በጉጂ ዞን ንግድ ባንክ ስራ በማቆሙ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ መውሰድ አልቻሉም
ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመንግስት ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጹት በቀድሞዋ ክብረመንግስት በአሁኑ አዶላ ወዮ ከተማ የሚገኘው ክብረመንግስት የኢትጵያ ንግድ ባንክ ካለፉት 9 ቀናት ጀምሮ ስራ በማቆሙ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ለመውሰድ ተችግረዋል። ቤተሰቦቻችን ለችግር ተዳርገዋል የሚሉት ሰራተኞች፣ አቤቱታ ቢያቀርቡም፣ የኔትወርክ ችግር ነው ጠብቁ ከመባል ውጭ መፍትሄ ሊያገኙ አልቻሉም። ፖሊሶችን ጨምሮ ሁሉም የመንግስት …
