በደቡብ ክልል በጉራፈርዳ ወረዳ በመዠንገርና ደገኛ በሚባሉት ነዋሪዎች መካከል በተነሳው ግጭት ብዙ ነዋሪዎች መገደላቸው ተሰማ
መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በቴፒ አካባቢ በመዠንገር ብሄረሰብና ደገኛ በሚባሉት ነዋሪዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ተባብሶ በርካታ ህዝብ ካለቀ በሁዋላ የመከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው ገብቶ ለጊዜያው ያበረደው ቢመስልም፣ ግጭቱ ወደ ጉራፈርዳ ወረዳ አቅጣጫ ተዛምቶ እስካሁን ከ20 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውና በርካቶችም በመሰደድ ላይ መሆናቸውን የአካባቢው የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ምንጮች እንደሚሉት ካለፉት ሶስት ቀናት …