http://www.eaglewingss.com/%E1%89%A0-%E … %E1%8B%AD/

በ ኖርዌጅያንዋ የሶስት ወር ፀሃይ
January 30, 2015
በ ኖርዌጅያንዋ የሶስት ወር ፀሃይ
Samson K.

By Samson K.

በሶስት ወሯ የፀሃይ ድምቀት
ሰዉ ራሱን ከፍቶ ሊያሳርግ የራስን ድብርት፤
ተደርድረዉ ውበት እና ድብርት
ዉስጠትና ዉጭ – ሊሆኑ የምድር ትዕይንት ፤
አንዱ ሊያራግፍ የታፈኑ የወራትን ድብርት ፣
የታፈነች ፅጌረዳም ድንግል የዉበት አሸት ፣
ራስዋን ፈልቅቃ አንደ ባህሩ እምቡጥ ቀንድ ኣውጣ –
ራሰዋን ልታሳይ -ራስዋን ልጣ – ከደመና ጋግርት ፤ዉበትን ልታዋጣ

የነፍሳት ህብረት በዝግመተ ጋግርት ላይ- – ለዚያ ድብርት፤ለጣዉንቱ ጭጋግ ጭንቀት
ለዚያ ቅዠት አዚም-፣ ዉግምት፣ ዝጋት፣ ግዚያዊ ስንብት
ሕይወት ጓጉታ ራስዋን ልተነፍስ ዉስጣዊ ስቃይዋን
ፍላጎትዋን ለሶስት ወርዋ ፀሐይ ንግስት፤

ፀሃይን ለመሞቅ የመሞቅ ግርግር -ለዉጭ ብርሃን ጨረር እሽቅድምድም
ሁሉ ራሱን ሰጥቶ ራሱን ከፍቶ ፀሀይቷን ሊቆዝም
የሰባን ፅልመት የደመና ጋግርት -ሊያቀልጥ ከራስ ላይ የራስ አዚም ፤
ሽብሽብ ቁርፍድ ቆዳ ከራስ ለጋ እንቡጥ ፅጌረዳ
መሳ ለመሳ ፣ስጋ ከነፍስ፣ ሳቅ ካዘን ፣ መደዳ- ለመደዳ
ታፍነዉ የከረሙ ከዛ ጋግርት ጭፍጝግ- የደመና ጓዳ ፤

ሁሉም ራሱን ፈታ- እሷን አምኖ ፀሃይቷን- ያችን….. ባዳ
ራሱን ሊያራግፍ ከራሱ ያዚም ኣቁማዳ
ቢፍታታ ቁርፍድ ቆዳ ከራስ ፅገረዳ ፣በሶስት ወሯ የፀሃይ ማለዳ፤
ነፍሳት እስዋን አምነው ሊ ሞ ቋ ት – ሁሉም ራሱን ሰጥቶ ሊታደላት
በራስ ናፍቆት ጉጉት፣ እስዋን ጥበቃ ራሱን ስጥቶ፣ ሊሞቃት
እስዋን ሙቆ ፣እስዋን ጠጥቶ፣ እስዋን ተጠርቅቶ ፣ እስዋን ሊፈነዳት ፤

እውነትና ሐሰት ፣ ደስታና ስቃይ
ፍቅርና ኩነኔ፣ ገመናና ሃፍረት
በሙቀትዋ -በብርሃንዋ -በስዋ አደባባይ እንዲያ ተበረግደዉ ፣
በግለትዋ ግለዉ ነፍሳት ተዘናግተዉ
መሸሽጊያ ሳይኖራቸዉ ፣
ምነዋ ማዝገሟ ቁ…ል..ቁል – ድንገት ሳይታሰብ – ደግሞ ………ሳትነግራቸዉ ፤

Ray1

ነካስ ለጋስ ኖሯል ..ይሄ ጋግርት የጭጋ ግ ደመና
ጭጋግ ሆኖ ራስን መሸሸጊያ
ራስን መደበቂያ -በራስ ዉስጥ- የራስን ገመና
በወራት የበረዶ ጝጝር- በፅልመተ የጭጋግ ደመና ፤

ግዜና መከራ አስኪያልፍ በደመና ራስን ድብብቆሽ
ራስን ሊያሳርፉ -ራስም ፣የራስን አንድዮሽ
በጭፍጝጝ ደመና በፅልመት -ዉሸታሙን ዉጩን ድብብቆሽ
ራስን በራስ ቀብሮ – ራስ ሲያምጥ ፣ ራስን ሊያቆይ – በራስ ዉስጥ -የብርሃን ግርዶሽ ፤

አስተማረኝ አሳየኝ ፣ባዳዋን ዉሸታሟን የፀሃይ ንግስት
አንዱ ግሎ ገሎ ሲዝናናባት – አንዱም ግሎ ገሎ ሲታይባት
አንዱም ዉስጡ በርዶ ዉጩን ሲቀልጥባት- እስዋን ቆሞ ሲቃጠላት ፤
ራስ ቆሞ በራስ ተዋርዶ
ለራስ አዛኝ አልቃሽ ጠፍቶ
ስም በሰዉ ሐገር – ሐገር በሰዉ ተሸልቶ
በሰዉ ሐገር ፀሃይ ራስ ተበርግዶ፤

የዘር ዕምነት እዚም እዚያም- ታስሮ- – በራስ አንገት -የሰዉ ማተብ
በሰዉ ሐገር ፀሃይ፣ እንተፍ እንተፍ፣ የመምሰል -ዱብ ዱብ
ሰዉ ሲሮጥ ራሱን ጥሎ ሊያሳይ -መፈጠሩን በሰው አምሳል
ሰዉ -ለሰዉ አድሮ ራሱን ጥሎ ሲልሹዋሽዋ- -እንደነዚያ የበረዶ ዉሾች ያንገት ፅናፅል፤
አየነዉ… ከደመና ያንን በሰዉ አርጥባን ድግስ ደጋሹንም ስሙን ፋቂ ስደተኛ – ባላገሩን ፖለቲከኛ
ነግሮ ኣስገዳይ የጁን በጁ ፣ ኣደግዳጊ ባዶ የምላስ ዳንኪረኛ- ባላገሩን ዘመንተኛ
ኣየነው ያዉም ከጨለማ ፤ በሶስት ወራ ፀሃይ እስዋን ታምኖ ሲጫወት አርበኛ

‘ሀ’
-ብታማላት
ለ-‘ ሁ’ ፣
‘ሁ’ም
ብታሳብቅ ለ- ‘ሂ’ ፣

ሂ -ግን ይኸዉ አለች
‘ሀ’ ብላ አፍዋን ሳትከፍት
እንደሳቀች ሂሂሂሂሂ ……..እንዳለች
ምን ይጠቅም ? ብላ ማሰማቱ የራስ.
አ..ሄሄ…. እህ ህን
….አ..ሆ.ሆ.ን..
እኔስ እኖራለዉ ዉስጤ – በራስ አምባዬ
በእዮሃ አበባየ -መስከረም ጠባዬ
በቀዳማዊ አፍሪካዊ ንግስት ያስራሶስት ወራ ፀሃዬ
እኔስ እደምቃለዉ ገና ከዚህም ከፅልመተ ደመና
ከራስ አምባየ በዚያች አፍሪካዊት
የጨረቃ ድምብል ቦቃ –
አፄ ቤት ከገባችዉ አዉቃ፤
እንዲህ…እንዲያ… እያለ እያዋዛ የነገረኝ
ያ -የራስ ሃሳብ የደመና ጓደኛዬ ፣
ነካስ ዕውነት ኖሯል መ ሻ ሉ
ያ በጭፍጝጝ ደመና ያለዉ የራስ መብራት ጓዳዬ።

ShareThis
Share this: