ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ሕዝቡን ከአምስቱ ውሾችና ከኢካቦድ ጥፋት ይታደግ ዘንድ የቀረበ ጥሪ

በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ክፉን ሥራ እግዚያብሔር ይገልጣል፤
የዐርብ ፍቅረኞችም በትንሳዔው ይወድቃሉ

የተሰወረ የማይታይ፣ የተከደነ የማይገለጥ የለምና ሆኖም እስኪገለጥ ግን የአካልብት ልክፍት የማይቀር ነውና ባለንበት ዘመን በፓትርያርክ በብጹዕ አቡነ መርቆሪዎስ በሚመራው በሕጋዊው ውጭ በሚገኘው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቅዱስ ሲኖዶስ በገጠመው ወከባ ሁላችንም እራሳችን ባለመመርመር ባለመታደል ዋኖቻችን ለሆኑት በጹአን አባቶቻችን ለልፋታቸው ምስጋና ሳንሰጥ ጭራሽ ከሳሽ ብንሆንባቸውም እግዚያብሔር አምላክ “በውሃ ውስጥ ባለፍክ ጊዜ ካንተ ጋር እሆናለሁ በወንዞችም ውስጥ ባለፍክ ጊዜ አያሰምጥህም፣ በእሳትም ውስጥ በሄድክ ጊዜ አትቃጠልም ነበልባሉም አይፈጅህም” ኢሳ 43፡2 በሚለው ቃል እየተጽናኑ፤ “ብነኖርም ለእግዚያብሔር ብንሞትም ለእግዚያብሔር  ነው”ብለው ሳይበገሩ በአንድነት ቆመው ይልቁንም የከዳተኞች ክፋት ለቀኖች ክፋት መስታወት ሆኗቸው ጊዜውን እየዋጁ የያዙትንም አልበተኑም።

ከዳተኞች ግን መንጋውን በመጠበቅ ለተጉት አባቶች አጋዥ ከመሆን ይልቅ የሥጋ ምኞት ለመፈንቅለ ሥልጣን ህሊናን የሸጡበት የተሳከሩ መነኩሴ መሰል አምስቱ ከልቦች የራሳቸው የልክፍት አረር በአባቶች ላልይ ተኩሰው ህዝቡን ለመከፋፈልና የአባቶችንና የምዕመናንን ስም እንበለ ከነቱ በማጉደፍ በየዋሁና የሲኖዶሱ ስብከተ ወንጌል የጅርባ አጥንት በአባ ወልደተንሳዔ ስም በመነገድ ምዕመናን በምዕመናን ላይ በማነሳሳት ዘመቻ ተጠምደዋል። የዚህም ወጤቱ እየታየ ነው። ወንጌል ሰባኪ አባ ወልደ ተንሳዔን እኛን ሲያስተመሩን በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር “ አውጣኝ ያለ ወጣ፣ አባላኝ ያለም በላ፣ ተኝቶ ተገኝቶ አሳማ ተበላ” እንዳሉን ሁሉ ዛሬ በተገላቢጦሽ መሰሪዎቹ አምስቱ ከልቦች እርስዎን ተኝተው ያገኙዎት በሚመስል ሁኔታ በስምዎ ነገደው እርስዎንና ቤተክርስቲያንን ከመብላታቸው በፊት እንደእግዚያብሔር ቃል “አንተ የምትተኛ ተነስ ንቃ ጊዜው መሽቷልና” በርትተው ይጸልዩ። ምናልባትም ተጎድተውም ቢሆን ለቤተክርስቲያኒቷ አንድነት ሲሉ ትልቁን የወንጌል ተራራ ይቅርታን ይድፈሩና መሰሪዎች ኢካቦድ በጨለማ የተከሉትን በይቅርታ በመንቀል ታሪክ ይስሩ። ጊዜው መሽቷል።

በተለይም በኢትዮጵያ በግፍ የለነጻነት የታፈነውን ህዝብ እንደቤተክርስቲያን ቀደምት አባትነታቸው የኢትዮጵያዊውን መከራነ ፍዳ እረፍት ነስቷቸው ገፈኞች ቀንበራቸውን ከሕዝቡ ላይ እንዲያነሱ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በመላው ዓለም አደባባይ ለነጻነት በመጮህ ላይ የሚገኙትን በሁለት ጎን የተሳሉትን የየኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሊቀ ጳጳስና የሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ  ጸሐፊ አረጋዊው ብጹዕ አቡነ መልከ ጻዲቅን ለምን ወያኔን አወገዙ፤ ለምን የእስልምና እምነት ተከታዮች ኢትዮጵያዊያን ናቸውና በኢትዮጵያዊነታቸው ስለሚደርስባቸው በደል ቤተክርስቲያን ትጮሃለች በማለት በመናገራቸው ለምን በዚህ የወያኔን ግፍ አጋለጡ በሚል ዲያቢሎሳዊ ተልዕኮ አባቶችን በድረ ገጾቻቸው በማዋረድ ሴራቸው እየተስተዋለ ነው።

ሆኖም ሊቀ ጳጳሱ ብጽዕ አቡነ መልከ ጻዲቅ እውነት አርነት ያወጣቸው እንደ እግዚያብሔር ቃል በሁለት ጎን የተሳሉ ናቸውና በእምነታቸው ቆመው ከእግዚያብሔር በቀር ማንም በሳቸው ሥልጣን እንደሌለው በማስረገጥ ከተገፉት ጋር የቆሙ አረጋዊ አባት ናቸው። እነዚህ የምግባር ድሆች ከልቦች እንደቃሉ ሳይሆን እንደ ዶላሩ የሚሰብኩበት የመበለቶች ተረት ተረት የሆነ ቀኖና ቤተክርስቲያን ፈርሶ ወይም ተጥሶ በህጸጽ የተሞላው ሁሉ የግድ ቄስ ካልሆነ፣ ክህነት ያልሰጠ የማርያም ጠላት የሚሉና በተግባርም ያሳዩ፤ ከገፊዎች ጋር በመቆም ስብከቱን በሃሰት ፍቅር ያበዱበት በአጠቃላይ በመምህርና በአባ (መነኩሴ) ስም የተነሱ ጥቅመኛ ከልቦች ከቤተ እግዚያብሔር መልካምነት እንዲጠፋ በማድረግ ሕጋዊውን በውጭ የሚገኘውን ቅዱስ ሲኖዶስ በማወክና በመፈታተን ላይ ይገኛሉ።

እነዚህ አምስቱ አካልብት የእግዚያብሔርን ተግሳጽ የናቁ፣ መስዋዕቱን ያቃለሉ፣ ዋናዎቹን የማያከብሩ ምናልባትም በስደት ስም በሲኖዶሱ የኤሊ ልጆች ሾልከው ገብተው የተሾሙና የመኖሪያ ፍቃድ ማገኛ መጠለያ በማድረግ ንጹሃን አባቶችን በማመስ ተልዕኮ ላይ ተሰማርተዋል። ቀደምት ዋናዎቹ ሲኖዶሱን ይዘው የተሰደዱ ሊቃነ ጳጳሳት አባቶች በነዚህ ከልቦች ተዋርደዋል፣ አይ ጊዜ! ስለዚህ በኢትዮጵያ ያለው ጥፋት ሳይበቃን በነሱም ሆነ በሌሎቻችን በደል የእግዚያብሔር ፍርድ ለወርድ የዳመነ ቢሆንም ይህንን ባለማስተዋል፤ መገሰጽን እንደመናቅና እንደመደፈር ቆጥረው የቆሙ መስሏቸው መውደቃቸውን ስተው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የማዕዘን ራስ የሆኑትን አባቶች ሲዘልፉ ተስተውለዋል።

እግዚያብሔር “ያከበሩኝን አከብራለሁ፤ የናቁኝም ይናቃሉ” ቢልም ካለመስማት ሽማግሌ ማጣት ከእግዚያብሔር ቅጣት አንዱ መሆኑንም ባለመረዳት በሊቀ ጳጳሱ በብጹዕ አቡነ ዜና ማርቆስና በብጹዕ አቡነ ይስሃቅ ሞት መቀጣታችንን አላስተዋሉም። ከዳተኞቹ ጭራሽ በነሱ ስም ንግድ የጀመሩትም ተስተዋል እንጅ ይህ የአምስቱ አካልብት የስመ አባዎችና መምህራን ድፍረትና ማናቸውም የቤተክርስቲያን ነጋዴ የአፍኒንና የፍንአስ ዕጣ ከመሆን አያልፍምን ዕምነታችንን የምንወድ ሁሉ ህጋዊው  ቅዱስ ሲኖዶስም ቤተእግዚያብሔር የጨካኝ ከልቦች ዋሻና መናከሻ ሊሆን አንፈቅድምና ስደተኛውም ብዙ መስዋዕትነትን የከፈለበት በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶሱ ለዚህ ከላይ ለተመለከተው ችግር በአስቸኳይ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል።

የሚገርመው አምስቱ ውሾች(ውሾች) እራሳቸው ወያኔ ሆነው አመጣጣቸውንም እያወቁ አንዴ ማህበረ ቅዱሳን፣ አንዴም ደግሞ ወያኔ ገብቶበታል እንዴ እያሉ በሌላ ጊዜ ደግሞ የፖለቲካ ሰዎች ተቆጣጥረውታል፣ ዶክተሮች አላስቀርብ አሉን በማለት በወያኔ ስም በማስፈራራት ሀቁን ለማፈለስና በጽናትና በአንድነት ያሉትን ቀደምትና ዋናዋዎቹን ሊቃነ ጳጳስ አባቶቻችንን ለመከፋፈል በፓትርያርኩ ስም የሚጠቀሙበት የልክፍት አዙሪት አስከፊ ቢሆንም ክብር ገን ከቀደሙት ዋናዎቹ አባቶቻችን አለቀቀችና የእገዚያብሔርን ስራ በመስራት በብርሃን መመላለሳቸውን ቀጥለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ እነዚስ አምስቱ ውሾች ቤተክርስቲያንንም ስደተኛውንም በመናቅ ግፋም ሲል የዋህ ሲያገኙ በማስጨብጨብ የረከሱ የአፍሚንና የፊንአስ ጊዜ  ስደተኛ ለማድረግ ከስም አይጠሩ አባታቸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለመፈጸም ልክፍታቸውን ቀጥለውበታል። የአድራጎታቸውን አስከፊነት አውቀው እንዲመለሱና ክፉ ስራቸውን እንዲተው በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ካህናትና ምዕመናን የተሰጣቸውን ምክክር አጣጥለውታል። ሆኖም ኢትዮጵያና ቤተክርስቲያን የክብር  በሮቻችን በመሆናቸው አሁንም ደግመን እየነገርን ከጥፋት ተመለሱና ኑና እንወቃቀስ እንላለን። ዳሩ ግን አምስቱ ከልቦች ክብር ከራሳቸው የለቀቀ የኑፋቄ ባሮች ናቸውና አባቶችን፣ቤተክርስቲያንና ምዕመናን፣ ለኢትዮጵያ ነጻነት የቆሙትን ዜጎች በአጠቃላይ ኢትዮጵያንና ህዝቧን የሚያዋርዱ ቡድንተኛ ኢካቦች ናቸውን ማስተዋል ጠፍቶባቸዋል።

እነዚህ አምስቱ አካልብት (ኢካቦድ) ኢትዮጵያን አገርና ህዝብ ፈርሶ እያለ የድረሱልን ጥሪ እየተስተጋባ በየማዕዘናቱ ኃይሉን በጸሎት ከማሰባሰብ ይልቅ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ለህዝቧ ዓይን የሆኑትን በማዋረድ ምንዝርና በሆነው አድመኝነት የነጎዱ እራሳቸው ኩነኔዎች ሆነው ኮናኝ የሆኑበት እራሳቸውን ሳያውቁ ሌላውን በቅዱስ መንፈስ የሚመረመራቸውን እናውቃለ የሚሉ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ለምን ጣሳችሁ ሲባሉ፣ ለንስሃ ከመዘጋጀት ይልቅ የህጸጽና የነውር አገልጋይ በመሆን የቡድንተኝነትና የአድመኝነት ቁማር በመጫወት የአገርን፣ የቤተክርስቲያን፣ የአባቶችን ክብርና የምዕመናንን  እንድነት በመሸርሸር እንጀራ የበሉበትን ተረከዝ በመንከስ ላይ ይገኛሉ። ከዚህም በላይ ኮቴያቸውን በህጋዊዊ ውጭ በሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ውስጥ እያሰሙ ነውና እነዚህ ኢካቦድ በሚያራግፉት የምንደኝነት አባራ ያላወቃቸውንና ያልጠረጠረውን በፓትርያርኩ ስም በመነገድ አንድነቱን ሸርሸረው በጥርጣሬ፣በምንደኝነት በኑፋቄ በመከፋፈል ላይ ናቸው። አምላካችን ለሁሉ አስተዋይ ልቡና ይስጠው።

ባሳለፍናቸው ረዥም ዓመታት ብጹአን አባቶቻችን ለአገርና ለምዕመናን የምትጸለዩ መሆናችሁን በትክክል ብናውቅም፤ ካዛ ባለፈ አፋጣኝ የህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ በመጥራት ወይንም አባቶቻችን እግዚያብሔር በሚያሳያችሁ መንገድ የምዕመናኑን የመንጋችሁን አንድነት ከከልቦችና (ከውሾች)  ከኢካቦድ ትታደጉትና ኢካቦድ በጨለማ የሰሩትን በብርሃን ትገልጡትና አንድነታችን ትጠግኑትና ያጠፋም ተጸጸቶ፣ ፍቅር ይሰፍን ዘንድ እየተማጸንን ምዕመናን ከእውነት ያልሆኑት እውነትን እንደማይሰሙ እንደ አባታቸው ሃሰትን ሲናገሩ ከራሳቸውና ከሃሰት አባታቸው ልጅነታቸውን እንዳሳወቁ በመገንዘብ ኢካቦድ (ከልቦች/ውሾች) ላቀዱት በሁከት የመከፋፈልና የግርግር የስም ማጥፋት በሽታቸውን ልክፍት የተነሳ ሰላም እንደሌላቸው አውቀን ሳንገበር በጊዜውም አለጊዜውም በዓለም ዙሪያ ቤተክርስቲያናችንን በመልካም ተጋድሎ በመጠበቅ ከቀደምት ዋናዎቹ አባቶቻችን ድምፅ እንድንሰማ እግዚያብሔር ይርዳን።

ከእግዚያብሔር ሥራ ፊት የኢካቦች ሥራ አይቆምም። የእግዚያብሔር ሰዎች አብረውን አሉና “ስቀሎ ስቀሎ”  የአርብ ፍቅረኞች በትንሳዔው ይገለጣሉ። ይበተናሉ። ይወድቃሉ።

እግዚያብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

በውነት እንዳልካቸው