Image

የመድረክ የወጣቶች ክንፍ ከፖሊስ እና ከፀጥታ አካላት እጅና ጓዋንት ሆኖ የክትትል፤ የኢንተለጀንስ እና የቁጥጥር ስራውን በአግባቡ እንዲሚወጣ ለመግለፅ እንፈልጋልን፡፡ የሚል የህዝብ ግንኙነት ስራ ትዝብት ውስጥ የጣለው የመድረክ ፓርቲ ከገንፍሌ ተነስቶ፣ በኣዋሬ ኣልፎ በየካ ክፍለ ከተማ የሚገኝ ኳስ ሜዳ መጨረሻው ያደረገው ሰለማዊ ሰልፍ ተጠናቀቀ።
Image

በዘጠኙ ፓርቲ ላይ የደረሰውን እስር ድብደባ እና እንግልት እንዳላወገዘ የሚነገርለት መድረክ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ሁለት ሺህ የሚጠጋ የኣዲስ ኣበባ ኑዋሪ የተሳተፈበት ሰልፍ በወጣቶች የመድረክ ኣመራር፣ የሴቶች ተወካይ፣ ኣቶ ቡልቻ ሚደቅሳና የወቅቱ የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ዼጥሮስ ባሰሙት ንግግሮች ተጠቃሏል።
ሰለማዊ ሰልፉ የኢህኣዴግ መንግስት ሊያርማቸው የሚገቡ፣ መመቻቸት ያሉባቸው ፖለቲካዊ ምህዳር፣ መወገድ ያለበት የፀረ ሽብር ህግ ፣ ምርጫው ፍትሃዊ እንዲሆን ሊያደረጉ የሚገቡ ስራዎች እንዲሰሩ፣ በየቦታው እያጋጠመ ያለው ዓፈና፣ እስርና እንዲሁም ግድያዎች እንዲቆሙ ጥሪ ቀርበዋል።
Image
የመድረክ ኣመራሮችና ወጣቶች እየመሩት የተካሄደው የሰለማዊ ሰልፉ ዓላማዎች የምያንፀባርቁ መፈክሮች በወጣቶች ኣባላት ተነበዋል። ከመፈክሮቹ

1- ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በነፃና ፍትሐዊ ምርጫ እንጂ በአስመሳይ ፕሮፓጋንዳ፣ በኃይልና በተጽኖ አይገነባም!!

2- የሀገራችን ችግሮች በነፃና ፍትሐዊ ምርጫ በሚገለጽ የሕዝብ ውሳኔ እንጂ በኃይል እርምጃ አይፈቱም!!

3- ከምርጫ በፊት የምርጫ ውድድር ሜዳው የሚስተካከልበት ውይይትና ድርድር እንዲካሄድ አጥብቀን እንጠይቃለን!!

4- በማስመሰያ ምርጫ በየአምስት አመቱ ሕዝብን ማታለልና ሀብቱን ማባከን ይቁም!!

5- የማስመሰያ ምርጫ ለማካሄድ ለሚባክነው የሀገርና የሕዝብ ሀብት ኢህአዴግ ተጠያቂ ነው!!

6- ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ በሌለበት ሁኔታ የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት እውን ሊሆን አይችልም!!

7- ሕዝባችን በ1ለ5 መረብ አፈናና ቁጥጥር ከሚካሄድ የምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ነፃ እንዲሆን እንጠይቃለን!!

8- ያለገለልተኛ የምርጫ አስተዳደርና ያለገለልተኛ የምርጫ ታዛቢ ታአማንነት ያለው ምርጫ ሊኖር አይችልም!!

9- ገለልተኛ የምርጫ ቦርድ በፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ይቋቋም!!

10- በካድሬዎች የሚከናወን የምርጫ አስፈጻሚነትና ታዛቢነትን አንቀበልም፣ እናወግዛለን!!

11- ነፃ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ታዛቢዎች ምርጫውን በነፃነት የሚከታተሉበትና የሚታዘቡበት ሁኔታ
እንዲመቻች እንጠይቃለን!!

12- በምርጫ ወቅት በታጠቀ ኃይል በሕዝባችን ላይ የሚፈጸም ማስፈራሪያና ወከባን እናወግዛለን!!

13- በሰላማዊ ተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ የሚካሄድ እስራትና ወከባ በአስቸኳይ ይቁም!!

14- ኢህአዴግ በመንግሥት ሀብትና ንብረት የሚያከሄደውን ሕገወጥ የምርጫ ዘመቻ እናወግዛለን!!

15- የጸጥታ ኃይሎች የሕዝብ አገልጋዮች እንጂ ሕዝብን ማስፈራሪያና ማሸማቀቂያ መሆን የለባቸውም!!

16- ያልተሟላ የምርጫ ሥነምግባር ኮድ ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ አያስችልም!!

17- ከድምጽ መስጫ ጣቢያዎች የተቃዋሚ ፓርቲ ታዛቢዎችን ማባረር የሕዝብን ድምጽ ለመስረቅ ስለሆነ በአስቸኳይ
እንዲቆም እንጠይቃለን!!

18- የሕዝብን ድምጽ መዝረፍ ዴሞክራሲን መገንባት ሳይሆን መቅበር ነው!!

19- የምርጫ ጣቢያዎች ከአስተዳደር አካላትና ከታጣቂ ሠራዊት ተጽኖና አፈና ነፃ ይሁኑ!!

20- በምርጫ ወቅት በምርጫ ጉዳዮች ፈጣን ውሳኔ የሚሰጡ ነፃና ገለልተኛ ዳኞች በየደረጃው እንዲኖሩ እንጠይቃለን!!

21- ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ማሰር፣ ማሰቃየትና መግደል ሕዝባችን በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የሥልጣን ባለቤት ለመሆን
የሚያካሄደውን ትግል አይገታም!!

22- ሀሳብን የመግለጽ ሕገመንግስታዊ መብታቸውን በመጠቀማቸው የታሰሩ የሕልና እስረኞች በሙሉ በአስቸኳይ ይፈቱ!!

23- በግፍ የታሰሩ ሰላማዊ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት፣ ጋዜጠኞችና የሙስሊሙ ማሕበረሰብ መፍትሔ አፈላላጊዎች በአስቸኳይ ይፈቱ!!

24- የፀረ-ሽብር ሕጉን ለፖለቲካ ዓላማ መጠቀሚያ ማድረግን እናወግዛልን!! ሕገ-መንግሥታዊ መብትን በማይጥስ
ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲሻሻልም እንጠይቃለን!!

25- የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ለገዥው ፓርቲ የሚያሳዩትን ወገንተኝነት በአስቸኳይ ያቁሙ!!

26- ሁሉም ፓርቲዎች በሕጋዊና ፍትሐዊ አግባብ ከመንግሥት በጀት ድጋፍ የሚያገኙበት ሥርዓት እንዲኖር አጥብቀን እንጠይቃለን!

27- በነፃነት የመሰብሰብና የመደራጀት መብታችን ይከበር!!

28- የአንድ አምባገነን ፓርቲ ሳይሆን ትክክለኛ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት እንሻለን!!

29- ኢህአዴግ ለሕገመንግሥትና ለሕግ ተገዥ በመሆን ለነፃ ምርጫ እራሱን እንዲያዘጋጅ እንጠይቃለን!!

30- የሕግ የበላይነት ባልተከበረበት ሁኔታ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት አይቻልም!!

31- የኑሮ ውድነቱና የተጎሳቆለው የሕዝባችን ሕይወት የኢህአዴግ የኢኮኖሚና ማሕበራዊ ፖሊሲ ውጤቶች ናቸው!!

32- በወገንተኝነትና በአድልኦ በሕዝባችን ላይ የሚጫን ግብር በአስቸኳይ ይስተካከል!!

33- በልማት ስም በሕገወጥና ግብታዊ በሆነ መንገድ ሕዝብን ማፈናቀልና ለችግር ማጋለጥ እንቃወማለን!!

34- የመሬት ወረራ ይቁም!!

35- በሙስና የተዘረፈው የሕዝብ ሀብት ለሕዝቡ ይመለስ!! ሙሰኞችም ለፍርድ ይቅረቡ!!

36- የውኃ፣ የማብራት፣ የትራንስፖርትና የስልክ አገልግሎቶች ችግሮቻችን በአስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን!!

37- የአህአዴግ አገዛዝ በሐይማኖቶች የውስጥ ጉዳዮች የሚፈጽማቸውን ጣልቃ ገብነቶች እናወግዛለን!!
እነዚህ መፈክሮች ለመላ ዓለም ይሰራጫሉ ተብለው ይጠበቃል።

Image
አዜብ መስፍን ከባለቤታቸው ህልፈት በኋላ የፓርቲው ሊቀመንበርና የጠ/ሚ/ር ስልጣን ለመረከብ አቅደው እንደነበረ ታማኝ ምንጮች አጋለጡ። የደህንነት ዋና ሹም የነበረው ወ.ስላሴ ወ/ሚካኤልን ከፊት በማስቀደም ወ/ሮ አዜብ የሞከሩትና በፓርቲው አንዳንድ አመራሮች “መፈንቅለ ድርጅት ሙከራ” ሲሉ ፈረጀውታል።

ከምንጮቹ የተገኘው ዝርዝር መረጃ ተከታዩን ይመስላል። አቶ መለስ ዜናዊ መሞታቸውን ተከትሎ በሕወሐት ውስጥ ሁለት አይነት ቡድኖች ብቅ አሉ። ወ/ሮ አዜብ የድርጅቱ ሊቀመንበር በመሆን የጠ/ሚ/ር ስልጣኑን ለመረከብ ካልሆነም ምክትል ጠ/ሚ/ርነትን ለመቆናጠጥ ከፍተኛ ፍላጐት አሳደሩ። ከአዜብ ጐን የቆሙት በረከት ስሞኦን “የመለስን ራዕይ የማስፈፅመው እኔ ነኝ” ሲሉ ለካድሬዎቻቸው ቀሰቀሱ።

በአንፃሩ እነስብሃት ነጋ ከጀርባ የሚመሩትና ፀጋይ በርሄ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ አርከበና ደብረፂዮን ያሉበት ቡድን በተቃራኒው ቆሞ በውስጥ አድፍጦ የፖለቲካ መስመሩን እያስተካከለ ነው። አዜብ ከጐናቸው ያሰለፏቸው የደህንነት ሹም ወ/ስላሴ፣ ገ/ዋህድን እንዲሁም ሚሊየነሩ ነጋ ገ/እግዚያብሄር መቀሌ ድረስ ኔትዎርክ ዘረጉ። አዜብን የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጐ ለማስመረጥ አዜብ የመደቡት በ10ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በአቶ ነጋ በኩል ወጪ እየተደረገ በነወ/ስላሴ አማካይነት ለበርካታ ካድሬዎች ይታደል ጀመር። አዜብ ያንን ሁሉ ገንዘብ ያለምንም ጠያቂ ፈሰስ ማድረጋቸውና ያለመጠየቃቸው አስገራሚ ነበር። ለካድሬዎች በነፍስ ወከፍ ከ3 እስከ 8 ሚሊዮን ብር ተከፋፈለ።

ካድሬው ድምፅ ለአዜብ በመስጠት የሕወሐት ሊ/መንበር ማድረግ እንዲሁም ወ/ስላሴን በፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባልነት ለማስመረጥ በተጨማሪ ጌታቸው አሰፋን እንዳይመረጥ ማድረግ የሚሉ መመሪያዎች ገንዘቡን ለሚቀበሉ ካድሬዎች ጥብቅ መመሪያ ከነወ/ስላሴ ተላለፈ። ካድሬው እነወ/ስላሴ የሰጡትን ገንዘብ በመቀበል ትእዛዙን ተፈፃሚ እንደሚያደርግ ነገራቸው። ጉዳዩን ሰምተው እንዳልሰሙ የሆኑት እነጌታቸው አሰፋ በጐን ካድሬውን እያስጠሩ « የሚሰጧችሁን ገንዘብ ተቀበሉ። የሚሏችሁን እሺ በሉ። በጉባኤው ላይ ግን ከእኛ ጐን ትቆማላችሁ» ሲሉ በማስጠንቀቂያ መልክ ነገሩ። ካድሬው ከነጌታቸው ጐን እንደሚቆም ቃል ገባላቸው። እነወ/ስላሴ፣ አባይ ወልዱ፣ ገ/ዋህድ..እንዲሁም በባለሃብት ሽፋን የአዜብን ተልእኮ ለማስፈፀም ሲሯሯጡ የከረሙት ነጋ ገ/እግዚያብሄር ጉባኤው ሳምንት እየቀረው በመቀሌ “ቡቡ ሂልስና አክሱም” በመሳሰሉ ሆቴሎች ካድሬውን በግብዣ ሲያንበሸብሹ ሰነበቱ።

የጉባኤው እለት ደረሰ። ለሕወሐት ሊቀመንበርነት እጩዎች ሲጠቆሙ ወ/ስላሴ እጅ በማውጣት “አዜብ መስፍን” ሲል ጠቆመ። ተሰብሳቢው ድጋፍና ተቃውሞ ሲጠየቅ 12 ጣቶች (ድምፆች) ብቻ ሲደግፉ የተቀረው አዜብን በመቃወም ውድቅ አደረገው። አባይ ወልዱ፣ ወ/ስላሴ፣ ቴዎድሮስ ሃጐስ፣ ትርፉ፣ በየነ፣ ገ/ዋህድ…ለአዜብ ድጋፍ ከሰጡ 13 ድምፆች ይጠቀሳሉ። አዜብ « የመለስ ራዕይ ሳይበረዝ ሳይከለስ ለማስቀጠል..» አልጨረሱም የመድረኩ መሪ ጣልቃ ገብተው « ስነ ስርዓት ..አሁን የእጩዎች ምርጫ እያካሄድን ነው» ሲል አርከበ ቀበል አድርግው « የመለስ ራዕይ የሚባል የለም። የፓርቲው ራዕይ ነው ያለው» ሲሉ አዜብ በግልምጫ እያዩ ተናገሩ። ካድሬው እንደካዳቸው ያወቁት አዜብ ንዴት በገፅታቸው ላይ ይነበብ ነበር። ብሽቀት የገባው ወ/ስላሴ እቅዳቸውን ጌታቸው እንዳኮላሸው የተረዳ ይመስላል። እጁን በማውጣት « ጌታቸው አሰፋ ለማ/ኮሚቴ አባልነት አይመጥንም። ሰካራም ነው፣ ሴሰኛ (ሴት በማማገጥ) ነው። ውሎና አዳሩ ሸራተን ነው። እንዳውም አቶ መለስ ዜናዊ በጌታቸው ዙሪያ ማጣራት እንዲካሄድ ያስጀመረው ምርመራ ነበር። ውሳኔ ሊሰጥበት ጫፍ ሲደርስ እንዳጋጣሚ ሞት ቀደመው። ስለዚህ ጌታቸው ለፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባልነት አይመጥንም» በማለት በእልህ ስሜት ይናገራል።

አስመላሽ ወ/ስላሴ (በቅፅል ስማቸው አባይ ነብሶ- በፓርላማ ከመለስ ዘናዊ ኋላ አዘውትረው የሚቀመጡና ጥቁር መነፅር የሚያጠልቁ አይነስውር) እጃቸውን በማንሳት በዚህ ዙሪያ መናገር እንደሚፈልጉ ይጠይቃሉ። ሲፈቀድላቸው እንዲህ አሉ፥ « አሁን ወ/ስላሴ እንዳለው በጌታቸው ዙሪያ ማጣራት ስናካሂድ ከነበርነው ሶስት ሰዎች አንዱ እኔ ነኝ። እንድናጣራ ያዘዘን መለስ ነው። የቀረበልን ጥቆማ “ጌታቸው ቪላ ቤት ገንብቷል፣ ሙስና ውስጥ ገብቷል” የሚሉ ነበሩ። ረጅም ጊዜ ስናጣራ ቆየን። ነገር ግን የተባለውን ቤትም ሆነ በሙስና ያፈራው አንዳች ነገር ልናገኝ አልቻልንም። ከዚያ በጌታቸው ላይ ጥቆማውን ያቀረበው ወይም ያመጣው ማነው?.ብለን ስንጠይቅ ወ/ስላሴ መሆኑን አወቅን።

በወ/ስላሴ ዙሪያ ለምን ማጣራት አናካሂድም ብለን ጀመርን። በስሙ፣ በወንድምና እህቱ እንዲሁም በቤተሰቡና በሌሎች ግለሰቦች በሙስና መበልፀጉን አረጋገጥን» በማለት የሙስናውን ማስረጃ በዝርዝር አባይ ነብሶ ለጉባኤው አቀረቡ። ለማ/ኰሚቴ የተጠቆመው ወ/ስላሴ 2 ድምፅ ብቻ በማግኘቱና ከጨዋታ ውጭ በመሆኑ ኩም አለ። ጉባኤው በነጌታቸው አሰፋ ድል አድራጊነት ተጠናቀቀ። የሙስናዋን ፋይል የያዙት ጌታቸው አሰፋ በቅድሚያ ያደረጉት ወ/ስላሴን ከስልጣን ማባረር ነበር። ከዛም እነገ/ዋህድን ጨምሮ ለአዜብ ገንዘብ ሲረጩ የነበሩትን እነነጋ ገ/እግዚያብሄርን በሙስናው ፋይል እስር ቤት መክተት የሚለውን እቅድ ተግባራዊ አደረጉ። የደህንነቱን ቢሮ እንዳሻው ይፈነጭበት የነበረውና የአቶ መለስና አዜብ ቀኝ በመሆን አገሪቱን በአፈና መዋቅር ሲያሰቃያት የከረመው ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል በበርካታ የደህንነት አባላት ጥርስ የተነከሰበት ጭምር ነበር። ይህን የሚያውቁት ጌታቸው አሰፋ በደህንነቶች ለተከታታይ ቀናት ወ/ስላሴ እንዲደበደብ ማድረጋቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።

Image

የጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን ወደ ሕወሐት ለመመለስ የፓርቲው ቁልፍ አመራሮች በምስጢር ሲመክሩ መስንበታቸውን የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። በአቶ ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል፣ አባይ ፀሐዬ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ፣ ፀጋይ በርሔ፣ አርከበ እቁባይና ስብሃት ነጋ የሚመራው የሕወሐት ከፍተኛ አመራሮች ከዚህ ቀደም ሲካሂዱት በነበረውና ህወሀት የጠ/ሚ/ ርነት ስልጣን መልሶ መያዝ ይኖርበታል፣ የሚለውን ምክክር ከዳር ለማድረስ አቋም መያዘያቸውን ያስታወቁት ምንጮቹ በተለይ በቅርቡ የተካሄደው የአራቱ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ በብአዴንና ኦህዴድ በኩል ቅሬታና ተቃውሞ እየበረታ በመምጣቱ የሕወሐት አመራሮች ስልጣኑን በእጃቸው ለማስገባት ቆርጠው መነሳታቸውን አስረድተዋል።

በብአዴን በኩል የአቶ በረከት ስሞን ከስልጣን መገፋት በደጋፊዎችቻቸውና አመራሩ በኩል ቅሬታ መፍጠሩን የጠቆሙት ምንጮቹ በረከት ስሞን የጠ/ሚ/ር ሃ/ማርያም አማካሪ ተብለው ቢሾሙም ነገር ግን በጠ/ሚ/ር ፅ/ቤት ቢሮ እንዳልተሰጣቸውና የተሰጣቸው ካዛንቺስ አካባቢ የሚገኘው የቀድሞ የደህንነት ቢሮ መሆኑን ምንጮቹ ገልፀው በዚህ ቢሮ ኩማ ደመቅሳ እንደሚገኙና በጠ/ሚ/ር ፅ/ቤት አዲስ ቢሮ ተገንብቶ ይሰጣችኋል የተባለው ተግባራዊ እንዳልሆነ አያይዘው አስረድተዋል።

በጠ/ሚ/ር ፅ/ቤት ቢሮ የተሰጣቸውና ከአቶ ሃ/ማርያም እያንዳንዷ እንቅስቃሴ ያልተለዩት አርከበ እቁባይ፣ አባይ ፀሐዬና ፀጋይ በርሄ ሲጠቀሱ በም/ጠ/ሚ/ር ቦታ ደብረፂዮን መኖራቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል። ለሕወሐት አመራሮች ሌላው ራስ ምታት የሆነባቸው የኦህዴድ ፓርቲ ከሕወሐት እኩል መገዳደር እያሳየ መምጣቱ ነው ያሉት ምንጮቹ በተለይ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ ኦህዴድ የተለያዩ የስልጣን ጥያቄዎች በማንሳት ድፍረት እያሳየ መጥቷል ብለዋል።

ሕወሐት የጠ/ሚ/ርነት ስልጣኑን መቆጣጠር የፈለገበት አንዱ ምክንያት ይህ መሆኑን ምንጮቹ አልሸሸጉም። በኦህዴድ በኩል የጠ/ሚ/ር ስልጣን ለኦሮሞ ይገባል በሚል ከዚህ ቀደም የነበረው የሕወሀት ስልጣንን አንሰራፍቶ የመያዝ አካሄድ መገታት አለበት የሚል አቋም እንደተያዘ ያስረዱት ምንጮቹ በተለይ የህወሀት አመራር የኦህዴድ አካሄድ እንዳልተዋጠለትና ከዚህ ቀደም ማን ጠ/ሚ/ር ስልጣን ይያዝ የሚለው የህወሀት ምክክር በእንጥልጥል ቆይቶ በቅርቡ ግን ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል ስልጣኑን መያዝ አለበት የሚል ውሳኔ ላይ መድረሱን ምንጮቹ አስገንዝበዋል። የደብረፂዮን ወደ ጠ/ሚ/ር ስልጣን የማምጣት እቅድ በተመለከተ አርከበ እቁባይ ተቃውሞ አሰምተው መከራከራቸውንና በመጨረሻ ግን ኦህዴድና ብአዴን ለመጨፍለቅ ሲባል አርከበ መቀበላቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል። የህወሀት አመራሮች ከስምምነት የደረሱበትን ጉዳይ ከቀጣዩ ምርጫ በኋላ ጠ/ሚ/ር አቶ ሃ/ማርያም ደሳለኝን ከብቃት ማነስ ጋር በማያያዝ ከስልጣን ለማውረድና በምትካቸው የጠ/ሚ/ርነቱን ቦታ ለደብረፂዮን ለመስጠት መወሰናቸውን ምንጮቹ አጋልጠዋል።

(ጨዋታው ተጀምረ፡፡ ይህ ጨዋታ ለሕዳሴው ግድብ ድጋፍ ሲባል የሚደረግ መሆኑን ያለማሳወቅ አያስፈልግም፡፡ ያለእንደዚህ ያሉ የድጋፍ ሰጪ ጨዋታዎች የህዳሴው ግድብ ፕሮጄክት አይጠናቀቅም ሲሉ ቃል አቃባዩ እንጂነር ስመኘው ገልፀዋል፡፡) በሃገራችን ኢትዮጵያ እንደ ውሃ ወለድ በሽታዎቻችን ብዛት ሁሉ ሁኔታ-ወለድ የሆኑ ብዙ ክስተቶች ያጋጥማሉ፡፡ከነዚህ መሃል በተለይ በፖለቲካው መስክ ሰዎች የሚያገኙት ስፍራ ከማንነታቸው ጋር የማይገጥም እየሆነ ተቸግረናል፡፡ አሁን ባለው ነባራዊ […]

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እጅግ ደማቅ በሆነ ሁኔታ ያካሄደ ሲሆን፤ በጠቅላላ ጉባኤው ሶስት ዋና ዋና ተግባራት ተካሄደዋል፤ የመጀመሪው አጀንዳ ኢር ግዛቸው በራሳቸው ፍቃድ ስልጣናቸውን በለቀቁ ጊዜ የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤው በሰጠው ስልጣን መሰረት አዲስ የፓርቲው ፕሬዚደንት መምረጡ ጉባኤው ተቀብሎ ያፀደቀ ሲሆን፤ በዚህ መሰረትም አቶ በላይ ፍቃዱ የፓርቲው ፕሬዚደንት ሆነው […]

የጠ/ሚ/ር ስልጣን ወደ ሕወሐት ለመመለስ የፓርቲው ቁልፍ አመራሮች በምስጢር ሲመክሩ መስንበታቸውን የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። በአቶ ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል፣ አባይ ፀሐዬ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ፣ ፀጋይ በርሔ፣ አርከበ እቁባይና ስብሃት ነጋ የሚመራው የሕወሐት ከፍተኛ አመራሮች ከዚህ ቀደም ሲካሂዱት በነበረውና ህወሀት የጠ/ሚ/ ርነት ስልጣን መልሶ መያዝ ይኖርበታል፣ የሚለውን ምክክር ከዳር ለማድረስ አቋም መያዘያቸውን ያስታወቁት ምንጮቹ በተለይ በቅርቡ […]



ጸሓፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
——–
    ኦሮማይ ከልቡ መጽሐፍ ነው፡፡ በአማርኛ ልብ-ወለድ መጻሕፍት (Novel) ታሪክ በጣም አነጋጋሪውና አከራካሪው መጽሐፍ ነው፡፡ እስከ አሁን ድረስ የህዝብ ፍቅር ካልተነፈጋቸው ጥቂት መጻሕፍት አንዱም ነው፡፡ በህይወቴ ብዙ ጊዜ እየደጋገምኩ ካነበብኳቸው መጻሕፍት መካከልም በመጀመሪያው ረድፍ ይሰለፋል፡፡ ይሁንና ሰዎች ለዚህ መጽሐፍ ያላቸው አድናቆት እንደየ አመለካከታቸው ይለያያል፡፡
  መጽሐፉ የብዙዎቹን አትኩሮት የሳበው ታሪኩ እውነት ነው ስለተባለ እና በመጽሐፉ ሳቢያም የደራሲው ህይወት ለአደጋ በመጋለጡ ይመስለኛል፡፡ ከመጽሐፉ ዐቢይ ገጸ-ባህሪያት አንዱ የሆኑት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ “የደም እምባ” በተሰኘው መጽሐፋቸው ተመሳሳይ እይታ አንጸባርቀዋል፤ እንደ ሻለቃ ዳዊት አባባል ኦሮማይ ባይታገድ ኖሮ ተወዳጅነቱ ይሄን ያህል አይገዝፍም ነበር፡፡ ሆኖም እኔ በዚህ አባባል አልስማማም፡፡ ደራሲው ባይሞት እና ታሪኩ እውነተኛ ባይሆን እንኳ “ኦሮማይ” ተደናቂ የመሆንን እድል አያጣም ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ ለዚህም በርካታ አብነቶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡
  
   “ኦሮማይ” በቅድሚያ ቀልብን የሚስበው በአጻጻፍ ብሂሉ ነው፡፡ ደራሲው ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው አጫጭር ዐረፍተ ነገሮችን ይጠቀማል፡፡ ይህም አንባቢው የመጽሐፉን የትረካ ቅደም ተከተል ሳይስት ድርሰቱን ያለድካም እንዲያጣጥም ያግዘዋል፡፡ ደራሲው ጠጣር ሃሳቦችን በቀላሉ ይዘረዝራል፡፡ የዘመኑ መንግሥት አሰራርን ለተደራሲው በሚገባው ቋንቋ ቀለል አድርጎ ያስረዳዋል፡፡ በሌላ በኩል መጽሐፉ ኪናዊ ውበቱን እንዳይስት ደራሲው በእጅጉ ተጠቧል፡፡ ዘይቤአዊ አባባሎችን ከዘመኑ የአነጋገር ፋሽን ጋር እየቀላቀለ አንባቢውን ያዝናናዋል፡፡ በተለይም “ኦሮማይ” ፈጠራ እየነጠፈ በዘመቻ ግርግር እና በንድፈ-ሓሳብ ዝብዘባ የሚፈበረኩ ቃላት የድርሰቱን ጎራ እያጠለሹ በመጡበት ዘመን አንባቢው በማይሰለቸው የቋንቋ ጥበብ የተጻፈ በመሆኑ የደራሲውን ልዩ ተሰጥኦ በጉልህ ያስረዳል፡፡ ሆኖም ኦሮማይ የዚያ ዘመን ድርሰት ብቻ አይደለም፡፡ በዚህ ዘመንም እንኳ ተደግመው ሊጻፉ ከማይችሉ ድርሰቶች መካከል ሊመደብ ይችላል፡፡ 
      ይበልጥ አስደናቂው ነገር ደግሞ ወዲህ ነው፡፡ ደራሲው ያንን ውብ መጽሐፍ የጻፈው በጥቂት ወራት ውስጥ ነው፡፡ ይገርማል! ሰውዬው በወቅቱ ምክትል የማስታወቂያ ሚኒስትር ነበር (በደንበኛ ስሙ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ቋሚ ተጠሪ ይባል ነበረ)፡፡ የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ሆኖም ይሰራ ነበር፡፡ በአዲስ ዘመን እና በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጦች ዝግጅትም ይሳተፋል፤ ዝግጅታቸውን በበላይነት ይቆጣጠራል፡፡ ቱባ ባለስልጣን በመሆኑ የብዙ ኮሚቴዎች አባል መሆኑም ይታመናል፡፡ በርካታ የቢሮክራሲ ስራዎችም ነበሩት፡፡ እና ከነዚህ ሁሉ የስራ ጋጋታዎች ጋር የሚታገል ሰው ያንን የመሰለ ውብ መጽሐፍ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንዴት ብሎ ነው የጻፈው? ይህንን በቀላሉ ማመን ይቻላል? በትርፍ ጊዜው መጻፉ ይቅርና የሙሉ ጊዜ ደራሲ ቢሆን እንኳ አስቸጋሪ መሆኑ አይቀርለትም፡፡ ሰውዬው ግን በዓሉ ነውና ቻለው! የስራ መደራረብ “ሳይበግረው” ኦሮማይን ከዘጠኝ ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እንዲያ ከሽኖ አቀረበው (የቀይ ኮከብ ዘመቻ ያበቃው በየካቲት ወር 1974 ነው፤ ኦሮማይ የታተመው በታህሳስ ወር 1975 ነው)፡፡ ችሎታ ማለት እንዲህ ነው!!
 ለኦሮማይ ዘመን አይሽሬነት ሁለተኛ አብነት ሆኖ የሚጠቀሰው ደግሞ የመጽሐፉ ጭብጥ ነው፡፡ በዚህ ላይ በርካታ ሰዎች የተለያየ አስተያየት ነው ያላቸው፡፡ አንዳንዶች በዓሉ ኦሮማይን የጻፈው የቀይ ኮከብ ዘመቻ ውጥረትና ውድቀትን ለመግለጽ ስለፈለገ ነው ይላሉ፡፡ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ “የመጽሐፉ ጭብጥ በርዕሱና በመጨረሻው ዐረፍተ ነገር ላይ ነው የሚገኘው” ብለው ነገር፡፡ አቶ መለስ ንግግራቸውን ሲያሰፉም “በዓሉ በመጽሐፉ  “እናንተ ደርጎች በኤርትራ ላይ ሙዝዝ ካላችሁ በአዲስ አበባ ያላችሁንም ስልጣን ታጣላችሁ” የሚል መልዕክት ነው ያስተላለፈው” ብለዋል፡፡ አቶ መለስ ይህንን ትንተና የሰጡት ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር የአልጀርሱን ስምምነት ፈርማ የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ በምትጠባበቅበት ወቅት “የስምምነቱ አካሄድ ኢትዮጵያን የሚጎዳ ነው” የሚል ሃሳብ ለሰነዘሩ ተቃዋሚዎች መልስ በሚሰጡበት ጊዜ ነው (ባልሳሳት ጊዜው የካቲት 1994 ይመስለኛል)፡፡ ሆኖም የኦሮማይ ጭብጥ በእንዲህ ዓይነቱ የፖለቲካ ዘውግ ብቻ የታጠረ አይደለም፡፡ ኦሮማይ በዘመኑ “አይነኬ” (taboo) የነበሩ በርካታ ጉዳዮችን ይነካካል፡፡ ለማስረዳት ይፈቀድልኝ፡፡
   
   የደርግ መንግሥት በወቅቱ የሀገሪቱን ህዝብ ከአቅሙ በላይ እያሯሯጠው ነበር፡፡ ህዝቡ በየዓመቱ ከሚመጣበት የዘመቻ መአት ሳያገግም በሀገሪቱ ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም የማያውቀው ግዙፉ የቀይ ኮከብ ሁለገብ ዘመቻ በጫንቃው ላይ ወረደ (ዘመቻው የጠየቀው የሰው ሀይልና ማቴሪያል ሳይደመር ሁለት ቢሊዮን ብር ወጥቶበታል፤ ይህም በወቅቱ ከሀገሪቷ በጀት ግማሽ ያህሉን ይሸፍናል)፡፡ ሆኖም በዘመኑ ወታደራዊው መንግሥት ያሻውን ቢያቅድና ቢፈጽም አይደፈሬ ነውና ማንም ሰው አፍ አውጥቶ አልተቃወመውም፡፡ በዓሉ ግርማ ግን ለመጪውም ዘመን ትምህርት በሚሆን መልኩ የቀይ ኮከብ ዘመቻን በግልጽ ቋንቋ ሄሶታል፡፡ ለምሳሌ በመጽሐፉ ውስጥ የጋዜጠኛ ጸጋዬ ኃይለማሪያም እጮኛ እንዲህ ትላለች፡፡
  
  “ኤጭ እቴ! ለሁሉም ነገር ቸኩሎ መሞት! ነጋ ጠባ ዘመቻ! እድገት በህብረት ብሎ ዘመቻ! ለጦርነት ዘመቻ፡፡ የኢኮኖሚ ግንባታ ዘመቻ፡፡ ማይምነትን ለማጥፋት ዘመቻ፡፡ የቁጥጥር ዘመቻ፡፡ አሁን ደግሞ የኤርትራን ችግር ለመፍታት ዘመቻ፡፡ የዘመቻ ባህል ፈጥረናል፡፡ ያለዘመቻ ኖረን የምንሞትበት ቀን መቼ ይሆን?”  (ኦሮማይ ፤ ገጽ 9)
 ጋዜጠኛው የመንግሥት ባለስልጣን ሆኖ ለእጮኛው ንግግር የሰጠው ምላሽ ይበልጥ የሚደንቅ ነው፡፡ “ጊዜ ያጥረናል፤ እብዶች ነን፤ ችኩል ትውልድ፤ ያበደ ትውልድ…” ወዘተ.. ይላታል (ኦሮማይ፤ ገጽ 10)
  በአንድ በኩል ጸሓፊው የዘመኑ ባለስልጣናት ለቀይ ኮከብ ዘመቻ መሳካት አኩሪ ገድል ሲፈጽሙ ያሳየናል፡፡ ወዲያው ዞር ይልና ደግሞ የመንግሥቱ የቀን ቅዠትና ሀገር አጥፊ ፖሊሲ ያስከተለውን ቀውስ በራሳቸው በባለስልጣናቱ አንደበት ይገልጽልናል፡፡ ለምሳሌ ከመጽሐፉ ዐቢይ ገጸ-ባህሪያት አንዱ የሆነው ኢኮኖሚስቱ መጽሐፈ ዳንኤል ዘመቻው በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ የሚፈጥረውን አሉታዊ ጫና በማስረዳት የዘመኑን አመራር እንዲህ ይሸረድደዋል፡፡
   “ይህንን የቆየ ችግር በዘመቻ እንፈታለን ብለን ስንረባረብ ከአሁኑ ሌላ ችግር እየፈጠርን ነው፤ 450 ከባድ የጭነት መኪናዎች፤ 250 ሼልቶ፣ 200 ከነተሳቢያቸው ወደ ሰሜን ማዞር ምን ማለት ነው? ባጭሩ ኢኮኖሚው ተናግቷል ማለት ነው፤ ደሞ አሁን የመኸር ጊዜ መሆኑን አትርሳ” (ኦሮማይ፤ ገጽ 75)
     ጋዜጠኛው በዚህ አባባል ተናዶ “ስብሰባው ላይ ምን ዘጋህ? ቅድም እንዲህ ብለህ አትናገርም ነበር፡፡ መድረኩ ለማንም ክፍት ነበር፡፡ማን ከለከለህ?” ሲለው መጽሐፈ ዳንኤል “ትቀልዳለህ ልበል?” በማለት በአጭሩ መልሶለታል፡፡ መጽሐፈ ልክ ነው፡፡ አንድ ሰው በሚፈልገው መንገድ ብቻ መደስኮር በሚፈቀድበት ስብሰባ ሐቁን እናገራለሁ ቢል የሚደርስበትን ቅጣት በደንብ ያውቀዋል፡፡ ለዚህም ነው በስብሰባና በጉባኤ ፊት እያስመሰሉ መለፍለፍ እና ለክፉ አሳልፎ የማይሰጥ ወዳጅ ሲገኝ ሐቁን መናገር የዘመኑ ወግ ሆኖ የቆየው፡፡
 
   በተመሳሳይ መልኩ ሰለሞን በትረ-ጊዮርጊስ የተባለው ገጸ-ባህሪ የያኔውን የፕሮፓጋንዳ አካሄድ እስኪበቃው ድረስ ሲወርፍ ይታያል፡፡ “እናንተ ጋዜጠኞች ጭንቀታችሁ ሁሉ ስታቲስቲክስ ነው፤ ይህን ያህል ሄክታር መሬት ታረሰ፤ ይህንን ያህል ህዝብ ተደራጀ፤ ይህን ያህል ሰዎች ከመሀይምነት ተላቀቁ፤ ነው የምትሉት፡፡ እንዲያው ወሬአችሁ ሁሉ ስታቲክቲክስ ነው፤ ዘገባችሁ ሰው ሰው አይሸትም፤ ስለ አሐዝ ስትጨነቁ ሰው ትረሳላችሁ” ይላል (ኦሮማይ፤ ገጽ 67)፡፡ እነኝህን የመሳሰሉ የስርዓቱን ጉድፍ የሚያሳዩ በርካታ አንቀጾችን መልቀም ይቻላል፡፡
    የቀይ ኮከብ ዘመቻ የመጨረሻ ግብ ናቅፋ የሚገኘውን የሻዕቢያ ዋና የዕዝ ማዕከል መቆጣጠር ተደርጎ ይታሰብ ነበር፡፡ ሆኖም ናቅፋ በቀላሉ የምትደፈር ሆና አልተገኘችም፡፡ ሺዎች እንደ ቅጠል ረግፈዋል፡፡ ሺዎች ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነዋል፡፡ ሁኔታውን በቅርበት የታዘበው ጋዜጠኛ ጸጋዬ ኃይለማሪያም ጦርነቱ ከኪሳራ ውጪ የሚፈይደው ነገር እንደሌለ ተገንዝቧል፡፡ ከናቅፋ ወደ አፍአበት ሲመለስ “አይዞን! ገና ሺህ ናቅፋዎች ይጠብቁናል” ብሎ ለተናገረው የዘመኑ ከፍተኛ ባለስልጣን “እኔ አንድ ናቅፋ ከወዲሁ በቅቶኛል፤ የጦርነትን አስከፊ ገጽታ ከአሁን በኋላ ላለማየት ቆርጫለሁ” በማለት ተቃውሞውን ገልጿል (በዓሉ ጦርነቱን ከተቃወመባቸው ዐረፍተ ነገሮች መካከል ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጠው ይህኛው ነው)፡፡
       *****
 “ኦሮማይ” ፈርጀ ብዙ የዕውቀት ድርሳን ነው፡፡ ረጅምና ውስብስብ የሆኑ እውነተኛ ታሪኮችን እጥር ምጥን አድርጎ በቀላሉ ያስነብበናል፡፡ ለምሳሌ የኤርትራ ችግር መሰረታዊ ምንጭ ምን እንደሆነ መረዳት የሚፈልግ ሰው ከሰለሞን በትረጊዮርጊስ ታሪካዊ ትንተና ብዙ ቁምነገሮችን ይጨብጣል (ኦሮማይ፡ ገጽ 78-86)፡፡ እንግሊዝ በኤርትራ ምድር የቀበረችው ፈንጂ፤ የኤርትራ ክፍለ ሀገርን ከኢትዮጵያ ጋር ለመቀላቀል የተደረገው ጥረት፤ የጀብሃና ሻዕቢያ አነሳስና በመካከላቸው የተፈጠረው ፍጭት፣ አብዮታዊ ሰራዊት ኤርትራን ከአማጺያን ለማጽዳት ያደረገው ዘመቻ ወዘተ… በሰለሞን አንደበት በሰፊው ተተንትነዋል (እርግጥ ትንተናው ሙሉ በሙሉ ትክክል ነው ለማለት አይቻልም፤ ግማሽ ያህሉ የደርግ መንግሥት በሚፈልገው መልክ የተቀናበረ ነው)፡፡
  
   የጎሪላ እና መደበኛ የውጊያ ስልትን በተነጻጻሪ ማወቅ የሚፈልግ ሰው ከኦሮማዩ ኮሎኔል ታሪኩ ወልዳይ ትንታኔ ብዙ ነገሮችን ይማራል፡፡ ኮሎኔል በትሩ ተሰማ እና አጋዥ ቡድኑ (እነ ተክላይ ዘድንግል ያሉበት) የዘመኑ የኢንተሊጀንስ ጥበብና ስልት ምን ይመስል እንደነበር በቃልና በድርጊት ያሳዩናል፡፡ ጋዜጠኛው ጸጋዬ ኃይለማሪያም አስቸጋሪውን የናቅፋ ተራሮች የመሬት አቀማመጥ ለዓይናችን ወለል ብሎ እስኪታየን ድረስ በማይሰለቸው ብዕሩ እያጣፈጠ ይተርክልናል፡፡ ስዕላይ ባራኺ እና ጓዶቹ ደግሞ የሚያስገርሙ ጀብዶችን እየተገበሩ ሻዕቢያ በሰርጎ ገቦቹ አማካኝነት አስመራን እንዴት ያሸብራት እንደነበር ያሳዩናል፡፡ የአስመራ ነዋሪዎች የአኗኗር ወግና ማሕበራዊ ህይወት፣ የከተማዋ ታዋቂ ሰፈሮችና ሆቴሎች፤ የመንገዶቹ ውበትና አቀማመጥ ወዘተ… በመጽሐፉ ዘርዘር ብለው ተጽፈዋል፡፡ በኔ እይታ አንድ ሰው ልብ ወለድ ተብሎ የተጻፈውን “ኦሮማይ”ን ቢያነብ ከአስር መጻሕፍት የሚያገኘውን ዕውቀት ሊገበይ ይችላል፡፡
        *****
     እንደዚያም ሆኖ ግን “ኦሮማይ” ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ አይደለም፡፡ ደራሲው የመጽሐፉን ተነባቢነት ለማጉላት ምናባዊ ገጸ-ባህሪዎችንና ታሪኮችን ጨማምሯል፡፡ ለምሳሌ ደራሲው የሁለት ሰዎችን ታሪክ አዳብሎ “ስዕላይ በራኺ” የተባለ ገጸ-ባህሪ ፈጥሮልናል፡፡ እንደዚሁ ደግሞ በመጽሐፉ ውስጥ የሻዕቢያ ሰዎች በዚሁ ስዕላይ በራኺ በተባለ ገጸ-ባህሪ መሪነት የሚያካሄዱት “ኦሮማይ” የተሰኘ ስውር ኦፕሬሽን የደራሲው ፈጠራ ነው (“ቢሮክራሲ” የተባለው የስለላ ኔትወርክ ግን ትክክለኛ ነው)፡፡
 
   ከኦሮማይ ገጸ-ባህሪያት መካከል ኮሎኔል መንግሥቱ ሀይለማሪያምና ኢሳያስ አፈወርቂን የመሳሰሉት በእውነተኛ ስማቸው ተጠቅሰዋል፡፡ አንዳንዶቹ ግን ስም የለሽ ሆነው በድርጊታቸው ብቻ ተገልጸዋል (ለምሳሌ “የቀይ ኮከብ ሁለገብ ዘመቻ ዋና ጸሐፊ” ተብለው በስራ መደባቸው ብቻ የተጠቀሱት ባለስልጣን አቶ አማኑኤል አምደሚካኤል ናቸው)፡፡ ከፊሎቹ ገጸ-ባህሪያት በእውነታው ዓለም የሚታወቁበት ስም በመጽሐፉ ውስጥ ተቀይሯል፡፡ ከነርሱ መካከል የጥቂቶቹ ትክክለኛ ስም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
1.      ኮሎኔል በትሩ ተሰማ= ኮሎኔል ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ (በደርግ መንግሥት የህዝብ ደህንነት ጥበቃ ሚኒስትር፤ ሆኖም ኮሎኔሉ “የኔ ምክትል ነው እንጂ እኔ አይደለሁም፤ እኔ በቀይ ኮከብ ዘመቻ አስመራ አልሄድኩም” በማለት አስተባብሏል)።
2.     ኮሎኔል ታሪኩ ወልዳይ= ኮሎኔል ተሻገር ይማም (የአንበሳው ሶስተኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ የነበረ፤ በ1974 በናቅፋ በተካሄደው አደገኛ ጦርነት ማብቂያ ላይ ራሱን የገደለ)።
3.     መጽሐፈ ዳንኤል= አቶ ፋሲካ ሲደልል (የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የማዕከላዊ ፕላን ሚኒስትር የነበረ)
4.     የሺጥላ ማስረሻ= አቶ ሽመልስ ማዘንጊያ (የኢሠፓ የፖሊት ቢሮ አባልና የርዕዮተ ዓለም ጉዳዮች ሃላፊ የነበረ)
5.     ጸጋዬ ሀይለማሪያም= የበዓሉ ግርማ ግርማ እና የቴሌቪዥን ጋዜጠኛው የጌታቸው ኃይለማሪያም ቅልቅል ይመስላል፡፡  
6.     ተድላ ረጋሳ= ሻለቃ ፍሰሓ ገዳ (የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የደርግ መንግሥት የፕሮቶኮል ሹም)
7.     ሰለሞን በትረ ጊዮርጊስ= ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ (በቀይ ኮከብ ዘመን የኤርትራ ክፍለ ሀገር ኢሠፓአኮ ተጠሪ እና የክፍለ ሀገሩ የበላይ አስተዳዳሪ፣ በኋላም የእርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ኮሚሽን ኮሚሽነር፤ በ1978 ከደርግ መንግሥት ተነጥሎ ወደ ውጪ ሀገር የኮበለለ)
8.     ስዕላይ ባራኺ= የሁለት ሰዎችን ታሪክ በመቀላቀል የተፈጠረ ነው፡፡ አንደኛው ተስፋሚካኤል ጆርጆ ነው (አቶ ተስፋሚካኤል በሀይለስላሴ ዘመን የደቀምሐረ ወረዳ ገዥ የነበረ ሲሆን በ1963 ኢሳያስ አፈወርቂን ከሲ.አይ.ኤ ጋር በማገናኘት ቁልፍ ሚና ተጫውቷል፣ ይህ ሰው በ1984 መጨረሻ ላይ በሻዕቢያ አዳኝ ኮማንዶዎች አዲስ አበባ ውስጥ ቫቲካን በሚባለው ሰፈር ተገድሏል)። ሁለተኛው ሰው ተክላይ አደን ይባላል (ተክላይ አደን የሻዕቢያ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የድርጅቱ የፖለቲካ ትምህርት ቤት ሃላፊ ነበር፤ በኋላ እጁን ሰጥቶ በሀገር ውስጥ ሲኖር ከቆየ በኋላ ደርግ ሲደመሰስ ወደ አውሮጳ ሄዷል)፡፡
9.     “ቢሮክራሲ”= አፈወርቂ ተወልደ መድሕን (ደሴ የተማረ የሻዕቢያ የውስጥ አርበኛና ሰላይ፣ “ቢሮክራሲ” በሚል ስም የሚታወቀውን የስለላ ኔትወርክ የሚመራው እርሱ ነው፡፡ በኋላ ግን ድሬ ዳዋ ላይ ተይዞ ተረሽኗል)፡፡
       *****
ስለኦሮማይ ይህንን ብያለሁ፡፡ ወደፊት አዲስ ነገር ከተገኘ መመለሴ አይቀርም፡፡ እስከዚያው ሌሎቻችሁ የምታውቁትን ጨምሩበት፡፡
   ሰላም!
አፈንዲ ሙተቂ
ሸገር-አዲስ አበባ
ጥቅምት 13/2006


—–
ጸሓፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
——
ከሰው ቤት ትቼው የሄድኩትን የመጽሐፍ መደርደሪያዬን ስበረብር “መስታወት” የተሰኘ የድሮ መጽሔት ምዝዝ ብሎ ወጣ፡፡ እንደ ዋዛ ዐይኔን ከመፅሔቱ ሽፈን ላይ ጣል ሳደርግም የ“አያልነሽ” ፎቶ ታየኝ፡፡ ከፎቶው አጠገብም እንዲህ የሚል ጽሑፍ ሰፍሮ አነበብኩኝ፡፡
   “አቶ መለስ የራሷ ድርጅት የላትም፤ እራሷ ድርጅት ትሆን እንጂ” ያሉት ሳያውቁ ቀርተው ነው ብሎ ማመን ያዳግተኛል”፡፡
    አቶ መለስ ዜናዊ እንዲህ ማለታቸው የተነገረው ገና ጫካ ሳሉ ከሲ.አይ.ኤው ፖል ሂንዝ ጋር ባደረጉት ውይይት እንደሆነ ተዘግቧል (በርግጥ አቶ መለስ ያሉት “ራሷ ድርጅት ናት” ሳይሆን “እርሷ በራሷ የምትታገል ታጋይ ናት እንጂ ከየትኛውም ድርጅት ጋር የወገነች አይመስለኝም” ነው፡፡ ፖል ሄንዝ የውይይቱን ጭማቂ በአሜሪካ ይፋ ካደረገ በኋላ በተለያዩ መጽሔቶች ላይ ታትሞ ነበር)፡፡
   ወይ “አያልነሽ”! ስንቱን ያንቀጠቀጠች ጀግና መሰለቻችሁ?! ለደርግ ራስ ምታት ሆና በጎንደር እና በጎጃም እንደፈለገችው ትንሸራሸር ነበር፡፡ በርሷ ጀግንነት የተመሰጠው የጎጃም ህዝብ “አያልነሽ!….ክላሽ ልግዛልሽ!” እያለ በሰርግ ላይ የሚዘፈን የአጀብ ዜማ እስከ መውጣት ደርሷል፡፡ በደርግ እግር የተተካው ኢህአዴግም በርሷ ምክንያት ክፉኛ ታውኮ ነበር፡፡ እርሷ ስትያዝ ደግሞ ኢህአዴጎች በየስፍራው የደስታ መድፍ መተኮሳቸው በሰፊው ተወርቷል፡፡ 
   የ“አያልነሽ” ነገር በጊዜ ሰረገላ ወደ ኋላ እያበረረኝ የድሮ ትዝታዬን ቀሰቀሰው፡፡ ስለ“አያልነሽ” አመጸኛነት ሳስብ የያኔው ትውልድ የዓላማ ጽናት ከፊቴ እየመጣ በሃሳብ አስተከዘኝ፡፡ “የኔ ትውልድስ እንደዚያ ዓይነት ፋኖዎችን ያወጣ ይሆን?” እያልኩ ደጋግሜ ራሴን ጠየቅኩኝ፡፡
  
    ከሀገር ጭምር አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ መነጋገሪያ ለመሆን የበቃችው ያቺ ሴት ዛሬ በትግሉ ውስጥ የለችም፡፡ ወደ ሰላማዊ ኑሮ ገብታ የልጆች እናት ሆናለች፡፡ ሆኖም የታሪካችን አካል ነችና በወቅቱ ስለርሷ ላልሰሙት ታሪኳን የማድረስ ግዴታ አለብን፡፡ እነሆ የአያልነሽን ወግ ከብዙ በጥቂቱ ልናወጋችሁ ነው፡፡   
*****
   የደርግ መንግሥት በግንቦት 20/1983 ሲገረሰስ ኢሕአዴግ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በመጣመር የሽግግር መንግሥት እንዲመሰርት ተወስኖ ነበር፡፡ ኢሕአዴግም በለንደኑ ኮንፈረንስ የተወሰነውን ውሳኔ ተቀብሎ ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ለልዩ ልዩ ድርጅቶችም የጉባኤ ጥሪ አስተላለፈ፡፡ በዚህም መሰረት በርካታ ድርጅቶች ወደ አዲስ አበባ መጉረፍ ጀመረ፡፡ ይሁንና በዚያ ዘመን ከኢህአዴግና ከኦነግ ቀጥሎ ከፍተኛ ስም የነበረው የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሀይሎች ቅንጅት (ኢ.ዲ.ሀ.ቅ) በጉባኤው እንዳይሳተፍ ተከለከለ (ኢዲሀቅ የኢህአፓ፣ የመኢሶን፣ የኢፒዲኤ እና የኢዲዩ ጥምረት ነበር)፡፡ በወቅቱ የኢትዮጵያ ጊዜያዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ ኢዴሀቅ በጉባኤው ላይ እንዳይሳተፍ የተከለከለበትን ምክንያት በሰኔ ወር አጋማሽ ለጋዜጠኞች ሲያብራሩ
  “ኢዴሀቅ በጊዜያዊ መንግሥቱ ላይ ጦርነት አውጇል፡፡ እስከ አሁን ድረስ ያወጀውን የጦርነት አዋጅ አላነሳም፤ ይህም የጦርነት አዋጅ ድርጅቱ በሰላምና በዲሞክራሲ ጉዳይ ላይ በሚመክር በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንደሌለው ያሳያል” ብለው ነበር፡፡
  
  አቶ መለስ እንዲህ በማለት የገለጹት ኢዴሀቅ የተመሰረተው በመጋቢት 1983 ነበር፡፡ ይሁንና ይህ ድርጅት በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ በጊዜያዊ መንግሥቱ ላይ ጦርነት አውጇል መባሉ ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኖ ነበር (ጊዜያዊ መንግሥቱ በግንቦት ወር 1983 የደርግ ውድቀትን ተከትሎ ነበር የተመሰረተው)፡፡ ኢዴሀቅ የደርግ ብሔራዊ ሸንጎ በመጨረሻ ጉባኤው ያስተላለፈውን ውሳኔ በመደገፍ ሚያዚያ 16/1983 መግለጫ አውጥቶ ነበር፡፡ በመሆኑም አቶ መለስ “ኢዴሀቅ ጦርነት አውጇል” ያሉት ያንን መግለጫ ተንተርሰው እንደሆነ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች በወቅቱ የተናገሩት ጉዳይ ነው፡፡
           *****
   ከጥቂት ጊዜ በኋላ አቶ መለስ የተናገሩት የጦርነት ወሬ ውሸት እንዳልሆነ የሚያረጋግጥ ጭምጭምታ ተሰማ፡፡ ከወደ ጎንደርና ጎጃም አካባቢ የጦርነት ዜና መናፈስ ጀመረ፡፡ ኢህአዴግ እና አንድ ያልታወቀ ሀይል ብርቱ ውጊያ ላይ መሆናቸው ተነገረ፡፡ የዚያ ያልታወቀ ሀይል ኮማንደርም ሴት ናት መባሉ ደግሞ የብዙዎችን ቀልብ ሳበ፡፡ ያ ሀይል ማን ነው? ሴቲቷስ ማን ናት?
   ኢህአዴግ በወቅቱ ስለውጊያው ትንፍሽ አላለም፡፡ ከአሜሪካና ከአውሮፓ የሚተላለፉ የተቃዋሚ ሬድዮዎችና አንዳንድ በራሪ ወረቀቶች ነበሩ ዜናውን ሲያስተላልፉ የነበሩት፤ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮም ወሬውን አልፎ አልፎ ይነካካ ነበር፡፡ ከነዚያ ምንጮች ለማወቅ እንደተቻለው በወቅቱ ከኢህአዴግ ጋር ሲዋጋ የነበረው የኢህአፓ ሰራዊት ነው፡፡ የሰራዊቱ ኮማንደርም “አያልነሽ” ነበረች፡፡ በርሷ የሚመራው ጦር ከ1970ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ በምዕራብ ጎንደር ቆላማ ክፍል (ወገራ፣ ጭልጋ፣ ቋራ ወዘተ…) እና በመተከል አውራጃ ሲንቀሳቀስ ነበር፡፡ (“መተከል” በዘመኑ የጎጃም ክፍለ ሀገር ትልቁ አውራጃ ሲሆን በደርግ የመጨረሻ ዓመታት ራሱን ችሎ “የመተከል አስተዳደር አካባቢ” ተብሎ ተሰይሞ ነበር፡፡ “መተከል” በአሁኑ ዘመን የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል አካል ሆኗል)፡፡
 
    አያልነሽ ደርግን ስትዋጋ ለብዙዎች ተራ ሽፍታ ትመስል ነበር፡፡ ይህም የደርግ ፕሮፓጋንዳ ክፍል የኢህአፓን መኖር ለህዝቡ ለማሳወቅ ባለመፈለጉ ምክንያት የመጣ ነው፡፡ ደርግ “ኢህአፓ ተደምስሷል” ብሎ በይፋ አውጆ ስለነበር አያልነሽ የኢህአፓ ኮማንደር መሆኗ ከተገለጸ “ኢህአፓ” አሁንም አለ እንዴ?” የሚል ጥያቄ ከህዝቡ ይነሳብኛል የሚል ፍርሃት ነበረው፡፡ ለዚህም ነበር የደርግ ሰዎች ኢህአፓን ትተው “ አያልነሽ… አያልነሽ..” ሲሉ የነበሩት፡፡ እንደ ደርግ ሰዎች አባባል “አያልነሽ ቀኛዝማች ስሜነህ የሚባሉ ጎንደሬ ልጅ ናት፡፡ የምትዋጋውም አባቷ በአብዮት ሀይሎች ስለተገደለባት የአባቷን ደም ለመበቀል” ነው፡፡
   ነገሩ ግን እውነት አልነበረም፡፡ አያልነሽ የኢህአፓ ሰራዊት የምዕራብ ክፍል ኮማንደር ነበረች፡፡ ከሰራዊቱ ጋር የተቀላቀለችውም በቂም በቀል ተነሳስታ ሳይሆን ድርጅቱ የከተማ የትጥቅ ትግሉን ትቶ ወደ ገጠር ባፈገፈገበት ጊዜ ነው፡፡ ታዲያ አያልነሽ የኢህአፓ አባል የሆነችው በልጅነቷ (በአስራ አንድ ዓመቷ) ነው፡፡ ይህች ሴት የተወለደችው በጎንደር ከተማ ሲሆን እውነተኛ ስሟ “የዓለም ገዥ ከበደ” ነው፡፡ “አያልነሽ” በኢህአፓ አባልነቷ የተሰጣት የትግል ስሟ ነው፡፡ እስከ አሁን ድረስ የምትታወሰውም በዚህ ስም ነው፡፡
           *****
   አያልነሽ በዘመነ ደርግ ሰራዊቷን በቆራጥነት መምራት ቀጠለች፡፡ በተለይ ጎጃምና ጎንደር የራሷ ነጻ ግዛት እስኪመስል ድረስ በህዝቡ ዘንድ ስሟ ተደጋግሞ ይወሳ ነበር፡፡ በ1980 መጨረሻ ገደማ በእርዳታ ሰራተኛነት ሽፋን የመተከል አውራጃ ዋና ከተማ የነበረችውን ፓዌን የጎበኘው የሲ.አይ.ኤው ዝነኛ ሰላይ ፖል ሄንዝ የአካባቢው ሰው ለአያልነሽ የነበረውን አድናቆት ልብ ብሎ አስተዋለ፡፡ እናም ከዓመት በኋላ ወደ ሰሜን አሜሪካ ለጉብኝት የጋበዘውን ወጣቱን የህወሐትና የኢህአዴግ መሪ አቶ መለስ ዜናዊን ስለአያልነሽ ጠየቀው፡፡ ታዲያ አቶ መለስም ልክ እንደ ደርግ ሰዎች የኢህአፓን ስም ላለማንሳት ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ነበረበት፡፡ በወቅቱ የኢህዴን (የአሁኑ ብአዴን) ስም እንጂ የኢህአፓ ስም ተጋንኖ እንዲወራ አይፈለግም ነበርና “አያልነሽ በራሷ የምትታገል ታጋይ ናት እንጂ በድርጅት የታቀፈች አይመስለኝም” በማለት ጉዳዩን በደንብ ሳያወሳው አለፈው፡፡
  
   ደርግ ተደመሰሰ፡፡ ኢህአዴግም በርሱ ቦታ መንግሥት ሆነ፡፡ የአያልነሽ ቀጣይ ትግልም ከአዲሱ መንግሥት ጋር ሆነ፡፡ ሁለቱ ሀይሎች ከአሲምባ ጀምሮ ይተዋወቃሉ፡፡ ሁለቱም ከፍተኛ ግጭቶችን አድርገዋል፡፡ ይሁንና ኢህአዴግ በጎንደርና በጎጃም የነበረው የኢህአፓ ሰራዊት በገበሬው ልብ የገባ ሰላልመሰለው አያልነሽና ጦሯን በቀላሉ የሚያባርራቸው ፋኖዎች አድርጎ ነበር የገመተው፡፡ በአማራው ምድር ሲገባ ግን ሁኔታው እርሱ ከጠበቀው ውጪ ሆኖ አገኘው፡፡ እርሱ ሞቷል ብሎ የገመተው ኢህአፓ የተሰኘው ታሪካዊ ጠላቱ ለቀጣይ ትግሉ አደጋ ሊሆን እንደሚችል ተረዳ፡፡ ስለዚህ እርሱም እንደ ደርግ “ኢህአፓ መጥፋት ያለበት  ድርጅት ነው” በማለት ወሰነ፡፡ በወቅቱ ተጠራርጎ ሊወድቅ የሚንገታተውን የደርግ መንግሥት በአንድ ዙር ካጠናቀቀው በኋላ በኢህአፓ ላይ ለመዝመት ቆረጠ፡፡
   
    ከላይ እንደገለጽኩትም በሰኔ 1983 መጀመሪያ ላይ ከኢህአፓ ጋር የሚደረገው ጦርነት በጎጃምና በጎንደር ተጀመረ፡፡ ሚዲያው “ደርግ ወድቆ ሰላም ሰፍኗል” በሚልበት ሰዓት ጎጃምና ጎንደር በጦርነት እሳት እየተለበለቡ መሆናቸው ታወቀ፡፡ ኢህአዴጎች ስም ያልሰጡት የዚያ ዘመቻ ዓላማ “ኢህአፓ”ን ማጥፋት ሊሆን እንደሚችልም በስፋት ተወራ፡፡
   
  ጦርነቱ ቀጠለ፡፡  በደርግ ላይ በተጎናጸፈው ድል ከፍተኛ ሞራል የሰነቀው የኢህአዴግ ጦር በኢህአፓ ላይ ተረባረበ፡፡ በቁጥሩ አነስተኛ በዓላማ ጽናቱ ግን ከፍተኛ የነበረውና በአያልነሽ የሚመራው የኢህአፓ ጦር በበኩሉ የኢህአዴግን ዘመቻ ለመመከት ጥረት ማድረጉን ቀጠለ፡፡ በጦርነቱ ሳቢያ ጎጃምና ጎንደር ለእንቅስቃሴ አስቸጋሪ ሆኑ፡፡ በተለይ ደርግ ከወደቀ በኋላ አዲሱን የኢህአዴግ መንግሥት በገፍ ለመቀላቀል ይጠባበቁ የነበሩ ቀደምት የኢህአዴግ ታጋዮች፣ ከስደት ተመላሽ ምሁራንና ሌሎች የኢህአዴግ ደጋፊዎች ከሱዳን ወደ አዲስ አበባ ለመንቀሳቀስ ክፉ ፈተና ገጠማቸው (በወቅቱ የአውሮፕላን ጉዞ ተቋርጦ ስለነበር ከሱዳን ወደ አዲስ አበባ የሚኬደው በመኪና ነው)፡፡
   
    የኢህአዴግ ሰዎች ጦርነቱን በቀላሉ የሚያጠናቅቁበትን መላ ዘየዱ፡፡ በዚህም መሰረት ዋናው ጦርነት የኢህአፓ ተዋጊዎች የቆራጥነት ምልክትና የጽናት አብነት በሆነችው አያልነሽ ላይ ማተኮር እንዳለበት ወሰኑ፡፡ በመሆኑም ኮማንደር አያልነሽን ማሳደድ ጀመሩ፡፡ እርሷን ለመግደል ወይንም ከነነፍሷ ለመያዝ እንዲቻል በርካታ ልምድ ያለውን “አሉላ ክፍለ ጦር” ወደ ስፍራው ላኩ፡፡  አያልነሽና ጓዶቿም ለዘመናት ሲታገሉበት የነበረውን የኢህአፓን እስትንፋስ ለማስቀጠል የሞት ሽረት ትግል ማካሄዳቸውን ቀጠሉ፡፡ ከሰኔ 1983 እስከ መስከረም 1984 ድረስ በልዩ ልዩ ስፍራዎች ከባድ ውጊያዎች ተካሄዱ፡፡ ይሁንና በብዙ እጥፍ ከሚበልጠው የኢህአዴግ ሰራዊት ጋር የተጋጠመው የኢህአፓ ሰራዊት በለስ ሳይቀናው ቀረ፡፡ በነሐሴ 1983 በጎንደር ክፍለ ሀገር ቋራ አውራጃ በተካሄደው ጦርነት እውቋ ኮማንደር አያልነሽ ከእልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ በኢሕአዴግ ተዋጊዎች እጅ ወደቀች፡፡ በመስከረም ወር አጋማሽ የኢህአፓ መስራች አባልና ለረጅም ጊዜ የጦሩ አዛዥ የነበረው ጸጋዬ ገብረመድህን (ደብተራው) ከጥቂት ጓዶቹ ጋር ተያዘ፡፡ ከጥቅምት እስከ  ህዳር 1984 በነበረው ጊዜ ሁሉም ነገር አበቃለት፡፡ የአህአፓ ጦር ለረጅም ዘመናት ሲታገልበት ከነበረው የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሙሉ በሙሉ ተደመሰሰ፡፡  
     ኢህአዴግ ከጎጃምና ጎንደር የማረካቸውን የኢህአፓ ሰዎች ወደ መቀሌ እስር ቤት ወሰዳቸው፡፡ ከአራት ወራት እስር በኋላ አያልነሽና ጥቂት ሰዎች የተሐድሶ ስልጠና ተሰጥቷቸው ተለቀቁ፡፡ እነ ጸጋዬ ገብረመድህን ግን በዚያው ቀሩ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ያሉበት ሁኔታ በግልጽ አይታወቅም፡፡
           *****
አያልነሽ በእስር ላይ እያለች ለአንድ ቀን በቴሌቪዥን መስኮት ታይታ ነበር፡፡ ታዲያ በወቅቱ እርሷን ያዩዋት ሰዎች መልኳ ቀደም ሲል ስለርሷ ያስቡት ከነበረው ውጪ ሲሆንባቸው በጣም ነበር የተደነቁት፡፡ “አያልነሽ” ሲባል ብዙዎች የጠበቁት ግዙፍ፤ ግድንግድ፤ ጨካኝ ፊት ያላት፤ መልከ ጥፉና አስፈሪ፣ ጎፈሬዋን ያንጨባረረች፣ ዕድሜዋ ከአርባዎቹ የሚበልጥ፣ የወታደር ልብስ የለበሰች ሴት ነበር፡፡ ሆኖም በቴሌቪዥን የታየችው አያልነሽ በግልባጩ የቀይ ዳማ፣ መለሎ፣ ዐይኖቿ እንደ ኮከብ የሚያበሩ፣ ጸጉሯ በስርዓቱ የተበጠረ፣ ሸንቃጣ ሰውነት ያላት፤ በጣም ቆንጆ የ27 ዓመት ወጣት ነበረች፡፡
                                                                                                   
  አያልነሽ ከእስር ከተለቀቀች በኋላ ለጥቂት ጊዜ በአዲስ አበባ ቆየች፡፡ በ1985 መጀመሪያ ላይ ወደ አውሮፓ ተሻግራ ሀገረ ስዊዘርላንድ ገባች፡፡ እዚያም ትዳር ከመሰረተች በኋላ የልጆች እናት ሆናለች፡፡
 
    አያልነሽ በዚያ ዘመን ስመ ገናና ነበረች፡፡ አሁንስ በምን ሁኔታ ላይ ነው ያለችው? በኔ በኩል ወሬው የለኝም፡፡ እርሷን የሚያውቋት ሰዎች ያላቸውን መረጃ ቢያካፍሉን መልካም ነው፡፡ በነገራችን ላይ ጋዜጠኛ ተስፋዬ ገብረአብ ውጪ ሄዶ ማስታወሻዎቹን ሲጽፍ ስለርሷ አንድ ነገር ይናገራል ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ ነገር ግን በአንድ ቦታ እንኳ የርሷን ስም አላነሳም፡፡ ከርሱ ይልቅ የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አያልነሽን በመጠኑ አስታውሰዋታል፡፡ በወቅቱ ኢህአዴግን ለመቀላቀል በሱዳን በኩል ወደ ሀገር ቤት የገቡት ዶ/ር ነጋሶ በጎንደር-አዲስ አበባ መስመር የነበረው የአያልነሽ ሰራዊት ወደ አዲስ አበባ ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ እንዳስተጓጎለባቸው መስክረዋል (ለማስረጃው “ዳንዲ” የተሰኘውን መጽሐፍ አንብቡት)፡፡

           *****
አያልነሽ በአጭሩ ይህቺ ነበረች፡፡ ስለርሷ የበለጠ የምታውቁ ሰዎች ያላችሁን መረጃ ልታካፍሉን ትችላላችሁ፡፡ በነገራችን ላይ የአያልነሽ የረጅም ጊዜ የትግል ጓደኛ የነበረው ገብረ እግዚአብሄር ወልደሚካኤል (ጋይም) አንዳንዶች እንደሚሉት ከአያልነሽ ጋር አልተማረከም፡፡ “ጋይም” በ1985 አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተደብቆ በነበረበት ወቅት አንድ ውስጠ-አዋቂ ለኢህአዴግ የጸጥታ ሀይሎች ጠቆመበት፡፡ ኢህአዴጎችም እርሱን የሚይዝ አዳኝ ጦር ላኩበት፡፡ ሆኖም “ጋይም” እጁን መስጠት ስላልፈለገ ተኩስ ተከፈተ፡፡ ከ30 ደቂቃ የተኩስ ልውውጥ በኋላ ሞተ፡፡ (ስለዚህ ጉዳይ በዝርዝር ለማወቅ ካሻችሁ ሚያዚያ 1985 የታተመውን እፎይታ መጽሔት አፈላልጉ፡፡ “የኢህአፓው ኮማንደር በአዲስ አበባ” የሚል ጽሑፍ አውጥቶ ነበር)፡፡
           *****
 አፈንዲ ሙተቂ
ሸገር-አዲስ አበባ
ጥቅምት 10/2006

————-
The writer, Afendi Muteki, is a researcher of the Ethnography and History of the peoples of East Ethiopia. He is an author of “Harar Gey”, an Ethnography book about the historical city of Harar. You can read some of his articles on his facebook page.
Facebook https://www.facebook.com/afendimutekiharar

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

ኔዘርላንድ የሚገኘው ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት በእንግሊዘኛ ምኅፃሩ ICC ዳርፉር ላይ የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አስመልክቶ ከፍቶት የነበረውን ክስ ማቋረጡን አስታወቀ።

በምሥራቅ አፍሪቃዊትዋ ሀገር በርዋንዳ የፕሬስ ሕግጋትች ነጻ ሆነዉ ቢቀመጡም፤ በሀገሪቱ የሚገኙ ጋዜጠኞች በነጻነት መሥራትና መፃፍ እንዳልቻሉ ለጋዜጠኞች የሚሟገቱ ድርጅቶች ዘግበዋል።

መሐሙድ የሱፍ የተወለደው በ1980ዓ.ም ከሶማሌ ክልል ርእሰ-መዲና ጅጅጋ 500 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘውዶሀን ከተማ ነው፡፡ ለቤተሰቡ ሰባተኛ ልጅ ሲሆን፤ አምስት እህቶችእና ሦስት ወንድሞች አሉት፡፡ በጅጅጋ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እስከ አስረኛ ክፍል ድረስ መዝለቁቢሳካለትም፤ ከዚህ በላይ ግን ሊቀጥል አልተቻለውም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የኢትዮጵያመንግስት የደህንነት ሠራተኞች የ1999ዓ.ም የግንቦት ሃያ በዓል በጅጅጋ ከተማ ስታዲዬም በተከበረበት ዕለት፣ የኦጋዴን ነፃአውጪ ግንባር […]

ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማያም ደሳለኝና ዉሸታቸዉ

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የሚናገሯቸዉ ንግ ግሮች በጣም አሳፍሪ ናቸዉ። አቶ ሐይለማሪያም ሰብእናቸዉ የተዛባ ነዉ፣እፍረት ከሚባል የህሊና ሚዛን አፈንግጠዋል፣ አገራችንና ህዝባችንን ወክለዉ በአለም መድረክ ላይ መንቀሳቀሳቸዉ ብሔራዊ ዉርደት ነዉ የሚሉ ብዙ ናቸዉ።
ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን የተዘጋጀዉን ልዩ ፕሮግራም ያዳምጡ።

http://goo.gl/sIujv2
http://goo.gl/sIujv2
ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማያም ደሳለኝና ዉሸታቸዉ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የሚናገሯቸዉ ንግ ግሮች በጣም አሳፍሪ ናቸዉ። አቶ ሐይለማሪያም ሰብእናቸዉ የተዛባ ነዉ፣እፍረት ከሚባል የህሊና ሚዛን አፈንግጠዋል፣ አገራችንና ህዝባችንን ወክለዉ በአለም መድረክ ላይ መንቀሳቀሳቸዉ ብሔራዊ ዉርደት ነዉ የሚሉ ብዙ ናቸዉ። ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን የተዘጋጀዉን ልዩ ፕሮግራም ያዳምጡ። http://goo.gl/sIujv2 http://goo.gl/sIujv2

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በጠራው ልዩ ጠቅላላ ጉባኤ ሁለት አጀንዳዎችን በመወያየት አፅድቋል፡፡ በመጀመሪያ አጀንዳነት የተነሳው የኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ ብሔራዊ ምክር ቤቱ የሰየመውን ፕሬዝደንት ተወያይቶ ያፀደቀ ሲሆን በሁለተኛ አጀንዳነት የተያዘው እና ምርጫ ቦርድ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ቁጥራችሁን አሳውቁኝ ባለው መሰረት የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ቁጥርን ወስኗል ፡፡ ጠቅላላ ጉባኤው በዛሬው ስብሰባ ከሁለቱ […]


አፈንዲ ሙተቂ
—-
የአንጋፋው አርቲስት የጌታቸው ካሳ እውነተኛ ስም “ጌታቸው እሸቴ” ነበረ፡፡ ይህ አርቲስት በኪነ-ጥበቡ ተማርኮ መዘፋፈን ሲጀምር አባቱ ድምጹን በሬድዮ ይሰሙታል፡፡ አባት “ልጅህ አዝማሪ ነው” መባላቸው ክብራቸውን የሚቀንስ ሆኖ ስለተሰማቸው ልጃቸውን ያስጠሩትና እንዲህ አሉት፡፡ “ከዛሬ በኋላ ከዘፈንክ ግንባርህን በጥይት እበሳዋለሁ”፡፡

 

Salah ibn Badiya, One of the legendary Sudanese pop stars.

 ልጅ ጌታቸው ግን በአባቱ ማስፈራሪያ አላረፈረም፡፡ ከውስጡ የሚንቀለቀለው የጥበብ ዛር አላስቀምጥ ስላለው ከአባቱ እየተደበቀ ወደ ዘመኑ ክለቦችና ልዩ ልዩ መድረኮች ጎራ እያለ መዝፈኑን ቀጠለ፡፡ በዚህን ጊዜም በአንጋፋው ጋዜጠኛ ጌታቸው ደስታ ዐይን ውስጥ ገባ፡፡ ጌታቸው ደስታም ወጣቱን ድምጻዊ በሬድዮ እንዲዘፍን ጋበዘው፡፡ ነገር ግን የዘፋኙ አባት ልጃቸው በሬድዮ እንደዘፈነ ቢሰሙ በልጁ ላይ አደጋ ሊያደርሱ እንደሚችሉ ገመተ፡፡ ስለዚህ ወጣቱን ለመደበቅ እንዲቻል ስሙን “ጌታቸው ካሳ” በማለት ቀየረው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ተወዳጁ አርቲስት ላለፉት አርባ አምስት ዓመታት ጌታቸው ካሳ ተብሎ እየተጠራ ነው፡፡

*****

አንጋፋው ሱዳናዊ ድምጻዊ “ሳላሕ ኢብን ባዲያ”ም ከኛው ጌታቸው ካሳ ጋር የሚመሳሰልበት ታሪክ አለው፡፡ የሳላሕ እውነተኛ ስሙ ሳላሕ ሼኽ ሙሐመድ ነበረ፡፡ በወጣትነቱ የዘፈናቸው ዘፈኖች በኦምዱርማን ሬድዮ ሲተላለፉ አባቱ እሳት ጎርሰው እሳት ለብሰው መጡለት፡፡ “አንተ አዝማሪ! ልታዋርደኝ ነው የምትፈልገው?… ከዛሬ ጀምሮ በኔ ስም የምትጠራ ከሆነ እረግምሃለሁ! ውርድ ከራሴ!” በማለት አስጠነቀቁት፡፡

  ሳላሕ የአባቱን ማስጠንቀቂያ ተቀበለ፡፡ ነገር ግን የአባቱን ስም ትቶ በሐሰት ስም መጠራቱን ነፍሲያው አልቀበል አለች፡፡ አሕመድ፣ ሰይድ፣ ኢብራሂም፣ ሱፍያን በመሳሰሉት የዐረብኛ ስሞች መጠራቱ አላመችህ አለው፡፡ ማን ተብሎ ይጠራ እንግዲህ?….  አንድ ቦታ ቁጭ ብሎ ሲያሰላስል እንዲህ የሚል ሐሳብ መጣለት፡፡

  “ሳላሕ አንተ የተወለድከው በገጠር ነው አይደል?… ለምን የገጠር ልጅ ነኝ ብለህ አትጠራም?… እግረ መንገድህንም የገጠር ሰው ታላቅ ተአምር መስራት እንደሚችል ታሳይበታለህ”

ሳላሕ በድንገት ውልብ ያለበትን ሓሳብ በተግባር ላይ ሊያውለው ተነሳ፡፡ የመጀመሪያ አልበሙን ሲያሳትምም “ሳላሕ ኢብን ባዲያ” (ሳላሕ የገጠር ልጅ) የሚል ስም ተጠቀመ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለሃምሳ ዓመታት በዚህ ስም እየተጠራ ነው፡፡

*****

ሳላሕ ኢብን ባዲያ ሱዳን ካበቀለቻቸው አንጋፋ አርቲስቶች አንዱ ነው፡፡ የሱዳንን ሙዚቃ በፍቅር የሚያዳምጡ አድናቂዎቹ በተለይም እንደ ብራቅ በሚወጣው ድምጹ በጣም ይገረማሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት እድሜው ወደ ሰባዎቹ አጋማሽ ቢሆንም በአዘፋፈን ዘይቤው ላይ ምንም ድካም አይታይበትም፡፡

ከሳላሕ ኢብን ባዲያ ዘፋኖች መካከል የሀገራችን ሙዚቃ አፍቃሪያን በደንብ የሚያዉቁት “ሻዕረ ዘሐብ” የሚለውን ዜማ ይመስለኛል፡፡ በነገዋ ዕለተ ቅዳሜ ከሳላሕ ቢን ባዲያ ጋር በሓሳብ ወደ ኦምዱርማን ትበሩ ዘንድ ይህንኑ ጨዋታ ጋብዘናችኋል፡፡

(ሳላሕ “ሻዕረ ዘሐብ”ን ሲዘፍን ለማየት ይህንን የዩቲዩብ ሊንክ ይክፈቱ)

—–

አፈንዲ ሙተቂ

ታሕሳስ 4/2007

ሀረር-ምሥራቅ ኢትዮጵያ

—

The writer, Afendi Muteki, is a researcher and author of the ethnography and history with special focus on the peoples of East Ethiopia. You may follow him on his blog and his facebook page by clicking the following links

 ነጻና ሚዛናዊ ምርጫ ለማካሄድ የሁሉንም ተወዳዳሪዎች ፕሮግራም ለሕዝብ የሚያደርስ በነጻነት የሚዘግብ መገናኛ ብዙኃን ወሳኝነት የዲሞክራሲ ባሕልና መሠረትም ነው።

በርካታ ጋዜጠኞች እስር ላይ በሚገኙባትና ያንኑ ያህል ቁጥራቸው የበዛ አገር ጥለው በተሰደዱባት ኢትዮጵያ በነጻነት መዘገብ የሚችሉ ጋዜጠኞች መኖር እያነጋገረ ነው።

ለጋዜጠኞች መብት ከቆሙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አንዱ Freedom House በቅርቡ ስለ አገሮች የነጻ ፕሬስ ይዞታ ባወጣው ዓመታዊ ሪፓርቱ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ቀጥሎ ጋዜጠኞች የታሰሩባት አገር መሆንዋን ዘግቧል። በጸረ ሽብር ሕጉና በወንጀለኛ መቅጫ የተከሰሱ ቢያንስ አስራ ሰባት ጋዜጠኞች በእስራ ላይ እንደሚገኙ ሌሎች በርካቶች እንደተሰደዱ በሪፖርቱ ዘርዝሯል።

የኢትዮጵያ መንግስት ባለ ስልጣናት በተደጋጋሚ “ጋዜጠኛ ሰለሆነ የሚታሰር ማንም…

ተጻፈ በ  

የዛሬ ‹‹ምን እየሠሩ ነው?››…

በእገዳው ቤተ ክርስቲያን ሕግን እንደጣሰች ቅ/ሲኖዶሱም አላዋቂ እንደኾነ ተደርጎ ተዘልፏል አማሳኞቹ ሐቅ ተናጋሪዎች ቅ/ሲኖዶሱ ደግሞ ጊዜ ያለፈበትን አፈና አንጋሽ ተደርጎ ተገልጧል የአማሳኞቹ ውንጀላ ከባድ ጥፋት ሳይኾን እንደ ‹‹ዳኅፀ ልሳንና የአፍ ወለምታ›› ተቆጥሯል የአማሳኞቹ ጉባኤ ሕግን የጣሰ ሳይኾን በቤተ ክርስቲያን ጠሪነት እንደተሰበሰበ ተጠቅሷል የውሳኔውን አፈጻጸም የሚያግደው ደብዳቤ ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ግልባጭ ተደርጓል ብፁዕ ዋ/ጸሐፊውና ብፁዕ ጠቅ/ሥራ …

* ‹‹በትጥቅ ትግልም የተሳተፈ፣ ዴሞክራሲ፣ ሰላም፣ ዘላቂ ልማትና እድገት እንዲመጣ ለማድረግ መስዋዕት የከፈለ ትውልድ አለ። ከእርሱ ትውልድ ተቀብሎ ደግሞ 2ተ ኛው ትውልድ ሥራ ጀምሯል።›› * ‹‹አንዳንድ ሀገሮች ያኔ 25 እና 30 ሚሊዮን እርዳታ ሲሰጡን ትልቅ እርዳታ ተደርጎ ነበር የሚታየው። ዛሬ እኛ የደረስንበት ደረጃ ሲታይ ደግሞ የህዳሴ ግድብን የመሰለ ወደ 4ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ግድብ በራሳችን ለመስራት መጀመራችን…›› * ‹‹በቅርቡ የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ፕሬዚዳንት በምንም ተዓምር ይህን ግድብ መጥቼ ማየት አለብኝ፣….እናንተ ለእኛም ሞራል ሆናችሁናል፣ ከእናንተ ቀጥሎ እኛም መስራት አለብን ብለው አቋም ይዘው ግድቡን መጎብኘት አለብኝ ብለው በተደጋጋሚ ጠይቀዋል፣ በቅርቡም መጥተው ያያሉ።›› * ‹‹በዘንድሮ ዓመት በዋና ዋና ሰብሎች የባለፈው ዓመት የዘንድሮን ሳይጨምር 2006 ዓመት ላይ ማለት ነው በዋና ዋና ሰብሎች 250 ሚሊዮን ኩንታል ተመርቷል፤ ከዚያ በላይ ደግሞ የስራስር ሰብሎች፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ሌሎች የቅመማ ቅመምና ቅባት እህሎች፣ ቡና የመሳሰሉት ሲጨመሩበት ከ300 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማምረት የቻለ አገር ሆኗል። ይሄ በህዝብ ቁጥር በሚከፋፈልበት ጊዜ ሀገሪቱ ራሷን በምግብ እህል መቻሏን ያስረዳል።›› – – – – –  አዲስ ዘመን፡- ሕገመንግሥታችን የአገራችንን የቁልቁለት ጉዞ ቀልብሶ የኢትዮጵያ ህዳሴ መሰረት እንዲጣል ያደረገ ነው ይባላል፤ ይህ ምን ማለት ነው? ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም፡ – በኢትዮጵያ ህዝቦች ከፍተኛ መስዋዕትነት ከተከፈለ በኋላ የኢትዮጵያን ህዳሴ ሊያረጋግጥ የሚችል ድል ተገኝቷል። ሕገ መንግሥታችን በዚህ ድል ላይ የተገነባ ሕገመንግሥት ነው፤ ከድሉ በኋላ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና […]

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም  ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ “የእኛ መንግስት…እራሱን አርዓያ በማድረግ ለሁሉም ህዝብ ትምህርት ያስተምራል፡፡ መንግስት እራሱ ህግን የማያከብር እና የሚጥስ ከሆነ ለህግ ያለውን ንቀት ይፈልፍላል፣ እያንዳንዱ ሰው ለእራሱ ህግ እንዲሆን ይጋብዛል፣ ስርዓተ አልበኝነትን ይጋብዛል” የዩኤስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ለዊስ ዲ. ብራንዲስ …

የአሜሪካንን የህዝብ ጠባቂ ፖሊስ የሚጠብቀው ፖሊስ ማን ነው? Read more »

ታኀሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድ ከፍተኛ አቃቢ ህግ ለስዊድን ሬዲዮ እንደገለጹት ምርጫ 97ትን ተከትሎ በህወሃት/ኢህአዴግ መራሹ ጦር ለተገደሉ ንጹህ ዜጎች ተጠያቂዎች ናቸው የተባሉ 12 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና አንድ ስዊድን አገር በሚገኝ ሌላ ወታደራዊ አዛዥ ላይ ምርመራ  እየተካሄደ ነው። ማስረጃዎች ተሰባስበው እንዳለቁ ክስ ሊመሰረት እንደሚችል የገለጹት አቃቢ ህጓ ፣ባለስልጣናቱ በየትኛውም አገራት ቢዘዋወሩ ተይዘው …

ታኀሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ለማድረግ የሚያስችሉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ለመጠየቅ መድረክ የፊታችን እሁድ የጠራው ሰልፍ እንዲደናቀፍ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ተጽእኖ ቢያሳርፉም፣ ተጽኖውን ሁሉ ተቋቁሞ የሰፈር ለሰፈር ቅስቀሳውን እያካሄደ መሆኑን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው አቶ ጥላሁን እንዳሻው ተናግረዋል። አዲስ አበባ መስተዳድር ሰላማዊ ሰልፉ እንዲካሄድ እውቅና ቢሰጥም፣ ቅስቀሳ ለማድረግ ሌላ እውቅና …

ታኀሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእስር ላይ የሚገኙ የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም የህሊና እሰረኞችን ጉዳይ የሚከታተሉት ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ከዚህ በፊት ለሎሚ መጽሄት በሰጡት አስተያየት ነው። ሰማያዊ ፓርቲ የሽብረተኞች መጠቀሚያ ሆኗል በሚል በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቀረበውን ዘገባ በመተቸታቸው እንዲሁም በኢትዮጵያ የጸረ ሽብር ህግ ላይ አስተያየት በመስጠታቸው የዲሲፕሊን ክስ ቀርቦባቸዋል። አቶ ተማም የኢትዮጵያ …

ታኀሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፊደራል ፍ/ቤት ከወንጀል ነፃ ናቸው በሚል ያሰናበታቸወን ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ  የክልሉ አስተዳደር እና ፀጥታ ነፃ አይደሉም በሚል ባቀረበው አቤቱታ ጉዳያቸው በክልሉ ካቢኔ መታየት ጀምሯል፡፡ የክልሉ ካቢኔ ባደረገው ውይይት ለሁለት የተከፈለ ሲሆን አንደኛው ወገን እንፍታቸው ሲል ሌላው ወገን ደግሞ በምርጫው  ላይ አሉታዊ ተጽኖ ስለሚያሳርፉ መፈታት የለባቸውም በሚል ሲከራከሩ ከቆዩ …

ታኀሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በትውልድ ኢትዮጵያዊ እና በዜግነት ፊላንዳዊ የሆኑት ከፍተኛ የእርሻ ሳይንቲስት  ዶ/ር የሺጥላ ደገፉ የክብር ሜዳልያውን የተሸለሙት ባለፈው ቅዳሜ ፣ ፊንላንድ 97ኛ አመት የነጻነት በአሉዋን ባከበረችበት ወቅት ነው። ዶ/ር የሺጥላ  ዕጽዋት ከየትና እንዴት በሽታ እንደሚይዛቸው፤ እንዴትስ በውስጣቸው እንደሚተላለፍና በራሳቸውም እንዴት እንደሚከላከሉ ከ23 ዓመታት ምርምር በሁዋላ  ሂደቱን ለመጀመሪያ ጊዜ በማግኝታችው ነው። …

“ዘ ጋርዲያን” (The Guardian) በተሰኘው ታዋቂ ጋዜጣ እ.አ.አ ነሐሴ 15 ቀን 2006 እንደ ተዘገበው፤ የጀርመን መንግሥትን በመወከል፤ ወ/ሮ ሔይደማሪ ዊዞረክ-ዜዩል (Mrs. Heidemarie Wieczorek-Zeul)፤ የጀርመን የልማት ሚኒስትር፤ ሐገራቸው እ.አ.አ. በ1904 በናሚቢያ ነዋሪዎች (ሔሬሮዎች) ላይ ስለ ፈጸመችው የዘር ማጥፋት ወንጀል ይቅርታ ጠይቀዋል። ለዚህም ወንጀል፤ ናሚቢያውያን (ሔሬሮዎች) ከይቅርታ መጠየቁ በተጨማሪ $4 ቢሊዮን ካሣ እንዲከፈል የጀርመን መንግሥትን መጠየቃቸው ተገልጿል። […]

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና በማኅበረ ቅዱሳን የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ክፍል ሓላፊ የሆኑት ዲ/ን ዶ/ር መርሻ አለኸኝ ከጥቂት ወራት በፊት በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣና በማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ ላይ በተከታታይ ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዘወርት›› በሚል ዐቢይ ርእስ ያቀረቡትን ጥናታዊ ጽሑፋቸውን ተከታትያለኹ፡፡ ዶ/ር መርሻ በተለይም ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዓለም አቀፍ ደረጃ በዓለም የክርስትና መድረክ የነበራትንና አሁንም ያላትን ልዩ […]


ፀሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ

——
   የክፍለ ሀገር ልጅ ነኝ (በአሁኑ አጠራር የ“ክልል” ልጅ ሆኛለሁ)፡፡ የክፍለ ሀገር ልጅ መሆኔም ብዙ ጥቅም አስገኝቶልኛል፡፡ የክፍለ ሀገር ልጅ መሆኔ ቅር የሚያሰኘኝ በአንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ ይህም በልጅነቴ የዓለም ዋንጫን በቀጥታ ስርጭት ለማየት አለመታደሌ ነው፡፡ የዚህም ምክንያት ከተማችን በዚያ ዘመን የቴሌቪዥን ስርጭት ያልነበራት መሆኑ ነው፡፡ በዚያ ዘመን በሰፊው የሀረርጌ ክፍለ ሀገር ውስጥ ከሚገኙት ከተሞች መካከል ቴሌቪዥን የነበራቸው ሀረር፣ ድሬ ዳዋ እና ጅጅጋ ብቻ ናቸው (እነዚህኛዎቹ ክፍለ ሀገር አይባሉም ማለት ነው)፡፡ ዛሬ የሳተላይ ዲሽ እንዲህ በየገጠሩ መበተኑ ላይቀር የደርግ መንግሥት ከሳተላት ዲሽ የሚከፈለውን የቀረጥ ክፍያ ከጣሪያ በላይ እየሰቀለ እኛን በመበደሉ የስራውን ይስጠው እላለሁ (ለነገሩ የአሁኑ መንግሥትም ቢሆን ከጭሮ ከተማ በስተቀር ለሌሎቹ የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች የቴሌቪዥን አንቴና አልተከለም፡፡ ኮንትሮባንድ ነው ቶሎ ከተፍ ብሎ ከልጓሙ የገላገለን!! እድሜ ለኮንትሮባንድ! እድሜ ለሀርቲሼክ መንገድ! እድሜ ለቶጎጫሌ መንገድ! ቂቂቂቂቂቂ)
    ——
   የዓለም ዋንጫ የሚባል የውድድር ዓይነት መኖሩን ያወቅኩት የማራዶና ስም በየልብሱ ላይ ታትሞ በመውጣቱ ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን ከላይ በገለጽኩት ምክንያት በልጅነት ዘመኔ የተካሄዱትን ሁለት የዓለም ዋንጫዎች በቀጥታ ስርጭት ለማየት አልታደልኩም፡፡ እነርሱም የአጣሊያው የዓለም ዋንጫ (1990) እና የአሜሪካው የዓለም ዋንጫ (1994) ናቸው፡፡ (ከዚያ በፊት የነበሩት ሁለት የዓለም ዋንጫዎች እኔ ከተወለድኩ በኋላ የተካሄዱ ቢሆኑም ዕድሜዬ ገና ስለነበረ እንዳለፉኝ አድርጌ አልቆጥራቸውም)፡፡
 
   ይሁን እንጂ ሁለቱንም የዓለም ዋንጫዎች ተከታትያቸኋለሁ፡፡ የቀጥታው ስርጭት ቢያመልጠኝም ጨዋታዎቹን በሁለት ቀናት ልዩነት በቪዲዮ ካሴት እናያቸው ነበር፡፡ ለዚህ የረዳችን የሁል ጊዜ መኩሪያችን የሆነችው ድሬ ዳዋ ናት፡፡ በዚህም መሰረት ዛሬ የተካሄደው ውድድር በድሬ ዳዋ በካሴት ይቀዳና በማግስቱ ወደ ገለምሶ ከች ይላል፡፡ እኛም በሚቀጥለው ቀን ሲቻል ወደ ሀብሮ አውራጃ አኢወማ መዝናኛ ማዕከል፣ ካልተቻለ ደግሞ “ፎቶ ማወርዲ” ከሚባለው ታዋቂ ፎቶ ቤት በመሄድ ጨዋታውን እየተስገበገብን እናየዋለን፡፡ በዚህ ዓይነት በውድድሩ ከተካሄዱት ጨዋታዎች መካከል ቢያንስ ግማሽ ያህል የሚሆኑትን አይቻለሁ፡፡ ድሬ ለዚህ ባለውለታችን ናት፡፡ ማን እንደ ድሬ!! (ቀሽቲ እኮ ናት)፡፡
——–                                          
     በቪዲዮ የምናየውን ጨዋታ ውጤት በቅድሚያ እናውቀዋለን፡፡ በዚያ ላይ ደምሴ ዳምጤ በአደገኛ ምላሱ እያጣፈጠ የሚሰራቸው ዘገባዎች አያመልጡንም፡፡ የአዲስ ዘመንና የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጦችንም እንከታተላለን፡፡ በ1986 ደግሞ የግል ጋዜጦችም ተጀምረው ስለነበረ እየተሻማን እናነባቸው ነበር፡፡ ታዲያ ይህ ሁሉ ቅድመ-መረጃ በቪዲዮ የተቀዳልንን ጨዋታ ጣዕም አያደፈርስብንም፡፡ እንዲያውም ደምሴ በዘገባው የጠቀሳቸውን ነጥቦች በጨዋታው ውስጥ ለመመልከት ስንል በከፍተኛ ተመስጦ ውስጥ እንገባለን፡፡
  ታዲያ ዘወትር የሚገርመኝ አንድ ነገር አለ፡፡ ያለፉትን አምስት የዓለም ዋንጫዎችን በቀጥታ ስርጭት ነው ያየኋቸው (እግር ኳስን በቀጥታ ማየት የጀመርኩት እንደኛ አቆጣጠር በ1988 በተካሄደው የEuro-96 ወቅት ነው፡፡) ቢሆንም እነዚህ በቀጥታ ስርጭት ያየኋቸው ጨዋታዎች ያኔ በቪዲዮ እየተቀዱ ከሁለት ቀናት በኋላ የምናያቸውን ጨዋታዎች ያህል አይጣፍጡኝም፡፡ ጎሉም ሆነ ጨዋታው፣ ተጫዋቹም ሆነ ቡድኖቹ፣ አሰልጣኙም ሆነ ዳኛው ያኔ በልብ ላይ ይቀራል፡፡ ከዚያ ወዲህ ግን ሁሉም ነገር ተለውጧል፡፡ በተለይም ባለፉት ሁለት የዓለም ዋንጫዎች ካየኋቸው ክስተቶች አንዳቸውም በአዕምሮዬ ውስጥ የሉም፡፡ ውጤቱንም ብትጠይቁኝ ልነግራችሁ አልችልም (እ.ኤ.አ በ2006 በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ዚነዲን ዚዳን ካሳየው ጣፋጭ ፉት ቦልና በፍጻሜው ጨዋታ ማቴራዚን በቴስታ ደረቱ ላይ መቶት ከመጣሉ ውጪ ማለቴ ነው)፡፡
በዚህ ጽሑፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁትን የዓለም ዋንጫ አስቃኛችኋለሁ፡፡ የአሜሪካውን የዓለም ዋንጫ በሌላ ጽሐፍ እመጣበታለሁ፡፡
==== 14ኛው የዓለም ዋንጫ በኢጣሊያ (Italy-1990)===
በኢጣሊያ የተካሄደው 14ኛው የዓለም ዋንጫ በእግር ኳስ ኤክስፐርቶች በጣም አሰልቺ የተባለለት ነው፡፡ በያንዳንዱ ውድድር የገቡት ጎሎች በአማካይ ከሁለት አይበልጡም፡፡ ቢሆንም ግን ያኔ ሁሉም ነገር እየጣፈጠን ነው ያየነው፡፡ ለኛ አሰልቺና አስቀያሚ የሆነብን የመጨረሻው ጨዋታ ብቻ ነው፡፡ በዚያ ጨዋታ ዳኛው ብዙ ቢጫና ቀይ ካርዶችን ማሳየታቸው ሳያንሰን አጨቃጫቂ “ሪጎሬ” ሰጥተው የጨዋታውን ስሜት አበላሹብን፡፡
  በዚያ የዓለም ዋንጫ የተካሄዱትን ጨዋታዎች በተመለከተ ዝርዝር ዘገባውን ከኢንተርኔት ስለምታገኙት እዚያ ውስጥ አልገባም፡፡ እኔ እዚህ የማደርገው ከአዕምሮዬ ያልጠፉ ክስተቶችንና ስብዕናዎች ማሳወቅ ነው፡፡
·        አስደሳቹ መጽሐፍ  
በውድድሩ ዋዜማ በጣም ተወዳጅ የሆነ አንድ መጽሐፍ ታትሞ ነበር፡፡ ርዕሱ “እግር ኳስ፤ ፊፋ እና የዓለም ዋንጫ” ይሰኛል፡፡ በአማርኛ ቋንቋ በስፖርት ዙሪያ ከተዘጋጁ መጻሕፍት እንደርሱ የሚማርከኝ የለም፡፡ ያ መጽሐፍ በርካቶቻችን እግር ኳስን እንድንወደው አስተዋጽኦ ያደረገ ይመስለኛል፡፡ በዓለም ዋንጫውን በንቃት እንድንመለከት ያስቻሉን መረጃዎችንም ሰጥቶናል፡፡ ያንን መጽሐፍ ያዘጋጁት የአዲስ ዘመን ጋዜጣ የስፖርት አምድ አዘጋጆች የነበሩት ግርማ ሰይፉ እና ፋንታሁን ሀይሌ ናቸው፡፡
ታዲያ ያ መጽሐፍ በአንድ ነገር አቀዣብሮኛል፡፡ መጽሐፉ በዝርዝር የሚያወሳቸውን እውቅ ተጫዋቾች በዓለም ዋንጫው ላይ የማያቸው መስሎኝ በጉጉት ስጠብቃቸው ነበር፡፡ በተለይም በ13ኛው የዓለም ዋንጫ ወቅት የተጫወቱትን ተጫዋቾች በናፍቆት እየጠበቅኳቸው ነው ውድድሩ የተጀመረው፡፡ ነገር ግን ብዙዎቹ የውሃ ሽታ ሆነው ቀሩ፡፡ ጥቂቶቹ ብቻ (ማራዶና፣ ቡርቻጋ፣ ቫንባስተን፣ ሩድ ጉሌት፣ ካሬካ፣ ጋሪ ሊነከር፤ ጆን ባርነስ፣ ሎታር ማትያስ፣ ሩዲ ቮለር ) በውድድሩ ውስጥ ነበሩ፡፡ የብራዚሉን ፓውሎ ሮቤርቶ ፋልካኦን ደግሞ ለተጫዋችነት ስጠብቀው አሰልጣኝ ሆኖ አገኘሁት፡፡
·        የአጂፕ ኩባኒያ ውለታ፡
ጨዋታው በጣሊያን ሀገር የተካሄደ በመሆኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ስርጭቱን ለማስተላለፍ ስፖንሰር የሆነው የኢጣሊያ ኩባኒያ የሆነው አንጋፋው ነዳጅ አቅራቢ “አጂፕ” ነው፡፡ ያኔ በየጨዋታው መሀል ሲነገር ከነበረው ማስታወቂያ እንደሰማሁት “አጂፕ” በኢትዮጵያ ውስጥ 120 የማደያ ጣቢያዎች ነበሩት፡፡ እስከ አሁን ድረስ ቢኖር ኖሮ 1200 ጣቢያዎች ሳይኖሩት ይቀራል?  
·        የካሜሩን ጉዞ

በዓለም ዋንጫው እጅግ ከፍተኛ ደስታ የፈጠረልን የካሜሩን አስደናቂ ጀብድ ነው፡፡ አርጀንቲናን፣ ሩማኒያንና ኮሎምቢያን ያሸነፈባቸው ጨዋታዎች ከማንም አዕምሮ ውስጥ አይጠፉም፡፡ ሮጀር ሚላ፣ ኦማም ቢይክ፣ ማካናኪ እና በረኛው ቶማስ ንኮኖ የዘወትር ትዝታዎቻችን ናቸው፡፡ ይሁንና ለዋንጫው በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው ያ አስደሳች ቡድን በእንግሊዝ ጉድ ተሰራና ከመንገድ ላይ ቀረብን፡፡
ያ ጨዋታ ከፍተኛ የዳኛ ተጽእኖ የታየበት መሆኑ አሌ አይባልም፡፡ ካሜሩን እንግሊዝን በሁለት ለአንድ እየመራ ወደ መጨረሻው ደረሰ፡፡ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ስምንት ደቂቃ ብቻ ሲቀረው ዳኛው የፍጹም ቅጣት ምት ለእንግሊዝ ሰጡ፡፡ በዚህም እኩል ሆኑ፡፡ በጭማሪው ሰዓትም ዳኛው በድጋሚ ለእንግሊዝ ሪጎሬ ሰጡና አፍሪቃዊያንን የባሰ አሳረሩ፡፡ ተቃጠልን ነው የምላችሁ!! በጣም ሚያሳርረው ደግሞ እነዚያን ሁለት ከይሲ ጎሎች ያስቆጠረው ከላይ የጠቀስኩትን መጽሐፍ አንብቤ በጉጉት ስጠብቃቸው ከነበሩት ተጫዋቾች አንዱ የነበረው እንግሊዛዊው ጋሪ ሊነከር መሆኑ ነው (ጋሪ ሊነከር በሜክሲኮ በተካሄደው 13ኛው የዓለም ዋንጫ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ነው የጨረሰው)፡፡
   ለኳስ እንደዚያ የተናደድኩበት ጊዜ የለም፡፡ ከኔ በላይ ደግሞ ኳስ አፍቃሪው ኢትዮጵያዊ ህዝብ እርር ነው ያለው፡፡ ታዲያ ጨዋታውን በቪዲዮ ማየት እንደጀመርን (“ቪዲዮው ተቀድቶ የሚመጣልን የጨዋታው ውጤት ከታወቀ በኋላ ነው” ያልኳችሁን አትዘንጉ) ማን እንደፈጠረው የማይታወቅ ወሬ በከተማችን ተዛምቶ ነበር፡፡ “ዳኛው ተጽእኖ ያደረገ መሆኑ ስለተረጋገጠ ጨዋታው ይደገማል” የሚል፡፡ ይህ ወሬ እውነት ነው ብለን ስንጠብቅ ከሁለት ቀን በኋላ እንግሊዝ ከጀርመን ጋር ትጫወታለች ተብሎ ተነገረ፡፡ እንደገና እርር!! እንደገና መቃጠል!! ደግነቱ ጀርመንና ጣሊያን እንግሊዝን ቀጥተውልናል፡፡
·        የማይረሱ ጨዋታዎች
የዓለም ዋንጫው የግብ ድርቅ ስላጠቃው “ወዝ የለውም” ይባል እንጂ ዘወትር ከሰው ህሊና የማይጠፉ ምርጥ ጨዋታዎችንም አይተንበታል፡፡ አርጀንቲናና ሩማኒያ፣ ካሜሩንና ኮሎምቢያ፣ ጀርመንና ኮሎምቢያ፣ ኢጣሊያና ቼኮዝሎቫኪያ፣ ብራዚልና ስዊድን፤ አርጀንቲና እና ኢጣሊያ፣ ጀርመንና ሆላንድ፣ አየርላንድና ሩማኒያ በጣም ጥሩ ጨዋታ አሳይተውናል፡፡
·        እጅግ ምርጥ ጨዋታ
ከላይ ከጠቀስኳቸው ጨዋታዎች ይበልጥ ሁሉንም ሰው ቁጭ ብድግ ያደረገው የአርጀንቲናና ብራዚል ጨዋታ ይመስለኛል፡፡ ከምድቡ ሶስቱንም ጨዋታዎች በአሸናፊነት ያጠናቀቀው ብራዚል ካሜሩንን እንኳ ማሸነፍ ባቃተው የአርጀንቲና ቡድን ተረታ፡፡ ለዋንጫ የጠበቅነው ቡድን ስለነበረ ልባችን ነው የተቆረጠው፡፡
·         አስደሳች ተጫዋቾች
 የሩማኒያው ጆርጅ ሃጂ፣ የአርጀንቲናዎቹ ዲየጎ ማራዶና እና ክላውዶ ካኒንጃ፣ የካሜሩኖቹ ሮጀር ሚላ እና ማካናኒ፣ የብራዚሎቹ ካሬካ፣ አሊማው እና ሙለር፣ የኢጣሊያዎቹ ሳልቫቶሬ ሺላቺ እና ሮቤርቶ ባጂዮ፣ የቼኮዝሎቫኪያው ቶማስ ስኩራቪ፣ የስፔኑ ሚሼል፣ የእንግሊዞቹ ጋሪ ሊነከር እና ፖል ጋስኮኝ፣ የእንግሊዙ በረኛ ፒተር ሼልተን፣ የጀርመኖቹ ሎታር ማትያስ እና ሩዲ ቮለር በጣም ምርጥ ተጫዋቾች ነበሩ፡፡  

·        የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች
በዚያ የዓለም ዋንጫ ላይ ካየኋቸው ተጫዋቾች መካከል ኮከብ ነው ብዬ የምመርጠው የኮሎምቢያውን ካርሎስ ቫልዴራማን ነው፤ በለው! በለው! አቤት ጨዋታ! አቤት ታክቲክ! አቤት አብዶ መስራት፣ ወይኔ! ወይኔ! (ወደዳችሁም ጠላችሁም ኳስ ድሮ ቀረ አቦ!)
ቫልዴራማ ኳስ ሲይዝ አስማት በሉት! ሜዳው ጠቦት ይሸከረክርበታል፡፡ በተለይም የጀርመን ተጫዋቾችን እያጥበረበረ ሲያታልላቸው ሁኔታው ሁሉ ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ሆኖባቸው ነበር፡፡ የካሜሩን ቡድንም ኮሎምቢያን አሸንፎ ወደ ሩብ ፍጻሜ ለማለፍ የቻለው በረኛው ቀሽም በመሆኑ እንጂ በኮሎምቢያ ቡድን ድክመት አይደለም፡፡ ቫልዴራማ በዚያ ጨዋታም ላይ ኮከብ ሆኖ ነበር የዋለው፡፡ ቫልዴራማ እ.ኤ.አ. በ1987 የላቲን አሜሪካ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ ተመርጦ ነበር (በ1986 ኮከብ የሆነውን ማራዶናን በልጦ ማለት ነው)፡፡
·        ምርጥ ወጣት ተጫዋቾች
በዚያን ጊዜ ለጨዋታው ልጅ እግር ከሆኑት መካከል በጣም ያስደሰቱኝ ሁለት ወጣቶች ናቸው፡፡ አንደኛው የስዊድኑ ቶማስ ብሮሊን ነው፡፡ ቡድኑ ሁሉንም ጨዋታዎች ተሸንፎ ከምድቡ ቢባረርም ብሮሊን በአጨዋወቱ ማንንም ነበር ያስደሰተው፡፡ ደግሞም በብራዚል ላይ አንድ ግብ አስቆጥራል (ብሮሊን በቀጣዩ የዓለም ዋንጫ ሶስተኛ ኮከብ ሆኗል)፡፡
   ሌላኛው የኢጣሊያው ሮቤርቶ ባጅዮ ነው፡፡ ሮቤ ለኢጣሊያ ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር አያያዙ አደገኛ መሆኑን አስመሰክሯል፡፡ እነዚህ ሁለት ተጫዋቾች በኢጣሊያው “ሴሪ አ” ተገናኝተው ምርጥ ፉት ቦል አሳይተውናል፡፡
·        የማይረሱ ተጫዋቾች
1.      ሬኔ ሂጉታ፡
የኮሎምቢያ በረኛ ነው፡፡ በሁኔታዎቹ ሁሉ እብድ በሉት፡፡ ኳስ በእግሩ እንጂ በእጁ ለመያዝ ይጠየፋል፡፡ ሲያቀብል በእግር! ሲቀበልም በእግር! በዚያ ሁኔታው ኮሎምቢያ ለሁለተኛው ዙር ማለፉ አስደናቂ ነበር፡፡ የሂጉታን እብደት ያጠናው የካሜሩኑ ሮጀር ሚላ ግን ሳያስበው ጉድ ሰራው፡፡ አቤት የያኔው የአፍሪካ ደስታ! አቤት የሚላ ዳንስ!! (አቤት የደምሴ ዳምጤ አዘጋገብ)!
2.     የአርጀንቲናው በረኛ፡
ስሙን ዘንግቼዋለሁ፡፡ ሁለተኛ በረኛ ሆኖ ነበር ወደ ኢጣሊያ የሄደው፡፡ ነገር ግን ዋናው በረኛ ከሶቪየት ህብረት ጋር በተደረገው ጨዋታ በመጎዳቱ እርሱን ተክቶ ወደ ጨዋታው ገባ፡፡ ከዚያ በኋላ ማን ይቻለው!!? በተለይም ኢጣሊያ በደጋፊዎቿ ፊት ተጫውታ በመለያ ምቶች በአርጀንቲና ስትሸነፍ የበረኛው አስተዋጽኦ ሌላ ነው፡፡ (ያኔ የውድድሩ ኮከብ በረኛ ምርጫ ባይደረግም ከሁሉም የሚበልጠው እርሱ ይመስለኛል)፡፡   
·        ምርጥ ግብ አዳኞች
1.      ቶማስ ስኩራቪ (ቼኮዝሎቫኪያ)፡
በሁለተኛው ዙር በኮስታሪካ ላይ የሰራውን ሀትሪክን ጨምሮ አምስት ጎሎችን ነው ያስቆጠረው፡፡ ሁለቱን ጎሎች ያስቆጠረው ቼኮዝሎቫኪያ አሜሪካን 5-1 ባሸነፈችበት ጨዋታ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ቼኮዝሎቫኪያ አሜሪካን ማሸነፏ ሶሻሊዝም በኢምፔሪያሊዝም ላይ የተጎናጸፈው ድል ተደርጎ ስለተወሰደ የአውራጃችን አኢወማ መሪዎች ከደስታ ብዛት ማበድ ነው የቀራቸው (ትልቋ ሶቪየት ህብረት በአርጀንቲና መሸነፏን ያልሰሙ ይመስል ጉራው ሌላ ነበረ)፡፡
  ፖለቲካው ሌላ ነው፡፡ ቶማስ ስኩራቪ ግን ያለምንም ማጋነን ነፍስ የሆነ ተጫዋች ነበረ፡፡ ጎል ለማግባት የተፈጠረ አጥቂ ነው፡፡ ይሁንና ከዚያ የዓለም ዋንጫ በኋላ በድጋሚ አላየሁትም (እነ ጆርጅ ሃጂንና ካርሎስ ቫልዴራማን ግን በድጋሚ ለማየት ችለናል)፡፡
2.     ሚሼል (ስፔን)
በጣም ጎበዝ አጥቂ ነበር፡፡ በምድብ ማጣሪያው በደቡብ ኮሪያ ላይ ሀትሪክ ሰርቷል፡፡ በቤልጅግም ላይ አንድ ግብ አስቆጥሯል፡፡
3.     ካሬካ  እና ሙለር (ብራዚል)፡
 አቤት ጨዋታ! አቤት ፍጥነት!! አቤት ዳንስ! በህይወቴ ካየኋቸው አስደሳች ተጫዋቾች መካከል ናቸው፡፡ ሁለቱም በጥምረት የሚያጠቁ ሲሆን ብራዚል ያስቆጠረቻቸውን አራት ግቦች ያገቡት እነርሱ ናቸው፡፡
    ካሬካ በስዊዲን  ላይ ሁለት ጎሎችን ካስቆጠረ በኋላ በቢጫ ማሊያው የደነሰው “ሳንባ” ዳንስ መቼም ቢሆን የሚረሳኝ አይሆንም፡፡ አስራ አንድ ቀጥሩ ሙለርም በኮስታሪካና በስኮትላንድ ላይ አንዳንድ ግቦችን አስቆጥሮ ቡድኑን ወደ ሁለተኛው ዙር አሸጋግሮታል፡፡
4.     ሮጀር ሚላ (ካሜሩን)፡
 ዓለም በሙሉ ነበር የተደነቀበት፡፡ በዓለም ዋንጫ በ38 ዓመቱ ተሰልፎ ከአዕምሮ የማይጠፉ ግቦችን ለማስቆጠር የቻለ ሰው እርሱ ብቻ ይመስለኛል (ይህ ሪከርድ ከአራት ዓመት በኋላ በራሱ ተሰብሯል)፡፡ የሚደንቀው ነገር ሮጀር ሚላ ግቦቹን ያገባው ከእረፍት በኋላ ተቀይሮ እየገባ ነው፡፡ በሩማኒያ እና ኮሎምቢያ ላይ ሁለት ሁለት ጎሎችን ካስቆጠረ በኋላ የደነሰው ዳንስ የሁሉም አፍሪቃዊ ትዝታ ነው (ደምሴ ዳምጤ ጨዋታዎቹን ሲዘግባቸው አፍ ያስከፍት ነበር)፡፡ ታዲያ እስከ አሁን ድረስ ያልገባኝ ነገር ሰውዬው ሮጀር ሚላ ሆኖ ቴሌቭዥኑ “ሚለር” (Miller) እያለ የሚጠራው መሆኑ ነው፡፡
5.     ሳልቫቶሬ ሺላቺ (ኢጣሊያ)
አስገራሚ ብቻ ሳይሆን የዘረኝነትን መጋረጃ የደመሰሰ ተጫዋች ነው፡፡ በሲሲሊ ደሴት ላይ ከምትገኘው የፓሌርሞ ከተማ ተወልዶ የሀብታሞቹን የሰሜን ኢጣሊያ ልጆች ለመብለጥ የቻለ ነው፡፡ ከሰሜናዊ ኢጣሊያ ከተሞች (ሚላን፣ ቶሪኖ፣ ሮማ፣ ፍሎሬንስ፣ ቬኒስ፣ ወዘተ…) የተገኙ ሰዎች በነርሱ እይታ “ደሀ” የሚባሉትን የሲሲሊና የሳርዲኒያ ሰዎችን ያለ ልክ ይንቋቸዋል፡፡ በሁሉም ነገር አንደኛ እኛ ነን ይላሉ፡፡ ሺላቺ ግን ሳይወዱት በግድ ወደ ውስጣቸው እንዲመለከቱ አደረጋቸው፡፡
  
  ይህ ተጫዋች ኢጣሊያ ባደረገቻቸው ሰባት ግጥሚያዎች ላይ ስድስት ግብ አስቆጥሯል፡፡ በዚህም የውድድሩ ኮከብ ግብ አግቢ በመሆን የወርቅ ጫማ ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል፡፡ ይሁንና ከውድድሩ በኋላ በኢጣሊያ ውስጥ በዘላቂነት ሊጫወት አልቻለም፡፡ ለረጅም ጊዜ ከኢጣሊያ ተሰዶ ለጃፓን ቡድኖች ይጫወት እንደበረ አውቃለሁ፡፡ አሁን ምን ላይ እንደደረሰ አላውቅም፡፡
  
·        የማይረሱ ጎሎች
1.      ከሮጀር ሚላ ጎሎች መካከል በሬኔ ሂጉታ ላይ ያስቆጠራት ሁለተኛዋ ጎል በዓለም የፉትቦል ተመልካቾች ዘንድ ዘወትር የምትታወስ ትመስለኛለች፡፡
2.     የቼኮዝሎቫኪያው ቶማስ ስኩራቪ በኮስታሪካ ላይ ያስቆጠራቸው ሶስት ጎሎችም አይረሱም፡፡
3.     የአርጀንቲናው ክላውዶ ካኒንጃ ብራዚልን ከጨዋታ ውጪ ያደረገችውን ጎል አስቆጥሮ ስንቱን አስለቀሰ?… ወይኔ ብራዚል! እንደዚያ ምርጥ ጨዋታ እየተጫወተ በመንገድ ላይ ቀረብን!
4.     የኮሎምቢያው ፍሬዲ ሪንኮን በጀርመን ላይ ያስቆጠራት ግብ ፈጽሞ አትረሳም፡፡ ያ ጨዋታ ግብ አልባ ሆኖ ወደ መጠናቀቁ ሲቃረብ ጀርመኖች በ88ኛው ደቂቃ ላይ አንድ ጎል አገቡ፡፡ በዚህም ኮሎምቢያ ያለቀለት መሰለ፡፡ ከዓለም ዋንጫ ሊባረር የሚባረርበት ጊዜ ቀረበ፡፡ ነገር ግን ካርሎስ ቫልዴራማ ብልሃቱን አምጥቶ ያገኛትን ኳስ አስተካክሎ ለፍሬዲ ሬንኮን አቀበለ፡፡ ሬንኮንም የአቻነቷን ጎል አስቆጠረ፡፡ ኮሎምቢያም በአንደኛው ዙር ከመባረር ተርፋ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈች፡፡
·        ኮከብ አሰልጣኝ
የጀርመኑ ፍራንዝ ቤከንባወር ኮከብ አሰልጣኝ ሆኖ መመረጡ ትክክል ይመስለኛል፡፡ ቡድኑ አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ ለዋንጫ ደርሶለታልና፡፡ እኛም ጀግናውን ቤከንባወርን በተጫዋችነት ዘመኑ ለማየት ባይቻለንም በአሰልጣኝነቱ በማየታችን እድለኞች ነን፡፡
·       የማይረሳው አሰልጣኝ
የአርጀንቲና አሰልጣኝ ካርሎስ ቢላርዶን ማንም የሚረሳው አይመስለኝም፡፡ ቢላርዶ ከሌሎቹ አሰልጣኞች የሚለይበት ነገር አሰልጣኞች ከሚቀመጡበት ወንበር ላይ በመነሳት ወደ ሜዳው እየሄደ ለተጫዋቾቹ እየጮኸ ምክር ቢጤ የሚለግስ መሆኑ ነው፡፡ ያኔ በተመለከትኳቸው ጨዋታዎች ሁሉ አሰልጣኞች ከወንበራቸው ሲነሱ አላየኋቸውም፡፡ ካርሎስ ቢላርዶ ግን ከተጫዋቾቹ እኩል ነበር የሚንቀሳቀሰው፡፡
በቀጣዮቹ የዓለም ዋንጫዎች ግን ያ ልማድ ተቀየረ፡፡ ሁሉም አሰልጣኝ ከወንበር እየተነሳ የሚመክር በመሆኑ ወንበር ላይ ተቀምጦ ጨዋታውን የሚያይ አሰልጣኝ ጠፋ (እኔ እንደታዘብኩት ከዚያ ወዲህ ካየኋቸው አሰልጣኞች መካከል ጨዋታው ከተጀመረ በኋላ የተለየ እንቅስቃሴ የማያሳዩት የሞሮኮ ቡድንን ለረጅም ጊዜ ሲያሰልጥኑ የነበሩት ሄንሪ ሚሼል እና በ2002 የኮሪያ-ጃፓን የዓለም ዋንጫ ሴኔጋልን ያሰለጠኑት ብሩኖ ሚትሱ ናቸው፡፡ ( ሄንሪ ሚሼል ቁጭ ብሎ ማስቲካውን ያኝካል፤ ጎል ከገባበት ግን ይናደድና ሲጋራውን ያቀጣጥላል፤ ብሩኖ ሚትሱ ደግሞ እጆቻቸውን በማጣመር ይቆሙና ይተክዛሉ)፡፡  
·        የጨዋታው ማስታወሻ
የዓለም ዋንጫው ከተጠናቀቀ በኋላ ብሄራዊ ሎተሪ ውድድሩን አጠቃልሎ የሚዘግብ ፖስተር በማሳተም አስደሰተን፡፡ የፖስተሩ አብዛኛው ክፍል ለሩብ ፍጻሜ የደረሱትን ስምንት ቡድኖችና የውድድሩ ቅመሞች የነበሩትን ምርጥ ተጫዋቾች በፎቶግራፍ ያሳያል፡፡ ከታች ደግሞ በውድድሩ የተከናወኑ ጨዋታዎች ውጤት በሰንጠረዥ ተጠቃልሎ ቀርቧል፡፡ ብሄራዊ ሎተሪ ፖስተሩን በነጻ ለማሰራጨት ያዘጋጀው ይመስለኛል፡፡ ይሁን እንጂ ለማንም ሰው በነጻ ሲሰጥ አላየሁም፡፡ ሁሉም ሰው በብር እየገዛው ነው በቤቱ ሲለጥፈው የነበረው፡፡ ያ ልምድ በቀጣዩ የዓለም ዋንጫም ተደግሟል፡፡ በዚህ ዘመን ያለው አሰራር ግን ሌላ ነው፡፡ የውድድሩን ፕሮግራሞች ለማሳየት በሚል ከጨዋታው በፊት የተዘጋጁ እንጂ የዓለም ዋንጫ ከተጠናቀቀ በኋላ የሚዘጋጅ የማስታወሻ ፖስተር አላየሁም፡፡

Read more ›

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

በምዕራቡ ሀገራት የግድግዳ ጡፍ ወይም ግራፊቲ እንደ ተመልካቹ እና ማህበረሰቡ አተረጓጎም ይለያያል። አንዳንዶች ግራፊቲን ከውንብድና ጋር ሲያገናኙ ሌሎች ስሜት የሚገለፅበት አንድ መንገድ እንደሆነ ይናገራሉ። ሐዋሳ ከተማ የሚገኙ የተወሰኑ ወጣቶች የግድግዳ ጡፍን እንደ አንድ የስዕል ጥበብ ነድፈው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ።

ናይጀሪያ በመጪዉ በምታካሂደዉ የምርጫ ፉክክር ለፕሬዝደንትነት የሚወዳደሩት እጩዎች ማንነት ታወቀ። ዋናዉ ተቃዋሚ ፓርቲ የእድገት ኃይሎች ምክር ቤት በምርህፃሩ APC በጡረታ ላይ የሚገኙትን የቀድሞዉ ወታደራዊ መሪ ሜጀር ጀነራል ሙሀማዱ ቡሀሪን እጩ ፕሬዝደንት አድርጎ አቅርቧል።

የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት FAO በያዝነዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2014 ከፍተኛ የሰብል ምርት መገኘቱን አመለከተ። እንደFAO ዘንድሮ ከ2,5 ቢሊዮን ቶን በላይ የሰብል ምርት በመመረቱ በዓለም የምርት ታሪክ አዲስ ሪከርድ ተመዝግቧል።

Image

‪#‎stopbanningofhijab‬

መንግስት በሰኪዩላሪዝም ሽፋን ህዝብን ሀይማኖት አልባ ለማደረግ የጀመረውን እንቅስቃሴ በአስቸኳይ ያቁም!

የኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 90(2) የሚደነገገው ትምህርት በማናቸውም ረገድ ከሃይማኖት፣ ከፖለቲካ አመለካከቶች እና ከባህላዊ ተጽእኖዎች ነጻ በሆነ መንገድ መካሄድ እንዳለበት ያስቀምጣል። የዚህን አንቀጽ ቀጥተኛ ትርጓሜ ስንመለከት በትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚሰጥ ትምህርት አንድን ሃይማኖት፣ የፖለቲካ ፓርቲ አቋም ወይም የተወሰነ ማህበረሠብን ባህልና እሴት ማንጸባረቅ አይኖርበትም። በተጨማሪም የአንቀጹን ትርጓሜ በምንመለከትበት ወቅት አንቀጹ ”ትምህርት” እንጂ የትምህርት ተቋማት እንደማይል እንገነዘባለን::

ይህም የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና ሀገራችን የብዙ ብሄር ብሄረሰቦችና የተለያዩ ሀይማኖት ተከታዮች በእኩልነት ተቻችለውና ተከባብረው የሚኖሩባት ስለሆነች ሁሉም የሃገሪቷ ዜጎች ትምህርት ላይ እኩል ተጠቃሚ እንደሆኑም ጭምር የሚያረጋግጥልን አንቀጽ ነው::

በአሁን ሰዓት የመንግስት አካላት ይህን አንቀጽ በመጥቀስ ተማሪዎች በትምህርት ተቋማት ውስጥ ሃይማኖታዊ ቀኖናዎችንና ማንነታቸውን እንዳተገብሩ እየከለከሉ ይገኛሉ፡፡ ይህን የህገ መንግስቱን አንቀጽ በሚቃረን ሁኔታ የትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ ላይ የራሱን ስልጣን በመጠቀም ትምህርት የሚለውን የትምህርት ተቋም የሚል ትርጓሜ ሰጥቶት የግልም ሆነ የጋራ(ስብስብ) ሀይማኖታዊ ቱፊቶችን(አለባበስ፣ አመጋገብ እና ፀሎት) እንዲከለከል አድርጓል::

የአንቀጹን ትክክለኛ ትርጓሜ ስንወስድ ግን በቡድን የሚደረጉ ሃይማኖታዊ ስርዓቶችንም ይሁን በግል እሚፈጸሙትን በምንም አይነት መልኩ ትምህርት ላይ ተጽዕኖ አያሳድር:: ከላይ የተጠቀሱት አንቀጾች ግን በቡድንም ይሁን በግል እሚፈጸሙትን ሃይማኖታዊ ስርዓቶችንም ከዚሁ የህገ መንግስቱ አንቀጽ አያይዘው ትክክለኛ ያልሆነ ትርጓሜ በመስጠት በርካቶችን ከትምህርት ገበታ እያባረሩ ፣ በርካቶችንም እያሰሩ ይገኛሉ፡፡

የሀገራችን Secularism ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ሁለት አበይት ነጥቦች ማካተት ይኖርበታል፡-

1/ Secularism ከአሁን በፊት በኢትዮጵያ ለረዥም ጊዜ በሰፊው የተስተዋለውን ያልተገባ የሃይማኖቶች ግንኙነት በማረም የአንድን ሃይማኖት የተናጥልና ኢ-ፍትሃዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጫና በማስወገድ የሃይማኖቶችን እከኩልነት ማረጋገጥ፣

2/ የSecularism አንፃራዊ ባህርይ በመገንዘብ የመንግስትና የሃይማኖት መነጣጠል የኢትዮጵያን ሃይማኖቶች ባሕርይ ከግምት ውስጥ ያስገባ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም Secularismን ከምዕራቡ Judeo- Christian ባህል አኳያ ብቻ ማየቱ በኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚገኙ ሁሉም ሃይማኖቶች አግባብነት ላይኖረው ስለሚችል ነው፡፡

የኢትዮጳያ መንግሰት Secular መሆኑን ለማረጋገጥ የወጡ የህገ-መንግስት ድንጋጌዎችም ከአጠቃላይ የ Secularism ዕይታ፣ ከሕገ-መንግስቱ አጠቃላለይ መንፈስና ዓላማ አንፃር እንዲሁም የሀገራችንን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ሊተረጎሙ ይገባቸዋል፡፡ በጥቅሉ Secularism ማለት ሀይማት አልባ መንግስት መመስረት እንጂ ሀይማኖት አልባ ህዝብ መፍጠር አይደለም፡፡ ስለዚህ መንግስት ሀይማኖት አልባ ህዝብ ለመፍጠር እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በአስቸኳይ ይቁም!

በተማሪዎች( በተለይ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ) ላይ የተከፈተው ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲቆምልን እንጠይቃለን፡፡ ተማሪዎች የተነፈጉትን መብት እስኪመለስላቸው ድረስ እኛም ፀንተን እንታገላለን!

የህገ-መንግስቱ አንቀጽ 90 ይከበር!

በሰኪዩላሪዝም ሽፋን የሚፈፀመው የሂጃብ ገፈፋ በአስቸኳይ ይቁም!!!

አላሁ አክበር!!!


(አፈንዲ ሙተቂ)
——
አሁንም ግን እደግመዋለሁ!! እኔ ህልመኛ ነኝ! ይህ የኔ ህልም በፈጣሪም ሆነ በሰው ልጆች ዘንድ “ብሩክ” ተብሎ የሚወደስ ነው፡፡ ስለህዝቦች ፍቅር፣ ህብረት፣ አንድነትና እኩልነት ማለም የዘወትር ተግባሬ ነው፡፡ መቼም ቢሆን ይህንን ከማድረግ ወደ ኋላ አልልም፡፡ እንኳንስ በደንብ የማውቃቸውን የኤርትራና የኢትዮጵያ ህዝቦችን ይቅርና አምስቱ የምስራቅ አፍሪቃ ሀገራት (ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ጅቡቲና ኤርትራ) በኮሎኒያሊስቶች የተሰመሩ ድንበሮችን በጣጥሰው በአንድ ግዛት ስር እንዲጠቃለሉ በጽኑ አልማለሁ፡፡ ምን ይሄ ብቻ! ትልቋ እማማ አፍሪቃም አንድ ሀገር እንድትሆን በብርቱ ነው የማልመው፡፡
*****
ኤርትራና ኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ ችግሮች በቆሰቆሷቸው አቧራዎች መነሾነት ሁለት ሀገር ሆነዋል፡፡ ፍቺያችን በደም የታጀበ መሆኑ በጣም ያሳዝነናል፡፡ ያስለቅሰናል፡፡ ይህ ማለት ግን “አንድ ላይ የመሆናችን ጉዳይ ለዘልዓለሙ አብቅቶለታል” ማለት አይደለም፡፡ ሰው ሰራሽ ድንበር በኛ መካከል ቢሰመርም ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋና ጂኦግራፊ በአንድ ላይ ያስተሳስረናል፡፡ የህዝቦቻችን የጋራ ታሪካዊ ውቅር መቼም ቢሆን አይፋቅም፡፡ 
  እኛና ኤርትራዊያን በጣም ነው የምንመሳሰለው፡፡ እንዲህ የሚመሳሰሉ ህዝቦች የማታ ማታ ተመልሰው አንድ የሚሆኑበትን ሁኔታ የዓለም ታሪክ አሳይቶናል፡፡ ሁለቱ ጀርመኖች ከአርባ አምስት ዓመታት በኋላ ተዋህደዋል፡፡ ሁለቱ የመኖችም ከሰላሣ ዓመታት በኋላ ሲዋሃዱ አይተናል፡፡ ታዲያ ይህንን እያየን የምን ተስፋ መቁረጥ ነው?
   እኛና ኤርትራዊያን ከመመሳሰልም አልፎ በጣም ነው የምንቀራረበው፡፡ በጣም እንዋደዳለን፡፡ ይህንን በቀላሉ ለመረዳት ኤርትራዊያንና ኢትዮጵያዊያን በዲያስፖራው ክፍለ-ዓለም የሚኖሩበትን ሁኔታ ማስተዋል ይበቃል፡፡ ወደየትኛውም የዓለም ሀገር ሄደን ብናይ ከማንም በላይ ለኤርትራዊያን የሚቀርቡት ኢትዮጵያዊያን ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ለኢትዮጵያዊያንም ከማንም በላይ የሚቀርቡት ኤርትራዊያን ናቸው፡፡ አምና (በህዳር ወር 2005) የሳዑዲ ዐረቢያ የጸጥታ ሀይሎች በኢትዮጵያዊያን ላይ የወሰዱትን በደልና ግፍ የተቀላቀላበትን ከሀገር የማባረር እርምጃ ከኢትዮጵያዊያን ጎን ቆመው ሲያወግዙ የነበሩት ኤርትራዊያን ብቻ ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያዊያን ባካሄዷቸው ሰልፎች ላይ ከኤርትራዊያን በስተቀር የሌላ ሀገር ዜጋ አልተሳፈተም፡፡
  
   የሜዲትራኒያን ባህርን በህገ-ወጥ ጀልባዎች በማቆራረጥ ወደ አውሮጳ ሲከንፉ ባህሩ የሚበላቸው ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ምንዱባንስ እንዴት ይረሳሉ?… ስለነርሱ በምንሰማው መጥፎ ዜና ሁለታችንም አንድ ላይ “እህ!” እያልንና በቁጭት እየተቃጠልን አይደለም እንዴ?… መርዶአቸው በአንድ ላይ እየደረሰን በአንድ ላይ ለቅሶ እየተቀመጥን አይደለም እንዴ?…
በደጉም ቢሆን መመሳሰላችንና መፈቃቀራችን ብዙ የተጻፈለት፣ ብዙ የተነገረለት ነው፡፡ ዛሬም ድረስ ያንን ሳቂታ የቤኒ አምር ወጣት የኛ ልጅ በመሆኑ ነው የምናውቀው፡፡ ዛሬም ድረስ ከኤርትራዊ ጎረቤቶቻችን ጋር ፋሲካና አረፋን በአንድነት እንታደማለን፡፡
*****
  እኛ ኤርትራን የምንፈልጋት ለወደቦቿ ስንል አይደለም፡፡ እኛ ኤርትራን የምንፈልገው ሁለመናዋ ከኛ ጋር ስለሚመሳሰልና አንድ ዓይነት ስለሆንን ነው፡፡ እኛ ኤርትራን የምንፈልገው ከነህዝቧ ነው፡፡ የኤርትራ ህዝብ የኛ ህዝብ ነው፡፡ እኛ ራሳችን የኤርትራ ህዝብ ነን፡፡ ኤርትራም ኢትዮጵያ ናት፤ ኢትዮጵያም ኤርትራ ናት፡፡ ኤርትራ ወደብ ባይኖራት እንኳ ይህ አቋማችን አይቀየርም፡፡ ታሪኳ፣ ባህሏ እና ቋንቋዋ እናንተ ከምታውቁት ተቀይሯል እስካልተባለ ድረስ ስለርሷ ማለማችንን አንተውም፡፡
 
  ህልማችን ጽኑ ነው፡፡ ወደፊት የትግበራ ምዕራፎቹን እያሰፋ የሚሄድ ነው እንጂ በእንጭጩ ተቀጭቶ የሚቀር አይደለም፡፡ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያም በአፋቤት ሽንፈት ሲያጋጥማቸው በተስፋ መቁረጥ ስሜት “ቤንዚን አይቆፈርበት፤ አልማዝ አይወጣበት፣ ሰው የለበት! Nothing`” እንዳሉት እኛም ተስፋ ቆርጠን ኤርትራንና ህዝቧን የምናጥላላበት ሁኔታ በፍጹም አይከሰትም፡፡ ቢኢዝኒላህ!! ኢንሻ አላህ!!
   እኛ ስለትልቋ ኤርትራ ማለምን ትተን “አሰብ የኢትዮጵያ ወደብ ናት” ከሚሉት የወደብ ጥማተኞች ጎንም አንሰለፍም፡፡ ፍላጎታችን “የኢኮኖሚ እድገት” በሚባለው የማቴሪያሊስቶች ዝባዝንኬ የሚመራ ባለመሆኑ ለጥቅም ብለን ህልማችንን በመንደር ደረጃ አናሳንሰውም፡፡ ቢኢዝኒላህ!!
   
    የእነዚህን የወደብ ጥማተኞች ቅስም ለመስበር በሚል የፖለቲካ ስሌት ተነሳስተን “የአሰብ ወደብ እጣ ፈንታ የግመሎች ውሃ መጠጫ ኩሬ ከመሆን አያልፍም” የሚል ታሪካዊ ተወቃሽነትን የሚያስከትል ቃልም አይወጣንም፡፡ ቢኢዝኒላህ!!
 
  እኛ ኤርትራዊያንን እንደኛው አድርገን ነው የምናያቸው እንጂ አንዳንድ ብስጩዎች በሚተነፍሷው ወሬዎች ተናደን “የቅኝ-ተገዥነት ስሜት ሰለባዎች ናችሁ” በማለት አንፈርጃቸውም፡፡ በምንም መልኩ ቢሆን ኤርትራዊ ወገናችንን የሚያሳቅቅና የሚያበሳጭ ክፉ ንግግር አንናገርም፤ ክፋታችንንና የውስጥ ጥላቻችንን የሚያሳብቅ ጽሑፍም አንጽፍም፡፡ በውስጣችን ስለኤርትራ መውደም እያሰብን በምላሳችን ብቻ “አንድ ህዝቦች ነን” እያልን የምንሰብክ መናፍቃንም አይደለንም፡፡ እኛ ኤርትራንና ህዝቧን የምንወደው ከልባችን ነው፡፡ ስለነርሱ የምናልመው ህልማችንም ከልባችን ከተወረወረ የፍቅር ፍላጻ የፈነጠቀ ነው፡፡
*****
ህልማችን የቅርብ ሳይሆን የሩቅ ነው! እጅግ በጣም ሩቅ!! ይሁንና ርቀቱን ፈርተን ማለማችንን አንተውም፡፡ ዘወትር ስለውቢቷ ኤርትራና ህዝቧ ማለማችንን እንቀጥላለን!! ከሩቁና መልከ-መልካሙ ህልማችን ጋር ወደፊት!!
—-
አፈንዲ ሙተቂ
ጳጉሜ 4/2006
—-
Afendi Muteki, is a researcher and author of the ethnography and history of the peoples of East Ethiopia. You may follow him on his facebook page. Just click this link

የአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ እጅግ ደማቅ በመሆነ ሁኔታ እየተካሄደ ነው። የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት አረንጓዴ ፤የአዲስ አበባ ምክር ቤት ቢጫ፤ የክልል ዞን ተወካዮች ቀይ ቲሸርቶችን በመልበስ ለጉባኤው ድምቀት ሰጥተውታል፡፡ ዛሬና ነገ በሚደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ምርጫ ቦርድ በድርጅቱ ደንብ ላይ የኮረም ቁጠር ይጠቀስ የሚል ጥያቄ በመቅረቡ፣ የቀረበው ጥያቄ ከሕግ ውጭ ቢሆንም ( ደርጅቶች የሚተዳደሩበትን ደንብ ምን […]

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለዛሬ አርብ (03/04/07) የጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ በደማቅ ሁኔታ ተጀምሯል። ጠቅላላ ጉባኤተኛው ወደ አዳራሹ የገባው ፓርቲው ያዘጋጀውን ነጭ ኮፍያ በአንድነት ያደረጉ ሲሆን የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት አረንጓዴ ፤የአዲስ አበባ ምክር ቤት ቢጫ፤ የክልል ዞን ተወካዮች ቀይ ቲሸርቶችን በመልበስ ለጉባኤው ድምቀት ሰጥተውታል፡፡ የጉባኤ ጠሪ ኮሚቴው መድረኩን ተቀብሎ፤ አቶ ብሩ ብርመጂ ንግግር አድርገዋል፡ […]

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የጠራው ጠቅላላ ጉባኤ የተጀመረ ሲሆን ተሳታፊዎች የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት አረንጓዴ ፤የአዲስ አበባ ምክር ቤት ቢጫ፤ የክልል ዞን ተወካዮች ቀይ ቲሸርቶችን በመልበስ ለጉባኤው ድምቀት ሰጥተውታል፡፡
Image

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አርብ (03/04/07) ጠቅላላ ጉባኤውን ያደርጋል፡፡ ፓርቲው ከዚህ ቀደም በታህሳስ 19/20/2007 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን አመት ሳይሞላ ሌላ ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ ለምን እንዳስፈለገ የጉባኤ ጠሪ ኮሚቴ የሆኑትን አቶ አስራት ጣሴን አነጋግረን ነበር፡፡ አቶ አስራት እንዳብራሩት በታህሳስ 2006 ዓ.ም ተካሂዶ በነበረው ጠቅላላ ጉባኤ ምርጫ ቦርድ ማብራሪያ ጠይቆ ነበር፡፡ አቶ አስራት በተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ማቋቋሚያ አዋጅ 573/2000 መሰረት ምርጫ ቦርድ የጠቅላላ ጉባኤ ሪፖርት ማብራሪያ መጠየቅ እንደሚችል ገልፀው በሀምሌ 25 ቀን 2006 ዓ.ም በፃፈው ባለ ሶስት ገፅ ደብዳቤ ዘጠኝ ማብራሪያ የሚፈልጉ ጥያቄዎችን አቅርቦ ነበር፡፡
Image
አንድነት ፓርቲ በበኩሉ ሀምሌ 30 ቀን 2006 ዓ.ም ለተጠየቁት ጥያቄዎች ማብራሪያ ላከ፡፡ ከተላከው ማብራሪያ በመነሳት ምርጫ ቦርድ ጥቅምት 19 ቀን 2007 ዓ.ም ጥያቄዎቹን ወደ 6 ዝቅ አደረገ፡፡ ፓርቲው በበኩሉ ጥቅምት 21 ቀን 2007 ዓ.ም ለተጠየቁት ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጠ፡፡ ከዚያ በመቀጠል ምርጫ ቦርድ ህዳር 10 ቀን 2007 ዓ.ም ሶስት ማብራሪያ ያስፈልጋቸዋል ያላቸውን ጥያቄዎች ያቀረበ ሲሆን ፓርቲውም ህዳር 11 ቀን 2007 ዓ.ም ማብራሪያ ሰጥቶባቸዋል፡፡
Image
ለአሁኑ ጠቅላላ ጉባኤ መጠራት ምክንያት የሆነው ህዳር 19 ቀን 2007 ዓ.ም ወደ አንድ ወርዶ በምርጫ ቦርድ የቀረበው ጥያቄ ነው፤ ፓርቲው የጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊ ቁጥሩን እንዲገልፅ የተጠየቀበት፤ ፓርቲው የጠቅላላ ጉባኤ ቁጥሩ 320 መሆኑን ገለፀለት፡፡ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ይህ ቁጥር ታህሳስ 19 እና 20 ቀን 2006 ዓ.ም በተደረገው ጉባኤ በተሻሻለው በደንብ ባለመካተቱ ተካቶ ይቅረብልኝ ሲል ጠየቀ፡፡ በዚህ ሁኔታ በፓርቲው ደንብ መሰረት የጠቅላላ ጉባኤ ቁጥር መወሰን የሚችለው ራሱ ጉባኤው በመሆኑ ጠቅላላ ጉባኤ መጥራት እንዳስፈለገ አቶ አስራት ጣሴ ገልፀውልናል፡፡
አቶ አስራት በመጨረሻ ባስቀመጡት ሀሳብ ምርጫ ቦርድ ምርጫ ሲደርስ እንዲህ ዓይነት ጥያቄ መጠየቁ እኛን አጣብቂኝ ውስጥ ለመክተት ቢሆንም ህጋዊ መሰረት ግን አልነበረውም ብሏል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በደንቡ ላይ የጠቅላላ ጉባኤውን ተሳታፊ ቁጥር የወሰነው ብቸኛው ፓርቲ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ብቻ እንደሆነ ታውቋል፡፡
Image
Image

ከአፍሪቃና ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ በጀልባ ፤ ባህር አቋርጠው አውሮፓ ለመግባት የሚሞክሩ ስደተኞች ቁጥር በየጊዜው በመናር ላይ ነው። ቁጥራቸው የሚያመዝነው የአፍሪቃ ስደተኞች መሆናቸውም ይነገራል። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን

(የሰማያዊ ፓርቲ ዘገባ) በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት ታፍሰውና ደብደባ ተፈጽሞባቸው ከታሰሩ በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበው ‹‹ህገ መንግስቱን በመናድ፣ መስቀል አደባባይ ላይ ንብረት በማውደም፣ በሁከትና ብጥብጥ›› እና በመሳሰሉት ክሶች ተከሰው እስከ 14 ቀን ቀነ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸው የነበሩት የሰማያዊና የሌሎች የ9ኙ ፓርቲዎች አመራሮች፣ አባላትና የሰልፉ ተሳታፊዎች በመታወቂያ ዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ፡፡ ከእስረኞቹ መካከል ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸው አዲስ አበባ ፖሊስ (ሶስተኛ) ታስረው የነበሩት ‹‹ህገ መንግስቱን በመናድ›› ክስ 14 ቀን፣ ፖፖላሬ ታስረው የነበሩት ‹‹መስቀል አደባባይ ላይ ንብረት በማውደም›› 7 ቀን፣ እንዲሁም ቤላ እስር ቤት ታስራ የነበረችው ወይንሸት ንጉሴ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠርና ህዝቡን በመረበሽ›› 7 ቀን፣ እንዲሁም ኮተቤ ታስረው የነበሩት እነ ፍቅረማሪያም በተመሳሳይ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር›› 10 ቀን ተቀጥሮባቸው የነበር ቢሆንም ከቀጠሯቸው ቀን ቀድም በመታወቂያ ዋስ እንዲፈቱ ተወስኗል፡፡ በሶስተኛ፣ ፖፖላሬ፣ ቤላና ኮተቤ የነበሩት እስረኞች ከትናንት ጀምሮ በመታወቂያ ዋስ እንዲወጡ ቢወሰንም ፖሊስ አንዳንድ እስረኞችን በተለይ ፖፖላሬና ሶስተኛ ታስረው የነበሩትን ነጥሎ ለማስቀረት ባደረገው ጥረት የመታወቂያ ዋስ አምጥተው እንዲፈቱ የተነገራቸው እስረኞች ‹‹አብረውን የታሰሩት ካልተፈቱ አንወጣም›› በማለታቸው ሳይፈቱ አድረዋል፡፡ ዛሬ ታህሳስ 2/2007 ዓ.ም ደህንነቶች ሶስተኛ ታስረው የነበሩትን መርከቡ ሀይሌ፣ ሳሙኤል አበበ፣ ምኞት መኮንን እና ሜሮን አለማየሁ እንዲሁም ፖፖላሬ ታስረው የነበሩትን ዮናስ ከድርና ተስፋዬ መርኔ ‹‹አብራችሁን ካልሰራችሁ አትወጡም!›› ብለዋቸው እንደነበር ታውቋል፡፡ ሆኖም በመታወቂያ ዋስ እንዲወጡ የተነገራቸው እስረኞች ‹‹እነሱ ካልወጡ እኛም አንወጣም›› በማለታቸው በአራቱም እስር ቤቶች የሚገኙት ሁሉም ታሳሪዎች የመታወቂያ ዋስ አቅርበው እንዲለቀቁ […]

ቅዳሜ ትብብሩ በጠራው ሰልፍ ለማገዝ ወደ ሰማያዊ ቢሮ ሄዶ ነበር። አግዞ ከዚያ ሲመለስ ይታሰራል። የመኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ የነበረው ወጣት ተስፋሁን አለምነህ ነው። የሰማያዊ አመራር አባላት በሙሉ ሲፈቱ አቶ ተስፋሁን ስለመፈታቱ የደረሰን ምንም አይነት መረጃ የለም። ሌላው ሕወሃቶች በአንድ በኩል የሰማያዊ አባላትን በመፍታታትቸው ምናልባት ልቦኖ መግዛት ጀመረው ይሆን እያሉ አንዳንዶች ማሰብ በጀመሩ ሰዓታት ሳይሞላ […]

Image
– የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ በዚህ ከቀጠለ ወያኔ እድሜ አይኖረውም::
– የያዝነው መስመር አያዋጣም:እስከመቼስ እንዲህ ይቀጥላል?” የሚሉ አመራሮች ተነስተዋል::
– ካድሬዎች ሕዝቡን እየዞሩ በመቀስቀስ ዳግም እንዲያደራጁ እየተደረገ ነው::

Minilik Salsawi

ከምርጫው መምጣት ጋር በተያያዘ የወያኔው ጁንታ በህዝብ እና በተቃዋሚ ሃይሎች ላይ እየወሰደ የሚገኘውን እርምጃ ተከትሎ በወያኔ/ኢሕአዴግ ፓርቲ ውስጥ በአመራሮች ደረጃ የውስጥ መተራመሱ መቀጠሉ ታውቋል::ሕዝቡን ማዋከብ እና ተቃዋሚውን ማሰር እንዲሁም በየጊዜው የሚከሰተው የውጪ ሃይሎች ጫና አደጋ ውስጥ ይከተናል ልንጠነቀቅ ይገባል የያዝነው መስመር አያዋጣም በሚሉ እና በሕወሓት አመራሮች መካከል ከፍተኛ የሆነ ውዝግብ መከሰቱን ለፓርቲው ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል::

የተወሰነን ከመተግበርና ከማስፈጸም ውጪ ምንም አስተያየት መስጠት አትችሉም የሚል የቁጣ ቃላቶች ከአቶ ደብረጽዮን የሚወርድባቸው የአቶ ሃይለማርያም የደቡብ ኢትዮጵያ ፓርቲ አመራሮች በማንኛውም የፓርቲ ስብሰባ ላይ የተባለውን ከመደገፍ ውጪ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ታዘዋል::በኢሕአዲግ ውስጥ እየተከሰተ ያለው የአካሄድ ልዩነት አመራሮቹን ከማተራመሱም በላይ በአሁን ወቅት እየተወሰዱ ያሉት እርምጃዎች ከምርጫ በኋላ ቢሆኑ ይሻላል የሚሉ አስተያየቶችና የምንከተለው መስመር አዋጪነቱ ምን ያህል ነው የሚሉ ጥያቄዎች በከፍተኛ አመራሩ መካከል ልዩነት መፍጠሩ ታውቋል::የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ መስመሩን ለማሳት አዳዲስ የተሳሳቱ መረጃዎች እና የቤት ስራዎች (በተለይ ለዲያስፖራው) እየተዘጋጁ መሆኑን የውስጥ ምንጮቹ ገልጸዋል::

ከአዲስ አበባ የሚደርሱ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ከተማዋ በውጥረት ውስጥ መሆኗ በገሃድ እየታይ ነው የሃገሪቱ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሕዝቡን ካለማስደሰቱም ውጪ ክፍተኛ የሆኑ የቢዝነስ ስራዎች ከቀድሞው በባሰ መልኩ ቀዝቅዘዋል::የገዢው ፓርቲ ተላላኪዎች በተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር ስለላ እያካሄዱ ሲሆን ሕዝቡም ያለውን ሁኔታ በንቃት እየተከታተለ መሆኑ ታውቋል:: የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ እንደጅምሩ ከቀጠለ ለውጥ እንደሚመጣ እና ወያኗም እድሜ እንደማይኖረው በሚነገርበት በአሁን ሰአት የወያኗ ጁንታ በምርጫው ለሚሳተፉ ተቃዋሚዎች ከፓርላማ 15% ወንበር እንዲመቻችላቸው ከምርጫ ቦርድ ጋር እየሰራ ሲሆን ፓርላማ መግባት ያለባቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦችን በመለየት እና በማዘጋጀት ላይ መሆኑ ታውቋል::

በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የተከሰተውን ውጥረት ተከትሎ ካድሬ የመንግስት ሰራተኞች ውጡና ቀስቅሱ አደራጁ በማለት ፓርቲያቸው መከራ አብዝቶብናል ሲሉ ማማረራቸው ተሰምቷል::ዳግም በየመንደሩ እየዞሩ በማደራጀት እና በመቀስቀስ ላይ የተሰማሩት ካድሬዎች ወጣቶችን በመቀስቀስ በማደራጅት በመመልመል ዙሪያ አዳዲስ ውይይቶች በኢሕአዴግ አመራሮች ትእዛዝ እየተሰጠ መሆኑ ታውቋል::በዚህም መሰረት አዲስ አበባ ውስጥ በየቀጠናው ካድሬዎቹ የመንግስት ሰራተኞች ስራቸውን እየተዉ ቢሯቸውን ዘግተው ለዚሁ የአደረጃጀት የምልመላ እና ቅስቀሳ ጉዳይ መሰማራታቸው ሲታወቅ መረጃውን ያደረሱኝ ተቃዋሚዎች ወያኔ ያደራጀውን ሃይል
ተጠቅመው የጀመሩትን የለውጥ ትግል ገፍተው መቀጠል አለባቸው ሲሉ አስገንዝበዋል::

ዕለቱ 9ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን እና የሕገ-መንግስታችን 20ኛ የልደት በዓል የሚከበርበት ህዳር 29፤ ቦታው ደግሞ ለዚሁ በዓል ተብሎ በፍጥነት እንዲደርስ የተደረገው የአሶሳ ከተማ ስቴድየም ነው፡፡ የኢ.ፌ.ድሪ ጠቅላላ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ የፌደሬሽን እና የሕዝብ ተወካዮችን ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎች፣የጎረቤት ሀገራት መሪዎች፣ ሚኒስቴሮች፣ የውጭና የሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች፣ የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች የባህል ቡድኖች…ብቻ ምን አለፋችሁ ኢትዮጵያ በስቴድየሙ ከትማለች፡፡ በዓሉ ሰፊ፣ ደማቅና ብዙ ሊባልለት የሚገባ ነበር፡ ስለዚህ ሌላው በይደር ይቆየንና ለዛሬ አንድን ለየት ያለ ክስተት መርጨ ላውጋችሁ።   ለበዓሉ ከታቀዱት ትርኢቶች አንዱ፣ ለ26 ቀናት ሀገሪቱን በመዞር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 204 ሚልዮን ብር የሰበሰበው እና ከታላቁ መሪ ለኢትዮጲያ ብሔር ብሔረሰቦች የተበረከተው የህዳሴ ግድብ ዋንጫ፣ ግድቡንም በአሉንም ወደምታስተናግደው የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ዋና ከተማ መግባት ነበር፡፡ ዋንጫው ወደ አሶሳ ስቴድየም እንዲገባ የታሰበውም ለየት ባለ መንገድ ነበር፤ በሄሊኮፕተር ከሰማይ። በእርግጥ ይህ ለየት ያለ አቀራረብ የታሰበለትን በአሉን የማድመቅ ግብ መትቷል ፡፡ ግቡን የመታው ግን አዘጋጆቹ ባሰቡት መንገድ አልነበረም። ታሪኩ እንዲህ ነዉ። አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ፡ የሚመራውን ቡድን በመያዝ የስቴድየሙን መሀል ከተቆጣጠረ የቡድኑን 26 ቀን ሀገር አቀፍ ጉዞ በሰፊው መተረክ ከመጀመሩ ነበር ዋንጫውን ያዘው የመከላከያ ሄልኮፕተር በድንገት ከተፍ ያለው፡፡ ሄልኮፕተሩ ወደ ሜዳው መሀል ጉዞውን ቀጥሏል፤ ሰራዊት ፍቅሬም ትረካዉን። ሄሊኮፕተሩ ወደ መሀል እስኪደርስ የተነቃነቀ ሰው አልነበረም፣ ቀጥሎ ምን ሊፈጠር እንደሚችል የገመተ የነበረም አይመስል። ልክ ሄልኮፕተሩ ሜዳው መሀል ደርሶ ከፍታ […]

በዛሬው እለት 2/4/2007 ዓ.ም ከክልል የመጡ የአንድነት አመራሮች እንዲሁም የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ፤ ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ፤ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና ታዋቂ ብሎገር እዩኤል ፍሰሀ በዛሬው እለት አንድነት ፓርቲን ተቀላቀሉ ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ከሚባሉት ፓርቲዎች አንዱ አንድነት መሆኑን ጠቅሰው ፓርቲውን በመቀላቀላቸው የተሰማቸውን ደሰታ የላቀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡


ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
—–

ዕለቱ መስከረም 2/1977 ነበር፡፡ በዚያች ዕለት ደርግ ከአጼ ኃይለሥላሤ መንግሥት ስልጣን የተረከበበት 10ኛው የአብዮት በዓል ይከበር ነበር፡፡ ያ በዓል ከቀደሙት በዓላት ለየት የሚልበት አንድ ነገር ታይቶበታል፡፡ ይህም የስመገናናው የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ) ምስረታ በይፋ መታወጅ ነው፡፡ ይህንን ድርብ ደስታ ለማድመቅ ተብሎ የተዘጋጀው ክብረ በዓል በሀገራችን ታሪክ በድጋሚ አልታየም፡፡ ለዚህ በዓል ማክበሪያ በትንሹ አንድ መቶ ሚሊዮን ብር ወጪ ሆኗል (ያ ገንዘብ በአሁኑ ስሌት ሁለት ቢሊዮን ብር ሊሆን ይችላል)፡፡

በዚያን ጊዜ ነው በአስራ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር የተሰራው ታላቁ የኢሠፓ የጉባኤ አዳራሽ ተመርቆ የተከፈተው፡፡ ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ፊት ለፊት ያለው የ“ትግላችን” ሀውልትም በዚህ በዓል ወቅት ነው የተመረቀው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለበዓሉ የታጨችው አዲስ አበባ በደማቅ መብራቶችና በልዩ ልዩ መፈክሮች ተጥለቅልቃ ነበር፡፡ እንግዶች በሚንቀሳቀሱባቸው ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ያሉ አሮጌ ቤቶች በግንብ አጥርና በትላልቅ የጨርቅ ሽፋኖች እንዲከለሉ ተደርገዋል፡፡ የክፍለ ሀገር ዋና ከተሞችና የአውራጃ ከተሞችም በመፈክሮችና በማጭድና መዶሻ ምስሎች አሸብርቀዋል፡፡ በዋና ዋና መንገዶች ላይ ያሉ የንግድ ድርጅቶችና የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በሶስት ቀለማት (አረንጓዴ፤ ቢጫ፤ ቀይ) የተዘጋጁ አምፖሎችን እንዲያበሩ ታዘዋል፡፡ በየቀበሌው የተቋቋሙ የኪነት ቡድኖችም ኢሠፓን የሚያወድሱ መዝሙሮችን አፍልቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የነጭና ጥቁር ስርጭቱን ትቶ ወደ ሙሉ የቀለም ስርጭት የተሸጋገረው በዚያች ታሪካዊ ዕለት ነው፡፡

በዚያ ታላቅ ክብረ በዓል ላይ የምስራቅ ጀርመን ኮሚኒስት ፓርቲ ዋና ፀሐፊና የሀገሪቱ መሪ የነበሩትን ጓድ ኤሪኽ ሆኔከርንና የየመን ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ (ደቡብ የመን) መሪ ጓድ ዓሊ ናስር አል-ሐሰንን ጨምሮ በርካታ የሶሻሊስት ሀገራት ልዑካን ተገኝተዋል፡፡ ከአፍሪቃም የዛምቢያው ኬኔት ካውንዳ፤ የዚምባብዌው ሮበርት ሙጋቤና የሞዛምቢኩ ጓድ ሳሞራ ማሼል የበዓሉ ታዳሚ ነበሩ፡፡ ዋናው የበዓሉ አከባበር ስነ-ስርዓት በኢሠፓ ጉባኤ አዳራሽና በአብዮት አደባባይ የተካሄደ ሲሆን በተለይም በአብዮት አደባባይ የተካሄደው ልዩ ትርዒትና ወታደራዊ ሰልፍ በሀገሪቱ ታሪክ ተወዳዳሪ አልተገኘለትም፡፡
*****
“ኢሠፓ” የሚባለው ዝነኛ ፓርቲ የተመሰረተው ለአምስት ዓመታት የዘለቀ መጠነ ሰፊ ዝግጅት ከተደረገ በኋላ ነው፡፡ ለፓርቲው ምስረታ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን እንዲያቀላጥፍና ህዝቡን በሶሻሊስታዊ ስርዓት እንዲያደራጅ በሚል “የኢትዮጵያ ሰርቶ አደሮች ፓርቲ አደራጅ ኮሚሽን” (ኢሠፓአኮ) የተባለ ከፍተኛ የአስፈጻሚ አካል በመስከረም 1972 ተመስርቶ ነበር፡፡ ይህንን ኮሚሽን ማቋቋሙ ያስፈለገው “የሰርቶ አደሩን ፓርቲ ለመመስረት የሚቻለው ህዝቡን በማንቃትና በማደራጀት በአንድ ማዕከል ዙሪያ ካሰባሰቡ በኋላ ነው ” በሚለው የኮሚኒስቶች ርዕዮተ-ዓለማዊ መርህ መሰረት ነው፡፡ የዚህ ኮሚሽን ተጠሪ በመሆን በየክፍለ ሀገሩ የተመደቡ ወኪሎች የየአካባቢው የበላይ ውሳኔ ሰጪዎች ነበሩ፡፡ የኮሚሽኑን ዓላማ የሚገልጸው “የኢሠፓአኮ ተልዕኮ ይሳካል” የተሰኘ መፈክር በመላው ኢትዮጵያ ተደጋግሞ ይሰማ ነበር፡፡
  ኢሠፓ የተመሰረተው ለአምስት ቀናት በተካሄደ መስራች ጉባዔ ነው፡፡ በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ በድርጅታዊ አሰራር የተዘጋጀ ምርጫ ተደረገ፡፡ ጓድ መንግሥቱ ኃይለማሪያም የፓርቲው ዋና ጸሐፊ ሆነው መመረጣቸውም ተነገረ፡፡ ከርሳቸው ጋርም መቶ ሰማኒያ ሶስት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ተመረጡ፡፡
*****
የኢሠፓ አወቃቀርና አሠራር በሌሎች የሶሻሊስት ሀገራት ከታዩት ኮሚኒስት ፓርቲዎች ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ፓርቲው የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት የበላይ ነው፡፡ የፓርቲውና የአስፈጻሚ አካላቱ ግንኙነት የጎንዮሽ ሳይሆን ከላይ ወደታች የተዘረጋ መዋቅራዊ መልክ ነበረው፡፡ በመሆኑም ኢሠፓ በየትኛውም እርከን ላይ ላሉት አስፈጻሚ አካላት የበላይና አመራር ሰጪ ነው፡፡ ይህ አወቃቀር በሀገር አቀፍ፣ በክፍለ ሀገርና በአውራጃ ደረጃ የተዘረጋ ነው፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የነበሩት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አመራር የሚቀበሉት ከኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ነው፡፡ በክፍለ ሀገርና በአውራጃ ደረጃ ያሉ መስሪያ ቤቶችም ከኢሠፓ ጽ/ቤት ነው አመራር የሚሰጣቸው፡፡ በመሆኑም የአውራጃና የክፍለ ሀገር የኢሠፓ ኮሚቴ አንደኛ ፀሐፊ ሆኖ የተመደበ ሰው በፕሮቶኮልም ሆነ በስልጣኑ ከሌሎች ተሿሚዎች ሁሉ ይበልጣል፡፡
 የኢሠፓ መዋቅር በኢ-መደበኛ ሁኔታ ሁሉንም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች አዳርሷል፡፡ በያንዳንዱ የመንግሥት መስሪያ ቤት፣  በማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅቶችና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ “የኢሠፓ መሰረታዊ ድርጅት ጽ/ቤት” የሚባል መምሪያ ነበረ፡፡ የዚህ መሰረታዊ ድርጅት ዓላማ የኢሠፓን ርዕዮተ ዓለም ማስተማርና ከበላይ አካል የመጡ መመሪያዎች ተፈጻሚ መሆናቸውን መቆጣጠር ነው፡፡ ለፓርቲ አባልነት ብቁ የሆኑ ጓዶችን መልምሎ የአባልነት መታወቂያ የሚሰጠውም እርሱ ነው፡፡
ኢሠፓ በፕሮፓጋንዳው ዘርፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ያደርግ ነበር፡፡ የፓርቲው ልሳን “ሠርቶ አደር” የሚባለው ሳምንታዊ ጋዜጣ ነው፡፡  መስከረም ደግሞ የፓርቲው የርዕዮተ ዓለም መጽሔት ነው፡፡ የፓርቲው አባላት በሁለቱ ህትመቶች በወጡ ጽሑፎች ላይ የመወያየት ግዴታ አለባቸው፡፡
 ኢሠፓ የደርግ መንግሥት ከስልጣን እስከተወገደበት ጊዜ ድረስ ቆይቷል፡፡ በስልጣን ላይ በነበረባቸው ሰባት ዓመታት በጠቅላላው ከ100, 000 ያላነሱ አባላትን አፍርቷል፡፡ አባላቱ ከሲቪልም ሆነ ከጦር ሀይሉ ክፍል የተመለመሉ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ የፓርቲ አባል በስራ ቀናት ከካኪ የተሰፋ ሱሪና ኮት የመልበስ ግዴታ አለበት (ይህ መመሪያ የወጣው “የሀገር ውስጥ ምርቶችን ማበረታታት አለብን” በሚል መነሻ ነው፤ ካኪው በቃሊቲ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ነው የሚመረተው)፡፡ 
ከላይ እንደገለጽኩት የኢሠፓ ዋና ፀሐፊ ጓድ መንግሥቱ ኃይለ ማሪያም ነበሩ፡፡ ፓርቲው ምክትል ዋና ፀሐፊ በይፋ ባይሰይምም የጓድ መንግሥቱ ተከታይ ሆነው ሲሰሩ የነበሩት ጓድ ፍቅረ ሥላሤ ወግደረስ ናቸው፡፡ የርዕዮተ-ዓለም መምሪያ ሃላፊው ጓድ ሽመልስ ማዘንጊያ ሲሆኑ ጓድ ብርሃኑ ባይህ የውጭ ግንኙነት መምሪያ ሃላፊ ነበሩ፡፡ ጓድ ሸዋንዳኝ በለጠ የኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሃላፊ፤ ጓድ ተካ ቱሉ የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን ሃላፊ፣ ጓድ ደበላ ዲንሳ የማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ፣ ጓድ ሜጀር ጄኔራል ገብረየስ ወልደሃና የወታደራዊ ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ ነበሩ፡፡ ከሁሉም በላይ ስልጣናቸው ገንኖ የነበረው  ግን የድርጅት መምሪያ ሃላፊው ጓድ ለገሠ አስፋው ናቸው፡፡
  *****
ኢሠፓ የምስረታ ጉባኤውን በሚያካሄድበት ወቅት (ጳጉሜ1-ጳጉሜ 5/1976) ሀገሪቱ በከፍተኛ ድርቅ ተጠቅታ ነበር፡፡ ከአምስት ሚሊዮን የማያንሱ ዜጎች በትግራይ፣ በወሎ፣ በጎንደር፣ በኤርትራ፣ በሀረርጌና በባሌ ክፍላተ ሀገር በቸነፈር ተጠብሰው በሞት አፋፍ ላይ ነበሩ፡፡ አንዳንድ የሀገር ተቆርቋሪዎች መንግሥት የፓርቲ ምስረታ ጉባኤውን ለሌላ ጊዜ እንዲያስተላልፍና የ10ኛ አብዮት በዓልን እንዲያስቀር ቢወተውቱም ሰሚ አላገኙም፡፡ የወቅቱ መንግሥት የድርቁ መኖር ከታወቀ በአብዮት በዓል አከባበሩ ላይ ጥላውን ያጠላል በማለት የምዕራብ ሀገራት የዜና አውታሮች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ከልክሎአቸው ነበር፡፡ ይሁንና አንዳንድ ሚዲያዎች የዜና ዘጋቢዎቻቸውንና የቪዲዮ ሪፖርተሮቻቸውን በድብቅ ወደ ሀገር ውስጥ በማስረግ የዓለም ህዝብ አስከፊውን ድርቅ እንዲያየው አድርገዋል፡፡ በነዚያ ሪፖርተሮች የተቀረጹ ምስሎችን የተመለከቱ የዓለም ህዝቦች ለድርቅ የተጋለጠውን ኢትዮጵያዊ ረሀብተኛ ለመታደግ በተንቀሳቅሰዋል (በሰር ቦብ ጊልዶፍ አስተባባሪነት የተሰባሰቡ የዓለማችን እውቅ አርቲስቶች Live Aid የተባለውን የሙዚቃ ዝግጅት ያቀረቡት ያኔ ነው፡፡ አርቲስቶቹ በዝግጅቱ ላይ በጋራ ያዜሙት We are the world የተሰኘው ዜማ ከምንጊዜም ምርጥ ዜማዎች መካከል አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል)፡፡
   የደርግ መንግሥት በህጋዊ መንገድ ፈቅዶላቸው የመጡ ጥቂት የሶሻሊስት ሀገራት ዘጋቢዎች ደግሞ “ድርቅ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ እየቀጠፈ ለዚህ በዓል ከፍተኛ በጀት መመደብ አግባብ ነውን?” የሚል ጥያቄ በይፋ በማቅረብ የሀገሪቱን ከፍተኛ ባለስልጣናት አጨናንቀዋል፡፡ በመሆኑም የአብዮት በዓሉ ሲፈጸም መንግሥት በድርቅ የተጎዳውን ህዝብ ለመታደግ መንቀሳቀሱ ግድ ሆኖበታል፡፡ ሆኖም የመንግሥት እርምጃ በጣም የዘገየ በመሆኑ አምስት መቶ ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን በዚያ አስከፊ ድርቅ አልቀዋል፡፡
—–
አፈንዲ ሙተቂ
መስከረም 2/2007

ከትብብሩ የተሰጠ መግለጫ በአገዛዙ አረመኔያዊ እርምጃ ትግላችን አይቆምም! የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ባለፈው አንድ ወር ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል መርሃ ግብር ቀርጸን ስንቀሳቀስ ዋናው አላማችን የስርዓቱን አረመኔያዊነት ለህዝብ በማጋለጥ የኢትዮጵያ ህዝብ በትግሉ እንዲሳተፍ ማድረግ ነው፡፡ እንደጠበቅነው ገና ከጅምሩ የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ትግላችንን በጭካኔ ለማስቆም ጥሯል፡፡ ህዳር 27/2007 ዓ.ም የመጀመሪውን የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ በጠራንበት ወቅት ስብሰባውን በኃይል በትኗል፡፡ ትብብራችን ከመቸውም ጊዜ በላይ ያሰጋው ህወሓት/ኢህአዴግ በተለይ የህዳር 27/28 2007 ዓ.ም የአደባባይ አዳር ሰልፍን እንዳይካሄድ የትብብሩን አመራሮችና አባላቶቻችን በማዋከብ፣ በመደብደብና በማሰር ተጠምዶ ሰንብቷል፡፡ በተለይ በትናንትናው ዕለት ሰልፍ በወጣንበት ወቅት ስርዓቱ አመራሮችንን፣ አባላቶቻችንን፣ ተሳታፊዎችንን እንዲሁም አልፎ ተርፎ መንገደኛውን ህዝብ በጭካኔ ደብድቧል፡፡ አፍሶ አስሯል፡፡ ሙስሊም እህትና ወንድሞቻችን በየጎዳናው ታፍሰው የአገዛዙ አረመኔያዊ እርምጃ ሰለባዎች ሆነዋል፡፡ በርካቶችም በየእስር ቤቶቹ ታጉረዋል፡፡ እስካሁን ባለን መረጃ ከ300 በላይ የትብብሩ አመራሮችና አባላት የታሰሩ ሲሆን የትብብሩና የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርን ጨምሮ በርካታ አመራሮች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ድርሶባቸዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል የሆነው አቤል ኤፍሬም ራሱን እስኪስት ተደብድቧል፡፡ በሰላማዊ ሰልፉ የተገኙ ሴት አመራርና አባላት አንድ አገርን እየመራሁ ነው ከሚል አካል በማይጠበቅ መንገድ በጭካኔ ተደብድዋል፡፡ እነዚህ በጭካኔ የተደበደቡ አመራሮች፣ አባላትና የሰልፉ ተሳታፊዎች ህክምና እንዳያገኙ ተከልክለዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በጥበቃ ሰራተኝነት የሚሰሩ የ72 አመቱ አቶ ቀኖ አባጆቢር ከስራ ሲወጡ በደህንነት ኃይሎች ታፍነው የተወሰዱና እስካሁን የት እንደደረሱ ያልታወቀ ሲሆን ይህም አገዛዙ የመጨረሻው የአረመኔነት ደረጃ ላይ እንደደረሰና […]