የግብፅ ባለሥልጣናት የቀይ ባሕር የጀልባ አደጋን ለመሸፋፈን ሞክረዋል ሲሉ ከአደጋው የተረፉ ሰዎች ከሰሱ
ወደ ባሕር ለመጥለቅ ጥቅም ላይ የሚውል ጀልባ በግብፅ መገልበጡን ተከትሎ ከአደጋው የተረፉ ሰዎች የግብፅ ባለሥልጣናትን ከሰዋል። ጀልባው የተገለበጠው ቀይ ባሕር ላይ ነበር። ከአደጋው የተረፉ ሰዎች እንዳሉት አረብኛ ማንበብ ባይችሉም በአረብኛ የተጻፈ የዓይን እማኞች ሰነድ ላይ እንዲፈርሙ ተገደዋል።