ከህወሓት መውደቅ በኋላ

ከተስፋዬ ገብረአብ

“አበበ ባልቻ – እንደ ሕወሓት” በሚል ርእስ ‘ሰውለሰው’ በሚለው ድራማ ላይ የፃፍኩትን ተከትሎ አንዳንድ አስተያየቶችን ሳነብ ቆይቻለሁ። አበበ ባልቻ ሕወሓትን ወክሎ ሲተውን እንደነበር በብዙዎች ዘንድ ታምኖበታል። የአስናቀ አወዳደቅ የሕወሓት (አዜብ / መለስ)ን ፍፃሜ የሚያመለክት ስለመሆኑም ሰፊ ግንዛቤ አለ።

በድራማው ውስጥ፣ “የኢትዮጵያ ወኪልማናት?” የሚለው ጥያቄ ላይ ግን ልዩነት አለ። አንድ ሰው በብእር ስም cyberethiopia.com ላይ እንዳሰፈረው ከሆነ የኢትዮጵያ ወኪል ከማህሌት ይልቅ የአስናቀ ሚስት ናት። እንዲህ ሲል አብራርቶታል፣

“…የመስፍን ሚስት ኢትዮጵያን ትወክላለች ተብሏል’ ሲል (መባል አለመባሉ አንድ ነገር ሆኖ)፣ ይሄ ምን ማለት ነው? በድራማው ውስጥ ማህሌት ቤተሰቧን የምትወድና “ስኬታማ” እናት ብትሆንም ለባሏ ግልጽነት ይጎድላታል። ሚስጥሯን ከባሏ ይልቅ ለአስናቀ መንገር የሚቀላት እናት ናት። ከአንድም ሁለት ሶስት ጊዜ ቃሏን ስታጥፍ ትታያለች። ማህሌት ለባሏ ግልጽ ልትሆን አልቻለችም። ከባሏ ይልቅ ለአስናቀ ግልጽ መሆንን ስለመረጠች፣ ይህ ስህተቷ ሊያስከትል የነበረውን አደጋ፣ እንደ አጋጣሚ በፊልሙ ድንገተኛ መቋረጥና በአስናቀ መሞት ከአደጋ ያመለጠች ይመስላል። ይህን ታሪክ በምን መልኩ ነው ከኢትዮጵያ ጋር የምናያይዘው? ይልቁን የአስናቀ ሚስት ኢትዮጵያን እንደምትወክል አድርጎ ማየት ይቻላል። አስናቀ ቤቱን ማስተዳደር እንዳልቻለ ባል፣ እንደ በዝባዥ መሪ ማየት ይቻላል። የአስናቀ ሚስት ቻይነትና ርህሩህነት በአንፃሩ ይስተዋላል። ለልጆቿ ያላት ፍቅር፣ ለአስናቀም ቢሆን ይቅር ባይነቷ፣ መልካም ሰው መሆንን እስከመረጠ ድረስ ለሱ ያላትን ፍቅር በማንም እንደማትተካ ማሳየቷ፣ አገርን መወከል የሚያስችል፣ ትክክለኛ የእናትነትና “የሚስትነት” ባህሪ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የአስናቀ ወሮበላነት፣ እንደ አባት ልጆቹን በወጉ ማስተዳደርና ማሳደግ አለማቻሉ፣ ሴት ልጁን ለህልፈት መዳረጉ፣ ወንድ ልጁ ከእናቱ ጋር የቁምስቅል ኑሮ እንዲኖር መፍረዱ ወዘተ… በትክክልም የአስናቀ ሚስት አገርን እንድትወክል ያደርጋታል….” (የዚህን ፅሁፍ የቋንቋ አጠቃቀም አርቄዋለሁ)

ከላይ ባለው ፅሁፍ አስተያየት የማይስማሙ አሉ። ይልቁን የአስናቀ ሚስት የትግራይ ክልል ወኪል ስለመሆኗ ይገምታሉ። እኔም ይበልጥ ወደዚህኛው አስተያየት አደላለሁ። በህወሃት አገዛዝ ይበልጥ እየተሰቃየ ያለው ክልል ትግራይ መሆኑን ብዙዎች አያምኑም። እንግዲህ ተደራስያን የጥበብ ስራዎችን በተለያየ መንገድ መገንዘብ መብታቸው ነውና በዚህ ጉዳይ መከራከር ተገቢ አይሆንም።

“ሰውለሰው” ድራማ አለመቋረጡና ከሶስት ሳምንታት በሁዋላ እንደሚቀጥል እየተነገረ ነው። በርግጥ ድራማው ከቀጠለ አጓጊ ይሆናል። ምክንያቱም በድራማው ውስጥ ከህወሃት መውደቅ በሁዋላ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ እንዴት ሊቀጥል እንደሚችል በምናብ ልናይበት እንችላለን። “በድራማው ውስጥ ኢትዮጵያ ማናት?” ለሚለው አከራካሪ ጥያቄም በትክክል ምላሽ ማግኘት ይቻላል።

“ሰውለሰው” የተባለው ድራማ ሲቀጥል ቁልፍ ለሆኑ አንዳንድ ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ምላሽ እያገኘን እንደምንሄድ ግልፅ ነው። እንደ ባለፈው የድራማው ፍፃሜ ከሆነ ህወሃት ወድቋል። በአንፃሩ የመስፍን ወልደማርያም የህጋዊነት የአስተሳሰብ መንፈስ የበላይነቱን ጨብጧል። ማህሌት መንታ መንገድ ላይ ቆማ፣ ያልፈፀመችውን ወንጀል ለመደበቅ እየጣረች ነው። ህወሃት በህገወጥ መንገድ ያከማቸው ገንዘብ ወደ ሼክ መሃመድ አላሙዲ የባንክ አካውንት ተዘዋውሮአል። በዚህ መሃል የትግራይ ክልል (የአስናቀ ሚስት) የምታገኘው ፖለቲካዊ ትርፍ ከቶ ምን ሊሆን ይችላል? የአስናቀ ሚስት በወንጀለኛው ባሏ ሞትና ውድቀት የሚሰማት ምን ይሆን? ከሁለት ሳምንታት በሁዋላ ድራማው ከቀጠለ የዚህን ምስጢር ፍንጭ ለማግኘት እንሞክራለን። ይህ ብቻ አይደለም። በመጪው ዘመን የኦህዴድና የብአዴን አመራር አባላት እጣ ፈንታ ምን ይሆናል? ይህም ትንቢታዊ ታሪክ ይኖረው ይሆናል። የመድሃኒት እናት ከአንድ ልክስክስ የህክምና ባለሙያ ጋር ሆና በልጇ እና በልጅ ልጇ ላይ በፈፀመችው ወንጀል የሚደርስባትን ችግር በቀጣዩ የድራማው ተከታታይ ክፍል እናየው ይሆናል። የመዲ እናት ስትተውን ኦህዴድና ብአዴንን እያሰብን ሊሆን ይገባል።

“ሶስና” ሆና የምትጫወተውን ገፀባህርይ በጣም ነው የምወዳት። ከልጅቱ ጋር ፍቅር ይዞኛል ለማለት እደፍራለሁ። በንግግሯ ወንዶችን ቆሌያቸውን ስትገፋቸው በተለይ ከልቤ እዝናናለሁ። የአበሻ ሴቶች ጥያቄ ወኪል ሆኖ ትታየኛለች። ሳቋ፣ እንባዋ፣ ስድቧ ሁሉም ያምርባታል። የምትሞቅ የምሽት የሻማ ብርሃን ናት። ከወያኔ መውደቅ በሁዋላ አዲሳባ ሄጄ ይህችን ሴት ማግኘቴ አይቀርም። እኔ ወዳለሁበት አካባቢ በድንገት ብቅ ካለችም እንግዳዬ አድርጌ ልጋብዛት እፈልጋለሁ።

“ሰውለሰው” ድራማ ላይ ኢትዮጵያ ተስፋ፣ የሃገር ምሰሶ ሆኖ የሚተውነው ገፀባህርይ መስፍን የሚናገራቸውን በጥንቃቄ መረዳት ይገባል። የምንመኘውን ስርአት የሚያንፀባርቅ ነው።

በመጨረሻ “ሰውለሰው” ድራማ ፖለቲካዊ ይዘት እንዳለው ብዙዎች ሳይገነዘቡ መቆየታቸውን ከተፃፉ አስተያየቶች መረዳት ችያለሁ። ወደፊት በድራማው ላይ ተከታታይ አስተያየት የመስጠት አሳብ አለኝ። እስከዚያው የቃጂማው ጊዮርጊስ በቸር ያሰንብተን።

9 Comments on “ከህወሓት መውደቅ በኋላ”

  1. ጥሩ ጽህፍ ነው ግን ወያነ በ ድራማ ብቻ አይበቃም የውም ካበቃ ባሃላ የትግርያ ሰዎች ምን ሊሆኑ የተደረገ ድርድር የለንም እናም እንደሳቻው ልናሰብ ይጋበናልን.ከኤርትራ ተቃራርጥዋል የኤትዮጵያ አፋር አድርገው ትግርይ የበር ፍንጭ ለማግጝት በፈጨርጨር ነው.
    ይትግራይ ሕዝብ መጻኢ ማይት አለብን.ክትግራይ ይምናግጝው ወይስ የሚወስድብን በድንብ መራጋገጥ ይነርብናል.

  2. I do not have words. In short I would only say Bravo Tesfu. Keep up the good work.
    Wondata. Yante aynent yiweled.
    Mot le woyane & its colleagues.

  3. Tesfaye,

    You better keep quiet. your time is over and you always think of Ethiopia at kilil level. Ye dekemik wedogeba weyane .

  4. አንተ ሶስናን እንደወደድካት እኔም አንተን በጣም ነው የምወድህ::

    I have never seen “Sew Le Sew” but the way your observation is pointed at is something special. Woyane through his mouthpiece ETV has designed such type of Drama to make the people, who shout loudly for their rights, silent. Drama it televised is so far found sufficient enough to silence the bark of the various groups of dissents (as a dog become silent when he gets his bone).

    In my opinion the strategy works well as majority of the program followers are the hot groups of society. It is because of the fact that such rubbish program called DRAMA is ”Invisible hand” of the ruling party, I am not fooled by it; and the so called artists who are voraciously eating up everything they assume is of birr value.

    I wonder how you view the Drama from different perspective and fooled those “SMARTS” of Arat Kilo who initially sketched it to fool the nation. Now anybody who is fond of watching drama has to hairsplitting each and every actions of the charter and his/her words against the tyranny’s hardball.

    Thank you Tesfaye G/Ab

  5. ለመሆኑ ህወሐት ይወድቃል ብለህ ታስባለህ:: መቼ?
    ምነው ይህች ኤርትራዊነትህ ላትደበቅ የደበቃት:: እውን ካሁን በሁዋላ ዳግም በአዲስ አበባ ጫት ቤቶች እታያለሁ ብለህ ታስባልህ::ዘበት! በሆነ ተዓምር የሚነግሰ ቢኖር ሆድ አደር ከሀዲ መሆንህን ይረሳ ይመስለሃል::

  6. ትግረ ከሊሉ ኢትዮጵያ አበቃላት ስለዚ ውጭ ሃገር ሁኖ መጮህ ሳይሁን..ለዚች አገር ብትክክል መስራት ይገብናል….ትግሪዎች አምበሶች ናቸው:ይህ ሃቅ ነው ዝምብለን ከሃቅ ወጥተን ውስትን ሃቅ አስመስሎ ኣንናገር ከተባለ ግን ኣንደ አማራ የሚወስ የለም ብየ ነው ማምነው…..

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*