ፕላስቲክ የሚያብላሉት የአፍሪካ ነፍሳት

ዶ/ር ፋቲያ ካሚስ ናይሮቢ ውስጥ በሚገኝ ቤተ ሙከራ ምርምር እያደረገች ነው።እሷ የምትመራው ቡድን ፕላስቲክ የሚበላ ነፍሳት ላይ ነው ጥናት የሚሠራው። “ጠዋት ስንገባ ሁላችንም ደስ አለን። ፕላስቲኩ ተፈርፍሯል” ትላለች።ጥቁሩ ነፍሳት ፕላስቲኩን መብላቱ ትልቅ ድል ነው። ነፍሳቶቹ ፕላስቲኩን ከበሉ በኋላ ማብላላት ይችላሉ።