እየተጠበቁ ያሉት በራሪ የአየር ላይ ታክሲዎች መቼ ዕውን ሊሆኑ ይችላሉ?
ያለፈው ዓመትን የፓሪስ ኦሊምፒክ ያደምቃሉ ተብለው ከተጠበቁ አዳዲስ ፈጠራዎች አንዱ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ የበራሪ ታክሲዎች አገልግሎት መጀመር ነበር። በኤሌክትሪክ የሚሠሩት በራሪ ታክሲዎች ሳይንደረደሩ የሚነሱ እና ሲያርፉም በአንዴ የሚቀመጡ እንደ ሄሊኮፕተር የሚያገለግሉት በራሪዎች ሲሆኑ ወጪ፣ ድምጽ እና የአየር ብክለትን የሚቀንሱ ናቸው ተብለው ነበር። ምን ገጠማቸው?