ስሙን ቀይሮ ከሚመጣ ወያኔና ከድል አጥቢያ አርበኞች መጠንቀቅ ነው
ዋለልኝ መኮንን
አምባገነናዊው የወያኔ ገዛዝ የፈጠረው አስከፊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ምስቅልቅሎች ምክንያት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ጎሳ ፆታ ቃቅንቃ እድሜ ሀይማኖት ሳይል በከፍተኛ ሁኔታ ህዝቡ ሀገራዊ ስሜት እንዳይኖረው በሀገሩ ላይ የባእድነት ስሜት እንዲሰማው ይባስ ብሎም ሀገሩን ጥሎ እንዲሰደዱ ሆነዋል:: ወያኔ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት የፈጠረው አምባገነንዊ የፖለቲካ ሥርዓት በሃገራችን ከፍተኛ ቀውስና የተንሠራፋው ድህነትና ሥራ አጥነት እንዲሰፍን አድርገዋል ህዝቡን በማምለጥ ሠርቶ ለማግኘትና የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ህይወት ለመለወጥ ስደትን ቢሹም ከኢኮኖሚያዊ ፍላጎት በስተጀርባ ወያኔ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት የፈጠረው አምባገነንዊ የፖለቲካ ሥርዓት ዋነኛ መንስኤ መሆኑ መዘንጋት የለበትም::
ጠቅላይ ሚንስቴሩ በስልጣን በቆዩባቸው አመታቶች ሆን ብለው ሰምተው እንዳልሰሙ በመምሰል አይተው እንዳላዩ በመምሰል የተለያዩ ወንጀሎችን በኢትዮጵያውያንና በጎረቤት አገሮች ህዝቦች ላይ ሲፈፅሙ ሲያስፈፅሙ ከርመዋል:: ልክ እንደወያኔዎቹ ፍርድ ቤት መለስ ዜናዊ ይከሰስ ቢባል ሊያስጠይቃቸው ከሚችሉ ክሶች መካከል የሃገርን ጥቅም አሳልፎ መስጠት፣ የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት አለመረጋገጥ፣ ለሕዝብ ፍላጎት ተገዢና ተጠያቂ መንግሥት አለመኖር፣ የሕግ የበላይነት አለመከበር፣ የፍትሕ፣ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ እጦት፣ ከወያኔ ካድሬ ውጭ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የመሬት ባለቤት እንዳይሆን ማድረግ፣ አስከፊና የተንሰርሳፋ ሙስና ከከፍተኛ የወያኔ ባለስልጣናት እስከ ተራ ካድሬ ድረስ መዘፈቅ …….. ተዘርዝረው የሚያልቁ አይመስለኝም::
መለስ ዜናዊ አይሙቱ እንጂ ቢሞቱ ነብስ ይማር የማልላቸው/የማይባሉበት ዋነኛ ምክንያት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሰው የስራ ባህል እንዲጠፋ በማድረጉ መሆን አለበት:: በመጀመሪያ ደረጃ አንድ ሃገር ህዝብ የእድገት ባህልና እምነት መሆን ያለበት ስራና ስራ ብቻ ነው የወያኔው ጠቅላይ ሚንስትር ግን ያደረጉት ተቃራኔውንና ሃገር አፍራሽ ተግባር ነው:: የወያኔን ስልጣን የሚያስጠብቅ ሁሉ ሰረቀም ነጠቀም ዘረፈም ገደለም ምንም የማይጠየቅበት ስርዓት ፈጥረዋል ጤናማ የውድድር የስራ እድል እንዳይኖር አድርገዋል በኢትዮጵያ ውስጥ የወያኔ አባል ደጋፊ በመሆን ብቻ ከሌላው የህብረተሰብ ክፍል የተለየ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርገዋል:: በአንድ ወቅት የወያኔው ጠቅላይ ሚንስቴር በአንድ ለናቱ ቴሌቢጅናቸው ልማታዊ ባለሃብት ብለው ሲሸልሙ ውለው በሰልስቱ ያንኑ የሸለሙትን ግለሰብ አፋልጉልኝ ያዙልኝ እያሉ ሲቀልዱ ነበረ::
የወያኔው ጠቅላይ ሚንስትር አያድርገውና ሞቱም አልሞቱም ፈለጉም አልፈለጉም መንበረ ስልጣኑን ጥለው መሄድ አለባቸው ልቦና ከሰጣቸው በፈቃደኝነት ካልሆነ ግን…….:: የኢትዮጵያ ህዝብ ላለፉት ሃያ አንድ አመታት እድል ሰጥቶዋቹ ነበረ ነገር ግን በመጀመሪያም ድርጅት መስርታቹ ጠብመንጃ አንስታቹ ጫካ ስትገቡ የተሳሳተ የፖለቲካ አቅጣጫ ይዛቹ ስለመጣቹ ከሀገርና ከህዝብ ጥቅም ይልቅ የራሳችሁን ጥቅም ስለምታስቀድሙ ቅን ስላልነበራቹ ህዝባዊ መሰረት ስላልያዛቹ ድሮ ከነበራቹ አመለካከትና ቂመኝነት መቀየር ስላልቻላቹ አሁን በቃችሁኝ እንዳላያቹ ተብላችሁዋል:: የኢትዮጵያ ህዝብ ለውጥ ነፃነት ስልጣን የሃገርን ሃብት በጋራ መጠቀም ሃሳቡን በነፃነት መግለፅ የፈለገውን የፖለቲካ አመለካከት ማራመድ አስፈልጎታል እናንተ በፈቃደኝነት ባተለቁ እንኩዋን በጉልበት አንበርክኮ ያስወርዳችሁዋል::
የወያኔ የኢህአዴግ ስልጣን መልቀቅ ከብዙ ግምገማ በኹዋላ ውሳኔ ላይ የደረሰውና ሊያስወርዳቸው አቅም ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ ተበጣጥሰው ያሉት የተቃዋሚ ድርጅቶች አይደሉም:: ብዙዎቹ ተቃዋሚ ድርጅቶች ብዙሃኑን የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ክፍል ያሳተፉ አይደሉም: የአካሄድ ልዩነት እንጂ የአላማ ልዩነት ባይኖቸውም አብረው መስራት አልቻሉም: ትልቅ ትኩረት የሚሰጡት ድርጅቱ ያለ ለማስመሰል እንጂ እስከ ታችኛው የህብረተሰብ ክፍል ድረስ ወርደው አላማችውን ማስተዋወቅ የአባላቶቻቸውንና የደጋፊዎቻቸውን ቁጥር መጨመር አይደለም: ብዙ ግዜ እርስ በእርስ አቃዋሚ ይሆናሉ ለአባላቶቻቸው ግልፅ የሆነ ድርጅታዊ መዋቀር የላቸውም:: እንደዚህ ያሉ መሰረታዊ ችግሮችን መፍታት ካልቻሉ ህዝቡ እስካሁን መስዋትነት የከፈለበትን ወያኔን ከስልጣን የማባረር ትግል ውጤት አልባ እንዳያደርገው ስጋት አለ::
ለውጥ ፈላጊው የኢትዮጵያ ህዝብ ትግሉን በተሳካ ሁኔታ ለመጨረስ በህቡዕ ካልተደራጁ ልክ ከዚህ በፊት እንደነበሩት ለውጦች የነመለስ አይነት ጭልፊቶች የድል አጥቢያ አርበኞች መስዋቱን ከንቱ ያደርጉታል:: ህዝቡን በህቡዕ ለማደራጀት ሃላፊነት ያለባቸው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የሚገኙ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች የሲቢክ ማህበራት የመረጃ ተቁዋማት ናቸው:: ህዝቡን በህቡዕ ለማደራጀት ሃላፊነት ያለባቸው ድርጅቶች በተቀናጀ መልኩ ለውጥ ፈላጊውን የህብረተሰብ ክፍል የጋራ ጥቅማቸውን በሚያስከብር መልኩ ማሰባሰብና ማወያየት አለባቸው:: የህን የመሳሰሉ መሰረቶች ካሁኑ ካልተሰሩ የትግሉ ውጤት በአንድ በኩል በድል አጥቢያ አርበኞች በሌላው በኩል ወያኔ አጭበርብሮ እራሱን የቀየረ መስሎ (መቸም አይቀየርም) ለመንግስትነት ሊቀርብ ይችላል::