የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ራዲዮ 3ተኛ ዓመት በጀርመን-ሙኒክ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።
መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቅዳሜ ከቀኑ 14 ሰዓት ጀምሮ ሙሉ ሌሊቱን ጭምር በደማቅ ሁኔታ በተከበረው የኢሳት 3ኛ ዓመት በዓል ላይ ‘ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል። በዝግጅቱ ኢሳት ከየት ተነስቶ የት ላይ እንደደረሰ በስፋት ያብራሩት የድርጅቱ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ነዓምን ዘለቀ፤ኢሳት ለወደፊቱ መድረስ ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ የተሰነቀውን ራዕይ ጠቁመዋል። ከፓናል ውይይቱ ተሳታፊዎች …