“እንደምርጫችን ወይ ጥይት ወይ እስራት ይጠብቀናል”
በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ የሚሠሩ ባለሱቆች አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል።መንግሥት ሱቃቸው በር ላይ የደኅንነት ካሜራ (ሲሲቲቪ) እንዲያስገጥሙ መመሪያ ሰጥቷል።በከተማው ያለውን የኢስላሚስት ታጣቂ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ነው የደኅንነት ካሜራው ያስፈለገው።ሆኖም ግን ነጋዴዎቹ ካሜራ ካስገጠሙ በአል-ሻባብ ታጣቂዎች ዒላማ ተደርገው ስለሚገደሉ ይፈራሉ።የደኅንነት ካሜራዎችን ካላስገጠሙ ደግሞ ፖሊስ ያስራቸዋል።