበ ሲሆን የሃገሪቱን የደህንነት ቢሮ በጋራ የሚመሩት ጸጋዬ:ጌታቸውና ደብረጺሆን በየቀኑ ለትግሪኛ ተናጋሪ ደህንነቶች በአጫጭር ስብሰባዎች መመሪያ እያወረዱ ከመሆኑም በላይ አደጋ ውስጥ መሆናቸውን እየደጋገሙ እንደሚናገሩ ምንጮቹ አክለዋል::
በአሁን ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ ወሳኝ የትግል ወቅት ላይ መሆኑን በማወቅ የበሰበሰውን የወያኔ አምባገነን ስርአት ለመጣል በጋራ አደባባይ በመውጣት የሚያካሂደውን አብዮት የመከላከያ ሰራዊት የፖሊሱ እና የብአዴን እንዲሁም የኦሕዴድ ፓርቲ ለውጡን እንደሚደግፉት የህዝቡን መነሳሳት እየጠበቁ መሆኑን እና ሕወሓት ከመስጋቱ የመጣ ከሻእቢያ ጋር በውስጥ ግንኙነቱን አጠናክሮ መቀጠሉን እንዲሁም ለተመረጡ የኤርትራ ስደተኞች የደህንነት ትምህርት የተሰጠ እንደሚገኝ እኚሁ ባለስልጣን መረጃ አድርሰውኛል::#ምንሊክሳልሳዊ
ህዳር 27 እና 28 ሰማያዊ ፓርቲ ከትብብሩ ጋር በመሆን ለነፃነት አደባባይ እንወጣለን፤ የማስተባበሩ ዝግጅት ቀጥሏል – በትግላችን ሰብዓዊ መብቶቻችንን እናስመልሳለን! ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር! ህዳር 20 2007







Ethiopian returnees from Tanzania
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
በሕገወጥ መንገድ ተታልለው ከሃገር ከወጡ በኋላ በታንዛኒያ እሥር ቤቶች ውስጥ ቆይተው እንደነበር የገለፃቸውን 435 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ወደ ሃገር እየመለሰ እንደሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል፡፡
ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ከፌደራልና ከክልሎች ለተውጣጡ የጸጥታና ደህንነት ሃላፊዎች እንደተናገሩት መንግስት አራት የጸጥታ ችግሮች አጋጥመውታል፡፡ የመጀመሪያው የሽምቅ ውጊያ የሚያደርጉ ሃይሎች የፈጠሩት ስጋት ነው ያሉት ዶ/ር ሽፈራው እነዚህን ሃይሎች እና ሽብርተኞችን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ፈተና መሆኑን ሲገልጹ፣ ከሃይማኖት ጋር ተያይዞ የሚፈጠረውን የአክራሪነት አደጋ ሙሉ …
ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቀድሞው የመከላከያ ኢታማጆር ሹም ሌተናንት ጄኔራል ጻድቃን ገብረትንሳይ የቦርድ ሰብሳቢነት የሚመራው ራያ ቢራ በቀድሞ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትና ህወሃትን ተጠግተው በሚነግዱ ነጋዴዎች ከፍተኛ አክስዮን የተመሰረተ መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ። ማይጨው ከተማ ላይ የተገነበው ፋብሪካው 600 ሚሊየን ብር የተከፈለ ካፒታል አለው። ከራያ ቢራ አክስዮን ባለድርሻዎች መካከል ሌተናንት ጄኔራል ጻድቃንን …
ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያውያኑ ኦስሎ በሚገኘው የእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ገዢው ሃይል የወሰደውን እርምጃ ከማውገዝ በተጨማሪ የኢንግሊዝ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስላሉበት ሁኔታ ወቅታዊ መረጃ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ባዘጋጀው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ አቶ አንዳርጋቸው የፍትህ ተምሳሌት፣ የነጻነት በር ከፋች ነው የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል። ኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን …
ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን እንደገለጸው የመንግስት ታጣቂዎች ወደ ሰማያዊ ብርሃን ቤተክርስቲያን በመሄድ ማፍረሳቸውን ለማወቅ የተቻለ ሲሆን አንድ ፓስተር እስከባለቤታቸውና ሌላ አገልጋይ ታስረዋል። የሃረር አብያተ ቤተከርስቲያናት ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዮሴፍ አምደማርያም ታስረው ሲፈቱ ሌላው የቤተክርስቲያኑዋ ፓስተር አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ። ቤተክርስቲያኗ በአገር አቀፍ ደረጃ ተመዝግባ የምትንቀሳቀስ መሆኗ ታውቋል። የክልሉ አፍራሽ …
ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የገዢው መንግስት በምርጫ 2007 ያለውን ተቀባይነት ለማጠናከር በማሰብ የተለያዩ የህብረተሰቡን ክፍሎች በየክፍለ ከተማው በማሰባሰብ የተሰሩ ስራዎችን በማቅረብ ለመመስገን ሙከራ ቢያደርግም፤ተሰብሳቢዎች ግን ምንም እንዳልተሰራና ተሰራ የተባለውም ችግር ያለበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የመንገዶች መበላሸት ያሳሰባቸው ነዋሪዎች በአካባቢው ላሉ አመራሮች የስራውን የጥራት ጉድለት ቢያሳውቁም የተስተካከለ ነገር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ “በ2006 የተሰራው …
የፕሮግራም መግለጫ
ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡
የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡
ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና
ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና
ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ
ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት
ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)
ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና
ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡
ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡
የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡
ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡