የማጭበርበሪያና የማደናገሪያ ስብሰባ ኢትዮጵያውያኖች ባደረጉት ተቃውሞ ምክንያት በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ተሰረዘ

የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም አለእፍረትና አለይሉኝታ በውጭ የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ በኢንቨስትመንት ሽፋን ገንዘቡን አምታቶ ለመሞጭለፍና እያባነናቸው የሚገኘው ህዝባዊ አመጽ የመነሳት ስጋት የህዝብን ትኩረት ለማስቀየር ህወሃቶች በትናንትናው ዕለት በብርሃነ ገብረክርስቶስ የሚመራ ልዑክ በዋሽንግተን ከተማ በመላክ የጠሩት ስብሰባ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ባደረጉት ተቃውሞ ምክንያት ተሰርዟል። የልዑካኑ ቡድን ለማጭበርበሪያ “የትምህርት ሚኒስቴር” ተብዬው በተላላኪውና በተለጣፊው ደመቀ መኮንን እንደሚመራ ቢገለጽም ዋናው የስብሰባው መሪና የበላይ ተቆጣጣሪው ከወያኔ መስራቾች አንዱ የሆነው ቀንደኛው የመለስ  አንጋች ብርሃነ ገብረክርስቶስ እንደሆነ ይታወቃል። በትናንትናው ዕለት በግላጭ እንደታየው ደመቀ መኮንን ንግግር በማድረግ ላይ እንዳለና ለሚቀርቡ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት በሚሞክርበት ጊዜ ብርሃነ ገብረክርስቶስ በሁኔታው ስላልተደሰተና ሽንፈቱን መቀበል ስላቃተው የድምጽ ማጉያ ከእጁ በመመንጨቅ፣ ደመቀን እንዳዋረደው በገሃድ ታይቷል። ለነገሩ ወያኔዎች የደመቀን አይነት ለሆዳቸው ያደሩ ሰዎችን ስለማያከብሯቸው እንደውሻ ነው የሚያዩዋቸው። ውሻ ስራው ከበር መጮህ ሲሆን እልፍኝ ልግባ ቢል በእርግጫ እንደሚመታና እንደሚባረር ብርሃነ ገብረክርስቶስም የህወሃትን የበላይነትን በትናንትናው ዕለት ደመቀን በማዋረድና ስዕብናውን በመንካት ህዝብ ፊት አብክቶታል። ሌላው ካድሬ ረደዋን አብደላም አንዳችም ቃል ሳይተነፍስ እንደተለጎመ የጋማ ካብት ልፍለፋና ቅጥፈት የለመደውን ምላሱን በአፉ አጣብቆ ወደመጣበት አቅንቷል።

ብርሃነ ገብረክርስቶስም የዋሽንግተን አምባሳደርነትን እንደእርስት ለብዙ ዓመታት ይዞ ከፍተኛ የኢትዮጵያን ሃብት ሲዘርፍና ለመለስ ዜናዊ የተለያዩ ንብረቶችን ሲያከማችና ከፍተኛ የሃገሪቷን የውጭ ምንዛሪ በመስረቅ የመለስን የውጭ ባንክ ሃሳብ ሲያደልብ  ቆይቶ ለተመሳሳይ ዘረፋ ወደ ብራሰልስ ተዛውሮ እንደነበር አይዘነጋም። አሁን ደግሞ በቅርቡ የውሸት ሥልጣን ይዞ ላይ ታች ለሚለው ለሆዳሙ ኃይለማርያም ደሳለኝ አለቃ ሆኖ፤ ነገር ግን ለማጭበርበሪያ በምክትልነት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ እንደተመደበ ይታወቃል።ትናንትና ግን ብርሃነን ቀልብ እርቆት ጭር እንዳለች ዶሮ ሲቁለጨለጭና ሲገለማመጥ የተመለከቱ አንዳንድ ሰዎች “አጠገቡ በመሆን ከውሲባዊ ፍላጎቱ አንስቶ ሁሉን ስራ ስትሰራለት የነበረችው ሰሎሜ ታደሰ አጠገቡ ስለሌለች ነው” ሲሉ ተደምጠዋል። እነዚሁ ሰዎች እንደተናገሩት የብርሃነ ከሰሎሜ ጋር መዳራት የኢትዮጵያን ህዝብ 5 ሚሊዮን ዶላር አስከፍሏል። የብርሃነ ገብረክርስቶስ የቀድሞ ሚስት ከዛሬ 12 ና 13 ዓመታት ገደማ በፊት ብርሃነን በዝሙት ጉዳይ ክስ መስርታበት ስለረታችው፣ ካሳ እንዲሆናት  5 ሚሊዮን ብር እንደተፈረደላት ይታወቃል። ይህንንም ገንዘብ አፍንጫውን እየተያዘ ግብር የሚያስከፍሉት የኢትዮጵያ ህዝብ ከጉሪሮሮው ነጥሎ ከፍሎታል።

በዚሁ ስብሰባ ላይ በአምባሳደርነት የተቀመጠው የተለጣፊው የኦ.ፒ.ዲ.ዮ. አመራር አባል የሆነው የስሙላ አምባሳደር ግርማ ብሩ ይሁን እንጅ፣ እውነተኛ ሥልጣን ያለው በዋሃደ በላይ ዕጅ እንደሆነ የታወቀ ነው። እንደ ግርማ ብሩ ያሉት ሆዳሞች ደግሞ ሌላ ተስፈኛ ሆዳም ማስከተላቸው ስለማይቀር እርሱም እንዳቅሙ በቅርቡ በወዶ ገብነት የኦሮምን ህዝብ ለወያኔ ሸጦ ፍርፋሪ ስልጣን ፍለጋ በስተርጅና የሚጎናበሰውን ንጉሴ ቢራቱን “የኮሚኒቲ ተወካይ” በሚል የውሸት ታፔላ ለጥፎበት በስብሰባው ላይ አፉን እንዲከፍት አድርጎታል። ንጉሴ ቢራቱ በደረሰበት የግል የኢኮኖሚ ቀውስ በተለይም ገዝቶት የነበረው ቤት ዋጋው ወድቆ የሚከፍለው ስላጣ የዋሽንግተንን የኦሮሞ ማህበረሰብ ገንዘብ መንትፎ ቢወሰድም ሊበቃው ስላልቻለና በታክሲ ስራም “ሌቦች ሊዘርፉኝ” ይችላሉ እያለ በፍርሃት ስለሚንቀጠቀጥና በአግባቡ ስለማይሰራ የረባ ገቢ ስላላገኘ ወደወያኔ ኢምባሲ መልከስከስ ከጀመረ ጥቂት አመታት እየተቆጠሩ ነው። ነገር ነገርን ያነሳዋል እንደሚባለው ቅሌታሙ ንጉሴ ቢራቱ በዘመነ ደርግ ቀንደኛ ካድሬ በመሆን ብዙ ወንጀል የፈጸመና የኢ.ሰ.ፓ.አ.ኮ. አባል በመሆን በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ምክትል ዳይሬክተርነት ከተሾመ በኋላ፣ በወቅቱ ቀንደኛ ካድሬዎች ወደሚላኩበት የኮሚኒስት አገር ወደ ቡልጋሪያ ለትምህርት ተልኮ ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ ወደአሜሪካን አገር በመምጣት “እኔ ኦሮሞ ነኝ፣ ጭቁን ነኝ” በማለት ብዙ ሰዎችን በማታለል የኦሮሞ ኮሚኒቲ በዋሽንግተን ዲሲ ሊቀመንበር በመሆን ለከፍተኛ ሥልጣን ሲቋምጥ ቆይቶ የነበረ ተዋርዶ አዋራጅ የሆነ ግለሰብ ነው። አሁን ደግም ተግልብጦ ለወያኔ በግምባር ቀደምትነት በወሬ አቀባይነትና አለቅላቂነት ተሰማርቷል። ይህ ወራዳ ግለሰብ ብዙ ጊዜ ካንዱ የፖለቲካ ፓርቲ ወደ ሌላው ሲገለባበጥ የተመለከቱ ሰዎች “ከመገለባበጥ ብዛት አጥንቱ ተሰባብሮ ስላለቀ ነው ሰውነቱ በስጋ ብዛት ተነርቶ የሚታየው” እያሉ ሲያወሩ ተደምጠዋል።

ህወሃት በጣም ሊገባውና ሊቀበለው ያልቻለው ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ህዝብ በሥልጣን ኮርቻ ላይ ከተፈናጠጠበት ጊዜ አንስቶ እንደ  ውጭ ወራሪ እንጅ እንደ ኢትዮጵያ መንግስት ቆጥሮት አያውቅም። ህወሃት የሚለካውና የሚመዘነው ለአምስት አመታት የአገራችንን ህዝብ ሲያርድና ህዝቧን ሲከፋፍል እንደነበረው እንደ ፋሽስቱ ጣሊያን እንጅ እንደ ኢትዮጵያዊ መንግስት አለመሆኑን ነው።  ህወሃትን ከጣሊያን ጋር የሚያመሳስለው ተግባሩ እንጅ፣ የበቀለውማ ከእኛይቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ነበር። ሆኖም በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች አንጋችነት ለሥልጣን የበቃ ስለሆነና አሁንም ተጠሪነቱ ለነዚሁ ባዕዳን ስለሆነና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለባዕዳን ሳያሰልስ አሳልፎ በመስጠት ላይ ስላለ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ከጫንቃው ላይ አውርዶ አንኮታኩቶ ሊጥለው አመቺውን ጊዜ እየጠበቀለት ነው የሚገኘው።

ብርሃነ ገብረክርስቶስ ህሊናው በዶላር ብዛት ስለሰከረ በደንብ ማሰብ ስለተሳነው ነው እንጅ ዋሽንግተን ከተማ ውስጥ ለበርካታ ጊዜ ስብሰባ ጠርቶ እየተዋረደ የሰረዘበት ጊዜ በርካታ ነው። በትናንትናው ዕለት በሃዋርድ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ህወሃቶች አስበው የነበረው “በውጭ የሚገኘው ህዝብ ድጋፍ እየሰጠን ስለሆነ በአገር ውስጥ ያላችሁ ተቃዋሚዎች በውጭ ያሉት ለእናንተ ድጋፍ ስለማይሰጧችሁ አመጽ እንዳታስነሱ” ለማለት ነበር። ለዚህም የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ካሜራ የሚቀርጹ ሰዎችን አስመጥቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ በቴሌቭዥን ለማስተላለፍ ነበር። በዚህ አጋጣሚ ከህወሃት ውጭ ያላችሁ ከዚህ የልዕካን ቡድን ጋር አብራችሁ የመጣችሁ ጋዜጠኞችና ሌሎችም ጊዜው ሳይመሽባችሁ በስደት ካለው ወገናችሁ ጋር እንድትቀላቀሉና እራሳችሁን ከወያኔ ባርነትና ተፅእኖ ነጻ እንድታውጡ እናሳስባችኋለን። ደመቀ መኮንንና ረደዋን አብደላም ብትሆኑ ያስቀየማችሁትን ህዝብ ይቅርታ ጠይቃችሁ ይህንን እድል ተጠቅማችሁ ወደ ወገናችሁ ብትቀላቀሉ ይሻላችኋል። ጊዜው ሳያልፍ ከዚህ በመስጠም ላይ ካለ መርከብ ላይ እራሳችሁን ፈጥናችሁ ብታድኑ ይሻላችኋል!!!

በትናንቱ ስብሰባ ላይ ለመገኘት የመጓጓዣና የሆቴል ወጭ ተከፍሎላቸው ከተለያዩ የአሜሪካና የካናዳ ከተሞች የመጡት አመዛኞቹ ሰዎች የህወሃት አባላት መሆናቸውን ተመልክተናል። ስብሰባው እዛው ወያኔ ኢምባሲ አስቀድመው ቢያደርጉት ይሻላቸው ነበር።ህወሃቶች በትናንትናው ዕለት የደረሰባቸውን ከፍተኛ ውርደትና እፍረት  እንደለመዱት “በደርግ- ኢሰፓዎችና በሻቢያዎች” ላይ አላከዋል። በጣም የሚገርመው ደገሞ ደርግና ሻቢያ ተዛምደው ወያኔንን ሲቃወሙ? ይህ የወያኔ ውሸት እግር አውጥቶ የሚሮጥ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ወያኔዎች ውርደት ከባድ ነገር ስለሆነ መቀበል ስላቃታቸውና ህሊናቸውን ስለሳቱ የሚናገሩትን ነገር አንኳ ትርጉም ይሰጣል የሚለውን ለማመዛዘን አልቻሉም። በየትኛው ጊዜ ነው ደርግና ሻቢያ አብረው የሰሩት??? ይልቅ የደርግንና የኢሰፓን ስም በማንሳት እንደ አህያ የጫናችሁባቸውን የሚሸከሙትን  እነ ንጉሴ ቢራቱን አስታስደንግጡ፣ አታሸማቁ። እነ መለስ ዜናዊና ብርሃነ ገብረክርስቶስ የሻቢያ ቅጥረኛነታቸው የሚያረጋግጥው በትናንቱ ስብሰባ “ባድማ የማነው” ተብሎ ብርሃነ ገብረክርስቶስ ሲጠየቅ ምነው አፉ ተቆለፈ??? በመጨረሻም ወያኔዎች ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ሲነሱ አሸምቀውበት በነበረው በደደቢት ዋሻ በሚመሰለው በወያኔ ኢምባሲ ስብሰባውን እንቀጥላለን ብለው በከፍተኛ ውርደት፣ ክስረትና ብስጭት ስብሰባውን እንዲሰርዙ ተገደዋል።  በዚሁ ርዕስ ላይ ተጨማሪ መረጃ ሰሞኑንን እናወጣለን። የኢትዮጵያ ህዝብ ድል ቅርብ ነው!!!