ከጉራፈርዳ የተፈናቀሉ አብዛኞቹ አርሶ አደሮች ወደ ቀያቸው ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆኑም
ኀዳር ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጋምቤላና በደቡብ ክልል አዋሳኝ በሆነው በጉራ ፈርዳ ወረዳ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ከፍተኛ የሰው ህይወትና ንብረት ከወደመ በሁዋላ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኖች ባለፉት ሁለት ቀናት የአካባቢውን አመራሮች በመሻርና በመሾም መረጋጋት እንደተፈጠረ በመግለጽ ተፈናቃይ አርሶደሮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለማግባባት ቢሞክሩም፣ አብዛኞቹ አርሶአደሮች ግን ለህይወታችን ዋስትና የሚሰጠን ስለማይኖር ወደ አካባቢው ለመመለስ ፈቃደኞች …