ለአራት ዓመታት ከኢንዱስትሪ ፓርክ ሠራተኞች ጋር በመኖር የተቀረጸው ፊልም፡ ‘ሜድ ኢን ኢትዮጵያ’
የዘጋቢ ፊልሙ ደራሲ እና አዘጋጆች ማክስ ደንካን እና ዘንየን ዩ ናቸው። ከፕሮዲውሰሮቹ አንዷ ታማራ ማርያም ዳዊት ናት። ‘ሜድ ኢን ኢትዮጵያ’ በዋርሶው ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል፣ በትሪቤካ ፊልም ፌስቲቫል፣ በሼፊልድ ኢንተርናሽናል ዶክመንተሪ ፌስቲቫል እና በሌሎችም ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ዕውቅና አግኝቷል። ፊልሙ የቻይና ባለ ሃብቶች ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት፣ ሥራ አጥነትን፣ ባህልን፣ ቤተሰብን፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት እና የአርሶ አደሮች የተጠቃሚነት ጥያቄን በዋናነት ይዳስሳል።