የአዲስ አበባ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ‘መስፈርት አላሟሉም’ ያላቸውን 400 የሚሆኑ ሠራተኞችን ከሥራ አባረረ
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት “በድልድል እና ምደባ” 400 የሚሆኑ ሠራተኞችን ከጥር ጀምሮ ከሥራ ማሰናበቱን ሠራተኞች እና ድርጅቱ ተናገሩ። ድርጅቱም የብቃት ፈተና እና ውድድር ያላለፉ ሠራተኞችን ከሥራ መቀነሱን ገልጾ “የሪፎርም ባሕሪ ነው” ሲል ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥቷል።