የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አለምነው መኮንን በአማራ ህዝብ ላይ የሰነዘሩትን ዘለፋ ተከትሎ የተነሳውን ተቃውሞ ለማብረድ የብአዴን የወጣቶች ሊግ ለአባለቱ  የስልጠና እና የግምግማ ስራ በባህር ዳር ፤ ደሴ እና ጎንደር እያከናወነ ነው። የካቲት 16  አንድነትና መኢአድ በጋራ የጠሩትን ሰልፍ ተከትሎ በባህር …

የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያን አየር መንገድ ንብረት የሆነውን ቦይንግ 767 አውሮፕላን  በመጥለፍ ጄኔቫ ያሳረፈው ሃይለመድህን አበራ፣ ከጸባዩ በተጨማሪ ብቃት ያለው አብራሪ መሆኑን ግለሰቡን የሚያውቁ ሰዎች ለኢሳት ተናግረዋል። ከስልጠና ጀምሮ የሚያውቁት ጓደኞቹ እንደተናገሩት ሃይለመድህን ለሰዎች ህይወት የሚጨነቅና ጥንቃቄ የሚያደርግ፣ አውሮፕላኑን ከጠለፈ በሁዋላ ተሳፋሪዎች ሳይቸገሩ እንዲያርፍ ማድረጉ የፓይለቱን ብቃት ያሳያል ብለዋል። …

የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አባላቱ ቅሬታቸውን የሰነዘሩት በ2ኛው የመከላከያ ሰራዊት በአል ላይ ነው። በቀን አንድ ዳቦ እና ሁለት ጭልፋ ወጥ ለእራትም በተመሳሳይ ሁኔታ የሚቀርብላቸው የመከላከያ ስራዊት አባላት፣  የቀን የምግብ ፍጆታ በጀታቸው ከህግ ታራሚዎች ያነሰ ነው። ወታደሮቹ  በቀን ስምንት ብር ከሃምሳ ሳንቲም በሆነ የምግብ በጅትየሚተዳደሩ ሲሆን፣ የሚቀርብላቸውን ዳቦ እንኳን  ለመብላት እንደሚቼገሩ …

የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጋርድያን እንደዘገበው የ18 አመቷ ወጣትና ነፍሰጡሩዋ ኢትዮጵያዊት በዝሙት ተግባር በመከሰሷ በድንጋይ ተወግራ ልትገደል እንደምትችል የምስራቅ አፍሪካ የሴቶች ስትራቴጂክ ኔትወርክ ወይም ሲሃ የተባለውን ድርጅት በመጥቀስ ዘግቧል። የ9 ወር ነፍሰ ጡሩዋ ወጣት በእስር ቤት ውስጥ ያለምንም ምንጣፍ በባዶ ኮንክሪት ላይ እንደምትተኛ ጋዜጣው ዘግቧል። ኢሳት ከወር በፊት ዜናውን ይፋ …

የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማጺው መሪ ሪክ ማቻር እና በ ፕሬዚዳንት ሳል ቫኬር ያለው ልዮነት እየስፋ መሆኑን ቅርበት ያላቸው ምንጮች በመግለጽ ላይ ይገኛሉ:: ከትላንት በስትያ በነዳጅ የበለጸገችው የአፐር ናይል ስቴት ዋና ከተማ ማላካል  ከባድ ጦርነት ተካሂዷል። ወደ ማላካል የሚደረጉ  የአየር በረራዎችች መሰረዛቸውንና አካባቢው በከባድ ጦርነት ውስጥ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሎል:: ማላካል የተባለው ቦታ …

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የካፒቴን ሃይለመድህን አበራ የጠለፋ ምክንያት  በአየር መንገዱ ውስጥ የሚታየውን የአስተዳደር መበላሸት ለአለም ለማሳየት ነው  ይችላል የሚለው ምክንያት አሳማኝ ነው ሲሉ አንድ የቀድሞው የድርጅቱ ሰራተኛ ገለጹ በኢትዮጵያ አየር መንገድ  በበረራ ደህንነት ስራ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ያገለገለውና በክትትልና ደህንነት ስጋት ከአመት በፊት ድርጅቱን ለቆ በስዊዘርላንድ ጥገኝነት የጠየቀው ሚካኤል …

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያን በጣሊያን ወራሪ ሃይል በግፍ የተጨፈጨፉበት ቀን በመላው አለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እየተዘከረ ነው። በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የሰምአታት ሃውልት ጀግኖች አባት አርበኞች በተገኙበት በአሉ ተከብሯል። የካቲት 12፣ 1929 ዓም አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የተባሉ ኢትዮጵያውያን ግራዚያኒን ለመግደል የጣሉትን ቦንብ ተከትሎ፣ የጣሊያን ወራሪ ሰራዊት በወሰደው እርምጃ  …

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዕምሮ ቸግር ፤ ዘገምተኝነት ፤ ሱስ ፤ ራስን መጣል ፤ የስነ ልቦና ችግር ፤ድብርት ፤ ከሰው መገለል፤ተስፋ መቁረጥ ፤ እራስን ማጥፋት ፤ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች፤ አሰገድዶ መደፈር ችግር የጣላባቸው ጠባሳ በህይወታቸው ላይ ከባድ ተጽኖ ሁኖ ይሰተዋልባቸዋል ሲል የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስጠናው ጥናት አመልክቷል፡፡ ከአርባ …

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር 702 የሆነውን አውሮፕላን በመጥለፍ ጄኔቫ ስዊዘርላንድ ያሳረፈው ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ እስካሁን ድረስ የጠለፋውን መንስኤና ምክንያት በግልጽ የመናገር እድል ባለማግኘቱ የአለም የመገናኛ ብዙሃን የተለያዩ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው። አንዳንዶች በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አስከፊ ጭቆናና ፓይለቱ አውሮፕላኑን እንዲጠልፍ እንዳነሳሳው ሲገልጹ ሌሎች ወገኖች ደግሞ …

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ ዮሃንስ ገ/እግዚያብሄር ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች በመኪና እንደገጩትና “ገና እንገድልሃለን” የሚል ዛቻ እንደሰነዘሩበት ለፍኖተ ነፃነት መናገሩን ጋዜጣው ዘግቧል። “ጋዜጠኛው ከአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው ጋር በፓርቲው ጽ/ቤት ቃለምልልስ አድርጎ ወደ መገናኛ አካባቢ ሲደርስ ኮድ 1 የታርጋ ቁጥር18345 የሆነ ሚኒባስ ታክሲ ሆነ ብሎ አደጋ …

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦህዴድ ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ፣ ምከር ቤቱ እንዳሰናበታቸው የመንግስት የመገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። አቶ አለማየሁ መታመማቸው ከተዘገበ የቆየ ቢሆንም እስካሁን ከስልጣን ሳይወርዱ ቆይተው አሁን ለምን ለማንሳት እንደተፈለገ ግልጽ አይደለም። በአፋር በቅርቡ በሚካሄደው የምክር ቤት ስበሰባ ላይ ፕ/ት አሊ ሴሮ …

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግርን ለመቅረፍ ይረዳሉ በሚል በብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ተገጣጥመው ወደስራ ከተሰማሩ አውቶቡሶች የቴክኒክ አቁዋማቸው ብቃት መጉዋደልና የመለዋወጫ እጦት ጋር በተያያዘ በየቦታው በብልሽት በመቆማቸው ምክንያት የአዲስአበባ ከተማ የትራንስፖርት እጥረት እንዲባባስ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ተሰምቷል። ከአዲስአበባ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የተገኘ መረጃ እንዳመለከተው በአሁኑ ወቅት በኮርፖሬሽኑ ከተገጣጠሙ 500 …

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፌብሩዋሪ 18//2014 በኤድመንድ ኮሚዩኒቲ ማእከል አዳራሽ በተዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የቫንኮቨር ነዋሪዎች በመገኘት የገንዘብና የቁሳቁስ እርዳታ አበርክተዋል። የእርዳታ አሰባሳቢው ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት አቶ ደበበ ጉሉ ያቀናበሩት፤ በአረብ አገሮች የተከሰተውን የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ የሚያሳዩ የቪዲዮ ቅጂዎች በዝግጅቱ ላይ ለእይታ በመቅረባቸው የወገኖቻቸውን ስቃይ በፊልሙ የተመለከቱ ታዳሚዎች …

የካቲት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አየር መንገዱ ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ጣሊያን በማምራት ላይ በነበረበት ጊዜ  ረዳት አብራሪው የጉዞውን አቅጣጫ በመቀየር ጄኔቭ አውሮፓላን ማረፊያ በማሳረፍ እጁን ለፖሊስ ሰጥቷል። የኢትዮጵያ መንግስት የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን የሆኑት ሬድዋን ሁሴን አየር መንገዱ የተጠለፈው ሱዳን በቆመበት ጊዜ በተሳፈሩ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ነው በማለት መጀመሪያ ላይ ለረዩተርስ መግለጫ ቢሰጡም፣ …

የካቲት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአርሴማ ቤተክርስቲያን የውስጥ ችግር ጋር በተያያዘ ከመንግስት ጋር በመሆን የድርጅት ስራ ሰርተዋል ተብለው የተወቀሱት አቡነ ገብርኤል፣ ትናንት ለአንድ ሰአት ያክል ታግተው ተለቀዋል። ህዝብ በመወከል ሲንቀሳቀሱ የነበሩት የአገር ሽማግሌዎች ታስረው በህዝብ ግፊት እንዲፈቱ ከተደረገ በሁዋላ፣ ለችግሩ መፍትሄ ያስገኛል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም፣ ችግሩ እልባት ሳያገኝ ቀርቷል። ጳጳሱ በህዝቡ …

የካቲት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቡናን ኤክስፖርት ከማድረግ ጋር በተያያዘ በክትትልና ቁጥጥር፣ በመረጃ አያያዝ፣ ያለብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ቡናን ወደውጭ ኤክስፖርት ከማድረግ እና በሁሉም አካባቢ የቡና ድርጅቶችን መጋዘኖች ክምችት ቆጠራ በወቅቱ ባለማድረግ ላይ ክፍተቶች እንደሚስተዋሉ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ያጠናው አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ ጥናቱ  ኤክስፖርት በማያደርጉ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ያለመውሰድ፣ በንግድ ፈቃድ …

የካቲት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የታክሲ ሹፌሮች አድማውን የመቱት አዲሱን የትራፊክ የቅጣት ደንብ በመቃወም ነው። በከተማው መሃል ላይ አሽከርካሪዎቹ ተሰብስበው የመኪና ጥሩምባ ማጮሃቸውን የገለጸው የኢሳት ወኪል፣ ከሰአዓታት በሁዋላ ታክሲዎቹ ከአደባባይ ላይ በመሰወራቸው ነዋሪዎች ታክሲዎችን ለማግኘት ሲቸገሩ ታይቷል። የገዢው ፓርቲ ሰዎችና ትራፊኮች፣ በመንገድ ላይ ያገኙትን ታክሲ በማስገደድ ሰዎችን እንዲጭን ለማድረግ ሞክረዋል። ፈቀደኛ ያለሆኑ …

የካቲት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጉርሻ ክፍያው ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ እንዲሰጣቸው ተብሎ የጸደቀበትና የክፍያ ማዘዣው ከከተማ  አስተዳድሩ ለሁሉም ወረዳዎችና ክ/ከተሞች በያዝነው ሳምንት እንደተላለፈላቸው ለማዎቅ ተችሎአል። የጉርሻ ገንዘቡ ከ1 ሺ 700  እስከ 4 ሺ 000 ብር የሚደርስ ሲሆን አገልግሎቱም ለስልክ፣ ለቤት ኪራይ እና ለትራንስፖርት መደጎሚያ ታስቦ የሚሰጥ ነው። ክፍያው በፋይናንስ መክፍያ  ሰነድ …

የካቲት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በሚካሄደው ድርድር በቅርቡ ከእስር የተፈቱት 7ቱ የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተሳታፊዎች ሆነዋል። ይሁን እንጅ ባለስልጣኖቹ ከሁለቱም ወገኖች ሳይሆኑ በገለልተኛነት በድርደሩ ላይ መገኘታቸውን ተናግረዋል። ገለልተኝነትን የመረጡበትም ምክንያት ሲናገሩ ደግሞ የጦር መሳሪያ የለንም የሚል ነው። የሳልቫኪር መንግስት ባለስልጣኖችን ያሰረው ከተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ነበር። …

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊ ክልል በቀላፎ አካባቢ የሚኖሩ 19 የየረር ባሬ ጎሳ የአገር ሽማግሌዎች በክልሉ ውስጥ የተፈጸመውን ከፍተኛ እልቂት ለጠ/ሚንስትሩ አቤት ለማለት ወደ አዲስ አበባ በሄዱበት ወቅት  አካባቢውን በሚጠብቁ ልዩ ሃይሎች ተይዘው መታሰራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ከእስር ያመለጡ አንዳንድ ሽማግሌዎች በትናንትናው እለት ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ከዚህ ቀደም በልዩ …

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮሚያ ክልል በቡሌ ሆራ ወረዳ፣ በሀገረማርያም ከተማ ከአርሴማ ቤተክርስቲያን ጋር በተያያዘ የተነሳውን የውስጥ ችግር ተከትሎ ችግሩን ለመፍታት የተመረጡት የሰበካ ጉባኤ አባላት ታስረው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ከተጠየቀባቸው በሁዋላ ህዝቡ ባሰማው ከፍተኛ ተቃውሞ የአገር ሽማግሌዎቹ በዛሬው እለት የተፈቱ ሲሆን፣ ህዝቡ በድል አድራጊነት ስሜት በሆታ አጅቦ ወደ ቤተክርስቲያን ወስዷቸዋል። …

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ አሸባሪ ካላቸው ግንቦት ሰባት እና ሌሎች ፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ በርካታ የአዲስ አበባና አማራ ክልል ወጣቶች ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት እየተጋዙ መሆኑን የአይን እማኞች ተናገሩ፡፡ ኢህአዴግ በጀመረው አዲስ አሰሳ በሀገሪቱ አንድንድ ቦታዎች ኢንተርኔትን ጨምሮ ስልክ እንዳይሰራ የተደረገ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎችም የመከላከያ ሀይል ተበትኗል፡፡ …

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ መስተዳድር የካቲት 2፣ 2006 ዓም ከእድር ተጠሪዎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ እያንዳንዱ እድር በነፍስ ወከፍ 8 ሺ ብር ለአባይ ግድብ ማሰሪያ እንዲከፍል ታዟል። ትእዛዙ የተጣለው የካቲት 2 ቀም 2006 ሲሆን፣ 650 እድሮች በነፍስ ወከፍ 8 ሺ ብር ይከፋላሉ። በዚሁ ከላይ በወረደው መመሪያ መንግስት ከእድሮች በአንድ ጊዜ …

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በጋዜጠኛ መሳይ መኮንንና የኢሳት የኮምፒዩተር ባለሙያ በሆነው ተቀማጭነቱ ቤልጂየም በሆነው የኢሳት ባልደረባ ላይ የተገኙ ባእድ የመሰላያ ሶፍትዌሮች ከጣሊያኑ ሃኪንግ ቲም የተላኩ መሆናቸውን ሲትዝን ላብን በመጥቀስ ታዋቂው ጋዜጣ ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል። ጋዜጣው ባወጣው ሰፊ ዘገባ መረጃዎችን ከኮምፒዩተሮች ላይ ለመውሰድ የሚያስፈልገው ባእድ ሶፍትዌር የተላከው ከጣሊያን ኩባንያ ጋር ቢሆንም፣ …

የካቲት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአርሴማ ቤተክርስቲያን የተነሳውን የውስጥ ችግር ተከትሎ ችግሩን ለመፍታት የተመረጡት የሰበካ ጉባኤ አባላት ታስረዋል። በህዝቡ የተመረጡት 15ቱ ሽማግሌዎች ችግሩን ለመፍታት በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ የቀጠናው ሃላፊ የሆኑት አቡነ ገብርኤል የሰበካ ጉባኤ አባላቱ እንዲበተኑና ችግሩን ለመፍታት እንደሚሞክሩ መግለጻቸው ህዝቡን አስቆጥቷል። ጳጳሱ  ለፌደራል ፖሊሶች በማመልከት የአገር ሽማግሌዎች እንዲታሰሩ ማድረጋቸውን የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ …

የካቲት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ተወላጆች ላይ በጅምላ ፀያፍ ስድብ የሰነዘሩት የብአዴኑ አመራር እና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የ አቶ ኣለምነው መኮነን መኖሪያ ቤት በድንጋይ መደብደቡን ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ የዘገበ ሲሆን፣ ዜናውን ተከትሎ ኢሳት ባደረገው ማጣራት የባለስልጣኑ መኖሪያ ቤት በ11 ፖሊሶች ሌትና ቀን እየተጠበቀ ነው። አቶ አለምነው የአማራው ህዝብ የትምክህት ለሃጩን …

የካቲት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ  በጽ/ቤታቸው ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከፎርቹን ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር አቶ ታምራት ገብረጊዮርጊስ በቀረበላቸው ጥያቄ በመቆጣት ዘለፋ ሰነዘሩ፡፡ አቶ ታምራት ለጠ/ሚኒስትሩ ያቀረቡት ጥያቄ በአሁን ሰዓት አገሪትዋን የሚመራት ማንነው ነው የሚል ይዘት ያለው ሲሆን ጠ/ሚኒስትሩም ብስጭታቸውን በምላሻቸው ወቅት አንጸባርቀዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ለዚህ ጥያቄ ቀጥተኛ …

የካቲት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ የፍትህ ቢሮ በክልሉ ውስጥ ለሚገኙ ፍርድ ቤቶች በጻፈው ደብዳቤ ማንኛውም ባለጉዳይ አቤቱታዎችን በኮምፒዩተር ካላስጻፈ ጉዳዩ እንዳይታይለት ወስኗል። በክልሉ የሚገኙ ዳኞች በበኩላቸው ውሳኔው የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ እና የእድገት ደረጃ ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው ይላል። ዳኞች እንደሚሉት አብዛኛው ህዝብ አቤቱታዎችን አስጽፎ የሚያቀርበው በወረቀትና በእስክር ቢቶ ሆኖ ሳለ፣ የድሆችን …

የካቲት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግብፅ የውኃና መስኖ ሚኒስትር መሐመድ አብዱል ሙታሊብ ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ለማድረግ በጠየቁት መሠረት ባለፈው ሰኞ አዲስ አበባ ቢገቡም፣ የዓባይ ግድብ ግንባታ እንዲቆም በመጠየቃቸው ውይይቱ በሰዓታት ውስጥ ተቋረጠ፡፡ ሪፖርተር እንደዘገበው  የግብፅ ሚኒስትር ከኢትዮጵያ አቻቸው አቶ አለማየሁ ተገኑና ከባልደረቦቻቸው፣ እንዲሁም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተወከሉ ባለሙያዎች ጋር ባለፈው …

የካቲት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ቋሪትና ጃቢጠህናን ወረዳዎች ይካሄድ የነበረው መረን የለቀቀ ህገወጥ የአራጣ ብድር ስርዓት በአስከተለው ቀውስ ከ250 በላይ ጠንካራ ነጋዴዎች ተሰደዋል ተባለ፡፡ ከፍተኛ ማታለል የነበረበት ይህ ህገወጥ የአራጣ ብድር ስርዓት ነጋዴዎችን ባዶ ያስቀረና ያሰደደ ከመሆኑ ባለፈ ብዙዎችን ለእብደትና ለቤት መፍረስ ዳርጓል ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉና ከ121 ሺህ ብር …

የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፍተኛ የግብርና ምርት  እንደተገኘ በመንግስት የመገናኛ ብዙሀን በሚገለጽበት በአሁኑ ወቅት ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ካላገኙ ህይወታቸው አደጋ ላይ እንደሚወድቅ መረጃዎች አመልከተዋል። የዓለም ባንክ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በመግብ ለስራ የታቀፉ ዜጎችን ሳይጨምር ከ3 ሚሎዮን ያላነሱ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። በምስራቅ አማራ፣ በደቡብ ምስራቅ ትግራይ፣ በአፋር …

የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደህንነት ሃላፊ ከነበሩት ከአቶ ወልደስላሴ ወልደ ሚካኤል  ጋር በግብረ-አበርነት የተከሰሱት የህወሃት ታጋዮች ከደሞዛቸው ጋር ፈጽሞ የማይመጣጠን ሃብት አግበሰው መገኘታቸው ታውቋል። በተለያዩ አለመግባባቶች የተነሳ እየተመሰረቱ ያሉ ክሶች የህወሃት ተጋዮች በህገወጥ መንገድ የሰበሰቡትን የሃብት መጠን ለማወቅ እየረዳ መሆኑን የገለጸው ዘጋቢያችን ከአቶ ወልደስላሴ ጋር በግብረ አበርነት የተከሰሱት የህወሃት ታጋዩ የአቶ …

የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደብረዘይት አየር ኃይል አባል የነበረው ምክትል መቶ አለቃ ዳንኤል የሽዋስ የኢህአዴግን ስርአት በመቃወም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊትን መቀላለቀሉን ግንባሩ ለኢሳት በላከው መግለጫ አስታውቋል። ም/መ/አለቃ ዳንኤል የሽዋስ የ L-39  ስኳድሮን ተዋጊ ጀት አብራሪ እንደነበር መረጃው ያመለክታል። ም/መ/አ ዳንኤል የሽዋስ “ተቃዋሚዎችን ትደግፋለህ ከእነሱም ጋር የጠበቀ ግኑኝነት አለህ በሚል …

የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግንባሩ ለኢሳት በላከው መረጃ ፣ ከኢህአዴግ መንግስት ጋር ድርድር ለማድረግ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ተገኝተው  በኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች ታፍነው የተወሰዱት የኦብነግ አመራሮች፣ የደረሰባቸውን ከፍተኛ ድብደባ ተከትሎ በአንድ ወታደራዊ ሆስፒታል ውስጥ ሲታከሙ ታይተዋል። የመንግስት የደህንነት ሰራተኞች ” ባለስልጣኖቹ በገዛ ፈቃዳቸው እጃቸውን እንደሰጡ ለማሳመን ያደረጉት ከፍተኛ ጥረት ባለመሳካቱ  አሰቃቂ …

የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚ/ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ በደቡብ ሱዳን የሚገኘው የዩጋንዳ ጦር በሂደት ለቆ ካልወጣ አካባቢው የጦርነት ቀጠና ሊሆን ይችላል ብለዋል። ሁሉም ሃይሎች የራሳቸው የሆነ ፍላጎት አላቸው ያሉት አቶ ሃይለማርያም፣ በደቡብ ሱዳን ሰላም ይመጣ ዘንድ የዩጋንዳ ጦር ጁባን ለቆ መውጣት አለበት ሲሉ አሳስበዋል ። አቶ ሃይለማርያም የገለጹት አቋም የደቡብ ሱዳንን መንግስት የሚያስከፋ …

የካቲት  ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከተማው ውስጥ የሚገኙ የመንግስት ተሽከርካሪዎች ፣ የግል ባለንብረቶችና ባለታክሲዎች በመላ አገሪቱ የጠፋውን ነዳጅ ተከትሎ ነዳጅ ለማግኘት ላይ ታች እየተንከራተቱ ሲሆን፣  የነዳጅ መጥፋቱን  ተከትሎ የትራንስፖርት ታሪፊም  ጨምሯል። ዘጋቢያችን እንዳለው ዛሬ ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀስ 0.25 ሳንቲም ተጨማሪ ገንዘብ ለመክፈል ተገዷል፡ ነዳጅ ማደያዎችን ተዘዋውሮ የተመለከተው ዘጋቢያችን፣ በከተማው የሚገኙ ነዳጅ ማደያዎች …

የካቲት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከታህሳስ ወር 2006 ዓም ጀምሮ በመዲናዋ  ሌሊት የሚጻፉ  የተቃውሞ ጽሁፎችን ማየት የተለመደ እየሆነ መምጣቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ትናንት ሌሊት በአስኮ መስመር ጀኔራል ዊንጌት ከሚገኘው አደባባይ ጀምሮ አወሊያ፣ካኦጄጄ፣ አስኮ የሚወስደውን ዋና መንገዱን በመሃል በሚከፍለው እስከ 2.5 ሜትር ቁመት ባለው ግድግዳ ላይ የሙስሊሙን የመብት ጥያቄና የትግል ቀጣይነት የሚያንፀባርቁ ጽሁፎች በተለያዩ …